Telegram Web Link
5days left❗️(በመላው ሀገሪቱ ስራ የማቆም አድማው 5ቀን ቀርቶታል)

በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሕክምና ባለሞያዎች ሰልፍ እያደረጉ ነው!

የሕክምና ባለሞያዎች የደሞዝ ጭማሪ እና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች የሚጠይቁ ሰልፎችና የተለያዩ ትእይንቶች በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች እየተካሄዱ ይገኛሉ።

በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በደቡብ፣ በሲዳማ፣ በትግራይ እና በሌሎችም ክልሎች የደሞዝ ጭማሪ እና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች የሚጠይቁ ሰልፎች እየተደረጉ ይገኛሉ።

በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ የሕክምና ባለሞያዎች፥ በጤና ተቋማት ውስጥ ሰልፍ ያካሄዱ ሲሆን የደሞዝ ጭማሪ እንደረግላቸው፣ የተለያዩ ጥቅማጥቅሞች እንዲረጋገጥላቸው እንዲሁም የሠሩበት የጦርነቱ ወቅት ያልተከፈለ የ17 ወራት ደሞዝ እንዲከፈላቸው ጥያቄ አቅርበዋል።

ይህ የኢትዮጵያውያን ህክምና ባለሙያወች ጥያቄ ነው?!

የአፍሪካ ዝቅተኛዋ ደሞዝ ከፋይ ሀገር

👉Specialist ሀኪም ወርሀዊ 120ዶላር
👉አጠቃላይ ሀኪም 84ዶላር
👉ነርስ 70ዶላር ወርሀዊ ክፍያ ምትከፍል ብቸኛ ሀገር ናት

ራሱን ለTB, Hepatitis, Virus, Hiv እና ሌሎች መሰል በሽታወች  አጋልጦ ሚሰራው ሀኪም የጤና insurance የለውም .... በትንሽ ክፍያ ሚሰራው የጤና ባለሙያ ለዚህ ሁሉ በሽታ ተጋልጦ እየሰራ  ያለ insurance እየሰራ የጤና መድህን እንኳን ተጠቃሚ እንዲሆን አይፈቀድለትም?

ህይወታችንን ሲያድኑ ኖረዋል አሁን ግን
ህይወታቸውን ልናድን ይገባል!!!

"የኢትዮጵያ መንግስት እና የጤና ሚኒስቴር ለህጋዊ ጥያቄዎቻችን እጅግ አስቸኳይ መፍትሄ ለመስጠት ሊሰሩ ይገባል " ብለዋል።


  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና መቼ ይሰጣል?።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መቼ ይሰጣል ?


👉በወረቀት ፈተናቸውን የሚወስዱ ተፈታኞች ፦ ሰኔ 23 ፣ ሰኔ 24 እና ሰኔ 25/2017 ዓ/ም

👉በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ1ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሰኔ 23 ፣ ሰኔ 24 እና ሰኔ 25/2017 ዓ/ም

👉በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ2ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሰኔ 26 ፣ ሰኔ 27 እና ሰኔ 30/2017 ዓ/ም

የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መቼ ይሰጣል ?

👉በወረቀት ፈተናቸውን የሚወስዱ ተፈታኞች ፦ ሐምሌ 1 ፣ ሐምሌ 2 እና ሐምሌ 3/2017 ዓ/ም

👉በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ1ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሐምሌ 1 ፣ ሐምሌ 2 እና ሐምሌ 3/2017 ዓ/ም

👉በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ2ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሐምሌ 4 ፣ ሐምሌ 7 እና ሐምሌ 8/2017 ዓ/ም


  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
5ኛ ዙር የ full stack development ስልጠና ምዝገባ በ ሃያሁለት ጀምረናል።

ከሚከተሉትን ያካትታል።
1. Python Programming Language
2. Front end Development (html,css, bootstrap and Javascript)
3. Backend development (PHP)
4. Database
5. Laravel Framework
6. Projects

በምዝገባ ላይ ነን :
☎️
0989747878
0799331774

በመራህያን የወደፊት ብሩህ ተስፋዎን የሚዘሩ ክህሎቶችን ይማሩ !!

አድራሻ፡ ሃያ ሁለት ፣ ከጐላጐል ወደ ቦሌ ሚወስደው ከ Hanan K Plaza አጠገብ ቢጫ ፎቅ ግራውንድ ፍሎር 10B

ለበለጠ መረጃ : @merahyan
#ከቴምር ሪልስቴት
🎯🎯7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ሣር ቤት አፓርትመንት እና ሱቅ ፒያሳ ለሽያጭ ያወጣነው 

👉2መኝታ 84ካሬ 5,392,800ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 94ካሬ 6,034,800ብር ሙሉ ክፍያ
👉3መኝታ 106ካሬ 6,869,400ብርሙሉክፍያ
👉3መኝታ 125ካሬ 8,025,000ብር ሙሉ ክፍያ

‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ 
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273
https://www.tg-me.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
የቡንደስሊጋው ሻምፒዮን ባየር ሙኒክ የሊጉን ዋንጫ በሜዳው አነሳ

ባየር ሙኒክ ከሞንች ግላድባህ ጋር በሜዳው ያደረገውን ጨዋታ 2ለ0 አሸንፏል።

ባየር ሙኒክ ተከታዩ ባየር ሊቨርኩሰን ከ ፍሬይ በርግ አቻ መለያየቱን ተከትሎ ለ34ኛ ጊዜ የጀርመን ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን ማረጋገጡ ይታወሳል።

2 ጨዋታዎች እየቀሩት ሻምፒዮን መሆን የቻለው ባየር ሙኒክ በሜዳው አሊያንዝ አሬና የሊጉን ዋንጫ አንስቷል። ኢንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጫዋች ሀሪ ኬንም የመጀመሪያ ዋንጫውን ከቡድን አባሎቹ እና ከደጋፊው ጋር አብሮ አጣጥሟል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
ETHIO-MEREJA®
Photo
በትግራይ ክልል እንዳትመሰክርብኝ በማለት የ14 ዓመት ታዳጊ በመድፈር በአሰቃቂ ሁኔታ የገደሉ ሁለት ግለሰቦች በእድሜ ልክ እስራት ተቀጡ

ያይንሸት ገብረዋህድ አመሃ የተባው ግለሰብ ነዋሪነቱ በፅምብላ ወረዳ ሲሆን መስከረም 25 ቀን 2016 ዓ/ም ከለሊቱ አምስት ሰዓት ላይ እንዳባጉና ከተማ ላይ ግሮሰሪ ከፍታ ራሷን የምታስተዳድርና የልጁ እናት የሆነቺውን ንግስቲ ገብረየውሃንስ የተባለች ሴት "አብረን እንደር ብየሽ እምቢ አልሺኝ" በሚል ቂም በመያዝና በቅናት በመነሳሳት ወደ መኖርያ ቤቷ በመግባት አልጋ ስር ተደብቆ በመቆየት የግል ተበዳይዋ በምትተኛበት ሰዓት ጭንቅላትዋ ላይ ሁለቴ በመምታት የግድያ ሙከራ መፈፀሙ የሰሜን ምእራብ ትግራይ ዞን አቃቢ ህግ አስታውቋል።

በዚህ ሳብያም ግለሰቡ በግድያ ሙከራ ወንጀል ተከሶ ጉዳዩ በፍርድ ሂደቴ ላይ ሳለ በዋስ እንዲወጣ ይፈቀድለታል። ይሄኔ ታድያ የግል ተበዳይ ልጅ የሆነችን የ14 ዓመት ታዳጊ ሄዋን ጎይትኦም በቀረበበት ክስ ላይ ምስክር ሆና መገለፆ በመገንዘብ እንዳትመሰክርብኝ በማለት በአሰቃቂ ሁኔታ ለመግደል አቅዶ ይንቀሳቀሳል።

በዚህም ታዳጊዋ አያቷ ጋር እንዳለች በማረጋገጥ ፈልጌሽ ነው ነይ በማለት ከአያቷ ቤት ይዟት በመውጣት ዓዲ ሰዱ እየተባለ ወደሚታወቅ ገደላማ ስፍራ ይዟት ይሄዳል። በመቀጠልም በአንገቷ በማነቅ መሬት ላይ የጣላት ሲሆን በሰአቱ አብሮት ከነበረ ተባባሪው መዓሾ ሰለሙን ደስታ የተባለ ግለሰብ ጋር በመሆን በታዳጊዋ ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመ ሲሆን የወንጀል ድርጊቱ ግን በዛ ያበቃ አልነበረም። የፈፀሙት ወንጀል እንዳይጋለጥ በሚል መረጃ ለማጥፋት በተደረገ ጥረት የታዳጊዋን ሁለት አይኖች በቢላ በማውጣት ተሸክመው ወደ ገደል በመወርወር ህይወቷ እንዲያልፍ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ቸዞኑ አቃቢ ህግ የፌ/ዲ/ሪ/ኢ የወንጀል ህግ አንቀፅ 539(1)(ሐ) በመጥቀስ በሁለቱም ግለሰቦች ላይ ግፍ የተሞላበት ወንጀል በመፈፀም ክስ የመሰረተ ሲሆን በዚህም መሰረት የቀረበለትን የክስ መዝገብ ሲመለከት የቆየው የዞኑ ፍርድ ቤት ሁለቱም ግለሰቦች በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ብይን መስጠቱን ብስራት ሬድዮ ከትግራይ ክልል ሰሜን ምእራብ ዞን አቃቢ ህግ ፅህፈት ቤት ያገኘው መረጃ ያሳያል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
ማንቼስተር ዩናይትድ 17ኛ ሽንፈቱን አስተናገደ

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ዩናይትድ በ2024/25 የውድድር ዘመን 17ኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል፡፡

በኦልድትራፎርድ ዌስትሃም ዩናይትድን ያስተናገደው ዩናይትድ ጃሮድ ቦውን እና ቶማስ ሱቼክ ባስቆጠሯቸው ግቦች 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡

በሌሎች የሊጉ 36ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጨዋታዎች ክሪስታል ፓላስ ቶተንሃምን 2 ለ 0 ሲያሸነፍ ኖቲንግሃም ፎረስት ከሌስተር ሲቲ 2 አቻ ተለያተዋል፡፡

በሌሎች ጨዋታዎች ኒውካስትል ዩናይትድ ቼልሲን 2 ለ 0 ሲረታ፤ ቶተነሃም በሜዳው በክሪስታል ፓላስ 2 ለ 0 ተሸንፏል፡፡ ኖቲንግሃም ፎረስት እና ሌስተር ሲቲ ያደረጉት ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
2025/06/30 15:08:48
Back to Top
HTML Embed Code: