Telegram Web Link
የኢትዮ መረጃ ቤተሰቦች የተለያዩ የኦንላይ ስራዎች መስራት ከፈለጋቹ በሸገር አድሚኖች የተከፈተው ቻናል አሁንኑ ይቀላቀሉ 👇👇

በርግጠኝነት ታተርፉበታለቹ👇👇

http://www.tg-me.com/sheger_crypto
እንቁላል ጣይ ዶሮ የሰረቀው ታዳጊ የ1 አመት ከ8 ወር እስር ተቀጣ

በምእራብ ጉጂ ዞን ሀምባላ ወረዳ ቢምቱ ከተማ  02 ቀበሌ ውስጥ አንድ ዶሮ ሲሰርቅ የተያዘው ግለሰብ ላይ የእስራት ቅጣት መወሰኑን የሀምባላ ፖሊስ አስታወቀ።

የሀምባላ ወረዳ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል እንደገለፀው ተከሳሽ ሮቤል ሽብሩ የተባለው የ18 አመት ታዳጊ ወጣት ሰኔ 3 ቀን 2016አ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ የአንድ ግለሰብን እንቁላል የምትጥል ዶሮ ሰርቆ በመውሰድ ሲሮጥ እጅ ከፍንጅ መያዙ ተገልጿል።

ግለሰቡ በፖሊስ የምርመራ መዝገብ በአስቸኳይ የተጣራበት ሲሆን የምርመራዉም መዝገብ ለአቃቢ ህግ ተልኳል።

አቃቢ ህግም ወድያውኑ ክስ መስርቶበት በአስቸኳይ ችሎት ውሳኔ እንዲሰጠው በመጠየቁ እንቁላል ጣይ ዶሮ የሰረቀው ታዳጊ ሮቤል ሽብሩ ሙሉ ለሙሉ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ1 አመት ከ8 ወር እስራት እንዲቀጣ  የሀምባላ ወረዳ ፍርድ ቤት ውሳኔ ማስተላለፉን የሀምባላ ወረዳ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን የላከው መረጃ ያመላክታል።

#ዳጉ_ጆርናል

@ethio_mereja_news
በአማራ ክልል ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸው ተገለፀ!

የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት እንዳስታወቀው በክልሉ ባለፉት 11 ወራት ብቻ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወባ በሽታ ተጠቅተዋል።የክልሉ ጤና ቢሮና የከተማ አስተዳደሩ ጤና መምሪያ ኃላፊዎችም በበኩላቸው በክልሉ የወባ በሽታ በከፋ ሁኔታ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ገልፀዋል።የክልሉ ጤና ተቋማት ኃላፊዎች እንደገለፁት በክልሉ ያለው ግጭት ሳቢያ በተደጋጋሚ የመንገዶች መዘጋጋት የወባ ሥራ ቁጥጥርን አዳክሞታል።የመድኃኒት ስርጭትን ደግሞ አስተጓጉሎታል።ይህም ችግሩ እንዲባባስ አድርጓል።ህብረተሰቡ ወባን ለመከላከል ያለው ዝቅተናኛ ግንዛቤና ቸልተኝነት ደግሞ ሌላው ምክንያት ነው ሲሉ ሀላፊዎቹ ገልፀዋል።

የክልሉ መዲና የባህርዳር ነዋሪዎች በበኩላቸው በከተማው የወባ ስርጭት መበራከቱን ይገልጻሉ።የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ የሆኑት መለአከ ብርሐን ፍሰሐ ጥላሁን «አሁን በባሕር ዳር ወባ ከቤቴ ጀምሮ አለ፣ ህፃናት እየታመሙ ነው፣ ባሕር ዳር ውስጥ ግንቦት ወር የወባ መነሻ ነው ተብሎ ስለሚታሰብ፣ ለህክምና ሰዎች ወደ ጤና ተቋም ሲሄዱ ወባ እየተገኘባቸው ነው፡፡» ብለዋል፡፡የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪ ኃላፊ ወ/ሮ ዓለም አሰፋ ሰሞኑን ለዶቼ ቬሌ እንደተናገሩት ህብረተሰቡ ያለው የትንኝ መከላከያ የአልጋ አጎበር አጠቃቀም ዝቅተኛ በመሆኑና ሌሎች የመከላከል ስራዎችን ቸል በማለቱ በሽታው በብዛት በከተማዋ መታየቱን አስረድተዋል፡፡ባለፈው ሳምንት 7ሺህ ሰዎች የወባ ምርመራ አድርገው በ2ሺህ 460 ሰዎች ላይ በሽታው ተገኝቷል ብለዋል፡፡

[DW]
Hamster‼️

Hamster ለምሰሩ የዕለቱ 5 million coin ያልወሰዳቹ

በዚ Link ተለቆል መመልከት ትችላላቹ👇👇

https://www.tg-me.com/sheger_crypto/231
ፓስፖርት እናስወጣላችኋለን እያሉ ግለሰቦችን ሲያጭበረብሩ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋሉ‼️

ፓስፖርት እናስወጣላችኋለን እያሉ ግለሰቦችን ሲያጭበረብሩ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋሉ። 
 
ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር ሊውሉ የቻሉት በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ልዩ ቦታ ኢሚግሬሽን አካባቢ ለግለሰቦች ፓስፖርት እናስወጣለን በማለት ሲያጭበረብሩ እንደነበረ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገልጿል። 
 
ነዋሪነታቸው አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የሆኑት አስራት አጎን አይዛ እና ስንታየሁ ለይኩን ኃይሌ የተባሉ ግለሰቦች የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ኢንተለጀንስ ዋና መምሪያ አባላት ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ሠራተኞች በደረሰው ጥቆማ መሠረት ባደረጉት ክትትል ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እየጣራባቸው ይገኛል። 
 
ኅብረተሰቡ ከመሰል ወንጀሎች ራሱን በመጠበቅ አጠራጣሪ ጉዳዮችን ሲመለከት በቅርቡ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት በጀመረው በዜጎች መረጃ መቀበያ (EFPAPP) ወይም በነፃ የስልክ መስመር 991 በመጠቀም ለፖሊስ መረጃ እንዲሰጥ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

@ethio_mereja_news
ኢትዮጵያ ምንም አይነት “የአቪዬሽን ደህንነት ስጋት የሌለባት ሀገር” ናት ሲል የዓለም አቀፉ አቪዬሽን ድርጅት ኦዲተሮች ማረጋገጫ ሰጥቷል ተባለ

የዓለም አቀፉ አቪዬሽን ድርጅት ኦዲተሮች ባለፉት 10 ቀናት የአቪዬሽን ኢንዱስትሪውን ደህንነት መፈተሻቸውን የገለጹት በብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት የሲቪል አቪዬሽን ደህንነት መምሪያ ዳይሬክተር አስራት ቀጀላ ፍተሻው የተከናወነው ከግንቦት 26 እስከ ሰኔ 6 መሆኑን አስታውቀዋል።

በቦሌ ኤርፖርት እና በሌሎች አየር ማረፊያዎች በተደረገው ኦዲት ኢትዮጵያ ምንም አይነት የአቪዬሽን ደህንነት ስጋት የሌለባት መሆኑን የድርጅቱ ገምጋሚዎች መገልፃቸውን ዳይሬክተሩ የፍተሻውን መጠናቀቅ አስመልክተው በሰጡት መግለጫ አመላክተዋል።

እንዲስተካከሉ አስተያየት የተሰጠባቸውን የሕግ ማዕቀፍ ማሻሻያ እና ሌሎች ጉዳዮች በፍጥነት እንደሚስተካከሉም ጠቁመዋል።

ከሲቪል አቪዬሽን ደህንነት አንፃር በድርጅቱ መስፈርት መሰረት በቁጥር የተሟላ የኦዲቱ ሪፖርት በቅርቡ አዘጋጅተው እንደሚያስረክቡ ተጠቅሷል።

ይህ የኦዲት ውጤት በዘርፉ ለመሰማራት ለሚፈልጉ አካላት ወደ ስራ እንዲገቡ፣ ለሀገሪቱ የቱሪዝም እና የአቪዬሽን ዘርፍ እድገት አስተዋፅኦው የላቀ ነው ተብሏል። ለዚህ ውጤት መገኘት በዘርፉ በቅንጅት የሚሰሩት የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የብሔራዊ መረጃ ደኅንነት አገልግሎት፣ ፌደራል ፖሊስ ፣ ጉሙሩክን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ሚና ትልቅ እንደነበርም በመግለጫው ተጠቅሷል።

@ethio_mereja_news
ተፈቶል‼️

ለረጅም ወራቶች በእስር ላይ የነበረው ገጣማ በላይ በቀለ ወያ ተፈቷል።

እንኳን ለቤትህ አበቃህ ወንድማችን 🙏

@sheger_press
#Notcoin

❤️Telegram wallet verify ማድረግ ያልቻላችሁ ወይም tonkeeper ላይ notcoin ያላችሁ መሸጥ የምትፈልጉ

😄 በዚህ አናግሩን 👉 @Birukepromo

❤️ልብ ይበሉ

በእነዚህ user name መጥታችሁ ስትገበያዩ ገንዘባችሁ 100% ይሰጣችኋል (ሀላፊነቱን @sheger_press ይወስዳል)

ክፍያው እንደ ስምምነታችሁ ይፈፀማል

በእነዚህ ሰዎች ለመገበያየት ስትሄዱ ያላችሁ ስክሪንሽት አድርጋችሁ ማሳየት ግድ ነው

ton space ቤታ ከሆነ ኮይናችሁ ደግሞ 0.2 ክፍያ ስለሚጠይቅ ቶን ኮይን ከሌላችሁ ቅድሚያ ከፍላችሁ መውሰድ

notcoinu ልካችሁ ስትጨርሱ አድሚኑ በተስማማቹበት ዋጋ ብራችሁ መልሶ ያስገባል!!


🚫ለማጭበርበር የምትመጡ ካላችሁ ወዲያው Block ሰለምናረጋችሁ አትልፉ እንዳመጡ!!

ሲቀጥል የማትሸጡ አትምጡ ጊዜያችን አታቃጥሉ

ለተለያዩ ONLINE ስራዎች ለመስራት ይህን ቻናል ይቀላቀሉ👇👇
https://www.tg-me.com/sheger_crypto
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ህውሀት‼️

ህውሃት ዛሬ ባወጣው ግለጫ እኔ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድን ይቅርታ አልጠየኩም።በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጨው ስህተት ነው ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ህውሃት ሁለት ክንፍ አለው አንዱ የተሳሳተ መረጃን የሚሰጥና የሚያሳስት ቡድን ሌላኛው የተሰጠውን የተሳሳተ መረጃ የሚያርም እንደሆነ እየተሰማ ነው።

ከዚህ የሚያተርፈው ሁሌ ስሙን ከሚዲያው ላለማጥፋት የሚያደርገው አንዱ ስልት መሆኑ ብዙዎች እየገለፁት ነው።

ለአብነትም ከሰሞኑ ከፓርቲው መከፋፈል ጋር በተገናኘ የሰጠው መግለጫ ተጠቃሽ ሆኖ ቀርቧል።

ሌሎችም በርከት ያሉ ጉዳዮች እየተነሱ ነው።(wasu)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አዲስ ታሪፍ‼️

የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን፣ አዲስ የተዘጋጀ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ ረቂቅ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ለሚንስትሮች ምክር ቤት እንደሚያቀርብ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሠራጨው መረጃ አስታውቋል።

ባለሥልጣኑ፣ የሃይል አቅራቢ ተቋማት ባቀረቡት የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ ጥናት ላይ የቅድመ ግምገማ ሂደቱን አጠናቆ፣ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችና ባለድርሻ አካላት ግብዓቶችን እያሰባሰበ መኾኑን ገልጧል።

የታሪፍ ማሻሻያውን አዘጋጅተው ያቀረቡት፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ናቸው።(wazema)

@ethio_mereja_news
Forwarded from Sheger Press️️
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዋን ራይድን ያልተገደበ ዕለታዊ፣ ሳምንታዊ ወይም ወርሃዊ ጥቅሎችን በቴሌ ብር በመግዛት ወጪ ቆጣቢ በሆኑ አማራጮች ተጠቃሚ ይሁኑ።

መተግበሪያውን ያውርዱ | ይመዝገቡ| ቤተሰብ ይሁኑ!

𝐃𝐫𝐢𝐯𝐞𝐫 𝐀𝐩𝐩https://shorturl.at/bdyFO

𝐏𝐚𝐬𝐬𝐞𝐧𝐠𝐞𝐫 𝐀𝐩𝐩https://shorturl.at/lJLZ6

የማኅበራዊ ትስስር ድኅረ ገጾቻችንን ይቀላቀሉ

Facebook: https://www.facebook.com/rideinone

Instagram: https://www.instagram.com/rideinone

Telegram Group: http://www.tg-me.com/rideinone9744

TikTok: https://www.tiktok.com/@rideinone

የናንተ የሆነውን ዋን ራይድን ምርጫዎ ያደርጉ በአንድ ይጓዙ! ዋን ራይድ
ባንክ ተዘርፏል ተባለ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሬማ ቅርንጫፍ በታጠቁ ሃይሎች ከ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ዝርፊያ እንደተፈጸመበት ተገለጸ

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን ሚዳ ወረሞ ወረዳ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሬማ ቅርንጫፍ ትናንት ሰኔ 06 ቀን 2016 ዓ.ም በአካባቢዉ ይንቀሳቀሳሉ በተባሉ የታጠቁ ሀይሎች ዝርፊያ መፈፀሙን የሚዳ ወረሞ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሠይድ ኢብራሂም ገልፀዋል ፡፡

የታጠቁት ሃይሎች ከዚህ በፊት ለአጎራባች መርሃቤቴ ወረዳ የተላከዉን ሰዉ ሰራሽ የአፈር ማዳበሪያ አስገድደዉ በሚል ክስ የቀረበባቸው ሲሆን አሁን ደግሞ ከኢትዮጽያ ንግድ ባንክ ሬማ ቅርንጫፍ ከ 2 ሚሊዮን ብር በላይ መዘረፉን ተናግረዋል ሲል የዘገበው የወረዳው ኮሙኒኬሽን ነው፡፡

በሌላ በኩል ታጣቂዎቹ ብሩን የወሰዱት አካውንታችን ለምን ታገደ በሚል ቁጣ እንደሆነም ከአካባቢ ምንጮች ተሰምቷል።(wasumohammed)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት ሱዳን ውስጥ ከነበሩ ቀሪ የጉሙዝ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉሕዴን) ታጣቂዎች እና ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ነጻነት ንቅናቄ (ቤሕነን) አመራሮች ጋራ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መግባባት ላይ እንደደረሰ የክልሉ ዜና አውታር ዘግቧል።

የክልሉ መንግሥት ካኹን ቀደም በአገር ውስጥና በውጭ ይንቀስቀሱ ከነበሩ ከቤንሻንጉል ሕዝብ ነጻነት ንቅናቄ እና ከጉሙዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ አመራሮች ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረሙ ይታወሳል።

ሱዳን ውስጥ ይኖሩ ነበር የተባሉትና ክልሉ መንግሥት ጋር ስምምነት የተፈራረሙት የጉሙዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ታጣቂዎች ብዛት ስንት እንደኾነ ዘገባው አላመለከተም።

@ethio_mereja_news
ተቃዋሚው ኦብነግ በተያዘው ወር አጋማሽ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በድጋሚ በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ለመሳተፍ የምርጫ ቅስቀሳ እያደረገ መኾኑን አስታውቋል።

ኾኖም ደጋፊዎቹ መታወቂያ ለማግኘት ወይም ለማደስ አኹንም ችግሮች እየገጠሟቸው እንደኾነ ፓርቲው ገልጧል።

ተቃዋሚ ፓርቲዎችና የግል ዕጩዎች ለሚያነሷቸው ቅሬታዎች ምርጫ ቦርድ ምላሽ እየሰጠ መኾኑን የገለጠው ፓርቲው፣ ቦርዱ በጅግጅጋ ፍትሃዊ ምርጫ ለማካሄድ ቁርጠኛ መኾኑን አሳይቷል በማለት መስክሯል።

በጅግጅጋ በድጋሚ ምርጫ የሚካሄደው፣ ቦርዱ በ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ የተገኘውን የምርጫ ውጤት በመሰረዙ ነው። ኦብነግ፣ በክልሉ የተካሄደው የድምጽ ሰጪዎች ምዝገባ ከፍተኛ ችግር ታይቶበታል በማለት ከምርጫው ራሱን ማግለሉ አይዘነጋም።

@sheger_press
በፋኖ ታጣቂዎች ውስጥ የመሪነት ቦታ አላቸው የሚባሉት እስክንድር ነጋ፣ የፋኖ ታጣቂዎች ከመንግሥት ጋር ለመደራደር ከውሳኔ አልተደረሰም በማለት ለቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ፕሮግራም ተናግረዋል።

በአማራ ክልል በተለያዩ ዞኖች የሚንቀሳቀሱ የፋኖ ቡድኖችን ለማዋሃድ እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደኾነና የውህደቱ ሂደት ሲጠናቀቅ ከመንግሥት ጋር ድርድር የማድረግና ያለማድረግ ጉዳይ ውሳኔ እንደሚያገኝ እስክንድር ገልጸዋል።

@ethio_mereja_news
ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው አማጺ ቡድን በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ግራር ጃርሶ ወረዳ ግንቦት 25 ፈጸመው በተባለ "ማንነት ተኮር" ጥቃት ከ20 በላይ ንጹሃን እንደተገደሉ ምንጮች ለዋዜማ ተናግረዋል።

በክልሉ የተለያዩ ዞኖች ሰሞኑን በመንግሥት ወታደሮችና አማጺው ቡድን መካከል ተከታታይ ውጊያዎች እየተካሄዱ ስለመኾኑ ዋዜማ ከምንጮቿ ተረድታለች።

በቄለም ወለጋ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደ መኾኑን፣ ነዋሪዎችም ከቤት ለመውጣት እንደተቸገሩና ውጊያው በተለይ የመከላከያ ሠራዊት ካምፕ በሚገኝበት ሰዮ ወረዳ እየተካሄደ እንደኾነ ተናግረዋል።

በምስራቅ ወለጋ ዞን ቢሎ ቦሼ፣ ሌቃ ዱለቻ እና ኑኑ ቁምባስን ወረዳዎችም በተለይ የመከላከያ ሠራዊት ካምፖች በሚገኙባቸው ጅማቴ እና አዳሚን በተባሉ አካባቢዎች ከባድ ውጊያዎች እየተካሄዱ እንደኾነ ተሰምቷል።

በምዕራብ ሸዋ ዞን ግንደበረትና ጀልዱ ወረዳዎች እንዲኹም በሰሜን ሸዋ፣ በጉጂ፣ በምሥራቅ ሸዋና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞኖች የተለያዩ ወረዳዎች ግጭት ሲካሄድ መሰንበቱ ታውቋል።

@ethio_mereja_news
News‼️

ላለፉት በርካታ አመታት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ከመንግስታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተበድረው ያልከፈሉት 900 ቢሊየን የሚሆን ብርን የገንዘብ ሚኒስቴር እንዲወርስ መወሰኑን ሸገር ከዋዜማ ሁነኛ ምንጮቿ ሰምታለች።(wazema)

@sheger_press
#NEWSALERT

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 37 ቢሊየን ብር የካፒታል ማሳደጊያ እንዲሰጠው ተወሰነ‼️

የካፒታል ማሳደጊያ ገንዘቡ ከአለም ባንክ ይገኛል ተብሏል

ዋዜማ- መንግስታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሁን ካለው 43 ቢሊየን ብር ካፒታል በተጨማሪ ከ37.1 ቢሊየን ብር በላይ(650 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር) የካፒታል ማሳደጊያ ገንዘብ እንዲሰጠው ተወሰነ።

ውሳኔውም የንግድ ባንኩን አጠቃላይ ካፒታል ከ80 ቢሊየን ብር በላይ የሚያደርገው ሲሆን፣ይህም ከሌሎች ከግል ባንኮች አንፃር ያለውን የበላይነት እጅግ ያገዝፈዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ካፒታል እንዲያድግ የተወሰነው ትላንት ሰኔ 7 ቀን 2016 ዓ/ም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባደረገው ስብሰባ ሲሆን ፣ በዚህም ምክር ቤቱ ፣ በባንኩ የሪፎርም እና የካፒታል ማሳደጊያ ዕቅድ ላይ መምከሩን ገልጾ ፣ የባንኩን ካፒታል ለማሳደግ በሙሉ ድምጽ መወሰኑም ታውቋል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በመግለጫው ለባንኩ የሚሰጠውን የካፒታል ማሳደጊያ ገንዘብን ያልገለጸ ሲሆን ፣ ዋዜማ የካፒታል ገንዘቡ ከሚተላለፍበት ከገንዘብ ሚኒስቴር ምንጮቿ ባገኘችው መረጃ ለመንግስታዊው ባንክ የሚሰጠው የካፒታል ማሳደጊያ ገንዘብ ከ37 ቢሊየን ብር በላይ መሆኑን አረጋግጣለች።

የዋዜማ ምንጮች አክለው እንደገለጹትም የመንግስታዊውን ባንክ ካፒታል በዚህ ደረጃ ለማሳደግ የተፈለገበት አንዱ ምክንያት ኢትዮጵያ የባንኩን ዘርፍ ለውጭ ገበያ እየከፈተች በመሆኑ መንግስታዊውን ባንክ ጠንካራና ተወዳዳሪ አድርጎ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖም በመገኘቱ ነው።

የካፒታል ማሳደጊያው ገንዘብም ከአለም ባንክ ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮቻችን ነግረውናል።

የኢትዮጵያ መንግስት ከአለም ባንክ እና ከአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም(አይ ኤም ኤፍ) ጋር እያደረገ ባለው ድርድር የሀገሪቱን የፋይናንስ ተቋማት ማጠናከር የሚለው አንዱ አጀንዳ በመሆኑ ፣ ለንግድ ባንክ የሚገኘው የካፒታል ማሳደጊያ ገንዘብም ኢትዮጵያ ከአለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ጋር የምትፈራረማቸውስምምነት አካል መሆኑንም ተገንዝበናል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ከሰሞኑ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ2017 ዓ/ ም በጀትን በንባብ ባቀረቡበት ወቅት : አለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ከኢትዮጵያ የሚፈልጓቸውን ብር ማዳከም አይነት ፖሊሲዎችን ሀገሪቱ በቅርቡ አትተገብርም ማለታቸው ከእነ አለም ባንክ ጋር እየተደረገ ያለውን ድርድር ያከተመለት ቢያስመስለውም ፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከአለም ባንክ በሚገኝ ድጋፍ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የካፒታል ማሳደጊያ ገንዘብ ላይ ከውሳኔ መድረሱ የሀገሪቱን እና የገንዘብ ተቋማቱን የድርድር አዝማሚያ አመላካች ሆኗል።

በከፍተኛ ደረጃ ካፒታሉ እንዲያድግ የተወሰነለት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኢትዮጵያ ውስጥ በሰጠው ብድርም በሰበሰበው ቁጠባም በእያንዳንዳቸው አንድ ትሪሊየን ብር ያለፈ ብቸኛ የኢትዮጵያ ባንክ ነው። [ዋዜማ]

@sheger_press
@sheger_press
ለእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

@ethio_mereja_news
2024/06/16 08:29:43
Back to Top
HTML Embed Code: