በአገር አቀፍ ደረጃ 77 ሺህ ለሚሆኑ ተማሪዎች የሪሚዲያል ፈተና እየተሰጠ ነው፤
-----------------------------------
(ግንቦት 25/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር በአገር አቀፍ ደረጃ የሪሚዲያል ፕሮግራም ለተከታተሉ 77 ሺ ለሚሆኑ ተማሪዎች ፈተና እየተሰጠ መሆኑን አስታወቀ።
በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ማሻሻያ ዴስክ ኃላፊ ኢዶሳ ተርፋሳ (ዶ/ር) እንደገለጹት ፈተናው እየተሰጠ ያለው በ41 ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ በተዘጋጁ 64 የፈተና ማዕከላት ነው።
ፈተናውን ከግንቦት 25 አስከ ግንቦት 29 ለመስጠት መርሃ ግብር ተይዞ የነበረ ቢሆንም በኢድ አል አድሃ (ዓረፋ) በዓል ምክንያት አርብ ግንቦት 29 የሚሰጠው ፈተና ወደ ቅዳሜ ግንቦት 30 /2017 ዓ.ም መዛወሩን ዶ/ር ኢዶሳ ተናግረዋል።
ከፈተናው አስቀድሞ ተማሪዎች የሬሚዲያል ትምህርት በተከታተሉባቸው ዩነቨርስቲዎች የሙከራ ሞዴል ፈተናዎች መውሰዳቸውን የገለጹት ሃላፊው የተሻለ ውጤት ለማምጣት እንደሚያስችላቸው ጠቁመዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/1AZxTe6GVn/

ኩረጃን የሚጠየፍ ትውልድ ለመፍጠር እስካሁን በተወሰዱ እርምጃዎች በሁሉም ዘንድ መተማመን መፍጠር መቻሉ ተገለጸ።
---------------------------//---------------------------
(ግንቦት 26/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ሥርዓቱ ያለውን መሰረታዊ ችግር ለመፍታት ከወሰዳቸው እርምጃዎች አንዱ የትምህርት ምዘናና የፈተና አስተዳደር ሥርዓቱን ማስተካከል እንደሆነ ይታወቃል።
በዚህ ሂደት እስካሁን የተሰሩ ሥራዎችን በማስመልከት ማብራሪያ የሰጡት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ትምህርት እውቀት ሲሆን ሰርተፊኬት ደግሞ ያንን እውቀት የምንለካበት ነው ብለዋል።
በስርቆት፣ በማጭበርበርና በኩረጃ የሚገኝ ነገር እውቀት ሳይኖር ሰርተፊኬት ማግኘት ነው ያሉት ሚኒስትሩ ይህ ደግሞ እውቀት አለመኖሩ ብቻ ሳይሆን ሰርተፊኬቱ እውቀት አለህ ስለሚለው ምንም ሳያቅ ሰርተፊኬት በእጁ ስላለው ብቻ እውቀት አለኝ ብሎ የሚያምን የህብረተሰብ ክፍል ይፈጠራል፤ ይህም ህብረተሰቡን በጣም እንደሚጎዳው አብራርተዋል።
በተለይም በትምህርት ዘርፉ ተንሰራፍቶ የነበረውን ማጭበርበር፣ ስርቆትና ኩረጃ ተማሪዎች ብቻ የሚያደርጉት ቢሆን ኖሮ የልጆቹ ችግር ነው ተብሎ ሊወሰድ ይችላል። ነገር ግን ይህን የሚያደርጉት ተማሪዎች፣ የትምህርት ቤት አስተዳደሮች፣ የክልል ባለ ስልጠናት እና ሌሎችም የኛ አካባቢ ልጆች እንዲያልፉ በሚል የሚያደርጉት በመሆኑ ከፍተኛ የሞራል ውድቀት ውስጥ የተገባበት እንደነበር አንስተዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፤
https://www.facebook.com/share/p/1AkHXHzEYy/

የከፍተኛ ትምህርት ቅድመ ምረቃ መርሃ ግብር ተማሪዎች መውጫ ፈተና ከሰኔ 2 እስከ 10 2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቁ፡፡
ተፈታኞች ለፈተና ሲመጡ ብሄራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) መያዝ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡
-------------------------------------------------------------------
(ግንቦት 27/2017 ዓ.ም) የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) እንደገለጹት 2017 የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 10 /2017 ዓ.ም. በ51 ዩኒቨርስቲዎች በተዘጋጁ 87 የፈተና ማዕከላት ይሰጣል፡፡
ፈተናውን በ238 የትምህርት መርሃ ግብሮች ለ190 ሺ 787 ቅድመ መደበኛ እጩ ተመራቂ ተማሪዎች በበይነ መረብ ለመስጠት አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁንም ዶክተር ኤባ ተናግረዋል፡፡
ለፈተናው 102 ሺ 360 ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ፤ 88 ሺ 422 ተማሪዎች ደግሞ ዳግም የሚፈተኑ መሆናቸውን መሪ ስራ አስፈጻሚው ገልጸው ተማሪዎች ወደ ፈተና ማዕከላት ሲመጡ አገር አቀፍ ፋይዳ /ብሄራዊ መታወቂያ መያዝ እንደሚጠበቅባቸውም ኃላፊው አስገንዝበዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/19CHegAwk1/

የትምህርት ጥራት ችግርን ከመሰረቱ ለመፍታት ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ልዩ ትኩርት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ።
ባለፉት ዓመታት በተሰራው ሥራ ከ17 ሺ በላይ አዲስ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተገንብተው ወደ መማር ማስተማር ሥራው መግባታቸውም ተገልጿል።
-----------------------------//------------------------
(ግንቦት 28/2017 ዓ.ም) በሀገራችን የሚስተዋለውን የትምህርት የጥራት ችግር ከመሰረቱ ለመፍታት ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ የሚኒስቴሩ የትምህርት ጥራትና ፕሮግራሞች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዮሐንስ ወጋሶ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
የትምህርት ጥራት ችግሮች በርካታ በመሆናቸው እነዚህን ችግሮች በአንድ ስትራቴጂ ብቻ መፍታት የሚቻል ባለመሆኑ በርካታ መፍትሄ እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚያስፈልግም አብራርተዋል።
በተለይም ትምህርትን በዘላቂነት ለመለወጥ ከተፈለገ ከመጀመሪያው መሰረቱ ላይ መስራት እንደሚገባ እምነት ተይዞ እንደ መንግስት በትምህርት ዘርፉ ለቅድመ ልጅነት ትምህርት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
በዚህም ትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ፖሊሲው ላይ የቅድመ አንደኛ ደርጃ ትምህርት ለ5 እና 6 ዓመት ህጻናት ነጻና የግዴታ እንዲሆን ማድረጉንና የቅድመ ልጅነት ዘመን ትምህርትና እንክብካቤ ፖሊሲ ማዕቀፍ በማዘጋጀት ወደ ሥራ መግባቱንም በመጥቀስ ለተፈጻሚነቱ ከሌሎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝም አብራርተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጣኑ፣ https://www.facebook.com/share/p/16GV2HcMvE/

በተለያዩ የትምህርት መስክ ሰልጥነው ወደ መምህርነት ሙያ መግባት ለሚፈልጉ አዲስ አማራጭ የአሠራር ሥርዓት ወደ ተግባር ሊገባ መሆኑ ተገለፀ።
አዲስ በተዘጋጀው አማራጭ የመምህራን ማሰልጠኛ ማዕቀፍ ላይ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
---------------------------------------
(ግንቦት 28/2017 ዓ.ም) በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስቴር በመምህርነት ሙያ የሚታየውን የሥልጠና እጥረት ለመቅረፍ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ሰልጥነው የሚገኙና ወደ መምህርነት ሙያ መግባት ለሚፈልጉ አዲስ የአሠራር ሥርዓት ወደ ተግባር ሊያሰገባ መሆኑን በሚኒስቴሩ የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ሙሉቀን ንጋቱ (ዶ/ር) ገልፀዋል።
ሀገራችን የመምህርነት ሙያ ማሰልጠን የረጅም ጊዜ ታሪክ ያለት ቢሆንም አማራጭ ወደ መምህርነት ለመግባት ለሚፈልጉት አዲስ መንገድ መክፈት ያስፈልጋል፤ ለዚህም ተጨማሪ ሥልጠና ወስደው መምህር መሆን የሚችሉበት የሥልጠና ማዕቀፍ ተዘጋጅቷል ብለዋል።
በተለይም በትምህርት ዘርፉ ከተደረገው የሥርዓተ ትምህርት ለውጥ ጋር አብሮ የሚሄድ ለደረጃው የሚመጥን የትምህርት ዝግጅት ያላቸው መምህራንን ለማፍራት የተለያዩ አማራጮች ተቀርፀው እየተሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
ሙ
በዚህም መምህር ሆነው መሥራት ለሚፈልጉ ምሩቃን በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ገብተው ተጨማሪ የመምህርነት ሙያ፣ የሚያስተምሩት ትምህርት አይነት ይዘት ፣ የትምህርት ቴክኖሎጂ እና የጋራ ኮርሶችን ስልጠና እንዲወስዱ ይደረጋልም ተብሏል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፣ https://www.facebook.com/share/p/1P8qR1ax51/

የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና መሰጠት ጀመረ፤
------------------------------------
(ሰኔ 02/2017 ዓ.ም) በዩኒቨርስቲዎች የሚሰጠው የቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተና ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሰኔ 10/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) እንደገለጹት ፈተናው የሚሰጠው በ51 ዩኒቨርስቲዎች በተዘጋጁ 87 የፈተና ማዕከላት ነው።
በዚህ ዓመት በሚሰጠው የመውጫ ፈተና 190,787 ቅድመ መደበኛ እጩ ተመራቂ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ እና ከዚህም ውስጥ 102 ሺ 360 ተማሪዎች ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ፈተናው በ238 የትምህርት መርሃ ግብሮች በሁሉም የፈተና መስጫ ማዕከላት በበይነ መረብ እንደሚሰጥም ዶ/ር ኤባ ጨምረው ገልጸዋል።

በበይነ መረብ የመፈተን አቅሙን በእጥፍ ማሳደግ መቻሉን የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ አስታወቀ፡፡
-----------------------------------------------------
(ሰኔ 2/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ደረጃ እንግዳ (ዶ/ር) በዩኒቨርስቲው እየተሰጠ የሚገኘውን የመውጫ ፈተና በማስመልከት በሰጡት ማብራሪያ ተቋሙ ተማሪዎችን በበይነ መረብ የመፈተን አቅሙን በእጥፍ ማሳደጉን ገልጸዋል።
ዩኒቨርስቲው ከዚህ በፊት በአንድ ጊዜ በበይነ መረብ ለ636 ተማሪዎች ብቻ የመፈተን አቅም የነበረው1336 ማድረሱን ዶ/ር ደረጀ ጠቁመዋል።
ዩኒቨርስቲው እስከ ሰኔ 10 /2017 ዓ.ም ለዕጩ ቅድመ መደበኛ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና እየሰጠ እንደሚገኝም ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል።
በበይነ መረብ የሚሰጠው መውጫ ፈተና ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ወጪ ቆጣቢና ስርቆትንም ለመከላከል ምቹ በመሆኑ ዩኒቨርስቲው በበይነ መረብ የመፈተን አቅሙን የበለጠ በማሳደግ በመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብርም የወረቀት ፈተናን በማስቀረት በበይነ መረብ ለመስጠት እቅድ እንዳለው ጠቅሰዋል።
ዩኒቨርስቲው ለዚህ ዓመት የመውጫ ፈተና በቂ ዝግጅት ማድረጉን የጠቆሙት ፐሬዚዳንቱ በመጀመሪያው ዓመት የመውጫ ፈተና 87% ፣ ባለፈው ዓመት ደግሞ ት 96.7 % ተማሪዎችን በማሳለፍ ለስራ ብቁ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡ ሙሉ መረጃውል ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፣
https://www.facebook.com/share/p/15xdxHHW2T/