Telegram Web Link
የትምህርት ዘርፉን አገራዊ ሪፎርም መሰረት በማድረግ ስራዎችን መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የለውጥና የሪፎርም አጀንዳዎች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።

(ግንቦት 11/2017 ዓ.ም) የስራ አመራር መሪ ስራ አስፈጻሚ ይበልጣል አያሌው (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት የአገር አቀፍ ሪፎርም አካል የሆነው የትምህርት ዘርፍ ሪፎርም በሙከራ ደረጃ ወደ ስራ ይገባል።

በሙከራ ደረጃ ወደ ስራ ለሚገባው የሪፎርም ትግበራ የመዋቅርና የአሰራር ስርዓት ማሻሻያ እየተደረገ እንደሆነም ዶክተር ይበልጣል አክለው ገልጸዋል።

የአሰራር ማሻሻያውን ተከትሎም አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች በአዲስ መልኩ ተሻሽለው እንዲዘጋጁ መደረጉንም ተናግረዋል።

የሙከራ ትግበራው በቅድሚያ በትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ከዚያም ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እስከ ትምህርት ቤቶች ደረጃ በደረጃ በተግባራዊ እንደሚደረግ አመልክተዋል።

በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የምርሞርና የማህበረሰብ ጉድኝት ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ሠራዊት ሀንዲሶ ዶ/ር) በበኩላቸው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚካሄዱ ሪፎርሞች ተቋማቱ ተልኳቸው በአግባቡ እንዲወጡ እንደሚያስችል ተናግረዋል።

የዩኒቨርስቲዎች ዓላማ ማህበረሰብን መለወጥ መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር ሠራዊት ተቋማቱ ያሉባቸውን የአሰራር ተግዳሮቶች በመለየት በአፋጣኝ መፍታት እንደሚጠበቅባቸውም ጠቁመዋል።

የተቋማዊ ለውጥ ስራ አስፈጻሚ አቶ ከበደ ግዛው በበኩላቸው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚካሄዱ የሪፎርም አጀንዳዎች ተቋማዊ ሊሆኑ እንደሚገባ አስረድተዋል።

የውይይት መድረኩ ዓላማ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የለውጥ ስራዎች የመልካም አስዳደርና የሪፎርም አጀንዳዎች የአሰራር ስርዓት ማስፈጸሚያ ስትራቴጂ ለመገምገም መሆኑንም አቶ ከበደ ጨምረው ገልጸዋል።
በኢትዮጵያና በአውሮፓ ህብረት ሀገራት የትምህርትና ስልጠና ተቋማት ጋር ያለውን የትብብር ግንኙነት ማጠናከር እንደሚገባ ተመላከተ፤

የአውሮፓ ህብረት የኢራስመስ (ERASMUS +) ትብብር የተዘጋጀ ጉባዔ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
------------------------------------------------

(ግንቦት 12/2017 ዓ.ም) የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በጉባኤው መክፈቻ ላይ እንደገለጹት በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ህብረት መካከል ያለውን የትምህርትና ስልጠና አጋርነት ጥራትና ተገቢነቱን በማሳደግ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል።

በትምህርትና ስልጠና ተቋማት መካከል ግንኙነት በማጠናከር ውጤታማ የልማት ትብብሮችን መተግበር እንደሚገባም ወ/ሮ ሙፈሪሃት አስገንዝበዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚና የብሔራዊ ኢራስመስ (ERASMUS +) ተወካይ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) በበኩላቸው በኢራስመስ የትምህርትና ስልጠና ድጋፍ እኤአ ከ2010 እስከ አሁን ድረስ ከ600 በላይ ኢትዮጵያውያን ነጻ የትምህርት እድል ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ዛሬ የተጀመረው የአውሮፓ ህብረት የኢራስመስ የትምህርትና ስልጠና ድጋፍና ትብብር ጉባኤ ዓላማ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ አገራት ያለውን የትምህርትና ስልጠና ግንኙነት ተጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ለመምከር መሆኑንም ዶ/ር ኤባ ጨምረው ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1BzpS7vnp8/
የኢትዮጵያ የልኡካን ቡድን በለንደን እየተካሄደ ባለው አለም አቀፍ የትምህርት ፎረም 2025 ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

(ግንቦት 14/2017 ዓ.ም) በትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የተመራ ልኡካን ቡድን በለንደን እየተካሄደ ባለው አለም አቀፍ የትምህርት ፎረም 2025 ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ እየተካሄደ ካለው የትምህርት ፎረሙ ጎን ለጎን ከእንግሊዝ የአለምአቀፍ ልማት ሚኒስትር ባሮነስ ቻፕማን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

በዚህም ክቡር ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው የትምህርት ዘርፍ ሪፎርም የገልጹላቸው ሲሆን በራስ አቅም በ “ትምህርት ለትውልድ’’ ህዝባዊ ንቅናቄ የትምህርት ቤቶች መሰረተ ልማት ማሻሻን በተመለከተ ስለተገኘው ውጤት አብራርተዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ከሥርዓተ ትምህርት፣ ከመምህራንና የትምህርት ቤት ዳይሬክተሮች ስልጠና እና ከእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ጋር በተያያዘ የተጀመሩ ሥራዎችን ጠቅሰው፣

እነዚህ በትምህርት ዘርፉ የተጀመሩ ሪፎርሞች በፍጥነት እንዲሳኩ የልማት አጋሮችና በተለይም የእንግሊዝ መንግስት ድጋፉን እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

የእንግሊዝ የአለምአቀፍ ልማት ሚኒስትሯ ባሮነስ ቻፕማን በበኩላቸው በቅርቡ በኢትዮጵያ ያደርጉትን ጉብኝት በማስታወስ በትምህርት ዘርፉ እየተደረገ ያለውን ለውጥ አድንቀዋል፣

የተጀመረውን የትምህርት ዘርፍ ሪፎርም ውጤታማ ለማድረግ ምንም እንኳን በእንግሊዝ መንግስት የተደረገው የበጀት ቅነሳ (budget cuts) ቢኖርም በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፍ የሚካሄደውን ሪፎርም ለመደገፍ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፤ https://www.facebook.com/share/p/1ArRKjyKhx/
የአፍሪካውያ ችግር በአፍሪካውያን መፍታት እንደሚገባ ተጠቆመ፤
በኢትዮጵያ ለሦስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የ2025 የኢራስመስ ጉባኤ ተጠናቋል።
----------------------------------------
(ግንቦት 15/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በጉባዔው ማጠቃለያ ላይ ባስተላለፉት መልእክት የአፍሪካ አገራትን ትብብር በማጠናከር የአፍሪካውያውያን ችግሮችን በአፍሪካውያን መፍታት ይገባል ብለዋል።

አፍሪካውያን ችግሮቻቸውን ለመፍታት በትብብርና በቅንጅት አጽንኦት ሰጥተው መስራት እንደሚጠበቅባቸውም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አስታውቀዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከመንግስት የሚመደበውን በጀት ከመጠቀም ባሻገር የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ተልዕኳቸውን ማሳካት እንዳለባቸውና በኢራስመስ ፕሮግራምንና የመሳሰሉ ፕሮጀክቶችን በመጠቀም ለሀገር ልማትና ብልጽግና መስራት እንደሚጠበቅባቸውም ክቡር አቶ ኮራ ጨምረው አስገንዝበዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/16Sy4Y3AHv/
የከፍተኛ ትምህርት ምርምርና ስልጠና ተቋማትና ኢንዱስትሪው ተጣምረው በጋራ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተጠቆመ።
---------------------------------------------
(ግንቦት 19/2017 ዓ.ም) ለአምስት የዘርፍ ኢንዱስትሪዎች የትስስር ፎረም አመራሮች እና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስተባባሪዎች ስልጠና ተስጥቷል።

የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በስልጠናው መክፈቻ ላይ እንደገለጹት የትምህርትና ስልጠና ተቋማትና ኢንዱስትሪው ተጣምረው በጋራ መሥራት አለባቸው።

የትምህርትና ስልጠና ተቋማትና የኢንዱስትሪ ትስስር ሀብትን በጋራ በማመንጨትና በመጠቀም የተሻለ አቅም ለመፍጠር እንደሚያስችልም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል።

ዘርፉ ተወዳዳሪ ዜጋና ሀገርን ለማበልጸግ ቁልፍ ሚና እንዳለው የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው የዘርፉ ተዋንያኖች የኢንዱስትሪውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ የመማር ማስተማር እና ምርምር ስራ በማከናወን ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ጉዳዮች ተ/መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሠራዊት ሀንዲሶ በበኩላቸው የስልጠናው ዓላማ የከፍተኛ ትምህርት ፣ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ፣ ምርምር ተቋማትና ኢንዱስትሪው በመቀናጀትና በመተባበር ሀገር የጣለባቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ ለማስቻል መሆኑን ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፤ https://www.facebook.com/share/p/16h5dTspAv/
ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል እድል አግኝቶ የሚማርበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እየተሰራ እንደሚገኝ የትምህርት ሚኒስትሩ ገለፁ።
---------------------------------------------

(ግንቦት 22/2017 ዓ.ም) በጋምቤላ ክልል በሰዎች ለሰዎች ግብረሰናይ ድርጅት ለሚገነባው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል።

በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በየአካባቢው መሠረተ ልማት የተሟላላቸው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ብቃት ያላቸውና ተወዳዳሪ ተማሪዎችን ለማፍራት እየተሠራ መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም በጋምቤላ ክልል የሚስተዋለውን ከፍተኛ የትምህርት ጥራት ችግርና የመማሪያ ክፍል ጥበት ለመቅረፍ የዚህ ትምህርት ቤት ግንባታ መጀመር አስተዋጸኦ የጎላ ይሆናል ብለዋል።

አክለውም ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል እድል አግኝቶ የሚማርበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር ግዴታ መሆኑን ጠቅሰው በዚህ ረገድ ሰፊ ሥራ እየተሰራ እንደሚገኝም አብራርተዋል።

በዚህም በመላ ሀገሪቱ 31 ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 15ቱ በትምህርት ሚኒስቴር እንዲሁም 16ቱ ደግሞ በሰዎች ለሰዎች ግብረሰናይ ድርጅት አማካኝነት እንደሚገነቡ አንስተው በተለይም በቂ የመሰረተ ልማት ባልተሟላላቸው ክልሎች ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ብለዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/19mtoujNie/
2025/07/10 13:46:46
Back to Top
HTML Embed Code: