Telegram Web Link
የናይጄሪያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ በ82 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ሙሃማዱ ቡሃሪ ባደረባቸው ሕመም ሕክምና ሲከታተሉ በነበሩበት ለንደን ሆስፒታል በዛሬው ዕለት ሕይወታቸው ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ሙሃማዱ ቡሃሪ በፈረንጆቹ ከ1983 እስከ 1985 በሀገሪቱ በወታደራዊ አመራርነት ያገለገሉ ሲሆን ÷ ከ2015 እስከ 2023 ደግሞ በፕሬዚዳንትነት ተመርጠው አገልግለዋል።

የቀብር ሥነ ሥርዓታቸውም ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ እንደሚከናወን ዘገባው አመልክቷል፡፡

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
14😢7🤔3👏1
ቼልሲ የዓለም ክለቦች ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነ

ቼልሲ ፒኤስጂን በማሸነፍ የ2025 የዓለም ክለቦች ዋንጫ ሻምፒዮን ሆኗል።

ለአንድ ወር ያህል 32 ክለቦችን በማሳተፍ በአሜሪካ ሲካሄድ የቆየው የፊፋ የዓለም ክለቦች ዋንጫ ዛሬ ፍጻሜውን አግኝቷል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በስታዲየም ተገኝተው በተከታተሉት የፍጻሜ ጨዋታ ቼልሲ ፒኤስጂን 3 ለ 0 በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል። የእንግሊዙን ክለብ ግቦች ኮል ፓልመር (2) እና ዦአዎ ፔድሮ አስቆጥረዋል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
57😱14👍10
2025/07/14 11:10:05
Back to Top
HTML Embed Code: