Telegram Web Link
#ramadan06
ረመዳንን ለመፆም ማሟላት ያሉብን 3 ሸርጦች

#ramadan #nesheed #menzuma #amharicneshida #ethiomuslim
#ramdan07
በረመዳን ውስጥ መቀነስ ያሉብን 3 ነገሮች

#menzuma #ethiomuslim #muslim #nesheed #amharicqoute
ተለቀቀ 💥ተለቀቀ 💥ተለቀቀ
👇👇👇👇👇
https://youtu.be/kT714egT-_o?si=BhswibOHPyvtArXN
የመድህ ጥግ?

ፉአድ ሸምሱ ስለ መንዙማ ስታስብ ልብህ ላይ ውል ከሚሉ ስሞች መካከል አንዱ ነው። አብዛኛውን የመድህ ስራዎቹን በ "ናፍቆት" ዙሪያ አርጎ በመስራት ታቀዋለህ። አሁንም እንደዛው በ ናፍቆት መድህ "ሠላሜ" ሊልህ መቷል።

" ሲወዱም በሙሀመድ፣ ሲናፍቁም በሙሀመድ
  ሙሀመድ ነው ሙሀመድ፣ ቢድኑም ቢታመሙ
"

ስለስራው ተዓምራዊነት ልንገርህ... ግጥሙን ታላቁና አንጋፋው ኡስታዝ ሰዒድ ከትበዉታል። ዜማው በተወዳጃችን ማዲህ ሙአዝ ሀቢብ የተቀመረ ሲሆን ተጨማሪ ዜማ ከኸይራቶች አለው። ቅንብሩም በኑር ዑመር እና በሀመር ቅንጅት የተሰናዳ ነው። 

" እሩህ የሌለዉን ግንዱን ሲያስለቅሰዉ
  እኛ ሩሁን ይዘን ወዴት እንድረሰዉ
"

ሌላኛው የዚህ ስራ ጠንካራ ጎን ግጥሙ ነው። ግጥሙ ከዚህ በፊት ተሰምቶህ ማያቅ አይነት የሙሀባ ስሜት ያሰማሀል። ቀስ በቀስ ውስጥህ የተዳፈነው ሙሀባ ሲያጉረመርም ይታወቅሀል። ከምንም በላይ የምቶዳት እናትህን ፍቅር ስታስብ ለአሽረፈል ኸልቅ ካለህ ፍቅር አንፃር  ምንም እንዳልሆነ ታስባለህ። ብሎም "ፋሩቅ ማነው? ሲዲቅ ማነው? የ ሙሀመድ አንደኛ አፍቃሪ እኔ ነኝ!" ያስብልሃል።

" ለኔም ኑልኝ እንጂ፣ ማየቱ ይድረሰኝ
  እንደዛች ጨረቃ፣ ናፍቆትሁ ሳይገምሰኝ "

ሙስሊም ነህ? ይህን ስራ ስማው!
ሙሀባ በርትቶብሀል? ይህን ስራ ስማው!
ናፍቆት ምን እንደሆነ አታውቅም? ይህን ስራ ስማው!
ስለ ረሱል መስማት ይስደሳሀል? ይህን ስራ ስማው!
መንዙማ ትወዳለህ? ይህን ስራ ስማው!
መንዙማ አትወድም? ይህን ስራ ስማው!
የግጥም ጥልቀት ላሳይህ? ይህን ስራ ስማው!
የድምፅ ስርቅርቅና ያስፈልግሃል? ይህን ስራ ስማው!


ኸሚስ ምሽት በ አልፋሩቅ መልቲሚድያ ፕሮዳክሽን ይለቀቃል ስማውና ትክክለኛ ሀሳብህን ኮመንት አርግልኝ። የ መድህ ጥግ መሆኑ አለመሆኑንም አንተው ወስን።
#ramadan10
3 ዩቲዩብ ላይ የሚገኙ አስገራሚና አስተማሪ ኢስላማዊ ፊልሞች።

#menzuma #ethiomuslim #nesheed #islamicquotes #islamhabesha
ይህ መንዙማ ለታላቁና ዒልምና መድህን ከሊቁ ሸህ ጫሌ ተግተውና ሸርበው ለአያሌ ዘመናት ተግተው በአማርኛ ቋንቋ በርካታ ድንቃ ድንቅ ዘመን ተሻጋሪ መንዙማዎችን ላበረከቱት፣ በዓደደ ማ ጀረል ቀለም ልባችንን ላቀለሙት፣ በዓደደማ ኸጠሁል ቀለም ነፍሳችንን ለኸጠፉት፣  በዓሩሰ ቁበቲል ኸድራ ሩሐችንን ለዳሩት፣ በአፍዶሉ ሰለዋቲላህ ዛታችንን ላኩነሰነሱት እንዲሁም በደማቅ ስራዎቻቸው የዓጀሙ ጌታ በሚል ማእረግ ለሚታወቁት የድምፃቸውን ለዛ ቀመስ ቃና ትተውልን ላለፉት ሊቁ ሸህ ሰዒድ አርባ ይሁንልኝ። እንዲሁም መንዙማን ማስተማርያና መታገያ፣ መብተክተኪያና መሻለኪያ፣ መናገሻና መታኮሻ፣ መታገሻና መላወሻ፣ ብሶት ማውጫና ፍቅር መግለጫ፣ መገዣና መጓዣ፣ መናዘዣና መዋዣ ላደረጉት ደጋግ የሐበሻ ሊቀ መዳሂያን ጥልቅ ፍቀርና ክብር ያለኝ መሆኑን ማሳያ ይሁንልኝ።
#ramadan13
ነቢያችን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ያደርጓቸው የነበሩ አምስት ዱዐዎች።

#ramadan #amharicqoute #ethiomuslim #menzuma #quotes
2025/07/06 08:19:22
Back to Top
HTML Embed Code: