Telegram Web Link
የውጭ ሀገር ዜጎች በትንሹ 150 ሺህ ዶላር በመውጣት የማይንቀሳቀስ የመኖሪያ ቤት ባለቤት እንዲሆኑ የሚፈቅደው አዋጅ ፀደቀ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ሀገር ዜጎች የማይንቀሳቀስ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የመሆን መብት አዋጅን አጸደቀ። ከአዲስ አበባ ውጪ መስራት ቢፈልጉ በወጣው መመሪያ መሰረት ክልሎች ተፈፃሚ እንደሚያደርጉም ተገልጿል።

የውጭ ሀገር ዜጎች ወደ #ኢትዮጵያ ገብተው በመኖሪያ ቤት ባለቤትነት ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የተቀመጠው አነስተኛ የገንዘብ መጠን 150 ሺህ ዶላር ነው ተብሏል።

“አንድ የውጭ ሀገር ዜጋ የሊዝ ዋጋውን ጨምሮ ለአንድ መኖሪያ ቤት ግንባታ ሙሉ ዋጋ ወይንም ለመኖሪያ ቤት ግዢ የሚመድበው አነስተኛ የገንዘብ መጠን ከ150 ሺ ዶላር ያነሰ ሊሆን አይችልም” ተብሏል።

150 ሺህ ዶላር ሁኖ የተቀመጠው አነስተኛ የገንዘብ መጠን በጊዜ ሂደት እየተሻሻለ እንደሚሄድም ተመላክቷል።

"ማንኛው የውጭ ዜጋ በማናቸውም ጊዜ፣ በአንድ ግዜ የሚኖረው የመኖሪያ ቤት ቁጥር አንድ ብቻ" መሆኑ የተቆመ ሲሆን ሚኒስቴሩ "ከአገር ጥቅም አንጻር አስፈላጊ ሁኖ ሲያገኘው ይህን ቁጥር በመመሪያ ማሻሻል ይችላል" ተብሏል።

የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሆነ የውጭ ሀገር ዜጋ “ለግለሰብ ወይም ለቤተሰብ የማከራየት መብቱ እንደተጠበቀ ሁኖ መኖሪያ ቤቱን ለንግድ አላማ ማዋል የተከለከለ መሆኑ” በአዋጁ ተቀምጧል።

ይህ የተገለጸው በምክር ቤቱ የከተማ፣ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአዋጁ ዙሪያ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡለት ጥያቄ ምላሽ እና ማብራሪያ በሰጠበት ወቅት ነው።መሬት የመንግስት እና የህዝብ እንደመሆኑ ለኢንቨስትመንት የሚመጡ ዜጎች መሬቱን የመሸጥ እና የመለወጥ መብት የላቸውም ተብሏል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
27👎16😁2😢2
ከኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ የሚወርድ ክለብ የለም፦ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን

በ2017 ዓም ከኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ የሚወርድ ክለብ እንደሌላ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ይፋ አደረገ፡፡

ፌደሬሽኑ ዛሬ ባካሄደው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ በቀጣይ አመት በዚህ አመት የተሳተፉት 18 ክለቦች እና ከከፍተኛ ሊጉ ያደጉ ሁለት ክለቦችን ጨምሮ በአጠቃላይ 20 ቡድኖች ተሳታፊ እንደሚሆኑ አሳውቋል፡፡ አዳማ ከተማ፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ መቐለ 70 ዕንደርታ እና ስሑል ሽረ በተቀመጠው የደረጃ ሰንጠረጅ መሰረት ወራጅ ውስጥ የነበሩ ክለቦች ናቸው፡፡

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
😁4529👍12👎2
ሩሲያ በ15 የአውሮፓ ሚዲያዎች ላይ እገዳ ጣለች!!

የአውሮፓ ህብረት በአመቱ መጀመሪያ ላይ በሩሲያ ሚዲያዎች ላይ ማዕቀብ መጣሉን ተከትሎ ሩሲያ 15 የአውሮፓ ሚዲያዎች ላይ እገዳ መጣሏን አስታውቃለች።

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ በሩሲያ ፌዴሬሽን ግዛት ውስጥ የውሸት መረጃን በማሰራጨት ላይ የተሳተፉ 15 የሕብረቱ አባል ሀገራት ድረ-ገፆች ላይ ገደብ ለመጣል መወሰኑን ገልጿል።

እርምጃዎቹ የተወሰዱት 27 አባላት ያሉት ህብረቱ በ8 የሩሲያ ሚዲያዎች ላይ ለጣለው እገዳ አጸፋዊ ምላሽ መሆኑም በመግለጫው ላይ ተካቷል።

የአውሮፓ ህብረት እና አባል ሀገራቱ ለውሳኔዎቹ ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ ናቸው ያለው መግለጫው፤ የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ ሚዲያ ላይ የተጣለውን እገዳ ካነሳ ሩሲያ ውሳኔዋን ድጋሚ ለማየት ፍቃደኛ መሆኗንም ገልጿል።

እስካሁን የትኞቹ የአውሮፓ ሚዲያዎች ላይ ማዕቀብ እንደተጣለባቸው ዝርዝር መረጃ አለመኖሩን አናዶሉ ዘግቧል።
58👍8
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ቴምር ሪልስቴት
‼️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ፒያሳ ለሽያጭ ያወጣነው ሱቅ

‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ 
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273
https://www.tg-me.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Telegram :@KalTemerRealEstate
14🥰1
🎉🎉እንኳን ደስ አላችሁ🎉🎉

አፍሮ ስፖርት በመጀመሪያ ዲፖዚት እስከ 500% BONUS የሚያገኙበት አድል ይዞላችሁ መጥቷል 😱😱

እንግዲያውንስ ምን ይጠብቃሉ አሁኑኑ የአፍሮ ስፖርት አካውንት በመክፈት እና ዲፖዚት በማድረግ የእድሉ ተካፋይ ይሁኑ::💸💸

@afrosportsbet
https://afrobetting.net/
4
አዋሽ_ባንክ ከ22 ቢሊዮን ብር በላይ ዓመታዊ ትርፍ አስመዘገበ

አዋሽ ባንክ በ2024/25 የሂሳብ ዓመት ያልተጣራ ትርፍ ከግብር በፊት ከ22 ቢሊዮን ብር በላይ ዓመታዊ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ።

አዋሽ ባንክ ትናንት ባወጣው መግለጫ እንደገለጸው ባንኩ በዚህ ሂሳብ ዓመት 64 ቢሊዮን ብር ጠቅላላ ገቢ በማስመዝገብ 77 በመቶ የሚሆን እድገት አሳይቷል።

በተጠናቀቀዉ የሂሳብ ዓመት የባንኩ ተቀማጭ ሂሳብ ብር 332 ቢሊዮን መድረሱንና ከዚህም ውስጥ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ድርሻ ብር 37.3 ቢሊዮን ወይም 11.24 በመቶ መያዙን ገልጿል።

ባንኩ በመግለጫው፤ በሂሳብ አመቱ ጠቅላላ ካፒታሉ አምና ከነበረበት የ10 ቢሊዮን ወይም የ37 በመቶ እድገት በማስመዝገብ በሰኔ 30፣ 2025 37 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል ብሏል።

ባንኩ በሂሳብ ዓመቱ ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች በድምሩ ከ219 ቢሊዮን ብር በላይ ብድሮችን የሰጠ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ20 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ሲል አክሎ ገልጿል።

“አዋሽ ለሁሉ” በተሰኘው የዲጂታል የብድር አገልግሎት አማካኝነት ከ301 ሺህ በላይ ለሆኑ ደንበኞች ያለ ምንም ማስያዣ ከ493 ሚሊዮን ብር በላይ በሂሳብ ዓመቱ የዲጅታል ብድር ተሰጥቷል ተብሏል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
46👍1😱1
ራሺያ ግዙፏን የማዕድን ስፍራ ተቆጣጠረች !

በአውሮፓ ግዙፍ የሆነውን የሊቲየም ክምችት የሚገኝበትን ስፍራ በዶንባስክ ግዛት የሩሲያ ጦር ተቆጣጥሯል ።

ወደ ፊት እየገሰገሰ የሚገኘው ጦሩ 74 ከመቶ የዶምባስክን ግዛት መቆጣጠር ችሏል ።

ሼቭሼንኮ የተባለው ስራ በራሽያ ቁጥጥር ስር መዋሉ አሜሪካ ከኪዬቭ ጋር የገባችው የማዕድን ማውጣት ውል 'ውሃ በላው' ሊባል የተቃረበ ይመስላል ።

ትራምፕ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ባይደን በሞኝነት ለለገሱት በቢሊየን የሚቆጠር ገንዘብ በካሳ መልክ ማዕድን አውጥተው እንዲጠቀሙ ከዩክሬን ጋር መስማማታቸው ይታወሳል ።

የኬዬቭ ሹማምንት አሜሪካ ተጨማሪ መሳሪያዎችን እንድትሰጣቸው ቢማፀኑም ዋሺንግተን እንቢ ብላለች ።

ይባስ ብሎ ለአሜሪካ ሊሰጥ የነበረውን የማዕድን ማውጫ ስፍራ አሁን የሩሲያ ጦር ተቆጣጥሮታል ።

ሊቲየም ለኤሌትሪክ መኪና ባትሪ ማምረቻ ዋነኛ ግብዐት ነው ። ቻይና ይህን ምርት እየተጠቀመች የኤሌክትሪክ መኪናን በገፍ እያመረተች ነው ። አሜሪካ እና አውሮፓም የኬዬቭን ሊቲየም ማዕድን በገፍ ቋምጠውበታል ። ይሁን እና ዋነኛውን ስፍራ ራሽያ ይዛዋለች ። ሌላኛው የማዕድን ማውጫ ለማዕከላዊ ዩክሬይን የቀረበ መሆኑ እፍይታ ነው ። ግን እንደ ሼቭሼንኮ አይሆንም ።
91👍18👏2
የኢራኑ ፕሬዚዳንት ሀገራቸው ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ጋር ያላትን ግንኙነት የሚያቋርጠውን ሕግ ፈረሙ
*

የኢራኑ ፕሬዚዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ኢራን ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማቋረጥ ያስችላታል የተባለውን ሕግ አጽድቀዋል።

የኢራን ፓርላማ ከሳምንት በፊት ባደረገው ስብሰባ ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ በኢራን ላይ ጫና እያሳደረ ነው፤ ይህን ደግሞ ኢራን መታገስ የለባትም፤ ከዚህ ተቋም አባልነት ለመውጣት ጊዜው አሁን ነው በማለት ሕግ አጽድቆ ወደ ፕሬዚዳንቱ ልኮ ነበር።

ፕሬዚዳንቱ በዛሬው ዕለት ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ጋር ኢራን የምታደርገውን ትብብር እንደታቋርጥ ፓርላማው ያቀረበውን ሰነድ መፈረማቸውን አስታውቀዋል።

ኢራን እዚህ እርምጃ ላይ የደረሰችው እስራኤል እና አሜሪካ በኢራን ኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ ጥቃት ካደረሱ በኋላ ኤጀንሲው ባሳየው ቸልተኝነት እና ተገቢውን ሽፋን ባለመስጠቱ ነው ተብሏል።

ኢራን የኒውክሌር የጦር መሳሪያ ባለቤት ልትሆን ነው፤ ይህን እውን ለማድረግ የሚያስችላትን ዩራኒየም እያበለፀገች ነው በሚል እስራኤል እና አሜሪካ የኢራንን የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎችን አጥቅተዋል።

ኢራን በበኩሏ የተለያዩ ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል እና በመካከለኛው ምስራቅ ወደሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች አስወንጭፋለች።


  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
83👍13
🎁"አዝናኝ እና ተሸላሚ የሚያረጎትን ጥያቄ አፍሮ ቤት ይዞላቹ መቷል!"🎁

ናፖሊ እግር ኳስ ክለብ የሚጫወትበት እስታዲየም🏟 ስም ምን በመባል ይጠራል

የዚህን ጥያቄ መልስ ታውቁታላችሁ?

እንግዲያውንስ መልሱን ኮሜንት ላይ ያሳውቁን!

በትክክል ያገኙ የመጀመሪያ 10 ሰዎች የ500 ብር 💵 ተሸላሚ ይሆናሉ!🎁

መስፈርቱም


1️⃣ https://afrobetting.net/ ላይ አካውንት መክፈት
2️⃣ የ afro sport ቴሌግራም ቻናል https://www.tg-me.com/afrosportsbet መቀላቀል
3️⃣ የፌስቡክ https://web.facebook.com/afrosportbet ቻናል መቀላቀል
4️⃣ የኢንስታግራም https://www.instagram.com/afrosportbet/ ፔጃችንን መቀላቀል/ Follow ማረግ

ተሸላሚ የሚሆኑትም የአፍሮ አካውንት ላይ ገብተው የሚወዳደሩ ሰዎች ብቻ እና ሶሻል ሚዲያዎቻችንን(Facebook,Instagram) Follow የሚያረጉ ናቸው።

መልካም እድል!
13🥰3👍1
እስራኤል በድጋሚ ጥቃት ብትሰነዝር  ከባድ ጥፊ ይጠብቃታል ሲሉ የኢራን ከፍተኛ ጄኔራል ተናገሩ

የኢራን ጦር ኃይሎች ዋና አዛዥ እስራኤል በሀገሪቱ ላይ ሌላ የጥቃት እርምጃ ከወሰደች ከባድ ጥፊ እንደሚደርስባት አስጠንቅቀዋል። ሜጀር ጀነራል አብዶልራሂም ሙሳቪ ለሊባኖስ አል-ማያዲን የቴሌቪዥን ጣቢያ እንደተናገሩት የኢራን ጦር ኃይሎች ባለፈው ወር የእስራኤል እና የአሜሪካ ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ሁሉንም አቅማቸውን እንዳልተጠቀሙ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል። "የእስራኤል አገዛዝ በቅርቡ በኢራን ላይ ባደረገው ወረራ ከባድ ሽንፈት ደርሶበታም፣ እናም ይህ የመሰለ ስህተት ከደገመ ከኢራን ህዝብ እና የጦር ኃይሎች የበለጠ ከባድ ጥፊ እንደሚደርስበት እናስጠነቅቃለን" ብለዋል ።

ሙሳቪ እስራኤላውያን እና ደጋፊዎቻቸው በኢራን ሪፐብሊክ ላይ ጉዳት ለማድረስ ኃይላቸውን ለአመታት ሲያሰባስቡ መቆየታቸውንም ጠቁመዋል። ኢራንን ኢላማ ለማድረግ እና ሀገሪቱን ለመከፋፈል እየፈለጉ ነው ለዚህም ደግሞ የኒውክሌርን ጉዳይ እንደ ምክንያት በመጠቀም ላይ ይገኛሉ ሲሉ ተደምጠዋል። እ.ኤ.አ ሰኔ 13፣ እስራኤል በኢራን ላይ ግልፅ እና የማያዳግም ወረራ ስትል በከፈተችው የጦር ዘመቻ በርካታ ከፍተኛ የጦር አዛዦች፣ የኒውክሌር ሳይንቲስቶችን እና ሲቪሎችን ህይወት ቀምቷል።ዩናይትድ ስቴትስ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተርን፣ አለም አቀፍ ህግን እና የኑክሌር መከላከል ስምምነትን በመጣስ ሶስት የኢራን ኒውክሌር ጣቢያዎችን በቦምብ በማፈንዳት ወደ ጦርነቱ ገብታለች።

በምላሹም የኢራን ጦር ሃይሎች በኳታር የሚገኘውን በምዕራብ እስያ ትልቁን የአሜሪካን አል-ኡዴይድ  የጦር ሰፈርን ኢላማ አድርጋለች።
55😁45
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በበጀት ዓመቱ ከ9 ሺህ በላይ ህገ-ወጥ የንግድ ድርጅቶች  ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ዙሪያ ከዘርፉ አመራሮች እና ባለሙያዎች ጋር ገምግሟል፡፡

በበጀት ዓመቱ ህገ-ወጥ ንግድን በመከላከልና በመቆጣጠር ፍትሃዊ የንግድ ስርዓት እንዲሰፍን ሰፊ ስራ መሰራቱን የተገለጸ ሲሆን  በ68 ሺ 3 መቶ 33 የንግድ ድርጅቶች ላይ የበር ለበር ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ በዘጠኝ ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና አራት  በህገ-ወጥ የንግድ ሥራ ተሰማርተው የተገኙ ድርጅቶች ላይ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ መወሰዱን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል፡፡

የህብረተሰቡን የኑሮ ውድነት ተጋላጭነት ለመቀነስ የእሁድ ገበያዎችን ቁጥር ወደ 24 ማሳደግ መቻሉን ተጠቁሟል።  በገበያዎቹ ላይ የሚቀርቡ መሰረታዊ የግብርና እና ኢንዱስትሪ በተመጣጣኝ ዋጋና ጥራት እንዲቀርቡ የተሻለ ክትትልና ቁጥጥር መደረጉን ጠቁመዋል፡፡

አክለው በበጀት ዓመቱ የነበረውን ጥንካሬ ይበልጥ በማጠናከር እና እንደ ውስንነት የተነሱ ጉዳዮችን በማረም በቀጣይ በጀት ዓመት የበለጠ ውጤታማ ስራ ለመስራት ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡
22👎7👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ቴምር ሪልስቴት
‼️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ፒያሳ ለሽያጭ ያወጣነው ሱቅ

‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ 
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273
https://www.tg-me.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Telegram :@KalTemerRealEstate
11
2025/07/14 15:22:35
Back to Top
HTML Embed Code: