Telegram Web Link
Channel created
<< ነገ ፣ አንተ ማነህ ባሉህ ጊዜ በኩራት የምትመሰክርለትን እኔነት ዛሬ መቀለስ ጀምር፤
ምሰሶህን ከመጽሐፍት📚 ፣ ማገርህን ከሰዎች👥 ፣ የማዕዘን ድንጋይህን ግን ከልብህ ❤️ውሰድ ።
ታዲያ ስለምታቆመው ውብ ሕንፃ 🏘መመካከር ትፈልግ እንደሆን የቤተሰባችን አባል ሁን ።
📗ስለ ስብዕና ግንባታ
📒ስለ አስተሳሰብ እድገትና
📕ስለ ታላላቅ አሳቦች እናወጋለን ።

ጽልመትን ሳይንቅ ሻማውን የለኮሰ ፣ ብርሃኑን አክብሯልና ጨለማን ያሳድዳል ። >>
💡@ethio_enlightenment 💡
እንደምን አላችሁ የEthio enlightenment ቤተሰቦች የመጀመሪያ ጨዋታችንን አሳብ በሚል ርዕስ ለመጀመር ወደናል
አሳብ ምንድን ነው?
አንድን አሳብ አሳብ የሚያስብለው ምኑ ነው?
የማያስብ ሰው አለ?
አለማሰብስ ይቻላል?

Earl Nightengale
"Everything begins with an idea."
<< ማንኛውም ነገር ከአሳብ ይጀምራል። >> ሲል ፤ Oscar Wilde ደሞ
''An idea that is not dangerous is unworthy of being called an idea at all.''
<< አደገኛ ያልሆነ አሳብ በጠቅላላው አሳብ ሊባል አይገባም! >> ይላል።
እናንተስ ምን ትላላችሁ?

<< ማሰብ የለየው ሰውን ከእንስሳ ሳይሆን ሰውን ከሰው ነው >>ሶቅራጥስ

💡@ethio_enlightenment 💡
...አንድ ቀን ሶቅራጥስ በአቴና ከተማ ሲዘዋወር በአንዱ አደባባይ ጠቢብ ሰው ቆሞ ስለ ጽናት(courage) ሲያስተምር ፣ ቁጥሩ የበዛ ሕዝብ ሲሰማው አስተዋለ። ከሕዝቡም ጋር ተቀላቅሎ የጠቢቡን ሰው ንግግር ማዳመጥ ጀመረ። ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ ድምጹን ከፍ አድርጎ በመጮህ ጠቢቡን በጥያቄ አቋረጠው።

<<ንግግርህን በማቋረጤ ይቅርታ ይደረግልኝና ጽናት ስትል ምን ማለት እንደሆነ ብትነግረኝ>> አለው።

<<ጽናትማ ጠላት እየቀረበህ ቢመጣም አንተ ግን ከቦታህ ሳትነቃነቅ መጠበቅ ነው...>> በማለት ጠቢቡ መለሰ።

<<ነገር ግን እቅድህ ከሽፎ መሸሽ ቢኖርብህስ?>> አለ ሶቅራጥስ።

<<በርግጥ በዚያን ጊዜ ጽናት ሌላ ይሆናል። ቦታህን ይዘህ አትቆይምና>> ጠቢቡ መለሰ።

<<ስለዚህ ጽናት ከቦታህ አለመነቃነቅ ወይንም ከቦታህ መሸሽ ማለት ካልሆነ ታዲያ ጽናት ምንድን ነው?>> ሶቅራጥስ ጠየቀ

ያ ጠቢብ ሰው በሕዝቡ ፊት እግሩ መንቀጥቀጥ ጀመረ...<<ሶቅራጥስ ሆይ ፈተንከኝ፤ አሁን ሳስበው በትክክል ጽናትን የማውቀው አልመሰለኝም>> አለ።

<<እኔም አላውቀውም>> አለ ሶቅራጥስ። <<ነገር ግን ጽናት አዕምሮህን ከመጠቀም የተለየ ነገር አይመስለኝም፤ የተለየ ቢሆን ደሞ ይደንቀኛል። ወንድሜ! በማንኛውም አደጋ ውስጥ ብትሆን ትክክለኛውን ነገር ብቻ ማድረግ ከቻልክ ያ ጽናት ነው >> በማለት ንግግሩ ላይ አከለበት።

<<እንዲያውም የጽናት ትክክለኛ ትርጉሙ እሱ ነው>> በማለት በአደባባዩ ከተሰበሰቡት አንዱ ጮኸ። ሶቅራጥስ ወደዚያ ሰው ዞሮ ተራመደና እንዲህ አለ...

<<እንግዲያውስ ጽናት ማሰብ እንደሚገባህ ማሰብ ነው በሚለው ትርጉም ለጊዜው ብንስማማስ... የጽናት ተቃራኒው ደግሞ አዕምሮን በስሜት እያስገደዱ መንዳት ነው ብንልስ?>> በማለት ጠየቀ።

ወደ ሶቅራጥስ ፊቱንም ልቡንም አዙሮ ይሰማ የነበረው ሕዝብ መስማማቱን ገለጠ። ሶቅራጥስ ጠቢቡ ተስማምቶ እንደሆነ ለማወቅ ቆሞበት ወደነበረው ከፍታ ፊቱን አዞረ...ጠቢቡ ግን በቦታው አልነበረም

ጥበብ ከጲላጦስ(ኃይለጊዮርጊስ ማሞ)

💡@ethio_enlightenment💡
ቤተሰቦች ለዛሬያችን ደግሞ እውነት በሚል ርዕስ መጥተናል
👉የእውነት ትርጉም ምንድን ነው?
👉እውነት የስምምነት ውጤት ነው? ወይስ ሌላ?
👉<<Truth is subjective, እውነት ከስሜት ጋር የተያያዘ ነው >> ለሚለን ወዳጃችንስ ምን መልስ ይኖረናል?
👉በእውቀታችን ልክ ሊቀያየር የሚችልስ ነገር ነው?

Joe klass <<The truth will set you free, but first it will piss you off.
እውነት ነፃ ያወጣዎታል ፣ ግን መጀመሪያ ያቆሽሾታል፡፡ >> ይል ነበር።

<<ወደ እውነት መድረሻው ማሰብ ብቻ ነው>> ሶቅራጥስ

💡@ethio_enlightenment 💡
...ፕሌቶ እንደ መምህሩ ሶቅራጥስ <<የእውነት ማረፊያ<ማሰብ> ነው። በማሰብህ የስሜት ሕዋስህ ተቀብሎ እውነትን ይነግርሃል፤ እውነትን የሚገልጥልህ ስሜትህ ሳይሆን አዕምሮህ ነው>> በማለት አስተምሯል።

የእርሱ ደቀመዝሙር አሪስጣጣሊስ ደግሞ የእውነትን መገለጫ logic አደረገው። <<የአንድን ነገር መድረሻ እውነት የሚወስነው መነሻው ነው>>...በማለት....

በአንድ ወቅትም እንዲህ አለ <<ለነፍስ ሰባት የጠባይ አይነቶች(የማወቅ መሠረቶች) አሏት። እነርሱም አእምሮልቡናማሰብአውቆ መንቀሳቀስመሞትሕያውነትና አለመቀዝቀዝ ናቸው። >>

ዳግመኛም እንዲህ አለ << ሰው በአስተዋይነትና በአዋቂነት ሕያው ይሆናል ማለት፤ በአእምሮ ያስባል፣ በመንቀሳቀስ፣ በመብላት፣ በመጠጣት፣ ከሌሎች ፍጥረታት የተለየ ይሆናል (ልዩነት አለው) >> አለ።

እኔ እንዲህ እላለሁ <ሕያውነት፤ በመንቀሳቀስ፣ በማሰብ፣ በማስተዋል፣ በማወቅ ባይሆን ኖሮ ፣ ሕይወታችን እንደእንስሳ ሕይወት በሆነ ነበር፤ ለሞት ለጥፋትም በደረስን ነበር። ለልባችንም ሕይወት፣ ማሰብ፣ ማወቅ፣ መንቀሳቀስ ባልሆነላት ነበር።>ይላሉ የአንጋረ ፈላስፋ ጸሐፊያን

...<<መነሻህ እውነት ሳይሆን መድረሻህ እውነት ሊሆን አይችልም>> የሚለው ፊሮ ደግሞ <አስቀድሞ ነገር ሰው ማሰብ በመቻሉ ነው ከእንስሳ የተለየው> የሚለው መነሻ በራሱ እውነትነት የሌለውና በግምት ላይ የተመሠረተ ነው። ምክንያቱም አሳብ በራሱ ጥያቄ የሚነሳበትና ማንም ርግጠኛ የማይሆንበት ነገር ነውና>> ይላል።

<ሰው የሚያስብ ፍጡር ነው፤ ሶቅራጥስ ሰው ነው፤ ስለዚህ ሶቅራጥስ የሚያስብ ፍጡር ነው>። ይኽ ግን ሁልጊዜ አይሰራም ፤ ምንአልባት ሰው ለሆነው ለሶቅራጥስ የሰራው እውነት ፣ ሰው ለሆነው ለሌላው ሰው ግን አይሰራም፤ ማሰብን የማያውቁ ብዙ ሰዎች አሉና>>...

እቀጥላለን....እየጠየቅንና ከመልሳችን ውስጥ ቁም ነገር እየመዘዝን... አለማወቃችንን ወደማወቅ እንጓዛለን...ያኔ እውነተኛው ብርሃን ይገለጥልናል.... አብራችሁን ቆዩ

💡@ethio_enlightenment 💡
⭕️⭕️
<< አዲስ ቀን የአዲስ ስሜት ማዋለጃ ክፍልና የትናንት አሮጌ ሁነቶች መቃብር ነውና ፤
ሁሌም ያለፈው ቀን የነበሩ መጥፎ ትውስቶች ላይ ድንጋይ እየጫንን ለተሻሉት ትንሳኤ መስጠት ይኖርብናል፡፡ >>

💡 @ethio_enlightenment 💡
እንዴት ናችሁ ቤተሰቦቻችን ለአብርሆታችን የተቻላችሁን ለማድረግ የምትጥሩ ፤ አሳቦቻችሁንና ጥያቄዎቻችሁን ያለ ገደብ እያቀበላችሁ የምትመግቡና...'ሲበላ አይወራም' ብላችሁ በዝምታ አኝካችሁ የምትውጡ ቤተሰቦቻችን ሁላችሁም ደስ ትላላችሁ።
👉 ለዛሬያችን ውበት የሚለውን ርዕስ ይዘን መተናል
📌 የውበት ትርጉም ምንድን ነው?
📌 የውበት መመዘኛችሁ ምንድን ነው?
📌 ውበት አካላዊ ነው ወይስ አዕምሯዊ?

Coco Chanel
<<Beauty begins the moment you decide to be yourself. ውበት ራስዎን ለመሆን ከወሰኑበት ቅፅበት ይጀምራል ፡፡ >> ሲል

John O’Donohue ደግሞ
<<Beauty is the illumination of your soul. ውበት የነፍስህ ብርሃን ነው >> ይላል
<< ውበት አስተሳሰብ ነው። >> የሚልም አለ።

👉አስተሳሰባችን ውበትን የምናይበት መነፅር ነው
💡💡 ሰናይ ጊዜ ይሁንላችሁ💡💡

💡 @ethio_enlightenment 💡
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
😳😁😔
<<...ስለጣለህ ጉዳይ ማሰብ ትፈልጋለህ?
መጀመሪያ ተነስ! >>

JOIN US👇
💡 @ethio_enlightenment 💡
<< ሐዘን የደስታ ብርሃን ባለበት ሁሉ ሁሌም የሚከተል የሰው ልጅ ጥላ ነው ፤
ግን ዘለዓለማዊው ማስታገሻ ፍቅር ፣ አይዞን ባይ ጓደኛና የተፈጠረውን የሚረዳ ወዳጅ ካለ ፣ የሐዘን ቁስሉም ህመሙም ፈጥኖ ይሽራል>>

እንደምን አላችሁ ቤተሰቦቻችን👋
እስኪ ጥልቅ ሐዘን ሲሰማችሁ ምን እንደምታደርጉ ጻፉልን....

💡 @ethio_enlightenment 💡
⭕️⭕️ጥቅሶች
<< ጠዋት የሚባል ደራሲ ሁሌም
ዶሮ ጮኾ ፣ ፀሐይ ወጥታ - ወፍ ሲዘምር ብዕሩን አንስቶ
በየአንዳንዳችን ቀን ላይ መጻፍ ይጀምራል፡፡
ሐሳብ ወስዶ-ሲከትብ የሚውለውም ስንነቃ ከምናሳየው
የመጀመሪያ ስሜት ነው፡፡
ስለዚህ ውሎህ ላይ እንዲኖር የምትፈልገውን ስሜት በጥቂቱም ቢሆን
ስትነቃ ፈንጥቀው ፣ አብሮህ ይውላል ፡፡ >>

💡 @ethio_enlightenment 💡
ቤተሰቦቻችን አላችሁ? ኑሩልን...ጭጋግና ጨለማውን ፣ ብርድና ውርጩን እየታገልን እንጨዋወት ዘንድ...
👉 ለዛሬያችን "ህይወት" የሚለውን ርዕስ ይዘን መተናል።
📌 ህይወት ምንድን ናት?
📌 የህይወት ፍልስፍና የምንላቸው ነገሮችስ?
ቡድሃ👇
<<life is suffering ፡ህይወት ስቃይ ናት>> ሲል
Sadh guru👇
<<life is nothing short of daily miracle ሕይወት ምንም ማለት አይደለም የዕለት ተለት ተአምር ነው>>ይላል...
እናንተስ?

👉አስተሳሰባችን ህይወትን የምንመራበት መንገድ ነው።
💡💡 ሰናይ ጊዜ ይሁንላችሁ💡💡

💡 @ethio_enlightenment 💡
2025/07/06 16:02:15
Back to Top
HTML Embed Code: