Telegram Web Link
ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሀገር-በቀል እውቀትን በመሰነድና በማበልጸግ ለማህበረሰብ ጥቅም ማዋል እንደሚጠበቅባቸው ተመላከተ፤ በሀገር-በቀል እውቀት ዙሪያ አውደጥናት ተካሂዷል።
--------------------------------------------------
(ሰኔ 18/2017 ዓ.ም) የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ጉዳዮች ተ/መሪ ስራ አስፈጻሚ ሠራዊት ሃንዲሶ(ዶ/ር) በአውደ ጥናቱ ላይ እንደገለጹት አገር-በቀል እውቀት ለተሻለ አገር ግንባታና ለማህበረሰብ እድገት እንዲውል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሀገር-በቀል እውቀትን በመለየት፣መሰነድ፣ በየዘርፉ ማደራጀት፣ መመርመር፣ ማወቅ፣ መረዳት እና ማበልጸግ እንደሚገባቸውም ኃላፊው ጨምረው ተናግረዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር አገር-በቀል እውቀትን በአደረጃጀት ፣ በአሰራርና በግብዓት በመደገፍ ዘርፉ ለማህበረሰብ ልማትና ለአገር እድገት ጥቅም ላይ እንዲውል እየሰራ መሆኑን መሪ ስራ አስፈጻሚው አመልክተዋል።

የማህበረሰብ ጉድኝት እና አገር በቀል እውቀት ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ ሰላም አለሙ በበኩላቸው ሀገር-በቀል ዕውቀት፣ ለአከባቢ ጥበቃና ለዘላቂ ልማት ግቦች መሳካት ያለው አስተዋፅዖ እየጎላ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫም ማግኘት ትችላላችሁ፤
https://www.facebook.com/share/p/1DDcgZ1Bzw/
አገር አቀፍ የቅድመ ልጅነት ዕድገትና ትምህርት ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ።
------------------------------------------------

(ሰኔ 17/2017 ዓ.ም) በንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ባለፉት ሁለት አመታት በመንግስትና በማህበረሰቡ በተሰሩ ስራዎች የቅድመ አንደኛ ትምህርትን በማስፋፋትና ተደራሽ በማድረግ ረገድ ስኬቶች እየተመዘገቡ መሆኑ ተገልጿል።

"ልጆቻችን ብሩህ ነገን እንዲፈጥሩ መሠረቱን ዛሬ እንጣል " በሚል በተከናወነው መርሃ ግብር ላይ የትምህርት ሚኒስቴርና የሌሎች ባለድርሻ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ቁልፍ መልዕክት አስተላልፈዋል።


የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት ቁልፍ መልዕክት የቅድመ ልጅነት እድገትና ትምህርት ላይ የቅድሚያ ቅድሚያ ትኩረት በመስጠት ሊሠራበት የሚገባው ጉዳይ መሆኑን የገለጹ ሲሆን አሁን ላይ ከሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶችና የልማት አጋሮች ጋር በተፈጠረው ቅንጅታዊ አሰራር አበረታች ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆኑን ጠቁመዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በበኩላቸው ባስተላለፉት ቁልፍ መልዕክት የትምህርት ጥራትን በማጐልበት የሀገርን ብልጽልግና በማረጋገጥና ዜጎች ከሚመዘገበው ልማት ተጠቃሚ ለማድረግ ትምህርት ቁልፍ ሚና ያለው መሆኑን በመግለጽ የቅድመ ልጅነት እድገትና ትምህርት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/1Fn8WFGMfh
ኦስትሪያ እና ኢትዮጵያ በከፍተኛ ትምህርቱ ዘርፍ በትብብር ለመሥራት የሚያስችላቸውን ውይይት አካሄዱ።
-------------------------------------------

(ሰኔ 18/2017 ዓ.ም) የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ በኦስትሪያ ምክትል የፋይናንስ ሚኒስትር ‘H.E. Andreas REICHHARDT’ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በዚሁ ወቅት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የትምህርት ጥራትና ብቃትን ለማረጋገጥ እየተተገበሩ ያሉ ሪፎርሞችን ለልዑካን ቡድኑ አብራርተውላቸዋል።

በተለይም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በተልዕኮና ትኩረት መስክ በመለየት በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን አንስተው በዘርፉ የበለጠ ውጤታማ ለመሆን በትብብር የሚሰሩ ተግባራት መኖራቸውንም አብራርተዋል።

የኦስትሪያ ምክትል የፋይናን ሚኒስትር H.E. Andreas REICHHARDT በበኩላቸው ኦስትሪያና ኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፍ የቆየ ትብብር እንደነበራቸው አንስተው ይህንን ትብብር የበለጠ አጠናክረው መቀጠል እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/16e9wjFp2b/
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቁልፍ የሪፎርም ስራዎች አተገባበርና አፈጻጸም ላይ ያተኮረ ጉባኤ ተካሄደ።

ሰኔ 20/2017 ዓ.ም) "አካዳሚያዊ ውይይት ለአካዳሚክ ልህቀት" በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው ጉባኤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዘዳንቶችና የአካዳሚክ ፕሮግራም ሀላፊዎች በቁልፍ የሪፎርም ተግባራት አፈጻጸምና አሁን ላይ ያሉበትን ደረጃ በተመለከተ ልምዳቸውን አጋርተዋል።

በትኩረትና ተልኮ መስክ ልየታ (differentiation) ፤ በሥርዓተ ትምህርት ክለሳ( Curriculum revision)፤በሠራተኞችና ተማሪዎች የሙያ እድገት (Staff and students career development)፤ በቁልፍ የአፈጻጸም አመላካች መነሻና ኢላማ ልየታ ፤ KPI baseline and target identification),፣ የአፈጻጸም ኮንትራት ውል (Performance contracting implementation ) እንዲሁም በብሄራዊ ፈተናዎች አስተዳደርና አፈጻጸም ላይ የተሻለ ተሞክሮ ያላቸው ተቋማት ልምድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በቀረቡት ተሞክሮዎች ላይ ሀሳባቸውን ያካፈሉት በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዬች መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ኤባ ሜጄና አንዳንድ ተቋማት የሄዱበትን እርቀት አበረታተዋል።

ይሁን እንጂ በተወሠኑ ተቋማት ያለው ወጥነትና ቁርጠኝነት በሚፈለገው ልክ ባለመሆኑ ተቋማቱንም ይሁን የተቋማቱን ስራ ሀላፊዎች ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፣ https://web.facebook.com/share/p/16pXWpbSTh/
ሚኒስቴሩ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምዕራብ ኦሞ ዞን ጀሙ ከተማ የሚያስገነባው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ተጀመረ።
---------------------------------------------------
(ሰኔ 22/2017 ዓ.ም) የትምህርት ቤቱን ግንባታ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታው ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት እንዲሁም የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተጀምሯል።

የትምህርት ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ይህ ትምህርት ቤት በአርብቶ አደር አካባቢ የሚገነባ መሆኑን በመጥቀስ እያንዳዱ የኢትዮጵያ ልጅ እኩል የትምህር እድል እንዲያገኝ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።

ሁሉም ዜጎች አኩል እድል አግኝተው የሚማሩበት እና የበቁ፣ ተወዳዳሪ የሆኑ ልጆችን ለማፍራት በሁሉም ቦታ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ይጠበቃልም ብለዋል።

በምክትል ርዕሰ መስተደድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማው ዘውዴ በበኩላቸው የዚህ ትምህርት ቤት ግንባታ ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርትን በፍትሃዊነት ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ የሚያደርገውን ጥረት ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፣
https://www.facebook.com/share/p/16pG3QJgKT/
የትምህርት ሚኒስትሩ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናን በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው አስጀመሩ።
--------------------------------------

(ሰኔ 23/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፣ የሚኒስቴሩ አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት እንዲሁም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ ከሾጌ የ2017 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተናን በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው አስጀምረዋል።

በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት ጠንክሮ ያጠና ተማሪ የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚችል በማንሳት ተማሪዎች ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲወስዱ አበረታተዋል።

የመጀመሪያ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና በዛሬው እለት በሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች መሰጠት ተጀምሯል።

ዘንድሮ በወረቀትና በበየነ መረብ ከ608 ሺ በላይ ተማሪዎች ፈተናቸውን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሃምሌ 08/2017ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል
2025/07/13 20:21:45
Back to Top
HTML Embed Code: