Telegram Web Link
" ራኒቲዲን ካንሰርን ሊያመጣ የሚችል ንጥረ ነገር በውስጡ በመገኘቱ ምክንያት ታግዷል " -  የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን

ለጨጓራ ተያያዥ ህመሞች በመድኃኒትነት ጥቅም ላይ ሲውል የነበረው ' ራኒቲዲን ' የተባለው መድሃኒት በኢትዮጵያ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዳይውል ማገዱን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን አሳውቋል።

የባለስልጣኑ የመድኃኒት ደህንነት ክትትልና የሕክምና ሙከራ መሪ ስራ አስፈጻሚ አስናቀች ዓለሙ ፤ " በመጀመሪያ ደረጃ በሌሎች ሀገር የወጡ ሪፖርቶችን አይተን ነበር። ስለዚህ በሀገራችንስ ይሄ መድሃኒት እንዴት ነው ?  የሚለውን በማገናዘብ የላብራቶሪ ምርመራ አድርገናል " ብለዋል።

በዚህም መድሃኒቱ ካንሰር ሊያመጣ የሚችል ንጥረ ነገር እንደተገኘበት መሪ ስራ አስፈፃሚዋ ገልፀዋል።

" በመሆኑም ይህንን መድሃኒት ከምዝገባ ፋይላችን አውጥተናል። የተሰራጩ መድሃኒቶችም እንዲሰበሰቡ እና ጥቅም ላይ እንዳይውሉ " ብለዋል።

" በዚህ በሰረትም ጥቅም ላይ እንዳይውል ታግዷል " ሲሉ አረጋግጠዋል።

" የጤና ባለሙያዎችም፣ የጤና ተቋማትም ሌሎች አማራጭ መድሃኒቶችን እንዲያዙ እና እንዲጠቀሙ ይህንን መድሃኒት እንዳይጠቀሙ " ሲሉም አሳስበዋል።

     T.me/ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
🌺Original Philips Steam Iron®

2000Watt & high steam output
Easy and effective
4steam settings
220 ml water tank
durable steam performance
Continuous steam up to 25g/min
Integrated water spray evenly

ዋጋ፦  💰🏷 3,600 ብር

📍ውስን ፍሬ ነው ያለን/ Limited Stock

        ☎️ 0901882392
        ☎️ 0931448106
Moving Helpers | Furniture Mover

Home moving furniture caster wheel heavy objects transporter small mover labor-saving moving wheels bed tool

የተለያዩ የቤት ውስጥ እቃዎችን ከአንድ ቦታ ወደ0 ሌላ ቦታ ማንቀሳቀሻ፣ ምርጥና ከብረት የተሰራ!

      💠ዋጋ፦ 1400 ብር

        ☎️ 0901882392
        ☎️ 0931448106
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነርን ጨምሮ ከ 6 በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን የአውሮፓ ኅብረት ሹማን ሽልማት ተበረከተላቸው

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት ልዑክ ቅጥር ግቢ በተካሄደ የአውሮፓ ኅብረት ሹማን ሽልማት (Schuman EU Awards) የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ ( ዶ/ር ) ጨምሮ ከስድስት በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ሽልማቱን ማግኘት ችለዋል ።

የዘንድሮው የአውሮፓ ኅብረት የሹማን ሽልማት ከተቀበሉት መካከል:- ጋሪ ኢስማኤል ዩሱፍ – የሆርሙድ የሴቶች ማኅበር መሪ፣ ጌቱ ሳቀታ – የአፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብቶች ሊግ መሥራች፣ መላኩ በላይ – የፈንዲቃ የባህል ማእከል መሥራች፣
መልካሙ ኦጎ – የቁም ለአካባቢ ሊቀ-መንበር፣ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር፣
ያሬድ ኃይለማርያም- የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማእከል ዋና ዳይሬክተር ይገኙበታል።

ይህ ሽልማት የአውሮፓ ኅብረት ሹማን ሽልማት “ዴሞክራሲን፣ የሕግ የበላይነትን፣ ሰብአዊ መብቶችን፣ መቻቻልን እና እኩልነትን በማስፋፋት ረገድ የላቀ አስተዋጽዖ ላበረከቱ ሰዎች” ዕውቅና የሚሰጥ መሆኑ ተነግሯል።

     T.me/ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
Sanford Room Heater / የቤት_ማሞቂያ

ለቀጣዩ ክረምት ከአሁኑ ይዘጋጁ!

በክረምት ሙቀት የሚሰጥ በበጋ ማቀዝቀዝ የሚችል ፋን ያለዉ Cool/Warm/Hot wind selection የራሱ የሙቀት መቆጣጠሪያ ያለዉ ሁሌም ሊጠቀሙበት የሚችሉት ዕቃ

👉Adjustable thermostat control
👉Cool/Warm/Hot/Wind selection
👉Overheat protection
👉Automatic control temperature
👉Power indicator light፣ 2000watt
👉Intergral carry handle

💦 ዋጋ፦ 3800ብር

       ☎️ 0901882392
       ☎️ 0931448106
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ህወሓት መልሶ ሕጋዊ እውቅና እንዲያገኝ የሚያስችለዉን የአዋጅ ማሻሻያ ወደ ፓርላማ መራ!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት “ከሕጋዊ እና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማዕቀፍ ውጪ” ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የፖለቲካ ቡድኖች መልሰው እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ለመመዝገብ የሚያስችላቸውን ድንጋጌ የያዘ የአዋጅ ማሻሻያን ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መራ።

በሥራ ላይ ባለው “የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ” ላይ የተደረገው ይህ ማሻሻያ፤ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የተሰረዘበትን የፓርቲነት ሕጋዊ እውቅና መልሶ እንዳያገኝ ያደረገውን የሕግ ጥያቄ የሚመልስ ነው።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአዋጅ ማሻሻያውን ተቀብሎ ወደ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመራው ዛሬ አርብ ግንቦት 23/2016 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ እንደሆነ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ጽህፈት ቤቱ ያወጣው መረጃ እንደሚያስረዳው ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት በአራት ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

ከእነዚህ ረቂቆች መካከል በሕገ ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አድርጎ ስለማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የቀረበው አዋጅ ይገኝበታል።

በተጨማሪም የንብረት ማስመለስ አዋጅ እና የነዳጅ ውጤቶች የግብይት ሥርዓትን ለመደንገግ የቀረበው አዋጅም ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ ውሳኔ የተሰጠባቸው ሕጎች ናቸው።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፤ በዛሬው ስብሰባ ውሳኔ እንደተላለፈበት በቀዳሚነት የጠቀሰው የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ አዋጅ ነው። ማሻሻያ የቀረበበት በ2012 ዓ.ም. የወጣው የምርጫ ሕግ፤ እውቅና የተነፈጉ የፖለቲካ ፓርቲዎችን መልሶ ከመመዝገብ ጋር በተያያዘ ክፍተት ያለበት እንደሆነ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ጠቅሷል።

“ከሕጋዊ እና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማዕቀፍ ውጪ የቆዩ የፖለቲካ ቡድኖች በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ ፍላጎት በሚያሳዩበት ጊዜ እነዚህን አካላት ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ አድርጎ ለመመዝገብ የሚያስችል ሥርዓት በነባሩ አዋጅ ላይ አልተካተተም” ሲል በሥራ ላይ ያለው አዋጅ ላይ የታየውን ክፍተት ይገልጻል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ የመራው ማሻሻያ ላይ የፖለቲካ ቡድኖች “በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ እና ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ፍላጎት በሚያሳዩበት ጊዜ” መልሰው ለመመዝገብ የሚችሉበትን ሥርዓት የሚዘረጋ እንደሆነም ተጠቅሷል።

ዛሬው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔ ላይ የተጠቀሰው የፖለቲካ ቡድኖች መልሶ የመመዝገብ ጉዳይ ከህወሓት ዳግም ሕጋዊ እውቅና የማግኘት ጉዳይ ጋር በተያያዘ ውዝግብ ፈጥሮ ነበረ ጉዳይ መሆኑ ይታወሳል።(ቢቢሲ)

     T.me/ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
ETHIO-MEREJA®
Photo
አቡነ ሉቃስ በተከሰሱበት የቅስቀሳ ወንጀል በ6 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወሰነ

አቡነ ሉቃስ በተከሰሱበት የቅስቀሳ ወንጀል ጥፋተኛ በተባሉበት ድንጋጌ በሥድስት ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወሰነ።

የቅጣት ውሳኔውን የወሰነው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ሕገ-መንግሥታዊና በሕገ-መንግሥት ሥርዓት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀል ጉዳዮች የሚመለከተው ችሎት ነው።

የፍትሕ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ በአቡነ ሉቃስ ላይ ከሦስት ወራት በፊት÷ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 247 (ሐ) እና አንቀጽ 258 (ሀ) ሥር እና የወንጀል ሕግ አንቀጽ 251 (ሐ) የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል የሚሉ ሁለት ክሶች ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

ተከሳሹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ-ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና የምሥራቅ አውስትራሊያ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣ በጠቅላይ ቤተክኅነት የገዳማት መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ-ጳጳስ ሆነው በማገልገል ላይ እያሉ ስለ ሰላም እና አንድነት የመስበክ ሐይማኖታዊ ግዴታቸውን በመተው ታኅሣስ 19 ቀን 2016 ዓ.ም በአሜሪካ ቴክሳስ እና አካባቢው በሚገኝ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ-ክርስቲያን ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ቤተ-ክርስቲያን ታቦት ወጥቶ በቆመበት ዐውደ-ምኅረት ላይ የአመፅ ቅስቀሳ ማድረጋቸውን የክስ ዝርዝሩ ያስረዳል፡፡

የዐቃቤ ሕግን ማስረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የተከሰሱባቸው ክሶች በአንቀጽ 247 (ሐ) ሥር ተጠቃልሎ የጥፋተኝነት ፍርድ ማስተላለፉ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም ዐቃቤ ሕግ ካቀረባቸው ሦስት የቅጣት ማክበጃ አስተያየቶች መካከል ፍርድ ቤቱ አንዱን የቅጣት ማክበጃ አስተያየት በመያዝ እና ተከሳሹም የቀደመ የወንጀል ሪከርድ የሌለባቸው መሆኑን መነሻ በማድረግ አንድ የቅጣት ማቅለያ ተይዞላቸው ዛሬ በዋለው ችሎት የቅጣት ውሳኔ ተሰጥቷል።

በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ በእርከን 23 ሥር በሥድስት ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ በሌሉበት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ (በታሪክ አዱኛ)

     T.me/ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
ሟችን የግብረ-ስጋ ግንኙነት በመፈፀም ሕይወቷ እንዲያልፍ ያደረገው ግለሰብ በጽኑ እስራት ተፈረደበት

ከሟች መኖሪያ ቤት በመግባት አፏን በጨርቅ ጠቅጥቆ፣ አንገቷን አንቆ በመያዝ የግብረ-ስጋ ግንኙነት በመፈፀም ሕይወቷ እንዲያልፍ ያደረገው ግለሰብ በጽኑ እስራት ተፈረደበት

አላዩ ሞገስ ደሳለኝ የተባለ ተከሳሽ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ በግምት 1፡30 ሲሆን በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ሽሮ ሜዳ አዲስ ተስፋ ትምህርት ቤት አካባቢ የ14 ዓመት የሆነችውን የግል ተበዳይ የምትኖርበት መኖሪያ ቤት በመግባት በጥፊ በመምታት፣ እንዳትጮህ አፏ ውስጥ ጨርቅ በመጠቅጠቅ እና አንገቷን በሁለት እጁ አንቆ በመያዝ በኃይል የግብረ-ስጋ ግንኙነት የፈጸመባትና አፏ ውስጥ ጨርቅ በመጠቅጠቁ እና አንገቷን በማነቁ ምክንያት ትንፋሽ አጥሯት ሕይወቷ እንዲያልፍ በማድረጉ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ተጣርቶ በፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት በወ/ሕ/አ/620/2/ሀ/ እና /3/ መሰረት በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 11ኛ ወንጀል ችሎት ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በክርክሩ ሂደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶ የመከላከያ ምስክሮችን ያሰማ ቢሆንም የቀረበበትን ክስ ሊከላከል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት በ19 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

(ፍትህ ሚኒስቴር)

     T.me/ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
2024/06/01 08:17:30
Back to Top
HTML Embed Code: