Telegram Web Link
M13 Samsung 128/6
Slightly used
fixed coast 14000etb

አናግሩን👇
@ethio_sellerr
ከሳውዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን ወደ ሀገር በመመለስ ስራ እስካሁን ከ9ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን መመለሳቸው ተነገረ።

በዛሬው እለት በሶስት ዙር በረራ 1 ሺህ 181 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ሁሉም ወንዶች እንደሆኑና 4 እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙበት የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታውቋል።

@sheger_press
@sheger_press
ኢትዮጵያ ፤ የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት እቅድ እንዳላትና ለእርሱም እየሰራች ነዉ ተባለ

ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አመታት የአፍሪካ ዋንጫ ውድድርን እንድታዘጋጅ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ መናገራቸውን ዳጉ ጆርናል ታዝቧል።

የአፍሪካ ዋንጫን እ.ኤ.አ በ 2029 ወይም በ2031 ለማዘጋጀት እየሰራን ነው ያሉት ሚኒስትሩ ለእቅዱ መሳካትም ቢያንስ ስድስት ደረጃቸውን የጠበቁ ስታዲየሞች አስፈላጊ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ካፍ ከዚህ በፊት ያልነበሩ አዳዲስ መስፈርቶችን በማስቀመጡ ኢትዮጵያ አንድም ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም እንዳይኖራት አድርጓል ሲሉም አቶ ቀጀላ መርዳሳ አስረድተዋል። ኢትዮጵያ የካፍን ደረጃ የሚመጥኑ ስታዲየሞች የሌላት በመሆኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ረዘም ላሉ ጊዜያት ከሀገሩ ዉጪ ለመጫወት ተገድዶ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።

የዉድድሩ አዘጋጅ ሀገራት ቢያንስ ስድስት ስታዲየሞችን እንዲያዘጋጁ ካፍ ቢያዝም ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ ምን ያህል ዝግጁ ናት የሚለዉ ግን አጠያያቂ ነዉ።

Via ዋልታ
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ የነበሩት አቶ ታዬ ደንደአ የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍና ጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው።

ክሱ የተመሰረተው በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሕገ-መንግስትና ሕገ-መንግስት ሥርዓት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀል ጉዳዮችን በሚመለከተው ችሎት ነው።

የፍትሕ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በተከሳሽ ታዬ ደንደአ ላይ ሶስት ክሶችን አቅርቧል።

በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 251/ሐ እና አንቀጽ 257/ሰ ስር የተመላከተውን ድንጋጌ እና የጦር መሳሪያ አዋጅን መተላለፍ የሚል ክስ አቅርቦባቸዋል።

በክሱ ላይ እንደተመላከተው÷ተከሳሹ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ ሆነው ሲሰሩ የሀገርን፣ የመንግስትንና የህዝብን ደህንነት ማረጋገጥ ሲገባቸው ይህን ወደጎን በመተው ፀረሰላም ኃይሎችን የሚደግፉ የፕሮፖጋንዳ መልዕክቶችን በማስተላለፍ በስማቸው በተከፈተ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ድጋፍ የሚገልጹ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ ነበር የሚል ነው፡፡

እንዲሁም ፍቃድ ሳይኖራቸው የጦር መሳሪያ አዋጁን በመተላለፍ በታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ከረፋዱ 5 ሰዓት ላይ በልደታ ክ/ከ ወረዳ 6 በሚገኝ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በተደረገ ብርበራ አንድ ታጣፊ ክላሽን ኮቭ መሳሪያ ከ2 ክላሽ ካዝና እና ከ60 ጥይት ጋር ይዘው መገኘታቸው ተጠቅሶ ክስ ቀርቦባቸዋል።

ተከሳሽ አቶ ታዬ ደንደአ በአራት ጠበቆቻቸው ተወክለው ችሎት ቀርበው የክስ ዝርዝሩ ተነቦላቸዋል።

ክሱ ከተነበበ በኋላ በጠበቆቻቸው በኩል የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጥያቄ ቀርቧል።
የችሎት ዘገባው የፋና ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኬንያ እና ኢትዮጵያ የንግድ ማነቆዎችን ለማስወገድ አዲስ ጥረት እንደጀመሩ ዘ ስታር ጋዜጣ ዘግቧል።

አዲሱ ጥረት የተገለጠው፣ የኬንያና ኢትዮጵያ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ቡድን ሰሞኑን በአዲስ አበባ የጋራ ስብሰባውን ባደረገበት ወቅት ነው።

በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2022 ኬንያ 95 ሚሊዮን ዶላር የሚገመቱ ሸቀጦችን ወደ ኢትዮጵያ የላከች ሲኾን፣ ኢትዮጵያ ጥራጥሬና አትክልቶችን ጨምሮ በተጠቀሰው ዓመት ወደ ኬንያ የላከችው ግን 26 ሚሊዮን ዶላር ብቻ እንደኾነ ዘገባው አመልክቷል።

በኹለቱ አገሮች ድንበር ዘለል ንግድ ውስጥ ሊወገዱ ከሚገባቸው ማነቆዎች መካከል፣ ታሪፍ ነክ ያልሆኑ ማነቆዎችና ባንዱ አገር ጥራቱ የተረጋገጠለት ምርት በሌላኛው አገር በድጋሚ ጥራቱ እንዲረጋገጥ የማድረግ አሠራር እንደሚገኙበት ዘገባው ጠቅሷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ዐቃቤ ሕግ የሽብር ተከሳሾችን ክስ እንዲያሻሽል በተሰጠው ብይን ላይ አቤቱታ አቀረበ!

ዐቃቤ ሕግ፣ በሽብር ወንጀል የተከሰሱትን የእነዶር. ወንድወሰን አሰፋን ክስ አሻሽሎ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤት ዛሬ ኀሙስ በሰጠው ብይን ላይ፣ “ምስክሮቼን ያጋልጥብኛል” በማለት አቤቱታ አቅርቧል፤ የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው ክሱ ካልተሸሻለ እንዲቋረጥ ጠይቀዋል፡፡በተከሳሶቹ የወንጀል ድርጊት “ተገድለዋል” የተባሉ ሰዎች፣ በክሱ ላይ በስም እንዲጠቀሱ ብይን ሰጥቶ የነበረው ፍርድ ቤቱ፣ በዛሬው ክርክር ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን፣ ከተከሳሾች ጠበቆች አንዱ ሰሎሞን ገዛኸኝ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

በእነዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ፣ ሰኔ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. በዐቃቤ ሕግ የሽብር ክስ የተመሠረተባቸው ተከሳሾች፣ ዛሬ ሚያዝያ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ችሎት ቀርበዋል፡፡የዛሬው ችሎት የተቀጠረው፣ ዐቃቤ ሕግ በፍርድ ቤት በታዘዘው መሠረት ክሱን አሻሽሎ ማቅረቡን ለመመልከት ነበር፡፡

የዐቃቤ ሕግ ክስ፣ ተከሳሾቹ በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈጸሙት የሽብር ወንጀል፣ የ217 ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ ብዙዎች መጎዳታቸውንና ከፍተኛ ንብረትም መውደሙን ሲያስረዳ፣ በተከሳሽ ጠበቆች ጥያቄ መሠረት፣ ሟቾቹ በስም ተጠቅሰው፣ ሌሎች ጉዳቶችም በዝርዝር ተገልጸው ክሱ እንዲሻሻል፣ ፍርድ ቤቱ ባለፈው ኅዳር 12 ቀን በይኖ ነበር፡፡

ኾኖም፣ ዐቃቤ ሕግ፣ ክሱ እንዲሻሻል የተሰጠው ብይን እንዲሻር በደብዳቤ አቤቱታ አቅርቧል፡፡ ለዚኽም በምክንያትነት ያቀረበው፣ እንደ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ የሟቾቹን ስም መጥቀስ “ምስክሮቹን ለጉዳት የሚዳርግ ነው፤” የሚል እንደኾነ፣ ከተከሳሽ ጠበቆች አንዱ ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ሰሎሞን ገዛኸኝ አስረድተዋል፡፡ጠበቆች በበኩላቸው፣ ዐቃቤ ሕግ የፍርድ ቤቱን ብያኔ አክብሮ ክሱን የማያሻሽል ከኾነ ክሱ እንዲነሣ መጠየቃቸውንም ተናግረዋል፡፡የግራ ቀኙን ክርክር ያደመጠው ችሎቱ፣ በጉዳዩ ላይ ትእዛዝ ለመስጠት ለግንቦት 12 ቀን መቅጠሩን፣ ጠበቃ ሰሎሞን ገዛኸኝ አመልክተዋል፡፡

በክስ መዝገቡ ላይ ከተጠቀሱ 51 የሽብር ወንጀል ተከሳሾች መካከል አራት የመገናኛ ብዙኀን ባለሞያዎችን ጨምሮ 23ቱ በቁጥጥር ሥር ውለው ጉዳያቸውን በመከታተል ላይ የነበሩ ናቸው፡፡ ከመካከላቸው አንዱ ለሕክምና እንደወጡ ማምለጣቸውን፣ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ተወካዮች ከዚኽ ቀደም ለፍርድ ቤት ማሳወቃቸውን ጠበቆቹ ገልጸዋል፡፡ጉዳያቸው በሌሉበት እየታየ የሚገኙ ተከሳሾችን፣ በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ውጤቱ ለቀጣዩ ችሎት እንዲቀርብም ፍርድ ቤቱ አዟል፡፡
(VoA)

@sheger_press
@sheger_press
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት 244 የስነምግባር ጥሰት የፈጸሙ ሰራተኞቹን መቅጣቱን እና በህግ ተጠያቂ ማደረጉን ገለፀ

👉 አገልግሎቱ አመራሮቹ እና ለሙስና ተጋላጭ የሆኑ ሰራተኞቹ ሀብታቸዉን እንዲያስመዘግቡ አድርጓል።

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎትከዚህ በፊት ይነሳበት የነበረዉን የሙስና ተግባር ለመከላከል የተለያዩ ለዉጦችን እየከወንኩኝ እገኛለሁ ማለቱን ብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል። ለዚህም በማሳያነት በባለፉት ዘጠኝ ወራት ያከወናቸዉን ተግባራት በዛሬዉ እለት ይፋ አድርጓል።

በተመሳሳይ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የስነምግባር ጥሰት የፈጸሙ 244 ሰራተኞቹን ከስራ እንዲታገዱ ፣ ከሀላፊነት እንዲነሱ እና በህግ እንዲጠየቁ ማድረጉንም አሳዉቋል።

አገልግሎቱ ይህንን ያለዉ በዛሬዉ እለት የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሕግ እና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የ2016 በጀት አመት የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸምን በገመገመበት ወቅት ነዉ።

የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የኢ - ፓስፖርት (E-passport) ለመቀየር የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እየከወነ መሆኑንም ብስራት ከሪፖርቱ ሰምቷል። በተመሳሳይ በዉጪ የሚታተመዉን ፓስፖርት በሀገር ዉስጥ ለማድረግ የዲዛይን ስራዎች ተጠናቅቀዋል የተባለም ሲሆን ህትመቱን ከሚሰራዉ ተቋም ጋር ዉል መታሰሩን እና ህትመቱን በአጭር ጊዜ ዉስጥ ለመጀመር ማቀዱንም ይፋ አድርጓል።

ተቋሙ የጸጥታ ችግር ባለባቸዉ ኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ስራዎቹን ለመከወን እንዳልቻለ የገለጸ ሲሆን በአንጻሩ በትግራይ ክልክ ተቋርጦ የነበረዉን አገልግሎት ለማስጀመር የዳሰሳ ጥናት መስራቱን አስታዉቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የኤርትራ ጦር ከዛላንበሳና አጎራባች ወረዳዎች ሰዎችን አግቶ እየወሰደ ነው ተባለ

የዛላአንበሳ ከተማ ከንቲባ ብርሃነ በርሄ ለጣቢያችን እንደተናገሩት ከምስራቃዊ ዞን  ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች ታግተዉ ተወስደዋል ብለዋል፡፡

ከዛላ አንበሳ 26 ሰዎች ፣ ከጉለም ወረዳ  50  እንዲሁም ከኢሮብ 28 ሰው በኤርትራ ሰራዊት እንደተወሰደ  ገልፀው በዚህ ሳምንት ደግሞ ቁጥሩ መጨመሩን መናገራቸውን ዳጉ ጆርናል ከኢትዮ ኤፍኤም ዘገባ ተመልክቷል።

አሁን ላይ ዛላንበሳ ከተማን ጨምሮ  ምስራቃዊው ዞን ሙሉ በሙሉ በኤርትራ ጦር ቁጥጥር ስር እንደሆነ የሚናገሩት የከተማዋ ከንቲባ ማህብረሰቡም ብዙ በደል እና ጥቃት እየደረሰበት ነዉ ብለዋል፡፡

የኤርትራ ጦር የአካባቢዉን ነዋሪዎቹ በአልጀርስ ስምምነት መሰረት  ኤርትራዊ እንደሆኑ በመግለጽ  በኃይል  እንደተቆጣጠረም ተነግሯል፡፡ የፌድራል መንግስት ምንም አይነት ትኩረት አልሰጠንም የሚሉት አቶ ብርሀነ ዳግም ጦርነት አንፈልግም ግን ደግሞ ማንነታችንን እና ህልውናችንን ሊያስከብርልን ይገባል ብወዋል።

በከተማዋ የሚገኙ መሰረተ ልማቶች በጦሩ  ሙሉ በሙሉ እንደወደሙ ተነስቶ  በከተማው እንዲሁም በአካባቢው ያለው ነዋሪ ለከፋ ችግር እንደተጋለጠም ተናግረዋል፡፡

ከዚህም ጋር ተያይዞ ከ 30ሺ በላይ ነዋሪ ተፈናቅሎ በመቀሌ፤ በአዲግራት እንዲሁም በተለያዩ አከባቢዎች በመጠለያ ጣቢያ እንደሚገኝ  አቶ ብርሀነ ገልፀዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በወላይታ ዞን የመምህራን ደመወዝ ባለመከፈሉ ትምህርት መቋረጡ ተገለጸ!!

ላለፉት ሁለት ወራት ገደማ ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው የገለጹ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ ዞን መምህራን፣ ካለፈው መጋቢት ወር ጀምሮ ትምህርት መቋረጡን አስታወቁ፡፡

ለከፋ ኢኮኖሚያዊ፣ ሥነ ልቡናዊ እና ማኅበራዊ ቀውሶች መጋለጣቸውን የተናገሩት መምህራኑ፣ አብዛኞቹም ኑሯቸውን ለመምራትና ቤተሰቦቻቸውን ለመመገብ እንደተሳናቸው አመልክተዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ዐማኑኤል ጳውሎስ፣ በዞኑ ከሚገኙ ስድስት የከተማ አስተዳደሮች እና 17 ወረዳዎች ውስጥ፣ የአንድ ከተማ አስተዳደር እና የ20 ወረዳዎች መምህራን ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው ገልፀውልኛል።
ከ18 ሺህ በላይ የውጭ ዜጎችን ከሀገር ተባረዋል

የኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በሐሰተኛ የመኖሪያ ፍቃድ በአገር ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከ18 ሺህ በላይ የውጭ አገር ዜጎችን ከአገር ማባረሩን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት ባቀረበው ሪፖርት ገልጧል።

ከአገር ከተባረሩት መካከል፣ ለሌሎች የውጭ ዜጎች ሐሰተኛ የመኖሪያ ፍቃድ አዘጋጅተው በገንዘብ ሲሸጡ የነበሩ እንደሚገኙበት ተቋሙ ገልጧል።

በኢንቨስትመንት ፍቃድ ወደ አገሪቱ የገቡ የውጭ ዜጎች ለበርካታ ዓመታት በሕገወጥ ሥራዎች ላይ ተሳታፊ ኾነው እንደተገኙም ተቋሙ ጠቅሷል።(ዋዜማ)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መልካምነት ለእራስ ነው 🥰

በአጋጣሚ ከማያቁት ሰው በርከት ያለ ገንዘብ በባንክ አካውንቱ ቢላክሎ ምን ያደርጋሉ ??? 🤔

ነገሩ እንዲህ ነው በአሰሪ እና ሰራተኛ አገናኝ እንዲሁም በድለላ ስራ ቤተሰቡን የሚያስተዳደር የባቱ ከተማ ነዋሪ የሆነው አቶ ቱፋ ሰለሞን የተለመደውን ስራ ለመስራት የእለት እንጀራውን ለማግኝት በስራው ለይ እያለ ባጋጣሚ ወደ ባንክ አካውንቱ 2,000,000 ብር ይገባል።

የዚን ጊዜ ከየት የመጣ በረከት ነው ብሎ ብሩን አውጥቶ ለመጠቀም አይደልም ያሰበው ከየት እንደመጣ ለማውቅ ነው የቸኩለው በስህተትም ይሆናል ብሎ አስቦ ነበር።

ፈላጊው እስኪገኝ ድረስ ለ1 ወር ያክል ገንዘቡን ሳይነካ ባለቤቱ እስኪመጣ ሲጠባበቅ ነበር። በመጨረሻም ከ1 ወር ቁይታ በዋላ አብነት ግርማ የተባለች የአዲስ አበባ ነዋሪ በስህተት ወደ ቱፋ ሰለሞን አካውንት ማስገባቷ ከተረጋገጠ በዋላ አቶ ቱፋ ሰለሞን ገንዘቡን ለባለቤቷ በመመለስ ታማኝነታቸውን አሳይተዋል።

ለፍቶ አዳሪው አቶ ቱፋ ለታማኝነታቸው ምስጋና ይገባቸዋል 🙏🙏🙏

@ethio_mereja_news
የተመድ የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ፣ በመጋቢት ወር በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በቀዎት፣ ኢፍራታና ጊደም እና አንጾቂያ ወረዳዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች፣ 18 ሺህ ነዋሪዎች ከቀያቸው እንደተፈናቀሉና 290 መኖሪያ ቤቶች እንደተቃጠሉ አዲስ ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል።

በክልሉ ኦሮሞ ልዩ ዞን በግጭት የተጎዱ 36 ሺህ 450 በላይ ሰዎች አስቸኳይ ዕርዳታ እንደሚፈልጉም ቢሮው ገልጧል።

በክልሉ በቀጠለው ግጭት ሳቢያ፣ 4 ሺህ 178 ትምህርት ቤቶች እንደተዘጉም ቢሮው የጠቀሰ ሲኾን፣ በምሥራቅና ምዕራብ ጎጃም እንዲኹም በደቡብ ጎንደር ዞኖች ብቻ 89 በመቶዎቹ ትምህርት ቤቶች በግጭቱ ሳቢያ ዝግ ናቸው ብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ፣ በአገሪቱ የሚዘረጋቸውን የቴሌኮም ታዎሩች ብዛት በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት በሦስት እጥፍ ለማሳደግ ማቀዱን እንደገለጠ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ኩባንያው ባሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ 2 ሺህ 500 የቴሌኮም ታዎሮች ያሉት ሲኾን፣ 1 ሺህ 500ዎቹ ታዎሮች ከኢትዮ ቴሌኮም ኩባንያ የተከራያቸው ናቸው። ኾኖም መላ አገሪቱን ለመሸፈን 7 ሺህ ታዎሮች እንደሚያስፈልጉት የኩባንያው ሃላፊዎች እንደነገሩት ዘገባው ጠቅሷል።

ዘገባው፣ በአገሪቱ በርካታ አካባቢዎች የተከሰቱ የጸጥታ ችግሮች ግን በኩባንያው እቅዶች ላይ ትልቅ እንቅፋት ደቅነውብኛል ማለቱንም ዜና ምንጩ አመልክቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የትግራዩ ተቃዋሚ ፓርቲ ባይቶና፣ አፍሪካ ኅብረት እና አጋር አገራት፣ የትግራይን ግዛቶችና የትግራይን ነባራዊ ኹኔታ "በተሳሳተ አኳኋን" ገልጠውታል በማለት ወቅሷል።

የሰባት አጋር አገራት ኢምባሲዎች ከሳምንት በፊት እንዲኹም አፍሪካ ኅብረት ትናንት ባወጧቸው መግለጫዎች፣ የተወሰኑ የትግራይ ግዛቶችን "አወዛጋቢ" ብለው በመጥራት የፈጠሩትን "ስህተት ያርሙ" በማለት ጠይቋል።

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ በመግለጫቸው፣ ራያ አላማጣ፣ ዛታ እና ኦፍላ ወረዳዎችን ጨምሮ "በአወዛጋቢ አካባቢዎች ማኅበረሰቦች መካከል ሰሞኑን የተፈጠረው ውጥረት" እንዳሳሰባቸው ገልጠው ነበር።

አፍሪካ ኅብረት በሕገ-መንግስቱ የታወቁ የትግራይ ግዛቶችን "አወዛጋቢ" ብሎ መግለጡ፣ "ለፌደራሉ መንግሥት ያለውን ወገንተኝነት ያሳያል" በማለትም ፓርቲው ከሷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ፈተናው በኦላይን ይሰጣል ተብሏል

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦን ላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ተገልጿል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ምክክር መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል ።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በሁሉም ክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን የሚወስዱ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን ይወስዳሉም ብለዋል።

የሀገር አቀፍ ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር (ዶ/ር) እሸቱ ከበደ በበኩላቸው ፈተናውን በኦንላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል።

ተማሪዎች የሙከራ ፈተና የሚለቀቅላቸው ሲሆን ደጋግመው እንዲሞክሩና እንዲለማመዱ ይደረጋልም ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ለዚህም እንዲረዳ የአሰልጣኞች ስልጠና በመሥጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሠጣቸውም ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት እንደሚጀምርም በመድረኩ ተገልጿል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አማጺው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ መከላከያ ሠራዊት ምዕራብ ኦሮሚያን "ከበባ ውስጥ በማስገባት ሕዝቡን በጅምላ እየቀጣ ነው" በማለት ከሷል።

ኦሮሚያ ክልል የአገሪቱ አብዛኛው ሃብት ምንጭ ናት ያለው አማጺው ቡድን፣ ኾኖም የፌደራሉ መንግሥት "ኦሮሚያን ለረጅም ጊዜ ሙሉ ከበባ ውስጥ ማስገባት አይችልም፤ አይፈልግምም" ብሏል።

መንግሥት ከምዕራብ ሸዋ ዞን ጀምሮ በመላው ምዕራብ ኦሮሚያ ባኹኑ ወቅት እየወሰደ ያለው ርምጃ፣ "የአማጺው ቡድን ተዋጊዎች ቤተሰቦችና ቡድኑን ይደግፋሉ ተብለው የሚጠረጠሩ ሰዎች በመንግሥት የሕክምና ጣቢያዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ፍርድ ቤቶችና የቀብር ቦታዎች አገልግሎት እንዳያገኙ ማድረግ" እንደኾነ ቡድኑ ገልጧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/06/16 19:53:57
Back to Top
HTML Embed Code: