Telegram Web Link
#ዓሹራእ

قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : " صِيَامُ يَوْمِ عَرَفَةَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ وَالسَّنَةَ الَّتِي بَعْدَهُ وَصِيَامُ يَوْمِ عَاشُورَاءَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ " رواه مسلم

የአሏህ መልእክተኛ ( ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) "የዐረፋ ቀን ጾም ያለፈውን አመትና የቀጣዩን አመት ወንጀል እንደሚያብስ ከአሏህ እጠብቃለሁ። የዓሹራ ፆም ደግሞ ያለፈውን አመት ወንጀል እንደሚያብስ ከአሏህ እጠብቃለሁ" ብለዋል። (ሙስሊም)
*

   ከዓሹራእ ቀን አንድ ቀን አስቀድሞ (9ኛውን ቀን) ወይም በመቀጠል የሚገኘውን (11ኛውን ቀን) መጾም የተወደደ ተግባር ነው ። ይህም የሆነው 10ኛው ቀን ብቻ ለይቶ መጾሙ ከአይሁዶች ጋር ሊያመሳስለን ስለሚችል ነው ። ነብዩም (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሙስሊም ውስጥ በሰፈረው ሐዲሳቸው   " ለሚቀጥለው ዓመት ከደረስኩ 9ኛውን ቀን እጾመዋለሁ " በማለት ተናግረዋል ፡፡
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኢና ሊላሂ ወዒና ኢለይሂ ራጂዑን

ሸይኽ ሰይድ ሙሐመድ ሚቅባስ ወደ አኼራ ሄዱ

የታዋቂው የእስልምና ሊቅ ሙጃሂድ ሸይኽ ሰዒድ ሙሐመድ ቡዴላ (የአብሬት ሸህ) ልጅ የነበሩት ሸይኽ ሰይድ ሙሐመድ ሚቅባስ ኑር ወደ አኼራ ሄደዋል::

ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸው ፣ለተማሪዎቻቸው እና ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ አላህ መፅናናቱን ይወፍቅ

ለሸይኽ ሰይድ ሙሐመድ ሚቅባስም መልካም ስራቸውን አላህ እንዲቀበላቸው፣ ምህረቱንም እንዲለግሳቸው፣ በጀነተል ፊርዶስም ማረፊያቸውን እንዲያደርግላቸው አላህን እንማፀነዋለን
መረጃ || ሼር በማድረግ ያዳርሱ |ሸይኽ ሰይድ ሙሐመድ ሚቅባስ ወደማይቀረዉ አኸራ ቤታቸዉ መሻገራቸዉ የሚታወስ ነዉ ።

በመሆኑም ለመላዉ ሙስሊም ማህበረሰብ የሸይኽ ሰይድ መሀመድ ሚቅባስ የቀብር ስነስርአት በጉራጌ ዞን ቸሀ ወረዳ አብሬት ቀበሌ የሚከናወን ለመሆኑ ለማወቅ ተችሏል ።

የቀብር ስነ ስርአቱ በአብሬት ከተከናወነ በሗላ አዲስ አበባ በሚገኘዉ ወለቴ አካባቢ በሚገኘዉ ቤታቸዉ መድረስ የምትችሉ ሲሆን ያልቻላችሁ ሩቅ የሆናችሁ አል ፋቲሀ በማለት አድርሱላቸዉ ።
( ምንጭ ሚዛን አዲስ)
2025/07/04 12:46:27
Back to Top
HTML Embed Code: