Telegram Web Link
አርኖ ሩሱቩዎሪ (Aarno Ruusuvuori 1925-1992 እኤአ)

💥የልማት ባንክ ህንጻ ነዳፊ

⚡️አርኖ ሩሱቩዎሪ ፊንላንዳዊ ህንጻ ነዳፊ፣ ፕሮፌሰር እና የፊንላንድ የኪነህንጻ ቤተመዘክር ስራአስኪያጅ ነበር።

⚡️ሩሱቩዎሪ በፊንላንድ እኤአ  በ1960ዎቹ ስመጥር ህንጻ ነዳፊ የነበረ ሲሆን ዘወትር በጥሬ ኪነህንጻ ዘይቤ (brutalism) የተጋለጡ የአርማታ ንድፎችን በዘመናዊው ፍልስፍና በመንደፍ   የሚታወቅ ነዳፊ ነበር።

⚡️አዲስ አበባ በተለምዶ ሱፐር ማርኬት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በ1960ዎቹ አጋማሽ ልማት ባንክ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሚገኙበትን በተጋለጠ አርማታ፣ በድግግሞሽ መርህ (modularization) እንዲሁም በሰፋፊ የአእማድ ርቀት የተገነባውን አስገራሚ ህንጻ ሩሱቩዎሪ ነበር የነደፈው።


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🛎 These 3 Packages will Start Tomorrow ( June 23) Morning @ 3:00 LT.

1. Advanced Structural Design
2. Bridge Design
3. Project Planning & Contract Administration


🔸Every Sunday Morning 3:00-8:00 LT.

📲
0911890392 / 0920933016
📌 Megenagna,Marathon Bldg, No. 614
https://www.tg-me.com/BeGetEngineering
ለመሬት ረገጥ ሀብት ግዢ አንዳንድ ጥንቃቄዎች
(Precautions in Real Estate Purchase)


መሬት ረገጥ ሀብትን (Real Estate) ስንገዛ ማሰብና መከወን ያሉብን ቴክኒካዊ ጉዳዮች በ22 ዝርዝሮች ተቀምጠዋል። 

በብዙ ሚሊዮን ብር ኢንቨስትመንት ስናደርግ እንደዚህ በጥልቀት ማየት የሚኖርብን ሲሆን፣ እነዚህ ዝርዝሮች ከአሻሻጮቹም ሆነ ከነጋዴዎቹ እውቀት በላይ በመሆናቸው ልፋት አከል ሥራዎች ሊሆኑ ይችላሉ።

በተጨማሪም አብዛኞቹ መሬት ረገጥ ሀብቶች የሚሸጡት በአካል በአገር ውስጥ ለሌሉ ደንበኞች ሲሆን፣ ባለሀብቶቹ ከማከራየት ባለፈ እንደ ኢንቨስትመንት ስለሚያዩዋቸው እንደተዘረዘሩት የሚጨነቅ ገዢም ሆነ ገንቢ እንዲሁም ተከራይ አይገጥሙንም። (ያከራየኝ ሰው ቤቱንም አይቶት አያቅም ሲባል አልሰማችሁም)

በቅርቡ ግን ሁላችንም በሰማይ ላይ ተንጠልጥለን መኖራችን ስለማይቀር ሁሉም ቴክኒካዊ ዝርዝሮች ሁላችንንም አንድ በአንድ እንደሚያገቡን እሙን ነው።

ስለዚህ እነዚህን ጥያቄዎች ለማወቅ አልሚዎችን ስንጠይቅ እንደደፋር ተቆጥረን  "ትገዛ እንደሆነ ግዛ አንተ ምን ስለሆንክ ነው የምትጠይቀው?" አይነት መልስ ልናገኝ እንደምንችል ይገመታል።

ወደ ዝርዝሩ፦

1. የአልሚ እና የገዢ ውሉን ህግ፣ ለህግ አዋቂ ከፍሎ ማስመርመር፤

2. የአልሚውን የበፊት የማልማት ዝናን መፈተሽ፤

3. ከተቻለ የተገነባን  ሀብት መግዛት፤

4. የተገነባም ሆነ ሊገነባ ያለ ከሆነ የቤቱን ፕላን በህንጻ ነዳፊ ማስመርመር፤ ( የእሳት ማጥፍያ የውሀ ስርአት ፣ የእሳት አደጋ ግዜ ማንቅያ፣ በእሳት አደጋ ጊዜ የአደጋ ማምለጫ ደረጃ እሳትና ጭስ የመቋቋም ስርዓት፣ የምግብ ማብሰያ እና መታጠብያ ቤት ሽታ ማስወገጃ፣ በቂ ተሽከርካሪ ማቆሚያ፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረግያ ወዘተርፈ መኖሩን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።)

5. የህንጻ አስተዳደር (facility management) ተገማች ወርሀዊ ወጪ ስንት እንደሆነ መጠየቅ፤

6. የመነሻ አፈር ምርመራን፣ የግንባታ ወቅት ተከታታይ የብረት እና አርማታ ምርመራ ምስክር ወረቀትን ጠይቆ ማየት፤

7. የኤሌክትሪክ ገመዶችና ስርዓቶችን በባለሙያ ማስመርመር፣ ተጠባባቂ ኃይል አመንጪ መኖሩን እና አቅሙን መጠየቅ፤ ቁመተ ረጅም ህንጻ ከሆነ ስለመብረቅ መከላከያ ስርአት መጠየቅ፤

8. የፍሳሽ መስመር ላይ በተጓዳኝ የሚዘረጋ የማስተንፈሻ ቱቦ እና ስርዓት መኖሩን ማረጋገጥ (የፍሳሽ ሽታ ማስወገጃ ዘዴ)

9. ህንጻው የከተማ የፍሳሽ መስመር አጠገቡ መኖሩን ማጣራት (አለበለዝያ በየወቅቱ የፍሳሽ ማስመጠጫ ተሽከርካሪ አዋኪነትን መቀበል)

10. በቂ የውሀ ማከማቻ እና አቅርቦት ስርአት እንዳለው በባለሙያ ማጣራት።

11. የፍሳሽ ማስወገጃ የቁመት ትቦዎች የሚያልፉበት ድምጽ በማያሳልፍ  በተከለለ ቀዳዳ እንደሚያልፍ ማረጋገጥ፤ (እነዚህ ቱቦዎች በድምጽ ስለሚረብሹ በየመታጠብያ ክፍሉ ተጋልጠው መገኘት የለባቸውም)

12. ለተሽከርካሪ መንገድ ቀረቤታ ካለው የድምጽ መከላከያ እርምጃዎች ምን እንደሆኑ ማጣራት፤

13. ለሳተላይት ርቀት ማያ (TV) ወይም ለበይነመረብ ፕሮቶኮል ርቀት ማያ (IPTV) የተዘጋጀ መስመር እንዳለው ማረጋገጥ (አለበለዝያ ሁሉም ሰው የሳተላይት ሰሃኑን ሰገነት ላይ ሰቅሎ የህንጻው መልክ እንደሚበላሽ መቀበል)

14. የተጣራ እና ያልተጣራ የሚሸጥ የቤት ስፋትን ማጣራት፣ (መተላለፍያ፣ ደረጃ፣ ተሽከርካሪ ማቆምያ ወዘተርፈ.... በነዚህ ስፋቶች መካተት አለመካተታቸውን ማጣራት)

15. የከፍታ ተሽከርካሪን (lift) የሰው የመጫን አቅምን፣  ብዛትን  እና ፍጥነትን ማጣራት።

16. የጥያራ  ማረፍያ (airport) በአካባቢው ካለ ጥያራው የሚያስነሳውን አዋኪ ድምጽ ዴሲቤል በተንቀሰቃሽ ስልክ መለካት፤

17. አካባቢው ከቤተ እምነቶች በድምጽ ማጉልያ የሚወጡ ድምጾች እንዳሉ ማረጋገጥ፤

18. የሚገዛው ቤት ዋና ዋና ክፍሎች አቅጣጫን ማወቅ (ለምሳሌ ወደ ሰሜን የሚከፈት ክፍል በፍጹም ፀሐይ የማያገኝ ከመሆኑ የተነሳ በአርማታ በተሰራ ህንጻ ውስጥ፣ በአዲስአበባ ከተማ አውድ እጅግ ቀዝቃዛና የሚደብት መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል)

19. የሚቻል ከሆነ አልሚው የመስኮቶች ክፍተት ላይ ትንኝ-ከላ ወንፊትን ከመስታወቶች አዳብሎ እንዲሰራ ማመላከት፤

20. አካባቢው በቋሚነት ከሚከሰት መጥፎ ሽታ ነፃ እንደሆነ ማረጋገጥ፤

21. ልማቱ ላይ እጅግ የበዛ አባወራ እንዲኖርበት የተነደፈ ከሆነ ወደልማቱ የሚወስዱ ተመጣጣኝ ስፋት ያላቸው መጋቢ መንገዶች እንዳሉ ማረጋገጥ፤

22. በመጨረሻም ባለብዙ ወለል ባለብዙ መኖርያ  የጋራ መኖርያ ቤት የሚሰራ ከሆነ እና እንደ ባህላችን በቀስታ ተቁላልተው የሚሰሩ ምግቦች የሚበስሉባቸው ማብሰያ ክፍሎች የሚኖሩ ከሆነ ማብሰያ ክፍሎች ውስጥ ያለውን የሽታ ማስወገጃ ስርአት በጥልቅ መመርመር ያስፈልጋል። አንደኛ ካንዱ ቤት ወደ አንዱ ቡና እና ወጥ ሽታ እንዳንቀባበል፣ ሁለተኛው ደግሞ ሽታዎች  ከምግብ ማብሰያ ወደ መኝታ እና እንግዳ መቀበያ እንዳይገቡ ሲባል ነው።

(ዳዊት በንቲ፣ መምህር እና ሕንፃ ነዳፊ)


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የአዲስ አበባ ከተማ ኮሪደር ልማት 33 ቢሊዮን ብር እንደወጣበት ተገለፀ

የአዲስ አበባ ከተማ ኮሪደር ልማት 33 ቢሊዮን ብር እንደወጣበት ተገለፀ። የኮሪደር ልማቱን ተግባራዊ ለማድረግ በተደረገ ጥናት መሰረት ከ40 ቢሊዮን ብር በላይ የበጀት እቅድ ተይዞለት የነበረ ሲሆን፤ ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ በመሰራቱ በ33 ቢሊዮን ብር እየተገባደደ እንደሆነ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግበዋል።

https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Useful Tip

ቴሌግራም Officially ወደ ገንዘብ መስሪያ አፕነት እየተለወጠ ነው በትላንትናው እለት ሰው በመጋበዝ ብቻ በርካታ ገንዘብ የመሰብሰብ እድልን ፈጥሯል ብዙዎችን ገና አልነቁበትም እመኑኝ ከየትኛውም ኤርድሮፕ በላይ በዚ ገንዘብ ታገኛላችሁ።
👇👇

https://www.tg-me.com/major/start?startapp=371415119
ዛሬ ሀምሌ 3 አዲስ አበባ ከተማ ያጋጠመ❗️

በአዲስ አበባ በግንባታ ላይ የነበረ ህንፃ በመኖሪያ ቤት ላይ ተደርምሶ በመኝታ ላይ የነበረ የአንድ ሰዉ ህይወት አለፈ

ዛሬ ሀምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም  ከንጋቱ 11:45 ሰዓት ላይ በለሚ ኩራ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 14 አርሴማ ቤተክርስቲያን አካባቢ እየተገነባ ያለ ህንፃ ከስሩ ባለ መኖሪያ ቤት ላይ ተደርምሶ የአንድ ሰዉ ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

ህይወታቸዉ ያለፈዉ ግለሰብ በቤት ዉስጥ ተኝተዉ የነበሩ በጾታ ወንድ የሆኑ የ50 ዓመት ዕድሜ የተገመቱ መሆናቸውን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል።

በስፍራዉ ፈጥነዉ የደረሱት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችና የአካባቢዉ ማህበረሰብ ባደረጉት ርብርብ ሶስት ሰዎችን ከአደጋዉ መታደግ ችለዋል።

በአዲስ አበባ የግንባታ ስራ ላይ በተለይም በግለሰቦች የሚገነቡ ግንባታዎች የደህንነት መስፈርቶችን ጠብቆ ባለመስራታቸዉ በሰዉ ህይወትና ንብረት ላይ በተደጋጋሚ አደጋዎች እያጋጠሙ ይገኛል።

የግንባታ ስራዎች በሚከናወኑበት ጉዳዩ የሚመለከታቸዊ አካላት ግንባታዎቹ የአደጋ ደህንነት መስፈርት ተጠብቀዉ ስለመሰራታቸዉ የተጠናከረ ቁጥጥር በማድረግ የማስተካከያ እርምጃዎችን መዉሰድና የህግ ተጠያቂነትን ማስፈን ያስፈልጋል ሲል ኮሚሽኑ አሳስቧል።


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የአዲስ አበባ ከተማ ሪል ስቴት ገበያ በዋጋ ደረጃ ለመስከኑ የኦቪድ ግሩፕ አስተዋፅዎ ቀላል አይደለም ። ኦቪድ ግሩፕ በሪል ስቴት ልማት ክንፉ ፣ የገነባቸው ቤቶችን በብዛት ለገበያ ማቅረቡ የሪል ስቴት ገበያው እንዲሰክን አድርጓል - ወይም ሰብሯል ።

ቀደም ባሉት ወራት በዋጋ ሽቅብ ይጎን የነበረው የሪል ስቴት ገበያ የዋጋ ቅናሽ እየታየበት ነው - ዋጋውን ጣሪያ የሰቀሉ ጭራሽኑ ጠያቂ አጥተዋል ።

ግዙፉ የሪል ስቴት ዘርፍ ዘገር ነቅናቂ ሆኖ የቀረበው ኦቪድ - በታሪክ ተመዝግቧል ...... ብራቮ ዮናስ ታደሰ !

በአዲስ አበባ ከተማ የሪል ስቴት የካሬ ሜትር ዋጋ ወቅታዊ ነፀብራቅ ምን መልክ ይዟል ተብሎ ቢታይ - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ባስጠናው ጥናት የአንድ ካሬ ሜትር የሪል ስቴት መገንቢያ ዋጋ ከ 30,000 ብር እስከ 40,000 ብር - አለፍ ብሎም እስከ 50,000 ብር ነው ።

ነገር ግን ይህንን ዋጋ ብዙዎቹ የሪልስቴት አልሚዎች በፍፁም አይቀበሉትም ። ይልቁኑ እንደየ ሪልስቴት ግንባታው ደረጃ የሚለያይ ቢሆንም በአልሚዎች ጥናት የሪል ስቴት የግንባታ ዋጋ በካሬ ሜትር ከ 63,000 ብር እስከ 70,000 ብር ይደርሳል።

የሪል ስቴት መገንቢያ ቦታ በሁለት መንገድ ይገኛል ። አንድም ከአስተዳደሩ ሁለትም ከግለሰቦች በግዥ ። ከግለሰቦች በግዥ የሚገኘው ውድ እንደመሆኑ በግንባታው ላይ የመሬት ዋጋ ፣ የሠራተኛ እና የመሳሰሉ ወጪዎች ሲጨመሩበት ዋጋውን ማናሩ አይቀርም ።

ኦቪድ ግሩፕ ገበያውን ከመቀላቀሉ በፊት አብዛኛዎቹ አልሚዎች ለገበያ ያቀረቡትን ሪል ስቴት በካሬ ከ 80,000 ብር እስከ 120,000 ብር ይጠሩ ነበር - በውጭ ምንዛሪ ደግሞ በካሬ ሜትር ከ 3,000 እስከ 4,000 ዶላር ድረስ ይጠራሉ - ከዚህም በላይ ዋጋ የሚጠራላቸው ቅንጡ ሪልስቴቶች እዚህም እዚያም እንዳሉ አሉ!

በአሁኑ ገበያ ግን በካሬ ሜትር 70,000 ብር እና ዙሪያውን ፣ በውጭ ምንዛሪም 2,000 እና ዙሪያውን እየተጠራ ይገኛል ። ከዚህ ባለፈም ከ10 እስከ 20 በመቶ ቅናሽ ማማለያ እየተሰጠ ነው ።

በዚህ መሀል ማን ሰንጥቆ መጣ !? ለሦስት አስርት ከግንባታ ተገልሎ የቆየው የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በለውጡ ዳግም አንሰራራ - ረሻድ ከማል የሚባል ዶዘር መጣለት - ፌቤኮ ተገማች ባልሆነ መንገድ በዋና ዋና ግንባር ቦታዎች ሁነኛ ህንፃዎችን ገንብቶ ባልተጠበቀ ዋጋ ቤቶችን ገንብቶ ለገበያ ሲያቀርብ - ገበያው ከኢኮኖሚ ማንሰራሪያ ባሻገር ለብዙሃኑ ሃብት ሆነ ...

ግን ግን የግልና መንግስት አጋርነት ( PPP ) ከመንግስት በ 70/30 ቀመር መሬት የወሰዱ ሪል ስቴት አልሚዎች በስንት ብር ቢሸጡት ያዋጣቸው ይሆን !?

በ70 ሽህ ? መንግስት ከተገነባው ሪል ስቴት ድርሻውን ሲወስድ አልሚዎቹ የመገንቢያ ዋጋውን እንዴት አብቃቅተው አትራፊ ይሆኑ ይሆን - ልናይ ኋላ!

በልዩ ሁኔታ የሚታይ ቢሆንም የፐርፐዝ ብላክ ዋጋ ሳያስደምም የሚቀር አይደለም - የፐርፐዝ ብላክ ነገር እስካሁን መጨረሻው ባይለይም አምስት ቢሊየን ብር ቦታ ገዝቶ ፤ በ 60 ቢሊዮን ብር 113 ወለል ህንፃ ከነ አጀቡ ገንብቶ - ከአክሲዮን ድርሻ ጋር ፣ መቶ ካሬ ሜትር ቤት በ 1.5 ሚሊዮን ብር ፤ ቆየት ብሎም በ3.5 ሚሊዮን ብር ሂሳብ ( በካሬ ሜትር 15,000 ብር እና 35,000 ብር መሆኑ ነው ) መዋዋሉ ከትርፋማነት ቀመር ውጭ ነው ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሪል ስቴት ዘርፍ ለመኖሪያ ፈላጊው ጥሩ አማራጭ ገበያ እንዲሆን ካስፈለገ የመሬት አቅርቦት ፣ የፋይናንስ አማራጭ ፣ የሸማች መብት ጥበቃ ወሳኝነት አላቸው - በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ቢሊየነሮች የገቡበት ዘርፍ መሆኑ ልብ ይሏል - የዚያኑ ያህልም የተካኑ ባለካልኩሌተሮችም ዘርፉን ተቀላቅለዋልና መፍዘዝ ጥሩ አይደለም !


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ተዓምረ_Dog 🐕🚀🐕🚀🐕🚀🐕

😵 በሁለት ቀናት ውስጥ 9.4 ሚሊዮን ህዝብ ተቀላቅሏል::

🙀 Varified ነው

😳 #Tap ማድረግና #Task የለውም (ጊዜ አይወስድም)

😻 ስትጀምሩ ቴሌግራም ላይ የቆያችሁበት ዓመት አስልቶ #Coin ይሰጣችኋል

🙀 "Who are you dawg?" የሚል ጽሁፍ ከመጣላችሁ አካውንታችሁ @Username የለውም ማለቱ ነው - አስገቡበት::

🙀 ብዙ ተከታይ ያላችሁ የራሳችሁን link በማጋራት ራሳችሁንም ሌሎችንም ጥቅሙ::

😻 ያልጀመራችሁ - ጊዜ አትውሰዱ:: በአቃራጭ የመጣ የማይደገም እድል ነው::
👇👇👇

https://www.tg-me.com/dogshouse_bot/join?startapp=cfb5cSz1TdO8TWlQQe0jTw
Structural behavior of cantilever beams A famous photograph by Benjamin Baker, in which through a living model the cantilever structural principle on which the solution to the Firth Bridge over the Forth was based.

To illustrate the structural theory of a cantilever beam (Gerber), a human demonstration was carried out. The loads were represented by the person sitting in the middle of the span of the suspended span. The arms of the persons seated on both sides represented the traction at the joints; the wooden bars, the compression at the lower elements, and the bricks, the anchor points located at the pylons. The chairs represent the granite piles. Imagine the chairs 500 m apart and the men's heads as high as St. Paul's cross (London church, 104 m) their arms are represented by steel beams and the canes by 3.5 m diameter tubes at the base you get a good notion of the structure.

Heinrich Gerber applied in 1866 a theory that consisted in subdividing the continuous beam through ball-and-socket joints "which define a point of zero bending moment". This type of beam with intermediate joints is what is now known as a Gerber beam. The position where these hinges are located allows for influencing the behavior of the beam; therefore, it is not only used directly in some structures but in some projects, a real beam can be idealized by assimilating it to a Gerber beam, whose isostatic allows a simple approximate calculation.


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
5 Steps Of Load Pathway For Concrete Structures

The load pathway for a concrete structure involves the transfer of loads from the point of application to the ground. Here are the typical five steps in this pathway:

1. Load Application:
- Loads such as gravity loads (dead and live loads), environmental loads (wind, earthquake), and other imposed loads are applied to the structure.

2. Load Distribution:
- These loads are distributed across the surface or point of application (e.g., floors, roofs) and transferred to structural elements like beams and slabs.

3. Load Transfer to Vertical Elements:
- The distributed loads are transferred from beams and slabs to vertical structural elements such as columns and walls.

4. Load Transfer to Foundation:
- The vertical elements, in turn, transfer the loads to the foundation of the structure. This can include footings, pile foundations, or mat foundations.

5. Load Transfer to the Ground:
- Finally, the foundation transfers the loads to the ground, where they are dispersed into the soil, ensuring the stability of the entire structure.

⚡️Each of these steps is crucial for maintaining the structural integrity and ensuring that the loads are safely transferred to the ground without causing failure or excessive deformation in any part of the structure.


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የቤት ዋጋ እንዴት ሊቀንስ ይችላል?

"ቤት አትግዙ " የሚል የሶሻል ሚዲያ ቻሌንጅ የማከብረው ወዳጄ ልኮልኝ ተመለከትኩ።
አላማው በደምሳሳው ቤት ውድ ስለሆነ እስኪቀንስ ድረስ አትግዙ የሚል ነው...ይሄ ብዙም ውጤታማ ሊሆን የማይችል ቻሌንጅ እንደሆነ ቢታወቅም ሀሳቡ ግን የሚበረታታ  አይደለም ምክንያቱም ስሁት ነው።

የሪል እስቴት ዘርፍን በቅጡ ካለመገንዘብ የመጣ ቤት ተወዷል ብሎ ለውድነቱም አልሚዎችን ብቻ ተወቃሽና ተከሳሽ ለማድረግ የታሰበ የችግሩን መሰረት ያልተረዳ ነው።  እስኪ የዘርፉን አሰራርና ችግሩን እንድንረዳ ስለ ሪል እስቴት ኢንቨስትመንት ዋና ተዋናዮችና አስተዋጽኦዋቸው ጥቂት እንበል። 

ሀ) ባለድርሻ አካላትና ድርሻዎቻቸው

የሪል እስቴት ኢንቨስትመንት አምስት ዋና ዋና ባለድርሻ አካላት አሉት። የሀገራችንን ሁኔታ ታሳቢ አድርገን ስናቀርበው ከዚህ በታች የተገለጸውን ሊመስል ይችላል:-

፩) አልሚ (Developer) :- ስራ ፈጣሪ ነው፣ መሬትን ወደ ውጤታማ የሆነ ተፈላጊ የመኖሪያ ስፍራ በመቀየር ትርፍን የሚያገኝ መላ ፈጣሪ ነው፣ የገንዘብ አምጪ፣ የኪሳራሃላፊነት ወሳጅ፣ ቀጣሪ ሲሆን ዓላማው የገንዘብ ትርፍ ማግኘት፣ የቤት ችግር መቅረፍ ቢዝነሱ ያደረገ፣ ዘላቂ ንብረት ማፍራት፣ ጥሩ ስም መገንባት ...

፪) መንግስት(public organization):- መንግስት ዜጎች ቤት እንዲያገኙ የተለያዩ ፖሊሲዎችንና መመሪያዎችን ያወጣል፣ ለቤት ልማት የሚሆን መሬት ያቀርባል፣ የግንባታ ሂደቱን ይከታተላል፣ የግብይት ሂደቱን ይቆጣጠራል....

በሪል እስቴት ልማት ውስጥ የመንግስት ዋና ፍላጎት  የልማቱ ሂደት በስኬት ተከናውኖ   ዜጎች ቤት እንዲያገኙ ማድረግ፣  የህዝብ ሃብት የሆነው መሬት በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ ....

፫) ካፒታል ማርኬት:- ይህ ለግንባታም ሆነ ለቤት ገዢዎች ብድር የሚሆን የገንዘብ አቅርቦትን የሚያቀርቡ ባንኮችንና ሌሎች ወደፊት የሚመጡ የገንዘብ አቅርቦት የሚሰሩ ተቋማት ሲሆኑ ተሳትፏቸውም ለልማቱና ለቤት ገዢዎች ገንዘብ ማቅረብና ከልማት ሂደቱ ማትረፍ ነው። ፍላጎታቸው ኢንቨስትመንቱ አዋጭ መሆኑን ማረጋገጥ ነው።

፬) የቤት ገዢዎች (ተከራዮች) (ደንበኞች):- ዋና ፍላጎታቸው ለመኖር በቂ የሆነ ፣ በጊዜው ተጠናቅቆ መረከብ፣ በቂ ስፋት ያላቸው መገልገያ ክፍሎች ፣ በተመጣጣኝ ዋጋ ቤት ማግኘት ሲሆን። የቤት አልሚው ይህንን የቤት ገዢዎችን አቅምና ፍላጎት በገበያ ጥናት አጥንቶ መገንባት ይጠበቅበታል።

፭) የተለያዩ ባለሙያዎች (Development Team ) :- የሪል እስቴት ዘርፍ ብዙ ሙያዎችን የሚጠቀም ዘርፍ ነው። ለምሳሌ አርክቴክቶች፣ መሃንዲሶች፣ ገንቢዎች፣ የግብይት ሂደት ውስጥ ያሉ ባለሙያዎች፣ የፋይናንስ፣ የባንኪንግ ፣ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ባለሙያዎች፣ IT ባለሙያዎች፣ የህግ ባለሙያዎች ወዘተ.... ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው ። ባለሙያዎቹ በግልም በህብረትም በየሙያቸው ያለውን ከፍተኛና ፈጠራ የተካተተበት የደንበኞችን  ፍላጎት መሰረት ያደረገ ውጤት እንዲመጣ የማድረግ ሃላፊነት አለባቸው።

ለ) ቤት ዋጋ እንዲቀንስ የሚጠበቅባቸው አስተዋጽኦ

የሪል እስቴት ልማትና ግብይት የተሳካ እንዲሆን ከላይ የተዘረዘሩት ባለድርሻ አካላት የሚጠብቃቸውን ያለማጓደል ሊያበረክቱ ይገባል።

ለምሳሌ :-
፩) መንግስት ለአልሚዎች መሬት በቅናሽና በብዛት ካቀረበ፣  የዲዛይን ማጽደቅና ክትትል ስራውን ካሳለጠ፣ ግብይቱ የሚመራበት መመሪያና ግብይቱን የሚመራ  አካል ሰይሞ በስርዓት እንዲመራ ካደረገ፣ በርካታ ቤቶችን ለሚገነቡ አልሚዎች የግንባታ  ከቀረጥ ነጻ እንዲያስገቡ  ካደረገ።

፪) የገንዘብ አቅራቢ ተቋማት ለአልሚዎችና ለቤት ገዢዎች በቂ የሆነ የገንዘብ አቅርቦት ካደረጉ
፫) ቤት ገዢዎች ጠንክረው ሰርተው ቁጠባን ባህላቸው ቢያደርጉና እቅም ከፈጠሩ

፬) ባለሙያዎች ገበያውንና የቤት ገዢዎችን አቅምና ፍላጎት ያገናዘቡ ቤቶች የሚገነቡበትን ዲዛይን፣ ወጪ ቀናሽ የግንባታ ቴክኖሎጂ ፣ የአከፋፈል ስርዓት በጥናት ላይ በተመሰረተ ሁኔታ ካዘጋጁ

፭) አልሚዎች ዘርፉን በእውቀት በባለሙያዎች እንዲመራ ካደረጉ

ሐ) መውጫ በምሳሌ

ነገር ግን ከአምስቱ  አንዱ ሲያጎድል ዘርፉ ውጤታማ እንዳይሆን ሊያደርግ ይችላል በሌሎቹ አካላት ላይም ተጽዕኖን ያሳድራል ።

ለምሳሌ :- ባለሙያዎች ገበያውን ያላገናዘበ ውድ ቤቶች ንድፍ ቢሰሩና የሰሩትም ቢገነባ  ቤት ገዢዎች ሊገዙት አይችሉም፣ ካልተሸጠ ባንኮች ያበደሩት ብር በወቅቱ አይመለሰም፣ የቤት ችግርን ስለማይቀረፍ መንግስት ላይ ተጽዕኖ ይፈጥራል ከልማቱ ማግኘት የነበረበትን ገቢ ያሳጣል፣ አልሚውም ይከስራል...

ስናጠቃልለው የቤት ዋጋ ሊቀንስ የሚችለው በአልሚዎች ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ከላይ የተጠቀሱት አካላት የተናበበ የጋራ ተሳትፎ ሲኖር ብቻ ነው።

በ ደሳለኝ ከበደ
(አቶ ደሳለኝ ከበደ ሲቪል መሀንዲስ፣ ስራ ተቋራጭ፣ አሰልጣኝ እና ጸሀፊ ሲሆኑ በግንባታው ዘርፍ ላይ ሰፊ ተሞክሮ ያላቸው ባለሙያ ናቸው)


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ዜና ዕረፍት!

የዝነኛው ሳሊኒ ኮንስትራክሽን ባለቤት ሲሞን ፔትሮ ሳሊኒ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

በአገራችን ኢትዮጵያ በርካታ ብሔራዊ እና ግዙፍ የግንባታ ፕሮጀክቶችን በማከናወን ዝናን ያተረፈው ሳሊኒ ኮንስትራክሽን ባለቤት በ92 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

እኚህ ግለሰብ 1.5 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ሀብት እንዳላቸው የፎርብስ መጽሔት መረጃ ያሳያል።


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#Ethio construction team በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን በደረሰው አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለፀ ለመላው ወገን መፅናናትን ይመኛል!!
https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Watering the concrete with water after pouring:

👉 increases the strength of concrete and the durability of the building.
👉 reduces the permeability of concrete due to water evaporation.
👉 completes the cohesion and reaction of cement that continues for a period after pouring.

⚡️Watering the concrete with water after pouring is very important. It must be done for a period of at least one week, twice a day, to reach 70% of its resistance in a week.


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Did you know?

💫The reasons for honeycomb in concrete:

1. Inappropriate workability of concrete.

2. Use of stiff concrete mix or the concrete is already set before placing.

3. Improper vibration of concrete in formwork.

4. Over reinforcement.

5. Use of larger size aggregates in excessive amounts.

6. Formwork is not rigid and watertight.

7. Concrete is poured from more than allowable height.

8. Congestion of steel is preventing the concrete to flow over all corners.


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2025/06/30 14:17:13
Back to Top
HTML Embed Code: