Telegram Web Link
ኒውካስል ዩናይትድ የካራባኦ ካፕ ሻምፒዮን ሆነ

ኒውካስል ዩናይትድ በካራባኦ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ ሊቨርፑልን በማሸነፍ አሸናፊ ሆኗል።

ምሽት 1 ሠዓት ከ 30 ላይ በዌምብሌይ ስታዲየም በተደረገው የካራባኦ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ ኒውካስል ዩናይትድ በአሌክሳንደር አይዛክ እና በርን ግቦች ሊቨርፑልን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ሊቨርፑልን ከሽንፈት ያልታደገች ብቸኛ ግብ ፌደሪኮ ኬዛ ከመረብ አሳርፏል።

የባለፈው ዓመት የመድረኩ ሻምፒዮን ሊቨርፑል ለተከታታይ ሁለተኛ ዓመት የካራባኦ ዋንጫ የሚያሳካበትን ዕድል ሳይጠቀም ቀርቷል። የ47 ዓመቱ የኒውካስል ዩናይትድ አስልጣኝ ኤዲ ሀው ከፈረንጆቹ 1956 በኋላ ኒውካስል ዩናይትድን የዋንጫ ባለቤት አድርጓል።


    T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
👍36🥰43
አዲስ አበባ❗️#መሬት_መንቀጥቀጥ

ከጥቂት ደቂቃዎች
በፊት (3:56) ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት አዲስ አበባ እና የተለያዩ የክልል ከተሞች ተሰምቷል።

ከደቂቃዎች በፊት ንዝረቱ በአዲስ አበባ የተለያዩ ቦታዎች እና የክልል ከተሞች ተሰምቷል።

    T.me/ethio_mereja
         ኢትዮ-መረጃ
👍45😱5👎21
በሬክተር ስኬል 5.1 የመሬት መንቀጥቀጥ ተለክቷል!

የአዋሽ አካባቢ ጠንካራ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደነበር እንዲሁም በአዲስ አበባ በርካታ አከባቢዎች እጅግ የጠነከረ ንዝረትም ለሰከንዶች ተሰምቷል።

ከአዲስ አበባ ውጭም በርካታ ከተሞች ላይ ንዝረቱ በደምብ ተሰምቷል። የመሬት መንቀጥቀጡ ከአዋሽ በ50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መከሰቱን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ጠቁሟል።

በሬክተር ስኬልም 5.1 መለካቱን አመላክቷል።

    T.me/ethio_mereja
         ኢትዮ-መረጃ
👍363
አዲስ አበባ‼️

በድጋሜ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት (6:20) ላይ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት አዲስ አበባ እና የተለያዩ የክልል ከተሞች ተሰምቷል።

ከደቂቃዎች በፊት ንዝረቱ 6ሰአት ከ20ደቂቃ ላይ በአዲስ አበባ የተለያዩ ቦታዎች እና የክልል ከተሞች ተሰምቷል።

    T.me/ethio_mereja
         ኢትዮ-መረጃ
👍7311
በደቂቃዎች ውስጥ ከፍተኛ ገንዘብ ማግኘት በምትችሉበት የአቪዬተር ጨዋታ እየተዝናናችሁ አሸናፊ ሁኑ።

ለመጫወት ይህን ሊንክ 👉👉https://bit.ly/3M9qBIw/ ሊንክ ይጫኑ።

ማህበራዊ ገፃችንን Follow በማድረግ የተለያዩ Giveaways ያሸንፉ👇
Telegram
Facebook
Instagram
TikTok
👍177🤔2👎1😢1
በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 53 #ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው መመለሳቸው ተገለጸ

መንግሥት በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ እና ታይላንድ ወታደራዊ ካምፕ ተጠልለው የነበሩ 53 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉን አስታወቀ።

ትላንት መጋቢት 7 ቀን 2017 ዓ.ም 23 ዜጎችን እንዲሁም ዛሬ መጋቢት 8 ቀነ 2017 አ.ም ደግሞ 30 ዜጎችን በአጠቃላይ በካምፑ የነበሩትን 53 ዜጎች እንዲመለሱ ማድረግ መቻሉን ገልጿል።

ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የተደረጉት ኢትዮጵያውያኑ ከማይናማር እገታ ወጥተው ታይላንድ ወታደራዊ ካምፕ የነበሩ መሆናቸውን ጠቁሟለ።

ኢትዮጵያውያኑ ወደ ሀገራቸው እነዲመለሱ የተደረገው ከኢትዮዽያ አየር መንገድ ጋር በመተባበር እና በአካባቢው ከሚገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመነጋገር መሆኑን አስታውቋል።

እስካሁን ከማይናማር እገታ ወጥተው ታይላንድ ወታደራዊ ካምፕ የነበሩ በመጀመሪያውና ሁለተኛው ዙር በጠቅላላው 130 ዜጎችን ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

    T.me/ethio_mereja
         ኢትዮ-መረጃ
👍5420🤯1
700 ሚልየን ብር ምንጩ ያልታወቀ ገንዘብ ታገደ!!

የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 2 ሺሕ 483 የገንዘብ ዝውውሮችን በማጣራት ከ700 ሚሊየን ብር በላይ በቁጥጥር ማሳገዱን አስታውቋል፡፡

አገልግሎቱ በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ላይ ከፍተኛ የሆነ ግኝቶችን ለህግ አስከባሪ ኤጀንሲዎች በማቅረቡ በንቃት እየመረመረ እና ሪፖርት እያደረገ መሆኑም ለአሐዱ ገልጿል።

በዚህም መሠረት ተቋሙ ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ 2 ሺሕ 483 በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር የተጠረጠሩ ሪፖርቶችን የተቀበለ ሲሆን፤ ከዚህም ውስጥ 120 መዝገቦች ለተጨማሪ አሰርምጃ ለሚመለከታቸው የሕግ አካላት ማቅረቡን አመላክቷል።

የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ አቶ እንዳለ አሰፋ ለአሃዱ እንደተናገሩት፤ እነዚህን ሪፖርቶች ተከትሎ በተደረገ ማጣራት ከ700 ሚሊየን ብር በላይ በሕ-ገወጥ መንገድ የተያዘ ገንዘብ በቁጥጥር ሥር ውሏል።

"ይህ ገንዘብ በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ በሙስና እና ሌሎች ሕገ-ወጥ ተግባራትን ጨምሮ ከከባድ የወንጀል ድርጊቶች ጋር የተገናኘ ነው" ብለዋል።

"ከተለያዩ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት የሚቀርቡ ሪፖርቶችና የድጋፍ ጥያቄዎች እየተበራከቱ መጥተዋል" ያሉት አቶ እንዳለ፤ አገልግሎቱ እነዚህን የእርዳታዎች ጥሪዎች በተገቢው መልኩ እንደሚቀበልና በቀጣይም በትብብር እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ከባንክና ከሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ጋር በመተባበርና አጠራጣሪ የፋይናንስ ግብይቶችን በማጣራት፤ በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘ ከፍተኛ ገንዘብ በኢኮኖሚው ውስጥ እንዳይዘዋወር ማድረጉንም አስረድተዋል።

"ባንኮች አጠራጣሪ ግብይቶችን ሲኖሩ ሪፖርቶችን በማቅረብ ረገድ ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ" ያሉት ሥራ አስፈፃሚው፤ "ከዚያም አልፎ በጥልቀት በመመርመር የሽርክና የገንዘብ ማጭበርበር ዘዴዎችን ለመለየት እና ለማስቆም ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርገዋል" ብለዋል።(አሐዱ)
👍60🤔84👎1
ገና ሲመዘገቡ እስከ 50% ቦነስ አሎት። ምን ይጠብቃሉ አፍሮ ስፖርት ድህረ ገፅ ላይ ይመዝገቡ።

እግር ኳስ ፣ ኢንስታንት ጌምስ እና ቨርችዋል ጌሞች ሁለም አፍሮ ስፖርት ላይ ያገኛሉ። ይዝናኑ ያሸንፉ!

አሁኑኑ  www.afrobetting.net ላይ ይግቡ ይመዝገቡና ይወራረዱ። 

follow us on 

Follow us on 👇
Telegram
Facebook
Instagram
TikTok
Website
👍204👎4👏3🤯2🥰1
እስራኤል በጋዛ ሰርጥ በሐማስ ላይ "ውጊያዋን በሙሉ ኃይል ጀምራለች" አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ

ከ400 በላይ ፍልስጤማውያን መገደላቸው ሪፖርት የተደረገበትን የጋዛ ጥቃት ገና የመጀመሪያው እንደሆነ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ተናገሩ።

እስራኤል በጋዛ ሰርጥ በሐማስ ላይ "ውጊያዋን በሙሉ ኃይል ጀምራለች" ሲሉ ኔታንያሁ አስጠንቅቀዋል፡፡

ጥር ወር ላይ ከተደረሰው የጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት በኋላ እስራኤል የፈጸመችው ከባዱ የአየር ጥቃት ነው ተብሏል።

ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት በርካቶች ለረመዳን ጾም የቀኑን የመጨረሻ ምግባቸውን እየበሉ እንደነበር የዓይን እማኞች ተናግረዋል።

በቦታው አስከሬኖች ወዳድቀው፣ የቆሰሉ ሰዎች ህክምና ለማግኘት እየተማጸኑ እንዲሁም እሳት ተቀጣጥሎ የነበረ ሲሆን፤ ሁኔታውንም አሰቃቂ ብለውታል።

ኔታንያሁ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት "ድርድሩ የሚቀጥለው በእሳት ውስጥ ብቻ ነው፤ ይህም ገና ጅምር ነው" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ አስተያየት የተሰማው የእስራኤል ጦር በጋዛ የሃማስ ይዞታዎች ናቸው በሚል ከፍተኛ የአየር ጥቃት ከከፈተ በኋላ ነው።

የጋዛ የጤና ሚኒስቴር በዚህ ጥቃት ከ400 በላይ ሰዎች መገደላቸውን እንዲሁም በመቶዎች የሚቆጠሩ መቁሰላቸውን አስታውቋል።

የተኩስ አቁሙ አሸማጋይ የሆነችው ግብጽ ይህንን የእስራኤል ጥቃት በጽኑ አውግዛለች።

    T.me/ethio_mereja
         ኢትዮ-መረጃ
👍50😢143👎3🤔3
https://youtu.be/3igcTI9JPd8?si=cgW8UF6iwmfy0PBk

🚀 Best online investment platform for gold🚀
Celebrating Our Members’ Successful Withdrawals!
Join Allied Gold Today – Your Success Story Starts Here!
💡 Online Earnings Made Effortless
💡 Partner with Excellence, Grow with Gold
Why Choose Allied Gold?
Trusted by 100,000+ Investors Worldwide
Secure Gold-Backed Investments with 24/7 Transparency
Instant Withdrawals & Dedicated Support
https://www.tg-me.com/Allied_Gold
https://www.alliedgoldinvestment.com/?invitation_code=B6897
👍132👏1
ከዛሬ ጀምሮ በምሽት የንግድ እና የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ የወጣውን ደንብ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጀምር ቢሮው አስታወቀ

አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ “በምሽት የንግድ እና የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ ያወጣውን ደንብ” ከዛሬ መጋቢት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚያደርግ አስታወቀ።

ተግባራዊ ይደረጋል የተባለው ደንብ በመዲናዋ ዋና መንገዶች ላይ የሚገኙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ቢያንስ እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ክፍት እንዲሆኑና አገልግሎት እንዲሰጡ ያስገድዳል።

ከዛሬ መጋቢት 10/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ይደረጋል የተባለው ደንቡን ለህብረተሰቡ የማስተዋወቅ ስራ ይሰራል ብሏል።

“በደንቡ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች ማብራሪያ በሁሉም የሚዲያ አውታሮች አማካኝነት ማህበረሰቡ እንዲያውቃቸው እንደሚደረግ እና ደንቡን የማስተዋወቅ ስራ እንደሚሰራ” አመላክቷል። በመዲናዋ ዋና መንገዶች ላይ የሚገኙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ቢያንስ እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ክፍት እንዲሆኑና አገልግሎት እንዲሰጡ የአዲስ_አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ መወሰኑን የተመለከተ ዘገባ ማቅረባችን ይታወሳል።

ንግድ ቢሮው ለአስራ አንዱም ክፍለ ከተማዎች ሰኔ 7 ቀን 2016 በጻፈው ደብዳቤ፤ ለንግድ ማበረሰቡ ውሳኔውን በማስገንዘብ ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስቧል። ቢሮው ዛሬ ባወጣው መግለጫ የስራ ባህልን ይበልጥ ለማዳበር፣ የኢኮኖሚ እድገትን ለማፋጠን፣ የከተማዋን ተወዳዳሪነት እውን ለማድረግ ቀን ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ በምሽት የንግድ እና አገልግሎት መስጫ ተቋማት አገልግሎት የሚሰጡበት ምቹ ሁኔታ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ ደንቡ መውጣቱን አስታውሷል።

    T.me/ethio_mereja
         ኢትዮ-መረጃ
👍536😱3👏2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ነገ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ነገ መጋቢት 11 2017 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሏል።

ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የፌዴራል መንግሥት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የአፈጻጸም ሪፖርትን መነሻ በማድረግ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ነው ምላሽና ማብራሪያ የሚሰጡት።
👎84👍44😁131
😎እኛን ከሌላው የሚለየን የሚገራርሙ ኦዶችን ስለምንሰጥ ነው! 💰

ምን ይጠብቃሉ አሁኑኑ እድሎን ይሞክሩ! ድህረ ገጻችን ላይ በመግባት ይመልከቱ👉https://bit.ly/3XbY3o7 ይጫኑ።

አፍሮስፖርት ማህበራዊ ገጾቻችንን Follow በማድረግ በየሳምንቱ የተለያዩ ሽልማቶችን ያሸንፉ፣ ቤተሰብ ይሁኑ። 👇
Telegram
Facebook
Instagram
TikTok
👍20👎1
ታጣቂዎች ከአዲስ አበባ ወደ ደብረማርቆስ ሲጓዝ የነበረ አውቶብስ አስቁመው ከ56 በላይ ሰዎች አግተው መወሰዳቸውን የአይን እማኞች አስታወቁ!!

ታጣቂዎች ከአዲስ አበባ ወደ ደብረማርቆስ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ አስቁመው ከ56 በላይ ሰዎች አግተው ወዳልታወቀ ስፍራ መወሰዳቸውን የአይን እማኞች ለአዲስ ስታንዳርድ አስታወቁ።

ክስተቱ የተፈጠረው #በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደገም ወረዳ ልዩ ስሙ አሊደሮ በተባለ ስፍራ በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ሰኞ መጋቢት 8 ቀን 2017 ዓ.ም መሆኑን ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸውን እንዳንጠቅስ የጠየቁ የአይን እማኝ ገልፀዋል።

የተኩስ እሩምታውን ተከትሎ ታጣቂዎቹ ከኦሮሚያ ልዩ ሀይል ጋር ውጊያ መጀመራቸውን ገልጸው "በወቅቱ ታጣቂዎቹ በዛ ያለ ሐይል ነበራቸው፣ ግማሹ ከልዩ ሀይሉ ጋር ሲታኮስ ቀሪው ሀይል ተሳፋሪዎችን ከአውቶብስ እየደበደበ ያስወርድ ነበረ" ብለዋል።

"ቅልጥ ያለ ተኩስ ነበረ፤ ወዲያው አውቶብሱ ጎማው ላይ መትተውት ቆመ" ያሉት እኚሁ የአይን እማኝ "ተሳፋሪዎችን ክፉኛ እየደበደቡ ያስወርዷቸው ነበረ፤ ቦታው ዱር ገደል ነው፤ የት እንደሚወስዷቸው አላውቅም፣ ብቻ እየደበደቧቸው ወደ ታች ይወስዷቸው ነበረ" ብለዋል።

ጥቃቱ የተፈጸመው አሊደሮ ነው፤ ከፊቼ እንደወጡ ከኢስት ፋብሪካ ዝቅ ብላ የምትገኝ ቦታ ናት” ያሉት እኚሁ የአይን እማኝ በወቅቱ እርሳቸው የከባድ ጭነት መኪና እያሽከረከሩ እንደነበረ ተናግረዋል።
ጥቃቱ ሰኞ መጋቢት 8 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ላይ መፈጸሙን የገለጹት እኚሁ የአይን እማኝ አክለውም የተኩስ እሩምታውን ተከትሎ የሚሄዱበትን አቅጣጫ ቀይረው የሚሆነውን ሲመለከቱ እንደነበረ አስታውሰዋል። በተጨማሪም “ታጣቂዎቹ ጸጉረ ጉንጉን እና ሸኔ የሚባሉት ናቸው” ሲሉ ገልጸዋል።

    T.me/ethio_mereja
👍89😭379🤯4😁2😢1
👍101
ETHIO-MEREJA®
Photo
ህወሓት “አደብ እንዲገዛ መደረግ አለበት” - አቶ ባርጠማ ፍቃዱ፤ የኢዜማ የፓርላማ ተወካይ

ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 11፤ 2017 እየተካሄደ ባለው የፓርላማ መደበኛ ስብስባ፤ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከተነሱ ጥያቄዎች ውስጥ የትግራይ ወቅታዊ ሁኔታን የተመለከተው ይገኝበታል። ገዢው ብልጽግና ፓርቲን በመወከል ከኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከሚገኘው ያያ ጉለሌ ምርጫ ክልል የተመረጡት ብርቄ ባህሩ ጥያቄውን ካነሱ የፓርላማ አባላት መካከል አንዷ ናቸው።

የፓርላማ አባሏ የፌደራል መንግስት እና ህወሓት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በጥቅምት 2015 ያደረጉትን የግጭት ማቆም ስምምነት በጥያቄያቸው አንስተዋል። “የፕሪቶሪያ ስምምነት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ያስገኘው ሰላም እፎይታ የሚሰጥ ነው” ያሉት ብርቄ፤ “ሰላምን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የስምምነት ነጥቦቹ ተግባራዊነት በምን ደረጃ ላይ ይገኛሉ?” ሲሉ ጠይቀዋል።

በስምምነቱ ላይ የሰፈረው መልሶ ማደራጀት እና ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው መመለስን በተመለከተ እየተከናወነ ያለው ስራ ምን እንደሆነም ጥያቄ አቅርበዋል። የፓርላማ አባሏ በትግራይ ክልል ያለው ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ “ወደ ግጭት እንዳያመራ” ያላቸውን ስጋት አንጸባርቀዋል። በክልሉ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ “ድጋሚ ዋጋ እንዳያስከፍለን ምን እየተሰራ ይገኛል?” ሲሉም ጥያቄቸውን ሰንዝረዋል።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ የጉራጌ ዞን፣ እዣ ምርጫ ክልል የፓርላማ ተወካይ የሆኑት አቶ ባርጠማ ፍቃዱ፤ “ለትግራይ ሁኔታ የማዕከላዊ መንግስት እልባት ለምን አይሰጥም?” ሲሉ ተመሳሳይ ጥያቄ አንስተዋል። ህወሓት “እስከመቼ ሰላም እየነሳ ይኖራል?” ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ህወሓት ባለው “የስልጣን ሱስ” “የትግራይ ህዝብን እረፍት በመንሳት”፣ “ሰላም እንዳይኖር የፕሪቶሪያ ስምምነት እየጣሰ ይገኛል” ሲሉ አቶ ባርጠማ ወንጅለዋል። እኚሁ የኢዜማ የፓርላማ ተወካይ የህወሓት ሰዎች “አደብ እንዲገዙ መደረግ አለበት” የሚል እምነት እንዳላቸው ሲናገሩ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፈገግታ ሲያሳዩ ተስተውለዋል።

የፊደራል መንግስት የትግራይ ሁኔታን “ማስተናገድ ያለበት” በፕሪቶሪያ በተፈረመው ስምምነት “መሰረት” መሆን እንደሚገባው አቶ ባርጠማ አመልክተዋል። “ተደራዳሪ የፌደራል መንግስትን ጨምሮ፣ ብልጽግናን ጨምሮ፣ በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን ያካተተ፣ ክልሉን የሚመራ ጤነኛ አደረጃጀት መፈጠር ያለበት ይመስለኛል” ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ አሳስበዋል።(ኢትዮጵያ-ኢንሳይደር)

    T.me/ethio_mereja
         ኢትዮ-መረጃ
👍8312👎5🥰3😱3😁1🤔1
የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ለአንድ ዓመት እንደሚራዘምና አመራሮቹም እንደሚቀያየሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት የ2017 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸምን ገምግሟል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድም ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ከምክር ቤት አባላት በፕሪቶሪያው ስምምነት አፈፃጸም ላይ ለተነሳው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ፤ "ስምነቱ ከፍተኛ ድል የተገኘበት ታሪካዊ ስምምነት ነው" ብለዋል፡፡

"ስምምነቱን የተፈራረምነው ያሸፍነውን ጦርነት አቋርጠን ነው፡፡ ይህም ለሰላም ያለንን ከፍተኛ ፍላጎት አሳቷል" ሲሉም ተናግረዋል፡፡

"መቀለ ከተማን ለመቆጣጠር አንድ ሁለት ቀን ሲቀረን የሰላም ስምምነት መፈራረማችን ለሰላም ያለንን ፍላጎት ያሳያል" ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ስምምነቱ በርካታ መሻሻሎች ስለማምጣቱ፣ ጊዜያዊ አስተዳዳር መቋቋሙ፣ የተለያዩ አገልግሎትን የማስጀመር ሁኔታ መኖሩ ከመሻሻሎቹ መካከል እንደሆኑ ጠቅሰዋል፡፡

ከስምምነቱ ጋር በተያያዘ ክፍተቶች መካከል የታጣቂዎች ጉዳይ መሆኑንም በምላሻቸው አካተዋል፡፡

የተሃድሶ ሥራውን በተመለከተም "የተሃድሶ ሥራው በተሟላ መንገድ አለመፈጸሙ በዋናነት የሚጎዳው የትግራይን ሕዝብ ነው" ያሉ ሲሆን፤ "ለትግራይ የሚላከው በጀት ለታጣቂዎች ከዋለ ልማት አይመጣም ማለት ነው" ብለዋል፡፡

ተፈናቃዮች በራያ እና በፀለምት ጥሩ ሥራ ተሰርቷል፡፡ በወልቃይት አከባቢ የተጀመሩ ሥራዎች ግን በሚገባው መንገድ አልሄዱም ሲሉም ተናግረዋል፡፡

"የፌደራል መንግሥት ዜጎችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ፍላጎት ቢኖረውም፤ በተፈናቃዮች ላይ የሚሰራ አፍራሽ ፖለቲካ አስቸጋሪ ሆኖብናል" ሲሉም ገልጸዋል፡፡

"ባለፉት 2 ዓመታት በፕሬዝዳንት ጌታቸው፣ በጄነራል ታደሠ ወረደ እና ጄነራል ፃድቃን ገብረተንሳይ የተመራው ግዚያዊ አስተዳዳር ጦርነት እንዳይኖር አድርጓል" ብለዋል፡፡

"ምንም እንኳን ቀድሞ በነበረ ጦርነት ላይ ብንወቅሳቸውም ባለፉት ሁለት ዓመት በነበረው ቆይታ ግን ማድነቅ ያስፈልጋል" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ "ግዚያዊ አስተዳዳሩ ጊዜው በመጠናቀቁ እሱን በተመለከተ ሥራዎች እየተሰሩ ነው" ብለዋል፡፡

በዚህም እስከ ቀጣዩ ምርጫ ያለውን የቆይታ ጊዜ ግዚያዊ አስተዳደሩ የሚመራበትን ሕግ የማሻሻል ሥራዎች እንደሚሰሩና አመራሮች የመቀያየር ሥራ እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡

"የትግራይ ሕዝብ ጦርነት በአይፈልግም፡፡ በውይይታችንም የተረዳነው ይህንን ነው፡፡ ጦርነት የሚፈልጉ ኃይሎች ጦርነት በእንደማያዋጣ መንገንዘብ አለባቸው፡፡ መከላከያ በሌሎች ክልልች ሥራ ላይ ነው በሚል ከሕግ አግባብ ውጪ የሚንቀሳቀሱ ከድርጊታቸው መቆጠብ አለባቸው" ሲሉ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል፡፡

    T.me/ethio_mereja
         ኢትዮ-መረጃ
👍734👎3🤔2
አፍሮስፖርትን መቀላቀል ብቻውን ያሸልማል❗️

💰ለመጀመሪያ ጊዜ ሲቀላቀሉን የእንኳን ደህና መጣችሁ ቦነስ ያገኛሉ፡፡

🤳እርሶም ይሞክሩት!

ድህረ ገጻችንን ለመጎብኘት ይህን ሊንክ 👉https://bit.ly/3XbY3o7 ይጫኑ።

አፍሮስፖርት ማህበራዊ ገጾቻችንን Follow በማድረግ በየሳምንቱ የተለያዩ ሽልማቶችን ያሸንፉ፣ ቤተሰብ ይሁኑ። 👇
Telegram
Facebook
Instagram
TikTok
Website
👍151🥰1
2025/07/09 02:18:36
Back to Top
HTML Embed Code: