Telegram Web Link
Coming soon...
የምስራች

አል ፋሩቅ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን የቀደሙ ስራዎቹና ቀዳሚው የዩ ቲዩብ ገፁ እንዳሉ ሆነው ስራውን የበለጠ በማሳደግና ዘርፉን በማብዛት በተለያዩ ዘርፎች የተለያዩ ፕሮግራሞችን የሚያገኙባቸውን ቻናሎች ሲያስተዋውቅ በታላቅ ደስታ ነው።
በዚህም በኢቅራእ ቲዩብ የተለያዩ ኢትዮጵያውያን ቃሪኦችን በልዩና መንፈስ በሚያድስ አቀራር የሚሰሯቸውን ቂርአቶች በተለያዩ ሪዋያዎች እንዲሁም ቁርአንን የተመለከቱ ርዕሰ ጉዳዮችን ያቀርባል። ይህም በህዝቡና በቁርዐን መካከል ያለውን ቅርበት ከማጥበቅና ኢትዮጵያውያን ቃሪኦችን ከማስተዋወቅ አንፃር የራሱን ድርሻ ይወስዳል።

     በአል ፋሩቅ ፊልምስ ደግሞ በፊት የሰራቸውና ነብዩላህ ዩሱፍንና የበኒ ሃሺም ጨረቃን የመሰሉ የተረጎማቸው ፊልሞች እንዳሉ ሆነው በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የተሰሩ ዘመነኛና በጥራታቸው ተስተካካይ የሌላቸው ታሪካዊ ኢስላማዊ ፊልሞችን በመተርጎም ወደናንተ ያደርሳል።

    በ  አልመዕሪፋ ቻናላችን ደግሞ የተለያዩ የሐዲስና ዳዕዋ ትርጉሞችን ጨምሮ ፈለገ ሐበሻን ,መርሃበን ሾውንና መሰል አዝናኝና አስተማሪ የሆኑ ፕሮግራሞችን ያቀርባል። ስለሆነም ሁላችሁ የፕሮግራሞቹን መጀመር ሰብስክራይብ እያደረጋችሁ እንድትጠብቁ በክብር እንጋብዛለን::
ዉድና የተከበራቹ የ አልፋሩቅ መልቲ ሚዲያ ተከታታዮች እንደሚታወቀዉ አልፋሩቅ መልቲሚዲያ ላለፉት 13 አመታት የተለያዩ ኢስላማዊ የኪነጥበብ ስራዎቹን በብዙ ዘርፍ ለናንተ በማቅረብ ይታወቃል ከብዙዎቹ መሀል የነብዩላህ የዩሱፍን(ዐ.ሰ)ታሪክ በአማርኛ ትርጉም በልዩ ሁኔታ በተከታታይ ወደናንተ ማድረሱ ይታወሳል ...አሁን ደግሞ በሰፊ መንገዶች ስለ እስልምናችን ለመዝከር የነብዩላህ ዩሱፍን (ዐ.ሰ) ታሪክን በነሺዳ መልክ በ ተወዳጁ ሙንሺድ አብዱሰላም አበራ ወደናንተ ይዞላቹ መቷል 
ቅዳሜ ምሽት ይጠብቁን
ተለቀቀ💥ተለቀቀ💥ተለቀቀ
👇👇👇👇
https://youtu.be/lrxwZZnSK4E?si=L1CF9t0yX-fEIXwS
2025/07/14 03:04:41
Back to Top
HTML Embed Code: