Telegram Web Link
የግንባታ ውል ሰነድ በግልጽ ማስቀመጥ ያለበት ነጥቦች:-

የፕሮጀክቱን ዲዛይን እና ዝርዝሮች:

የፕሮጀክት ባለድርሻ አካላትን ድርሻ፣ መብትና ግዴታ፣
➢የሚጠበቀውን የግንባታ ጥራት የሚገልጹ ትንታኔዎች፣
➢የፕሮጀክቱን ተጠባቂ የጊዜ ሰሌዳዎች፣
➢የፕሮጀክቱን ዋጋ እና አከፋፈል ሁኔታዎች፣
➢የደህንነት እና የጤና አጠባበቅ፣ መመሪያዎች፣
➢ፕሮጀክቱን የሚመለከቱ የሕግ ማእቀፎች
➢የፕሮጀክቱ ባለድርሻ አካላትን ፊርማ እና ማኅተም
➢ፕሮጀክቱ የሚፈልገውን የሰው ኃይል ብቃትና ብዛት
➢ፕሮጀክቱ የሚፈልገው ማሺነሪ አይነትና ብዛት
➢የእያንዳንዱን የሥራ አይነት ዝርዝርና የግንባታ ስነዘዴ
➢የፕሮጀክቱን ባለድርሻ አካላት ዝርዝር መረጃ


አንድ የግንባታ ውል ሰነድ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱትን ዋና ዋና ጭብጥ ጉዳዮች በግልጽ እና በዝርዝር ማስቀመጥ ይኖርበታል።

የተወሳሰበ፣ ያልተብራራ እና እርስ በእርሱ የሚጋጭ ሀሳብ ቢኖርበት ግን በሚኖረው የፍርድ ቤት ክርክር ባለድርሻ አካላትን በተናጠል አልያም በጋራ ኪሳራ ላይ ሊጥል ይችላል።

ይህ ሁኔታ ደግሞ ፕሮጀክቱን በጤናማ ግንኝነት ለመፈጸም እክል ሊፈጥር ስለሚችል ለጥራት ችግር እና ለጊዜ ብክነት እንዲጋለጥ ያደርገዋል። 


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍244😍1
አንድ ሰው ግንባታ እያከናወነ የጎረቤት ቤት ቢፈርስበት የጎረቤቱን ቤት እንዲያሰራ ይገደዳል ወይስ ሌላ የህግ እይታ አለ?

አንድ ሰው ግንባታውን ሲያከናውን የጎረቤቱን ቤት ቢናድበት ወይም በግንባታ ሥራው የተነሳ የጎረቤቱን ቤት ቢያፈርስ ተጠያቂ ነው።

💫የመፍረስ አደጋ ባይገጥምም እንኳን በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2077 (1) እና (2) መሰረት  አንድ ሕንጻ በሌላው ይዞታ ላይ ያልታሰበ ድንገተኛ ሌላ አደጋ ቢያደርስ የሕንጻው ባለቤት ተጠያቂ (ካሳ ከፋይ) ይሆናል።

▶️ይህም ማለት እንዲፈርስ ያደረገውን ቤት በእራሱ ወጪ እንዲጠግን/እንዲሰራ ይገደዳል።

ቢሆንም ግን በቁጥር 2079 መሰረት በግንባታ ወቅት (በተለይ ከቁፋሮ ጀምሮ ባሉት የመሰረት ሥራዎች ጊዜ) በሌላ የጎረቤት ሕንጻ ላይ የመፍረስ አደጋ ከመድረሱ በፊት አስቀድሞ ሥጋት ላይ ያለው ክፍል አስፈላጊውን ድጋፍ ወይም ጥንቃቄ እንዲደረግለት ማድረግ ይችላል።

▶️“ጎረቤት” የተባለው አካልም ይህ ስጋት ከተሰማው አስቀድሞ ጥንቃቄ እንዲደረግለት የመጠየቅ ሕጋዊ መብት አለው።

🚧ጠቅለል ሲደረግ፦ አንድ የሕንጻ ባለይዞታ በግንባታ ወቅት በጎረቤት ይዞታ ላይ የተገነባን ሕንጻ የመፍረስ ወይም የመሰንጠቅ ጉዳት ቢያደርስ እንዲሁም ሕንጻው በሚገነባበት ወቅትም ይሁን ከተጠናቀቀ በኋላ ከዚያ ሕንጻ ላይ እየወደቁ በሌላው ሕንጻ ወይም ይዞታ ላይ ለሚያደርሱት ጉዳት ተጠያቂ ነው (ፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2080)።

❇️የጎረቤት ሕንጻ ቢፈርስ ተጠያቂ የማይሆንበት አግባብ

▶️በጎረቤት ይዞታ ወይም ሕንጻ ላይ ጉዳት ቢደርስ የማይጠየቀው በሁለት ምክንያት ነው።

📜[አንደኛው] በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2078 (1)  መሰረት ጎረቤት የተባለው ባለይዞታ ይዞታውን ግንባታ ለሚያከናውነው ሰው የለቀቀለት እንደሆነ ወይም ግንባታ የሚያከናውነት አካል የራሱን ሕንጻ ለፈረሰበት ጎረቤቱ የሚለቅለት ከሆነ ነው።

📜[ሁለተኛው] “ጎረቤት” የተባለው አካል ሕንጻው የመፍረስ አደጋ እንዳይገጥመው ጥንቃቄ እንዲደረግለት የመጠየቅ መብት የሚኖረው ግን አስቀድሞ የገነባው ሕንጻ በመሬት ውስጥ፣ በመሬት ላይም ይሁን በአየር ላይ አዲስ የሚገነባውን ባለይዞታ የካርታ መስመር ያላለፈ ከሆነ ብቻ ነው።

🗂ለምሳሌ፦ አስቀድሞ የገነባው ጎረቤት የመሰረት ግንባታው ወይም ተንጠልጣይ የባልኮኒ ወለል ወደሰው ይዞታ አንድ ሳንቲሜትርም ቢሆን ካለፈ እንዲያስተካክል ወይም እንዲያፈርስ ይገደዳል።

አዲስ ግንባታ የሚገነባውም ሰው ጎረቤቱ ወደይዞታው ገብቶ የሰራውን የሕንጻ አካል እንዲያፈርስና እንዲያስተካክል ሳያስጠነቅቅ ማፍረስ የለበትም፣ በፍርድ ቤት በተቆረጠ ቀነ ገደብ እንዲያስተካክል ማሳሰብ ሲኖርበት በዚያ ቀነገደብ ካላስተካከለ ግን ትእዛዝ አስወጥቶ ማስፈረስ/ማፍረስ/ ይችላል።


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍376
የአለማችን ረጅሙ የእንጨት ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ በአሜሪካ ሊገነባ ነው

በአሜሪካ ዊስኮንሲን ግዛት ውስጥ የሚገነባው 55 ፎቅ ያለው አዲሱ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ የዓለማችን ረጅሙ የእንጨት ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ ይሆናል ተብሏል።

የሕንፃው ነዳፊ የሆነው ሚሼል ግሪን አርክቴክቸር (ኤምጂኤ) መስራች በአሜሪካ የዘመናዊ የእንጨት ግንባታ ፈር ቀዳጅ ሲሆን፣ በሰሜን አሜሪካ ታዋቂ በሆኑ ትላልቅ የእንጨት ግንባታ ፕሮጀክቶች ውስጥ መሥራቱም ታውቋል።

አዲሱ ሰማይ ጠቀስ የእንጨት ሕንፃ ሰፊ አረንጓዴ እና በርካታ ቴራሶች  የያዘ ሲሆን፣ አጠቃላይ ወጪው ከ700 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ይሆናል።

ሕንፃው እስከ 750 የሚደርሱ መኖሪያ ቤቶች፣ 17,600 ካሬ ሜትር የቢሮ ቦታ፣ 3,700 ካሬ ሜትር ቦታ የንግድ ሱቆች፣ 300 የሆቴል ክፍሎች፣ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች እና  ክፍት የህዝብ መናፈሻ ቦታዎች እና የእግረኛ መንገዶችን ያካተተ እንደሚሆን ታውቋል። 

ሰማይ ጠቀስ ሕንፃው በግንባታ ሂደት ውስጥ የትኛውንም ኮንክሪት እንደሚጨምር እርግጠኛ አይደለንም የሚሉት ነዳፊዎቹ፣ ነገር ግን ቁመቱን ግምት ውስጥ በማስገባት የተወሰነ ኮንክሪት እንደሚካተት እናምናለን ይላሉ።

ሰዎች ከእንጨት የተሠራ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ በቀላሉ በእሳት ሊያያዝ ይችላል የሚል ስጋት ሊኖራቸው ይችላል፣ ነገር ግን ከባህላዊው እንጨት በተለየ፣ በዘመናዊው ሁኔታ ለግንባታ የተዘጋጀው ጠንካራ የእንጨት ምሰሶ ከብረት ይልቅ እሳትን በተሻለ ሁኔታ መቋቋም የሚችል ነው ተብሏል።

በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ 25 ፎቆች ብቻ  የሚረዝመው የዓለማችን ረጅሙ በእንጨት የተገነባ ሕንፃ የሚገኘው በተመሳሳይ ዊስኮንሲን ግዛት ውስጥ ነው።

https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍38👏31
🌟Training (With Discount)

          🌟Online Class (With Certificate)

1. ETABS Price = 2000birr
2. Ms Project Price = 2500birr
3. Quantity Survey Price = 2000birr
4. Civil 3D Price =2500birr
5. Etabs With Safe Price = 3000birr
6. Advanced Structural Design Using ETABS, SAFE and SAP2000
7. Structural Design in ProtaStructure Software
8. Autocad Price = 2500birr
9. Sap2000 Price = 2500birr
10. Autodesk Revit Architecture
11. WatrGems


🫵 If u take More than 2 Course u will have Big Discount

🚧Prepared by Engineering Solution Abel Muluken

🫵For Registration - 0948552002 Or 0933575753 or @AbelMuluken

🚧Telegram Channel - https://www.tg-me.com/AbelMulukenEngineeringSolution

🚧YouTube Channel - https://youtube.com/channel/UCNxyykElOiXVKVlA4jXI2B
👍173
ይህ ግዙፍ የአፓርትመንት ኮምፕሌክስ መጠሪያ ስሙ Novy Okkervil ይባላል፤ በሩሲያ ነው የሚገኘው።

🏷እ.ኤ.አ በ2015 የተገነባው የመኖሪያ መንደር ከአለማችን ከሚገኙ ተመሳሳይ ግንባታዎች በቀዳሚነት እንደሚገኝ ይነግርለታል።

💫በዚህ መንደር ውስጥ ወደ 18 ሺህ የሚጠጋ ህዝብ ይኖርበታል።

⭐️እያንዳንዱ ሕንፃ ባለ 25 ወለል ሲሆን፣ በጠቅላላው ወደ ሕንፃው ለመግባትም ሆነ ለመውጣት 35 በሮች አሉት።


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍267💯3
ጥያቄ

በአንድ ተቋራጭ ሥር የሚሠሩ ምክትል ሥራ ተቋራጮች (Sub Contractors) የሠሩበትን የሥራ ክፍያ ዋናው ተቋራጭ አልከፍል ቢላቸው ክስ መስርተው በዋናው ተቋራጭ ውል ላይ የተመለከተውን የሥራ ዋጋ የማግኘት መብት አላቸው?
መልስ


በኢትዮጵያ የሕንጻ ነክ ሕጎች መሰረት በአንድ የሕንጻ ተቋራጭ ሥር የሚሰሩ ምክትል /ንዑስ/ ሥራ ተቋራጮች (Sub contractors) ወይም ሠራተኞች (labours) ዋናው ተቋራጭ ለሠሩበት ሥራ ሳይከፍላቸው ከቀረ እና ለሠሩበት ሥራ ዋጋ እንዲከፈላቸው ክስ ካቀረቡ ክሳቸውን ባቀረቡበት ጊዜ አሠሪው ለሥራ ተቋራጩ ሊከፍል በሚገባው ገንዘብ መጠን በቀጥታ ገንዘባቸውን የመጠየቅ መብት ስላላቸው ያንን ክፍያ የማግኘት መብት አላቸው።

ለምሳሌ፦ አንድ ተቋራጭ በውል ሰነዱ ውስጥ የአንድ ካሬሜትር የፎርምወርክ ሥራን በ500 ብር ሂሳብ ተዋውሎ ለምክትል ሥራ ተቋራጮች  (Sub contractors) በ300 ብር ተነጋግሮ ካሠራቸው በኋላ ክፍያ ሳይከፍላቸው ቢቀር (ቢያዘገይባቸው) ክስ ማቅረብ ይችላሉ።

ክስ ሲያቀርቡ ሥራውን ለመሥራታቸው ማረጋገጫ ካቀረቡ እና የሥራው ጥራት ታይቶ ተቀባይነት ካገኘ ዋናው ተቋራጭ የተዋዋለበትን 500ብር ሊከፈላቸው የሚችልበት አግባብ አለ ማለት ነው።


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍576
ኮንስትራክሽን ክሌም
         
የኮንስትራክሽን ክሌም ለመስራት የውሉ የክፍያ መንገድ ላምፕ ሰም ወይስ አድሜዠርመንት የሚለውን መለየት ግድ ነው።

የውሉ አይነትም ዲዛይን ቢድ ቢዩልድ(DBB) ወይም ዲዛይን ቢዩልድ(DB) ስለመሆኑ  መለየት ይገባል።

DBB እና DB የተለያየ ጀኔራል ኮንዲሽን ይጠቀማሉ።ለምሳሌ FIDIC 2017 Red Book ለDBB እና Yellow Book ለDB መጠቀም ይቻላል።

የክፍያ መንገዱ ላምፕ ሰም ወይም አድሜዠርመንት መሆኑ ግን የጀኔራል ኮንዲሽን እንድትቀይር አያስገድድም።

ለምሳሌ ፒፒኤ 2011 ቨርሽን ለሁለቱም የክፍያ መንገዶች ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።

ስፔሻል ኮንዲሽን ላይ የተለወጠ የጀኔራል ኮንዲሽን ክሎስ ያለ እንደሆነ ማረጋገጥም ቀዳሚ ተግባር መሆን አለበት።

ከዚህ በኋላ ለክሌሙ አግባብነት ያለውን የውል ድንጋጌ፣የህግ ድንጋጌ እና የጀኔራልና ስፔሻል ኮንዲሽን ድንጋጌ መለየትና መስፈርቱን የሚያሟላ ክሌም ማዘጋጀት ይቻላል።

ከዚያም ክሌሙ ለአማካሪ፣ለዲስፒውት ሪቪው ቦርድ፣ለአርቢትሬሽን ወይስ ለፍርድ ቤት መቅረብ እንደሚገባው ለመለየት ጀኔራል ኮንዲሽኑን እና በዋናነት ስፔሻል ኮንዲሽኑን ማየት ይገባል።

በጉባዔ አሰፋ


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍282
🌼🌼🌼እንኳን አደረሳችሁ!🌼🌼🌼

🌻አዲሱ አመት የሰላም ፣ የደስታ ፣የፍቅር ፣ የመተሳሰብ፣ የስኬት አመት ይሁንላችሁ!!!

🌼🌼🌼መልካም አዲስ ዓመት!🌼🌼🌼

https://www.tg-me.com/ethioengineers1
👍24🙏74👏1
የቻይና መሃንዲሶች ለትራንስፖርት ተስማሚ የሆነ የመንገድ መሠረተ ልማት ለመገንባት የሚያግዳቸው ተራራማ፣ ኮረብታማ እና ጎበርባጣ መልከዓ ምድር የለም ብሎ አፍን ሞልቶ መናገር ይቻላል።

https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👏66👍345🤔3
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን እንኳን ለመውሊድ በዓል አደረሳችሁ፣

መልካም በዓል!


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍6
የዓለማችን ድንቅ እስላማዊ የ ኮንስትራክሽን ስትራክቸሮች እንሆ

1. መስጂድ አል-ሀራም፡-

መካ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ የሚገኝ መስጂድ አል-ሀራም የአለማችን ትልቁ መስጂድ ሲሆን በእስልምና እጅግ የተቀደሰ ቦታ የሆነውን ካባንን ይከብባል። 

መስጂዱ በሀጅ ወቅት እስከ 4 ሚሊዮን ሰጋጆችን ማስተናገድ ይችላል።

2. መስጂድ አል-ነበዊ፡-

በመዲና፣ ሳውዲ አረቢያ፣ መስጂድ አል-ነበዊ በእስልምና ሁለተኛው ቅዱስ መስጂድ ነው።

የነብዩ መሐመድ መቃብር የሚገኝበት ሲሆን በግሩም አረንጓዴ ጉልላት እና በዓይነቱ ልዩ የሆነ የስነ-ህንፃ ጥበብ ይታወቃል።

3.ቡርጅ ካሊፋ፡ 828 ሜትር ላይ የቆመው ቡርጅ ካሊፋ በዱባይ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ፣ በአለማችን ረጅሙ ህንፃ ነው

ኢስላማዊ እና ዘመናዊ ኪነ-ህንፃዎች ቅልቅል ያለው እና ተወዳጅ የቱሪስት መስህብ ነው።

4. ሱልጣን አህመድ መስጂድ፡-

በተለምዶ ሰማያዊ መስጂድ በመባል የሚታወቀው በቱርክ ኢስታንቡል የሚገኘው ሱልጣን አህመድ መስጂድ የውስጥ ግድግዳውን እና ስድስቱን ሚናራዎችን በሚያጌጡ ሰማያዊ ሰቆች ይታወቃል። 

የኦቶማን አርክቴክቸር ድንቅ ስራ ነው።

5. ሀሰን II መስጂድ፡

በሞሮኮ ካዛብላንካ ውስጥ የሚገኝ፣ ሀሰን 2 መስጂድ በአለም ላይ ካሉት ትልቁ መስጊዶች አንዱ ነው እና አስደናቂ የእብነበረድ ውስጠኛ ክፍል፣ ውስብስብ የጣር ስራ እና አስደናቂ የባህር ዳርቻ አቀማመጥ አለው።

6. አልሀምብራ፡

በግራናዳ፣ ስፔን ውስጥ የምትገኝ፣ አልሀምብራ መጎብኘት ያለበት የእስልምና አርክቴክቸር ድንቅ ነው።

ይህ ቤተ መንግስት እና ምሽግ ውስብስብ የስቱኮ ማስዋቢያዎች፣ የፈረስ ጫማ ቅስቶች እና የተረጋጋ የአትክልት ስፍራዎችን ያሳያል።

7. የሼክ ዛይድ ታላቁ መስጊድ፡

በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ አቡ ዳቢ የሚገኘው የሼክ ዛይድ ታላቁ መስጂድ የዘመናዊ ኢስላማዊ ኪነ-ህንፃ ድንቅ ስራ ነው። 

ነጭ የእብነበረድ ጉልላቶች፣ ውስብስብ ቅርጻ ቅርጾች እና አስደናቂ የአበባ ንድፎችን ይዟል።

8. ታላቁ የኮርዶባ መስጊድ፡

በ8ኛው ክፍለ ዘመን በኮርዶባ፣ ስፔን ውስጥ የተገነባው ታላቁ የኮርዶባ መስጊድ የሞሪሽ፣ የጎቲክ እና የህዳሴ ስነ-ህንፃ ቅጦች ድብልቅልቅ የሚያሳይ የባህል ሀብት ነው። 

ውስጣዊ ክፍሎቹ ከ 850 በላይ አምዶች እና ውስብስብ ቢሞች ኣሉት።


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍2517
"በሕንጻ ግንባታ ሥራ selective material ከመጠቅጠቁ (ከመረምረሙ) በፊት ውኃ የሚጠጣው ለምንድነው? የጎንዮሽ ተጽእኖስ አለው ይላሉ?"
🏷የአፈር መጠቅጠቅ ሂደት ቅንጣቶች በመካከላቸው ያለውን ክፍተት ለመቀነስ የሚደረግ የመጫን ጉልበት (compaction) ትግበራ ነው።

💫በጣም የታመቀ፣ የተጠቀጠቀ አፈር የቅንጣቶችን ክፍተት በመቀነስ አፈሩ በጣም ጥቂት ቦታን (ስፋትን) እንዲይዝ ያግዘዋል።

⭐️ነገር ግን ይህንን የመጠቅጠቅ (ጥግግት) ደረጃ  የምናገኘው ጥሩ የእርጥበት መጠን ካለው  ነው። አፈሩ በጣም ጥሩ እርጥበት የሌለው ከሆነ የአፈር ቅንጣት ጥግግት በሚፈለገው ልክ ሊከናወን ስለማይችል ውስጥ ውስጥ  ያሉትን ክፍተቶች በሙሉ ለመሙላት አስቸጋሪ ይሆናል።  የተደፋው አፈር (Back filled or selective material) ሁሉም አካሉ በቂ እርጥበት እንዲኖረው ቢያንስ ከአንድ ሌሊት በፊት ቀደም ብሎ  ውኃ መጠጣት አለበት።

🌟የተወሰነ ጊዜ ቀድሞ ማጠጣት (አንደኛ) በሰዓቱ መርዘም የተነሳ የውኃውን የስርገት ሂደት በመጨመር እና ሁሉንም አካል የማግኘት (የማዳረስ) ዕድሉን በማስፋት ሁሉም የአፈር ቅንጣት በቂ እርጥበት እንዲያገኝ ያደርገዋል።

🌟(ሁለተኛ) የአፈሩ የመጠቅጠቅ ሂደት አስቀድሞ በውኃው ስርገት የተነሳ እየተከናወነ እንዲቆይ ያድርጋል። ያ ማለት የመጠቅጠቂያ ጉልበትን ይቀንሳል።

⚡️ሆኖም ግን የተመረጠው አፈር በቂ የሆነ የኮረት፣ የጓል እና የደቃቅ አፈር መዋጮ የሌለበት ከሆነ ውኃ ሲጠጣ የባሰ የላመ አፈር (silty) የመሆን እድሉን ስለሚጨምር ከሚፈለገው አገልግሎት አንጻር ጉዳት እንዳይደርስበት የውኃውን መጠን እና የሚጠጣበትን የጊዜ ርዝማኔ እንደአፈሩ አይነት እና እንደአካባቢው አየር የመመጠን ሥራ ከአንድ መሐንዲስ የሚጠበቅ የውሳኔ አካል ነው።


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍583🔥3
Call for Advanced Level Training
1) Building Advanced Structural Design
2) Bridge Design 
3
) Project Planning & Contract Administration .

●Every Sunday Morning 3:00-8:00 LT.
Registration is active
Class starts on October 6/2024

📲
0911890392 / 0920933016
📌 Megenagna,Marathon, No. 614
https://www.tg-me.com/BeGetEngineering
👍193🔥2
ይህ እስካሁን በሚድያ ምንም ያልተነገረለት የህንፃ ግንባታ መመርያ በአዲስ አበባ የግንባታ ታሪክ ከፍተኛው ተፅእኖ ፈጣሪ ይመስለኛል፣ የደብዳቤውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ችያለሁ ❗️

መስከረም 3 ተፈርሞ ለሁሉም ክፍለ ከተሞች በተላለፈው በዚህ መመርያ መሰረት ከ15 ሜትር እና በላይ ስፋት ያላቸው መንገዶች የሚያዋስኗቸው ይዞታዎች ዝቅተኛው የቦታ ስፋት ሴት ባክ (set back) ከተቀነሰ በኋላ ቢያንስ 500 ሜትር ካሬ መሆን እንዳለበት ይደነግጋል፣ ካልሆነ የግንባታ ፈቃድ አይሰጥም ማለት ነው።

በሌላ በኩል በነዚህ መንገዶች ላይ ዝቅተኛው የህንፃ የጎን ስፋት (frontage) ከ20 ሜትር ያላነሰ መሆን አለበት ይላል፣ ይህም ካልተሟላ የግንባታ ፈቃድ አይሰጥም ማለት ነው።

በዚህ ምክንያት በመቶ (ምናልባትም በሺዎች) የሚቆጠሩ ግንባታዎች እንዲቆሙ እየተደረገ ነው።

https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍23🤔114😭4👌1
🔶Advanced Structural Design

ST CHECK LISTS
እነዚህን መመዘኛ መስፈርቶች አሟልተን ነዉ ዲዛይን አሰገብተን  የምናስፈቅደው።
ለ 2 ወሩ Special Structural Design Package ስልጠና መጨረሻ ላይ እነዚህን በዝርዝር እንመለከታለን።

These are the checklists we will finally discuess for our 2months  special structural package course.
🔹Concrete Stru(Ordinary & High rise)
🔹Steel structure
🔸4 Software : Etabs, Sap, Safe
, Idea statica

https://www.tg-me.com/BeGetEngineering
👍144
2025/10/25 19:37:58
Back to Top
HTML Embed Code: