Telegram Web Link
ETHIO-MEREJA®
Photo
አሜሪካ “የእኩለ ሌሊት መዶሻ” ባለችው የኢራኑ ጥቃት የትኞቹን የጦር መሳሪያዎች ተጠቀመች?

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች ኢራን ውስጥ የሚገኙ ሦስት የኒውክሌር ተቋማትን በቦምብ መደብደባቸውን ማሳወቃቸው ይታወሳል።

አሜሪካ “የእኩለ ሌሊት መዶሻ” የሚል ስያሜ በሰጠችው ኦፕሬሽን ጂቢዩ 57 ወይም ማሲቭ ኦርዲናንስ ፔኔትሬተር (ኤምኦፒ) ቦምብ ተጠቅማለች፡፡

ይህ ‘ምሽግ ደርማሽ’ ቦምብ 13 ሺህ 600 ኪሎ ግራም የሚመዝን ሲሆን ከመፈንዳቱ አስቀድሞ እስከ 60 ሜትር ድረስ ወደ መሬት ሰርጎ የመግባት አቅም ያለው ነው፡፡

ቦምቡ 'ቢቱ ስቲልዝ' በተባለው አውሮፕላን አማካኝነት ከዒላማው ከ12 ሺህ እስከ 15 ሺህ ሜትር ከፍታ ላይ የተጣለ ሲሆን ያለው ክብደት እና የመሬት ስበት በሚያርፈበት ቦታ ላይ ውድመት እንዲያስከትል ያደርጉታል፡፡

የተቀመጠለትን ዒላማ እንደማይስት የሚነገርለት 'ምሽግ ደርማሹ' ቦምብ በውስጡ በተገጠመለት ጂፒኤስ በመጠቀም ነው ጥቃቱን የሚያደርሰው፡፡

በዚህም ከተጣለ በኋላ ምንም ዓይነት የዒላማ ለውጥ ወይም ቁጥጥር ማድረግ አይቻልም፡፡

የአንዱ ዋጋ ከ3.5 እስከ 4 ሚሊዩን ዶላር እንደሚደርስም ተመላክቷል፡፡

ይህንን ግዙፍ ቦምብ መሸከም የሚችለው የ'ቢቱ ስቲልዝ' አውሮፕላን ባለው ቅርፅ በተለይም በፀረ-አውሮፕላን አነፍናፊ መሳሪያ ላይ ወፍ ወይም በራሪ መስሎ መታየት መቻሉ በዒላማ ማክሸፊያ እንዳይመታ ያስችለዋል፡፡

በተጨማሪም ትክክለኛ ያልሆነ የራዳር መረጃ የሚያቀብል የኤሌክትሮኒክ ቴክኒክ ያለው ነው፡፡

ሌላው አሜሪካ የተጠቀመችው ከ1 ሺህ 600 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መወንጨፍ የሚችሉት የ'ቶማሃውክ ክሩዝ' ሚሳኤሎች ናቸው፡፡

ከሰርጓጅ መርከብ ላይ የተነሱት ሚሳኤሎቹ ከምድር በታች ያልሆነ ማለትም በምድር ላይ ያለ ዒላማን ለማጥቃት የሚውሉ ናቸው፡፡

በአሜሪካ የ“ሌሊት መዶሻ ኦፕሬሽን” 30 የሚሆኑ የ'ቶማሃውክ ክሩዝ' ሚሳኤሎች ከ640 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መወንጨፋቸው ተገልጿል፡፡

በራዳር ዕይታ ውስጥ እንዳይገባ በዝቅተኛ ከፍታ ላይ መንሳፈፍ የሚችለው ሚሳኤሉ ከተወነጨፈ በኋላ የዒላማ ብሎም የአቅጣጫ ቅየራ እንዲያደርግ ማዘዝ ይቻላል፡፡እያንዳንዱ 'ቶማሃውክ ክሩዝ' ከ1.5 እስከ 2 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ዋጋ ያለው ነው፡፡

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
77👏9👍3👎3
💸💲 ይመልሱ 10,000 ብር ያሸንፉ💲💸

በእግር ኳስ ታሪክ ብዙ የፊፋ ያለም ዋንጫ ያሸነፈ ሀገር ማን ነው

ትክክለኛውን ውጤት በአፍሮ ስፖርት የቴሌግራም  ወይም ፌስቡክ ቻናላችን ላይ ገብተው በመመለስ 10 ሺ ብር ይሸለሙ!

https://www.tg-me.com/afrosportsbet/663
https://www.facebook.com/share/p/1GfvEbhS7B/
15
#ቴምር ሪልስቴት
‼️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ፒያሳ ለሽያጭ ያወጣነው ሱቅ

‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ 
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273
https://www.tg-me.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Telegram :@KalTemerRealEstate
14
ኢራን በኢራቅ በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ የሚሳኤል ጥቃት ማድረሷን ተከትሎ ኳታር በኢራን ለተቃጣባት ጥቃት ተመጣጣኝ ምላሽ እንደምትሰጥ አስታውቃለች❗️

ማምሻውን በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮችን ማጥቃት የጀመረችው ኢራን በምዕራባዊ ኢራቅ የሚገኘውን አል-አሳድ የጦር ሰፈር በሚሳኤል መደብደቧን ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል።

ከሰዓታት በፊት የኢራን መንግሥት በኒውክሊየር መሰረተ ልማቶቹ ላይ በአሜሪካ ለተፈጸመበት ጥቃት ምላሽ እንደሚሰጥ ዝቶ ነበር።

በተያያዘ ኳታር በኢራን ለተቃጣባት ጥቃት ተመጣጣኝ ምላሽ እንደምትሰጥ አስታውቃለች።

የኳታር መከላከያ ሚኒስትር፥ ኢራን ኳታር በሚገኘው አል-ኡዴይድ የጦር ሰፈር ላይ ሚሳኤል ተኩሳለች፤ በዚህም ኢራን የኳታርን ሉዓላዊነት ተዳፍራለች ብለዋል።

ኳታር ከኢራን ለተቃጣበት ጥቃት ተመጣጣኝ ምላሽ የመስጠት መብቷ በዓለም አቀፍ ሕግ የተጠበቀ መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል። አክለውም፥ የኳታር የአየር መከላከያ ሥርዓት የከኢራን የተተኮሱ ሚሳኤሎችን በማክሸፍ ጥቃቱን መመከቱንም ተናግረዋል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
54😁20👏3🤔1😭1
ሳውዲ አረቢያ ኢራን "በኳታር ላይ" የፈጸመችውን ጥቃት አወገዘች
****

የሳውዲ አረቢያ መንግሥት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ በኩል ባወጣው መግለጫ ኢራን ማምሻውን "በኳታር ላይ" የፈጸመችውን ጥቃት በጽኑ አውግዟል።

የሳውዲ መንግሥት በመግለጫው ኢራን "በኳታር ላይ" ያደረሰችውን የሚሳኤል ጥቃት በጽኑ አውግዞ፤ ድርጊቱ የኳታርን ሉዓላዊነት፣ ዓለም አቀፍ ሕግና ቻርተርን እንዲሁም የመልካም ጉርብትና መርሆን የጣሰ ነው ብሏል።

አያይዞም፥ ድርጊቱን ከማውገዝ ባሻገር ኳታር ሉዓላዊነቷን ለማስከበር የምትወስዳቸውን እርምጃዎች ሳውዲ አረቢያ ትደግፋለች፤ ከጎኗ በመሆን ለማገዝም ዝግጁ ናት ብሏል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
38👎14👍4😁1
ETHIO-MEREJA®
Photo
"ኢራንን አመሰግናለሁ" – ፕሬዝዳንት ትራምፕ፤ "ለሰጠችን ደካማ ምላሽ እና ለቅድመ ማስጠንቀቂያው"

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ በኢራን እና በአሜሪካ መካከል የነበረውን የጦርነት ስጋት ሙሉ በሙሉ ያረገበ በሚመስል መግለጫ፣ ኢራን ለሰጠችው "ደካማ" የአጸፋ ምላሽ እና ለሰጠችው የቅድመ ማስጠንቀቂያ ምስጋና አቅርበዋል።

ፕሬዝዳንቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት አዲስ መልዕክት፣ የኢራንን ምላሽ "እጅግ በጣም ደካማ" ሲሉ የገለጹት ሲሆን፣ ዩናይትድ ስቴትስም ጥቃቱን "በጣም ውጤታማ በሆነ መንገድ" መመከቷን አስታውቀዋል።

"ኢራን የኑክሌር ተቋሞቿን ማውደማችንን ተከትሎ፣ እጅግ በጣም ደካማ የሆነ ምላሽ ሰጥታለች፤ ይህንንም እንጠብቅ ነበር" ብለዋል። "በአጠቃላይ 14 ሚሳኤሎች ተተኩሰው ነበር፤ ከእነዚህ ውስጥ 13ቱን መትተን ጥለናል፤ አንደኛው ደግሞ ጉዳት ወደማያደርስ አቅጣጫ ስለነበር 'በነጻ ለቀነዋል'። አንድም አሜሪካዊ ጉዳት እንዳልደረሰበት እና ምንም አይነት ውድመት እንዳልተፈጠረ ስገልጽ በደስታ ነው።"

"ከሁሉም በላይ አስፈላጊው ነገር፣ በውስጣቸው የነበረውን ሁሉ ከ'ሲስተማቸው' ውስጥ ማውጣታቸው ነው፤ ተስፋ እናደርጋለን ከዚህ በኋላ ጥላቻ አይኖርም። ኢራን የሰው ህይወት እንዳይጠፋና ማንም እንዳይጎዳ ላደረገችው የቅድመ ማስጠንቀቂያ ላመሰግናት እወዳለሁ።"

"ምናልባት ኢራን አሁን በክልሉ ውስጥ የሰላምንና የስምምነትን መንገድ መቀጠል ትችል ይሆናል፤ እኔም እስራኤል ይኸንኑ እንድታደርግ በሙሉ ልብ አበረታታታለሁ። ለዚህ ጉዳይ ትኩረት ስለሰጣችሁ አመሰግናለሁ!"

ይህ የፕሬዝዳንት ትራምፕ መግለጫ፣ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የነበረውን ቀጥተኛ ወታደራዊ ፍጥጫ በይፋ የሚያጠናቅቅ ይመስላል። ፕሬዝዳንቱ የኢራንን ምላሽ "ደካማ" በማለት የአሜሪካንን የበላይነት ቢያሳዩም፣ በተመሳሳይ ጊዜ ለሰላም በር በመክፈትና ምስጋና በማቅረብ ሁኔታው እንዲረጋጋ ያላቸውን ፍላጎት አመላክተዋል።

የፕሬዝዳንቱ ጥሪ እስራኤልንም ማካተቱ፣ አሁን ትኩረት የተደረገበት የእስራኤልና የኢራን ግጭት እንዲቆም የሚገፋፋ ሲሆን፣ ቀጣናው ከገባበት የጦርነት አዙሪት እንዲወጣ የሚያደርግ ነው ተብሎለታል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
57👍6😱2
በአዲስ አበባ በትራፊክ አደጋ የሦስት ዓመት ሕጻንን ጨምሮ የ9 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በዛሬው ዕለት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሦስት ዓመት ሕጻንን ጨምሮ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ እንደገለፁት÷ አደጋው በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ አባሳሙኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው የተከሰተው፡፡ ከኃይሌ ጋርመንት ወደ ዩኒሳ አደባባይ ይጓዝ የነበረ የፐብሊክ ሰርቪስ አውቶቡስ ከከባድ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ መንገድ ስቶ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ መግባቱን አብራርተዋል፡፡

ይህን ተከትሎም አውቶቡሱ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ ከገባ በኋላ ከዩኒሳ አደባባይ ወደ ኃይሌ ጋርመንት ሲጓዝ ከነበረ ዶልፊን ተሽከርካሪ ጋር መጋጨቱን ነው የገለጹት፡፡ በዚህም በዶልፊኑ ውስጥ ከነበሩት ተሳፋሪዎች መካከል አሽከርካሪውን ጨምሮ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተናግረዋል። ከሟቶቹ መካከል የ3 ዓመት ሕጻን እንደሚገኝ ጠቁመው÷ በአደጋው 8 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን አመልክተዋል፡

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
46😭29🤯3🥰2
እስራኤል እና ኢራን ዘላቂ ተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸውን ትራንፕ አስታወቁ

እስራኤል እና ኢራን ዘላቂ ተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸውን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስታወቁ።

ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት ጽሁፍ፥ ከ24 ሰዓት በኋላ ተግባራዊ በሚሆነው ስምምነት በሁለቱ ሀገራት መካከል ላለፉት 12 ቀናት ሲካሄድ የቆየው ጦርነት በይፋ ያበቃል ብለዋል።

የእስራኤል መከላከያ በትራምፕ ሀሳብ ዙሪያ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል። ኢራንም እስካሁን በጉዳዩ ላይ ያለችው ነገር አለመኖሩን አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
29👎9👏2😁2🥰1
ETHIO-MEREJA®
እስራኤል እና ኢራን ዘላቂ ተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸውን ትራንፕ አስታወቁ እስራኤል እና ኢራን ዘላቂ ተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸውን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስታወቁ። ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት ጽሁፍ፥ ከ24 ሰዓት በኋላ ተግባራዊ በሚሆነው ስምምነት በሁለቱ ሀገራት መካከል ላለፉት 12 ቀናት ሲካሄድ የቆየው ጦርነት በይፋ ያበቃል ብለዋል። የእስራኤል መከላከያ…
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ "የ12 ቀኑን ጦርነት" ለማስቆም የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት በድል አድራጊነት ካወጁ ከሰዓታት በኋላ፣ ኢራን በእስራኤል ላይ አዲስ የሚሳይል ጥቃት መሰንዘሯ የሰላም ተስፋውን ጥያቄ ውስጥ ከቶታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እስራኤልም በበኩሏ በኢራን ግዛት ውስጥ ያሉ ኢላማዎችን መምታቷን እንደምትቀጥል አስታውቃለች።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዳስታወቁት፣ ሀገራቸው ምንም ዓይነት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ አልደረሰችም። ሚኒስትሩ አክለውም "እስራኤላውያን ወረራቸውን ካቆሙ፣ ኢራንም መተኮሷን ታቆማለች" በማለት የኢራን እርምጃ በእስራኤል ድርጊት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ መግለጫ ትራምፕ ካወጁት ስምምነት ጋር በቀጥታ የሚጋጭ ነው።

በሌላ በኩል የእስራኤል ባለሥልጣናት ዋነኛ ግባቸው የነበረው የኢራንን የኑክሌር አቅም ማዳከም እንደተሳካ ቢገልጹም፣ ወታደራዊ ዘመቻቸው ግን ገና እንዳላለቀ አስታውቀዋል። ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የእስራኤል ባለሥልጣናት ለመገናኛ ብዙኃን እንደተናገሩት፣ በኢራን ውስጥ ሊመቷቸው የሚፈልጓቸው በርካታ ወታደራዊ ኢላማዎች አሁንም አሉ።

የተኩስ አቁም ስምምነቱ ቢታወጅም፣ ኢራን ለ25ኛ ጊዜ የሰነዘረችው የሚሳይል ጥቃት እና የእስራኤል ጥቃቱን የመቀጠል ዛቻ፣ እንደሚያሳየው፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ወታደራዊ ፍጥጫ አሁንም እንደቀጠለ ነው።

ይህ ሁኔታ የትራምፕ አስተዳደር ያወጀው ስምምነት በዋና ተዋናዮቹ ዘንድ ሙሉ ተቀባይነት ሳያገኝ የተደረገ የችኮላ መልዕክት ነው ወይ? የሚል ጥያቄ እንዲነሳ አድርጓል። በቀጣዮቹ ሰዓታትና ቀናት ውስጥ የሁለቱ ሀገራት ድርጊት የግጭቱን እውነተኛ አቅጣጫ የሚወስን ይሆናል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
65🥰2
New Workshop Alert!

🎨 Graphic Design Workshop – June 25! Learn. Create. Grow.

Online Workshop

Join us this June 25 for a hands-on workshop covering design tools, color theory, branding, and more. Perfect for beginners and aspiring designers.
📍 Limited seats available – reserve your spot now!

Includes certificate, & project-based learning

registration after the workshop:
          ☎️
0989747878
0799331774

For more info: @merahyan
6
የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የማለፊያ ውጤት 50 በመቶ እንዲሆን ተወሰነ

👉 የከተማ አቀፍ ፈተናው ውጤት ዛሬ ከሰዓት ይፋ ይደረጋል


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት፤ የ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የማለፊያ ውጤት 50 በመቶ እንዲሆን በዛሬው ዕለት ውሳኔ አስተላልፈዋል።

የቢሮው ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በከተማ አስተዳደሩ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በየዓመቱ መሻሻል እያሳየ መሆኑን ገልጸው ዘንድሮም ከአምናው የተሻለ ውጤት ለመመዝገብ መቻሉን አስታውቀዋል።

በዚህም መሠረት የተፈታኞች ውጤት ዛሬ ከሰዓት ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

በቀጣይ ጥቂት ቀናትም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ውጤት ይፋ እንደሚደረግ ተመላክቷል፡፡

የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ሰኔ 3 እና 4 ቀን 2017 ዓ.ም በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 194 የመፈተኛ ጣቢያዎች መሰጠቱ የሚታወስ ሲሆን፤ 70 ሺህ 525 ተማሪዎች የመልቀቂያ ፈተናውን ወስደዋል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
61😱3
✈️ በአፍሮ ስፖርት አቪያተር 98% የማሸነፍ ዕድል እንዳሎት ያውቃሉ! ✈️

💰ከአፍሮ ጋር ወደ ከፍታ ይብረሩ እና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ብሮችን ይሰብስቡ! 💸💸

🚀 እና ምን ይጠብቃሉ https://bit.ly/3XbY3o7 ይግቡና አሸናፊ ይሁኑ። ዛሬውኑ ይመዝገቡ እና መጫወት ይጀምሩ!

@afrosportsbet
14👍1
ዜና፡ “እኔ በወልቃየትም ይሁን ጸገዴ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እንጂ የማንነት ጥያቄ አለ ብየ አላምንም” - አቶ ጌታቸው ረዳ

“እኔ በወልቃየትም ይሁን ጸገዴ የማንነት ጥያቄ አለ ብየ አላምንም” ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ለአዲስ ሰታንዳርድ አስታወቁ፤ “የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ጥያቄ እንዳለ አውቃለሁ” ብለዋል።

ትላንት ሰኔ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በሁመራ የተካሄደውን ውይይት ተከትሎ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ባወጣው ሪፖርት “የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ የማንነት ጥያቄ ተገቢ መኾኑን እናምናለን ብለዋል” ሲል ያወጣው ሪፖርት አስተባብለዋል።

ዛሬ ሰኔ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ቀትር ላይ በጉዳዩ ዙሪያ አዲስ ስታንዳርድ የጠየቃቸው አቶ ጌታቸው “ከአውዱ ውጭ የተወሰደ ነው” ብለዋል።

በመድረኩ ላይ የገለጽኩት “እኔ በወልቃየትም ይሁን ጸገዴ የማንነት ጥያቄ አለ ብየ አላምንም፣ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ጥያቄ እንዳለ አውቃለሁ፤ ያም ሁኖ ግን የእኔ እምነት እንደተጠበቀ ሁኖ፣ እዚህ ያላችሁ ሰዎች አለ ብላችሁ የምታምኑ ከሆነ፣ የሆነ ይሁን ጥያቄ በሰላማዊ እና በህጋዊ መንገድ ብቻ ነው መፈታት ያለበት” የሚል ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በመድረኩ ላይ የነበሩት አብዘሃኛዎቹ የአስመላሽ ኮሚቴ መሆናቸው በመግለጽ “ወደ ደጋውም ወጥተን ህዝቡም ጋር ተነጋግረን የህዝቡ ስሜት ምን እንደሆነ በተሟላ መልኩ ለመረዳት እንሞክራለን” ስለ ነግሬያቸዋለሁ ብለዋል።

“ዋናው ነገር ግን ሁሉም ጉዳዮች በሰላም እና በህጋዊ መንገድ መፈታት  እንዳለባቸው ማመናችን ላይ” መሆኑን ትኩረት ያደረገ ገለጻ ነው የሰጠሁት ሲሉ አስታውቀዋል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
81👎18👍3😱2
በእስራኤል ጥቃት ተገደሉ የተባሉ 3 የጦር መሪዎች የኢራን የድል በዓል ላይ ተገኙ

በእስራኤል ጥቃት ተገደሉ የተባሉ 3 የኢራን ጦር መሪዎች የኢራን የድል በዓልን ከሕዝብ ጋር ሲያከብሩ መታየታቸውን አናዶሉ እና የኢራን የሀገር ውስጥ ብዙኃን መገናኛዎች ዘግበዋል።

እስራኤል ከሰኔ 13 ጀምሮ የኢራን የጦር ጀኔራሎችን መግደሏን ያስታወቀች ሲሆን፤ ሦስቱ የኢራን የጦር መሪዎች በትናንትናው ዕለት ኢራን የድል በዓሏን ስታከብር ከህዝቡ ጋር በመገኘት አክብረዋል ብለዋል ምንጮቹ።

ከዚህ ውስጥ አንዱ የሆኑት የእስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ኮርፕስ ቁድስ ኃይል አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ኢስማኢል ቃኣኒ በዓሉን ከሕብ ጋር ማክበራቸውን የኢራቅ የሀገር ውስጥ ብዙኃን መገናኛዎች ዘግበዋል።

በኢራን ታስኒም የዜና አገልግሎት የተለጠፈ ቪዲዮ ቃአኒ በዝግጅቱ ላይ ከተሰበሰቡት መካከል አሳይቷል።

በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ቃአኒ በእስራኤል ጥቃት ከተገደሉት የኢራን ጦር መሪዎች መካከል አንዱ እንደሆኑ ዘግቦ እንደነበር የሚታወስ ነው።

በተመሳሳይ የወቅቱ የመከላከያ ሚኒስትር እና የአየር ኃይል አዛዥ የነበሩ ብርጋዴር ጄኔራል አዚዝ ናስርዛዴህ በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ በመከላከያ ሚኒስቴር ላይ በተፈፀመ የአየር ጥቃት ተገድለዋል ተብለው የነበረ ቢሆንም በሕይወት እንዳሉ እና አሁንም በስልጣን ላይ እንደሚገኙ ተስኒም የዜና ወኪል ዘግቧል።

የአያቶላህ አሊ ኻሚኒ ከፍተኛ አማካሪ እና የደህንነት ዋና አማካሪ አድሚራል አሊ ሻምካኒ እ.ኤ.አ ሰኔ 13 ቀን 2025 በእስራኤል የአየር ጥቃት መሞታቸው ከተነገሩት አንዱ የነበሩ ናቸው። አድሚራል አሊ ሻምካኒ በድል በዓሉ ላይ በመገኘት የድል በዓሉን አክብረዋል ሲሉ የኢራን የዜና ወኪሎች ዘግበዋል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
128😁44👍11🥰6🤯1
2025/07/14 15:27:19
Back to Top
HTML Embed Code: