Telegram Web Link
ረቂቅ አዋጁ ፀደቀ

የህ/ተ/ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ረቂቅ አዋጁ፤ አዋጅ ቁጥር 1357/2017 ሆኖ በሁለት ተቃውሞና በአንድ ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል።

ዛሬ በምክር ቤት የፀደቀው ረቂቅ አዋጅ የሪል ስቴት አልሚ ድርጅት ያለደንበኛው ፍላጎትና ፈቃድ አጠቃላይ ግንባታው ቢያንስ 80 በመቶ ያልተጠናቀቀ ቤት ለደንበኞች ሊያስተላልፍ እንደማይችል አስቀምጧል።

በተጨማሪ በሪል ስቴት ልማት ላይ የሚሳተፍ ማንኛውም አካል የውሸት ማስታወቂያ ማስነገር እንደማይችልም አስቀምጧል።

የሪል ስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅ ምን ይላል ?

👉 የሪል ስቴት አልሚ የቦታና የተናጠል ይዞታ ማረጋገጫ አሰጣጥን በተመለከተ ፦

1) በከተሞች ለሪል ስቴት ልማት የሚውል ቦታ በሚከተለው አግባብ የሚቀርብ ይሆናል፤

ሀ. በአዲስ አበባ ከ5 ሺህ በላይ ቤት የሚገነባና የሚያስተላልፍ ወይም፤
ለ. እንደከተሞች ተጨባጭ የቤት ፍላጎትና ኢንዱስትሪ ፓርክ ያለበት አካባቢ ባለ ከተሞች ከ1 ሺህ በላይ ቤት የሚገነባና የሚያስተላልፍ ወይም፣
ሐ. ከነዚህ ባነሰ ስፋት ቤት ለሚፈልጉ ከተሞች ደግሞ 500 ቤት በላይ የሚገነባና የሚያስተላልፍ የሪል ስቴት አልሚ መሬት ቅድሚያ ተሰጥቶት በስፋት እንዲቀርብለት ይደረጋል።

2) የሪል ስቴት አልሚው የገነባውን ቤት በተናጠል ለቤት ፈላጊ በሽያጭ ለማስተላለፍ ግንባታው የተፈቀደለትን መስፈርት አሟልቶ 80 በመቶ ሲጠናቀቅ ለየቤቱ የተናጠል የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ እንዲሰጠው ሊጠይቅ ይችላል፤

👉 የሪል ስቴት አልሚ ግዴታዎች ምንድናቸው ?

የሪልስቴት አልሚ በውል ሰነዱ በህንጻ እዋጁ እና በሌሎች የህግ ማዕቀፎች የተመላከቱ ግዴታዎችን ማክበር እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪነት የሚከተሉት ግዴታዎች ይኖሩታል ፡-

1) ያለደንበኛው ፍላጎትና ፈቃድ አጠቃላይ ግንባታው ቢያንስ 80 በመቶ ያልተጠናቀቀ ቤት ለደንበኞች ሊያስተላልፍ አይችልም፡፡

2) በሪል ስቴት ልማት ላይ የሚሳተፍ ማንኛውም አካል የውሸት ማስታወቂያ ማስነገር አይችልም፡፡

3) ቤቶቹን ለመገንባት የሚያስችለውን የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ እና የግንባታ ፈቃድ ከሚመለከተው አካል ከመረከቡ በፊት ደንበኞችን መመዝገብና ቅድመ ክፍያዎችን መሰብሰብ አይችልም፡፡

4) በሕጋዊ መንገድ የተረከበው መሬት ሊያስተናግድ ከሚችለዉ የቤት ደንበኛ በላይ መመዝገብ አይችልም።

5) የመኖሪያ ቤት ገዢ ደንበኞች ማኀበር እንዲያቋቋም ያበረታታል ፤ የህንጻ መግለጫ ያስረክባል።

6) ከሚመለከተው የመንግሥት አካል የተሰጠውን የይዞታ ማረጋገጫ፣ የቤቱ የግንባታ ዕቃዎች ዓይነት፣ አርክቴክቸራል፤ ሳኒተሪ ፣ ስትራክቸራል እና ኤሌክትሪካል ዲዛይን፤ የግንባታ ፍቃድና የሪል ስቴት ልማት ፍቃዱን ቅጂዎች ከውል ሰነዱ ጋር አያይዞ ለደንበኛው መስጠት አለበት።

7) ደንበኛው ለከፈለው ገንዘብ ሕጋዊ ደረሰኝ መስጠት አለበት።

👉 ዋስትና ስለመስጠት ፦

የአገር ውስጥ አልሚ ቤቱን ሳይገነባ ለቤት ፈላጊዎች በቅድሚያ በሚሽጥበት ወቅት የሚከተሉትን የዋስትና ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት አለበት፡፡

1) የሪል ስቴት አልሚው በቤት ቅድሚያ ሽያጭ ስልት ለመስራት መፈለጉን አግባብ ላለው አካለ አሳውቆ ፈቃድ ማግኘት፡፡

2) ከቤት ገዥዎች የሚሰበስበውን ገንዘብ አግባብ ካለው አካለ ፈቃድ መሰረት በሚከፈተው የዝግ የባንክ ሂሳብ ገቢ ማደረግ ወይም ማስያዝ፣

3) የሪል ስቴት አልሚው በቅድሚያ መሽጥ የሚፈልገውን ቤት የመስሪያ ቦታ የይዞታ ማስረጃ ቤቱ ለተጠቃሚዎች ተገንብቶ እስከሚተላለፍ ድረስ በሚመለከተው አካል እንዳይሽጥ እንዳይለወጥ እንዲታገድ ማድረግ፤
📌 በዝግ የባንክ ሂሳብ ገቢ የተደረገው ገንዘብ የሚለቀቅበት ሁኔታ በደንብ ይወሰናል፡፡
አዋጁ ከላይ በ PDF ተቀምጧል።


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
ቀለም እና ህንጻ

💫After Image Effect

🚧በአረንጓዴ አካባቢ የሚሰሩ ሕንፃዎችን በዋናነት ቀይ ቀለም መቀባትን "After image effect" ተብሎ የሚጠራው የቀለም ሳይንስ መርህ ይፈቅዳል።

⭐️ዓይናችን ለረዥም ጊዜ አረንጓዴ ቀለምን ከተመለከተ አንጎላችን ሚዛናዊነትን (የቀለም ዲሞክራሲ እንበለው) ለመጠበቅ ተቃራኒው የሆነውን (Complementary) ቀይ ቀለምን መጠየቅ ይጀምራል።

በዚህም ሂደት ሁሉም መስራች የቀለም ዓይነቶች በ"Color field" ይገኛሉ ማለት ነው፤ አረንጓዴ ውስጥ ቢጫና ሰማያዊ ቀለማት አሉ፤ በዚህ ላይ ቀይ ሲጨመር መሠረታዊ ቀለሞች በሙሉ ተገኙ ማለት ነው።

❇️አንጎላችን ቀለማትን ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ነው የሚያስተናግደው።

🔰ከላይ ያለው ምስል የ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ነው።

Via Nita Color Centre


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አንድን ጨረታ የሚያሸንፈው ዝቅተኛ ዋጋ አቅራቢ ተጫራች ወይስ ከመሐንዲሱ ግምት ተቀራራቢ የሆነ ዋጋ ያስገባ ተጫራች?

💫ጨረታ ለተቋራጮች በሁለት አይነት መንገድ ሊፈጸም ይችላል:-

⭐️አንደኛ[1ኛ:- ግልጽ ጨረታ ሲሆን ማንኛውም ብቁ የሆነ፣ ህጋዊ ፍቃድ ያለው እና ፍላጎት ያለው ተቋራጭ መሳተፍ የሚችልበት በጋዜጣ ወይም በአካባቢው ባሉ የማታወቂያ መንገዶች ወይም በማህበራዊ መገናኛ ድረገጾች (website) ላይ በሚለቀቅ የተጫራችነት ግብዣ ጥሪ (Invitation to Tender) አማካኝነት ተጫራቾች ኩል ዕድል ተሰጥቷቸው እንዲሳተፉ የሚጋበዙበት ሂደት ሲሆን

⭐️ሁለተኛው[2ኛ:- ውስን ጨረታ የሚባል ነው። ውስን ጨረታ አንድ ተጋባዥ ወይም ውስን ቁጥር ያላቸው ልዩ መስፈርት የተሰጣቸው ተጫራቾች ጋር በሚደረግ ድርድር ወይም የመለያ ጨረታ አማካኝነት የሚከናወን የጨረታ አይነት ነው።



📄በግልጽ ጨረታ ሂደት ደግሞ አጫራቹ አካል ሁለት አይነት መንገድን ሊጠቀም ይችላል:-

🏷[አንደኛው] ፖስት ኳሊፊኬሽን (Post Qualification) የሚባል ሲሆን ሥራው ቀለል ያለ እና ማንኛውም ተጫራች ሊያከናውነው የሚችል ከሆነ ቅድሚያ ኢኮኖሚያው (የገንዘብ) መጠናቸውን መመዘን ነው።

በዚህ ሂደት ቅድሚያ ቅንሽ ዋጋ ያስገቡ ተጫራቾች ተለይተው እነዚያ ደግሞ በቴክኒካዊ ልኬት ተመዝነው አሸናፊ የሚለይበት መንገድ ነው።

🏷[ሁለተኛው] ፕረ ኳሊፊኬሽን (Pre-Qualification) የሚባለው ደግሞ ማንኛውም ተጫራች ቅድሚያ በቴክኒካዊ ልኬት ተመዝነው በኋላ በገንዘብ ዝቅተኛ ያስገባው አሸናፊ የሚሆንበት የጨረታ ምዘና መንገድ ነው።

በመሆኑ ይህ ሂደት በፌደራል የግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የወጣው መመሪያ ክፍል አምስት (5) ንዑስ ክፍል (1), (2) እና (3) ላይ በዝርዝር የተብራራ ነው።

🚧በመሆኑም በጨረታ ሰነዶች ምዘና (Bid Response Document Evaluation) ሂደት ላይ ተጫራቾት እንደጨረታ ሰነዱ አወጣጥ ተመስርቶ በቅድሚያ ዝቅተኛ ዋጋ ያስገቡትን በመምረጥ (Post Qualification ሂደትን በመከተል) በቴክኒካል ሰነዳቸው አXእናፊውን የሚለይበትን መንገድ ሊከተል ይችላል።

አልያም ደግሞ Pre-Qualification ሂደትን በመከተል ቅድሚያ የቴክኒካል ሰነዳቸው ታይቶ ብቁ የሆኑ ተጫራቾች ብቻ ተለይተው ዝቅተኛ ገንዘብ ባስገባ (Lowest bidder) የሚለዩበት መንገድ ነው።


ይህ ሁለቱም መንገድ በግል ፕሮጀክቶችም ይሁን በመንግሥት ፕሮጀችቶች ላይ ተግባራዊ ሊደረጉ የሚችሉና ህጋዊ እውቅና ያላቸው መንገዶች ናቸው።

ጨረታውን አከፋፈት በተመለከተ በ ክፍል 2 (2.2.1.5) ላይ እንደተብራራው ቃለጉባኤ ተይዞ፣ የጨረታውን አከፋፈት ሂደት ላይ ውይይት ከተካሄደባቸው ጉዳዮች በተጨማሪ ጨረታው ሲከፍተ የተገኙ ተጫራቾች ወይምህጋዊ ወኪሎቻቸው ስለጨረታው አከፋፈት ሂደት የሚያብራራ ቃለጉባኤ ላይ ስማቸውን እና ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይገባቸዋል።

አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የመሐንዲስን ግምት ያማከለ የጨረታ ሰነዶች ምዘና የሚካሄድበት አጋጣሚ አለ።

ይህም Federation Internationale Des Ingenieurs Conseil – FIDIC አንቀጽ 14 ላይ እንደተገለጸው ተጫራቾች መሐንዲሱ ገምቶ ያስቀመጠውን የግንባታ ዋጋ (Engineering Estimation of Construction Cost) እንደመነሻ በመቁጠር ተጫራቾች ከግምቱ በታች ከ20% በታችን የቀነሰ ዋጋ እንዳያስገቡ ወይም ከግምቱ በላይ ከ20% በላይ እንዳይጨምሩ ገደብ በማስቀመጥ ከዚህ እሳቤ ውጪ የሆኑትን የተጫራቾች ሰነዶች በመጣል በዚህ ክፍተተ (interval) ውስጥ ያሉትን ብቻ የማወዳደር ሥራ የሚሰሩበት መንገድ ነው።

ቢሆንም ግን ይህ አካሄድ ግምቱን ባወጣው መሐንዲስ (ግለሰብ) ጥንቃቄ እና እውቀት ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ብዙ ክፍተቶች የሚፈጠሩበት ቢሆንም  የፌደራል መንግስት የግዢ መመሪያ ቀድሞ በነበረው በዚህ አሰራር ላይ ግልጽ ማብራሪያ ሳያስቀምጥ አልፎታል።

መልካም ቀን! 🤚

https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በግንባታ ግዥ ዘርፍ ስራ ልምድ ወይንም ዓመታዊ ተርን ኦቨር አላሟላም ብለው ከጨረታ ተሳትፎ ለመውጣት ከመወሰኖ በፊት ይህንን ይንብቡ?

በፌደራል መንግስት እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥ መመሪያዎች ላይ ከተቀመጡ መሰረታዊ ጉዳዮች መካከል በግንባታ ግዥ ጨረታ ውድድር ላይ የስራ ልምዱ እና  ዓመታዊ ተርን ኦቨር ላይ በዶላር ምንዛሬ ለውጥ መሰረት የሚደረግ ማስተካከያ መኖሩ ሲሆን ይህም እንደሚከተለው ይሰላል።

1) ለጨረታ ግምገማ ዓላማ የሥራ ተቋራጩ በስራ ልምድነት እንዲያዝለት በሚያቀርበው የግንባታ ውለታ ዋጋ ላይ ማስተካከያ የሚደረግለት ሲሆን ይህም የሚሰላው ጨረታ ከሚቀርብበት የመጨረሻ  ቀን 28 ቀናት በፊት የነበረው የምንዛሪ ምጣኔን ውሉ በተፈረመበት  ጊዜ በነበረው የምንዛሪ ምጣኔ በማካፈል ከተሰላ በኋላ በሚገኘው ውጤት በማባዛት ነው።

2)በተመሳሳይም በጨረታ ግምገማ ጊዜ ለሚደረግ ማስተካከያ አላማ ለተርን ኦቨር ስሌት የሚወስደው ሥራ ተቋራጩ ያቀረበው አመታዊ የግንባታ ሥራ ተርን ኦቨር መጠን' ጨረታ ከሚቀርብበት የመጨረሻ ቀን 28 ቀን በፊት የነበረውን የምንዛሪ መጠን በእያንዳንዱ በጀት አመት የመጨረሻ ቀን ላይ ባለው የምንዛሪ መጠን በማካፈል ነው።

3) ሁለቱም ማስተካከያዎች የሚሰሉት የኢትዮዽያ ብሔራዊ ባንክ የሚሰጠውን የውጭ አገር ገንዘብ መሸጫ ዋጋ መረጃ መሠረት በማድረግ ይሆናል


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የመሬት መንቀጥቀጥ (Seismic load)

🏷የመሬት መንቀጥቀጥ በአንድ የግንባታ ንድፍ (በተለይ በስትራክቸራል ዲዛይን ሥራ) ሂደት ከግምት ውስጥ የሚገባ ከዋናዎቹ ጫናዎች (loads) መካከል ነው።

ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ ማባዣ (seismic factor) ለተለየያዩ አካባቢዎች የተቀመጠ ሲሆን ማብዣ ቁጥሩ የሚወሰነው ቀድሞ በነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ታሪክ (Historical records) መሰረት ነው።

በዚህ አግባብ በቀድሞው EBCS ምትክ የተቋቋመው በኢትዮጵያ የልኬት ኤጀንሲ (Ethiopian Standard Agency) በ2015 (እ.ኤ.አ) ለስትራክቸራል ዲዛይን ሥራ ከግምት ውስጥ እንዲገባ ባዘጋጀው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረትን በወሰነበት CES 160 ልኬት መሰረት ከፍተኛው የመሬት መንቀጥቀጥ ማባዣ አምስት (5) እንዲሆን ያረቀቀ ሲሆን ይህ ልኬት የተሰጣቸው አካባቢዎች፦

🏷1ኛ)፦ በአፋር ክልል፦ አፍዴራ፣ አርጎባ ልዪ፣ አሳይታ፣ አዋሽ ሸለቆ፣ ዳልፋጊ፣ ዱብቲ፣ ዱሌቻ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ ሀደሌላ፣ ሰመራ፣ ሰሙሮቢና ገላሎ

🏷2ኛ)፦ በአማራ ክልል፦ አንኮበር፣ አንጾኪያ ገምዛ፣ አርቱማ ፉርሲ፣ ባሶና ወራና፣ መንዝ ግሼ፣ ጅሌ ጥሙጋ፣ ቀወት፣ መንዝ ጌራ፣ መንዝ ማማ፣ ሞጃና ወደራ፣ ወይን አምባ፣ ጣርማ በር ናቸው።

⭐️በእነዚህ አካባቢዎች ዙሪያ ያሉ አካባቢዎች የሀገሪቱ ስምጥ ሸለቆ ዞኖች ስለሆኑ ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት የሚስተዋልባቸው ናቸው።

ነገር ግን በዚህ ሰሞን የሚስተዋለው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት በሬክታል ስኬል እስከ 5.2 የደረሰ መሆኑ ተዘግቧል።

ይህ ማለት የሀገሪቱ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ልኬት ከተቀመጠው ስታንዳርድ  ያለፈ ሆኖ የተመዘገበ ታሪክ ስለሆነ የስታንዳርድ (standard) ማስተካከያ ሊያስፈልገን ነው ማለት ነው።


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ማንኛውም ጨረታ ቴክኒካል እና ፋይንናሻል ፕሮፖዛል ከማዘጋጀት በፊት የሚከተሉትን ማድረግ እጅግ ጠቃሚ መሆናቸውን ልብ ይበሉ

1. ጨረታውን  ያወጣው ተቋም ያዘጋጀውን ጨረታ ሰነድ በጥልቀት ማንበብና መረዳት

[ምንም እንኳ አብዛኛው ተቋም PPA 2011 Standard Bidding Document ተጠቅሞ ወይም እንደ ግዥው በጀት ምንጭ አለም አቀፍ አበዳሪ ተቋማት ስታንዳርድ ጨረታ ሰነዶችን ተጠቅሞ የሚያዘጋጅ ቢሆንም እንኳ በጨረታ ሰነዱ የሚገኙ የተለያዩ ክፍሎች እንደየፕሮጀክቱና ተቋሙ ሁኔታና መረዳት የሚሞሉ እንደመሆናቸው የተዘጋጀውን ሰነድ ገዝቶ በግዥ ላይ በሰሩና ልምድ ባላቸው ባለሞያዎች በዝርዝር ማየት አስፈላጊ ነው]


2. የጨረታ ሰነዱን ገዝተን በዝርዝር ካየን በኋላ አሻሚ የሆኑ፣ ግልጽ ያልሆኑ እና መካተት የነበረባቸው የቀሩ ሰነዶች  አሉ ብለን ካሰብን፤ ጨረታውን ላወጣው ተቋም ማብራሪያ መጠየቅ አለብን

[ ማብራሪያን በተመለከተ እንዴት እና የት እንደሚጠየቅ የጨረታ ሰነዱን ክፍል አንድ ወይም ሁለት ላይ መመልከት ይኖርብናል። ይህንን ጥያቄ መሰረት አድርጎ ጨረታውን ያወጣው ተቋም ማብራሪያ መስጠት ይኖርበታል]


3. በግዥ/ጨረታ ላይ ልምድ ያለው ባለሙያ  የቴክኒካልና ፋይናንሻል ፕሮፖዛል ዝግጅቱን እንዲያከናውን ማድረግ፤


4. ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉን ቅጾች/forms/ በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገኙ መሆናቸውን በማረጋገጥ እነሱን ተጠቅሞ ማዘጋጀት ይገባል። ከዚህ በፊት ከተጠቀምናቸው ቅጾች ሊለዩ ስለሚችሉ በጥንቃቄ መረዳትና ማየቱ ተገቢ ነው።


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ጨረታ ውድቅ ሊሆንባቸው የሚችሉ ምክንያቶች

⚡️ጳጉሜን 4 ቀን 2016 ዓ/ም የወጣው የፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር 66 "የፌደራል መንግሥት ግዢና ንብረት አስተዳደር አዋጅ (PPPAA - Federal Public Procurement and Property Administration Proclamation) ቁጥር 1333/2016 ስለግዢ የተደነገገ ሕግ ነው።

በዚህ ህግ አንቀጽ 26 ላይ "ጨረታን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ውድቅ ስለማድረግ" የፈቀደ ሲሆን ይህንን ለማድረግ ያስቀመጣቸው ምክንያቶች፦

~ በግዢ አፈጻጸም ውጤት የሚያዛባ ስህተት ካገኘ
~ የተሻለ የሥራ ወይም ኢኮኖሚያዊ ወይም ማህበራዊ ጥቅም ካገኘ
~ የቀረቡት ተጫራቾች የጨረታውን ዝቅተኛ መስፈርት የማያሟሉ ከሆነ
~ የቀረበው ዋጋ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ካጠናው የገበያ ዋጋ ከፍተኛ ልዩነት ካለው
~ በጨረታው ያሸነፈው አካል ያስገባው ዋጋ ለጨረታው ከተያዘለት በጀት በላይ ከሆነ
~ ተጫራቾች የጨረታ ሂደቱን ለማዛባት እንደተመሳጠሩ የሚያሳይ መረጃ ካለ

በእነዚህ ምክንያት ጨረታ ያወጣው አካል ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ሊሰርዝ ይችላል ነገር ግን በዚህ ህግ መሰረት ጨረታው ከተሰረዘ ምክንያቱን የሚገልጽ ማስታወቂያ ለተወዳዳሪዎች  ማሳወቅ ይኖርባቸዋል በተለይ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በዚህ መሰረት ጨረታን ውድቅ ቢያደርጉ ተጠያቂ አይሆኑም።


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
መንግሥት በራሱና በውጭ ተቋራጮች ግንባታዎችን በመቆጣጠሩ የግል ሥራ ተቋራጮች ከሥራ ውጪ መሆናቸውን አስታወቁ‼️

መንግሥት የመንገድና የሕንፃ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት የራሱን የግንባታና የዲዛይን ድርጅቶች በማቋቋም፣ ፕሮጀክቶችን መያዙና የተቀረውን ለውጭ አገር የሥራ ተቋራጮች እየተሰጠ መሆኑ፣ የአገር ውስጥ የግል የሥራ ተቋራጮች ከሥራ ውጪ መሆናቸውን አስታወቁ።

ይህ የተገለጸው የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከግሉ የግንባታ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ባለፈው ሳምንት ባደረገው የምክክር ጉባዔ ላይ ነው።

ሚኒስቴሩ የአገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮች በአሥር ዓመታት ውስጥ በአገር ውስጥ ያላቸውን የገበያ ድርሻ ወደ 75 በመቶ፣ በቀጣናው ደግሞ የ25 በመቶ ድርሻ እንዲያሳድጉ ዕቅድ ቢይዝም፣ የሥራ ተቋራጮች በበኩላቸው መንግሥት በውጭ ተቋራጮች ላይ ያለውን ከፍተኛ ጥገኝነት፣ የክፍያዎች መዘግየት፣ በቅርብ የተካሄደው የኢኮኖሚክ ሪፎርም በኢንዱስትሪው ላይ ያሳደረውን ጫናና ሌሎችም ማነቆዎችን በማንሳት፣ መንግሥት በእርግጥ ኢንዱስትሪውን ያውቀዋል ወይ? የሚል ጥያቄ አንስተዋል።

አቶ ሀብታሙ ጌታቸው የተባሉ ተሳታፊ፣ መንግሥት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢንዱስትሪውን በብቸኝነት ወደ መቆጣጠር እያመራ ነው ሲሉ ወቅሰዋል።

‹‹ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያው ከመሰላቸትምም ተነስቶ ሊሆን ይችላል፣ ግን በመንግሥት በኩል ኢንዱስትሪውን በብቸኝነት የመያዝ ሒደት ነው እያየን ያለነው። መንግሥት የራሱን የዲዛይን፣ የኮንስትራክሽን ተቋማት እያደራጀና እያዘጋጀ ነው። ስለዚህ ፕሮጀክት ሲመጣ ራሱ ዲዛይን ያደርጋል፣ ራሱ ግንባታ ይፈጽማል፣ በጣም ከእሱ አቅም በላይ የሆነውን ለውጭ ኩባንያዎች ይሰጣል። ስለዚህ ለግሉ ዘርፍ ቦታው ባዶ ነው ብዬ ነው የምገምተው፤›› ብለዋል።

በሌላ በኩል በምክክር መድረኩ የቀረቡ ሁለት ጥናቶች፣ በአገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮች የሚገነቡ መንገዶች በ143 በመቶ፣ ሕንፃዎች ደግሞ በ110 በመቶ ከተያዘላቸው ጊዜ አሳልፈው እንደሚጠናቀቁ፣ ከተያዘላቸው በጀትም እንዲሁ የመንገድ ፕሮጀክቶች በ18 በመቶ፣ ሕንፃዎች ደግሞ በ35 በመቶ እንደሚያሳልፉ አመላክተዋል።

ከሚኒስቴሩ በኩል ጥናት ያቀረቡት ባለሙያ፣ ‹‹ከዚህ ጥናት በኋላ በፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስተባባሪነት በተደረጉ የፕሮጀክቶች ክትትል በብዙ ፕሮጀክቶች እያንዳንዱ እየተነጠለ ሲታይ የጭማሪዎቹ መጠን ከዚህም በላይ እንደሆነ ማየት ተችሏል፤›› ብለዋ።

ሳሙኤል ሳህለ ማርያም (ኢንጂነር) የተባሉ ጥናት አቅራቢ በበኩላቸው፣ የውጭ ኮንትራክተሮች የሚይዙት ግንባታ መጠን አነስተኛ ሆኖ፣ ነገር ግን የሚይዙት የገበያ ድርሻ እስከ 62 በመቶ እንደሚደርስ አሳውቀዋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞም ያሉ ሥጋቶች ላይ ማብራሪያ ሲሰጡ፣ ‹‹የግንባታ ዘርፉ አሁንም ትልልቅ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ትልቁን ድርሻ የያዙት የውጭ ሥራ ተቋራጮች ናቸው።
ይህንን ልንቀይርበት የምንችልበት አካሄድ እስካልተፈጠረ ድረስ አሁን በቅርብ ይህ ንግድ ለዓለም የንግድ ድርጅት ክፍት ነው የሚሆነው። ስለዚህ እኛ ምን ይዘን ነው የምንቀላቀለው? ምን ይዘን ነው ለውድድር ልንቀርብ የምንችለው? በዚህ ሁኔታ ከሆነ የምንቆየው ሁላችንም ተበልተን ነው የምናልቀው፤›› ብለዋል።

በሚኒስቴሩ በኩል የቀረቡት ባለሙያ የውጭ ተቋራጮች ጉዳይ እስከ ሉዓላዊነት የደረሰ ችግር ሊያስከትል ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ ያሉት የአገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮችና አማካሪ ኩባንያዎች 35 ሺሕ መድረሳቸውን፣ የባለሙያዎች ብዛትም 151 ሺሕ መሆኑን ጠቅሰዋል።

‹‹በቁጥር ይግዘፍ እንጂ በፌዴራልም ሆነ በክልል ደረጃ የመንግሥት ሜጋ ፕሮጀክቶች በብዛት የተያዙት በሚያሳዝን ሁኔታ በውጭ ኮንትራክተሮች ነው። መጀመሪያ የአገራችንን 75 በመቶ ይዘን የቀጣናውን 25 በመቶ ገበያ ለመያዝ ነው ዕቅዳችን። እነዚህ ቁጥሮች ሳይሆኑ እኛን የሚታደጉን ሄዶ ሄዶ ጉዳዩ የሉዓላዊነት ጉዳይ ጋር ይመጣል፤›› ብለዋል።

ሳሙኤል (ኢንጂነር) የውጭ አገር የሥራ ተቋራጮች ከዚህም ባሻገር ከበጀት ጋር የተያያዙ ጫናዎች እየፈጠሩ መሆናቸውን አሳውቀዋል።

‹‹አንድ በውጭ ተቋራጭ የሚሠራ በጀቱ 800 ሚሊዮን ብር የነበረ ፕሮጀክት፣ ግንባታውን በመሀል አቁመው 3.2 ቢሊዮን ብር ካልከፈላችሁን አንሠራም ማለታቸውን እናውቃለን። ቦሌ ክፍለ ከተማ የሚሠራው ስታዲየምን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ፕሮጀክቱ ሲጀመር በጀቱ ከሁለት ቢለዮን ብር ጥቂት ነበር ከፍ የሚለው። ግን በኋላ ላይ እስከ 12 ቢሊዮን ብር አይበቃም ማለታቸውን ሰምተናል፤›› ብለዋል።

ባለሙያው ይህ ዓይነቱ አሠራር ለአገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮች እንደማይሠራ ገልጸው፣ ኩባንያዎች፣ ከባንኮች ከግንባታ ዕቃ አቅራቢዎች ጋር ተያይዞ ሊሠራበት የሚችልበት ሁኔታ እንደሌለ ገልጸዋል።

የውጭና የአገር ውስጥ ተቋራጮች አፈጻጸምን በተመለከተ ለአብነት የቻይና ተቋራጮችን አፈጻጸም ያነሲ ሲሆን፣ ፕሮጀክቶችን በሚያገኙበት ወቅት ዕቃ አቅራቢ ፋብሪካ አዘጋጅተው፣ አማካሪ ኩባንያው የራሳቸው አገሮች ኩባንያ መሆኑንና ንዑስ ተቋራጮችም በራሳቸው እንደሚያዘጋጁ ጠቅሰው፣ የቻይና ኤግዚም ባንክ እዚህ ለሚሠሩ ሥራ ተቋራጮች የገንዘብ ፍሰት (Cash Flow) ችግር እንዳያጋጥማቸው እንደሚያቀርብላቸውና በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ የሚያልፍ የውጭ ተቋራጭ በተገቢው ሁኔታ ሥራውን አከናወነ እንደሚባል ተናግረዋል።

‹‹የእኛ ሥራ ተቋራጭ እኮ በክፍያ ምክንያት የሚያጋጥመው ጫና ምናልባት መንግሥትና ዘርፉ የእውነት ይተዋወቃሉ?› የሚል ጥያቄ እንዳነሳ ነው የሚያደርገኝ። የእውነት ይተዋወቃሉ ወይ? ዘርፉ እኮ እየሞተ ነው ያለው። ክፍያ በአግባቡ ካልተከፈለው የፕሮጀክት ቆይታ በከፍተኛ ሁኔታ ነው እየጨመረ የሚመጣው። ስለዚህ ይህንን ክፍተት መሙላት የሚያስችል የፋይናንስ ሲስተም ያስፈልጋል፤›› ብለዋል።

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ የትምጌታ አሥራት በበኩላቸው፣ መንግሥት ፕሮጀክቶችን ለአገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮች ለማስተላለፍ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል በውይይት መድረኩ ከተነሱ ዋነኛ ጉዳዩች የውጭ ምንዛሪ ላይ የተደረገው ሪፎርም በኢንዱስትሪው ላይ ሌላ ጫና ይገኝበታል።

‹‹የኢንዱስትሪው ገበያ የሚንቀሳቀሰው በጥቁር ገበያው ነበር፡፡ እዚህ ላይ ምንም ልንወሻሽ የሚገባ ነገር የለም። ለምን አንድ አቅራቢ ዕቃ ከውጭ አምጥቶ ለመሸጥ ለሒደት ማስፈጸሚያ (Procedure Issue) ብቻ የባንክን ምጣኔ ይጠቀማል። ለምሳሌ 60 ብር በነበረበት ሰዓት ለፕሮሲጀር የባንክን ይጠቀማል፡፡ ሌላውን ግን በጥቁር ገበያ ሴኪውር ያደርጋል። ከዚያ በኋላ ግን ዋጋ ሲያወጣ በጥቁር ገበያው ምጣኔ ነው የሚያወጣው፡፡ በዚህ ምክንያት የፕሮጀክት ዋጋ ከፍ ይላል፤›› ብለዋል።

በተጨማሪም፣ ‹‹ምንዛሪ በገበያው መወሰን ሲጀምር በፊት ግብር የሚከፍል የነበረው ባንክ በሰጠው ምጣኔ ነበር። ለምሳሌ ምንዛሪው ሰባት ብር ከነበረ፣ አሁን ግን 125 ሲሆን ግብሩም በዚያው መጠን ከፍ ይላል ምክንያቱም በደረሰኝ ገንዘቡን ዝቅ አያደርግም።

እንደነዚህ ዓይነት ዕርምጃዎችን እንዳይሄድና ኃላፊነት እንዲወስድ ብሔራዊ ባንክ አስገዳጅ መመርያ አውጥቶበታል። ያንን ስናይ ደግሞ ከኢንሹራንስና ከትራንስፖርት ጋርና ከሌሎች ሎጂስቲክስ ጉዳዮች ጋር የተገናኙ የወጪ ክፍያዎች አሉበት። ስለዚህ በኢኮኖሚክ ሪፎርሙ የኮንስትራክሽን ዘርፉ አሁንም እንደገና ደግሞ ሌላ ተጋላጭነት አጋጥሞታል፤›› ሲሉ አብራርተዋል።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ከመንግሥት ጋር ከተያያዙ ተግዳሮቶች ባሻገር ተቋራጮች በራሳቸው ደካማ የሆነ የውል አስተዳደር (Contract Administration) ትግበራ እንዳላቸውም ተጠቅሷል።
ሳሙኤል (ኢንጂነር)፣ ‹‹ለምሳሌ የዋጋ ማስተካከያ ይፈቀድልን በሚል ገንዘብ ሚኒስቴር ሲጠየቅ፣ ‹ማን ከለከላችሁ?› የሚል ጥያቄ ሲያነሳ፣ የከለከለን አማካሪው በልዩ ሁኔታ (Special Condition) በማስፈረም መሆኑን ሲገልጹ፣ ገንዘብ ሚኒስቴር እንደዚህ ያለ ውል ማን ፈርሙ አላችሁ? ብሎናል። የእኛንም ችግር ራሳችን መውሰድ መቻል አለብን። ግን ፍፁም የተከለከለ አይደለም። በፊት የ12 ወር ተባለ አሁን የ18 ወር ሆነ፣ ከዚያ ውጪ ግን ሙሉ ለሙሉ ይህ ፕሮጀክት ይህንን አያካትትም ብሎ መከልከልን ያመጣው በደካማ ውል አስተዳደር ትግበራችን ችግር ነው፤›› ብለዋል።

ከዚህ ባሻገር የአገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮች የግንባታ ጥሬ ዕቃ ከውጭ አገሮች ለማስመጣት፣ ከፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ ከ40 እስከ 60 በመቶ የሚሆነውን ያህል ገንዘብ የሚያወጡ ቢሆንም፣ ግዥ ለመፈጸም የሚዋዋሉት አገር ውስጥ ካለ አስመጪ ድርጅት ጋር በመሆኑ፣ ዕቃዎቹ ወደ አገር ውስጥ የሚገባበት ጊዜ ፍጥነት አስተማማኝ አለመሆኑን ጥናቶቹን ያቀረቡት ባለሙያዎች አስረድተዋል። (Reporter)


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
በሀገራችን_በህንጻ መዋቅር ጥናት ውስጥ ጥቂት ስለ Seismic (Earthquake) ታሳቢነት

ይህ ጽሁፍ የተዘጋጀው  ወቅታዊው የመሬት መንቀጥቀት ያሳደረብንን ስጋት አንጻር ጥቂት ለማለት ነው።

በሀገራችን ራሱን የቻለ የዲዛይን ኮድ አለን ካሉን የዲዛይን ኮዶች መካከል አንዱ ስለ Seismic Design የሚንመራበት ES EN 1998-1:2015 Design of Structures for Earthquake Resistance የሚለው ይገኝበታል።

የመዋቅር ዲዛይን የሚሰራው ባለሙያም ዲዛይኑን የሚያጸድቀውም መኮንን በዚሁ  መሰረት ዲዛይን ተሰርቶ ወደ ግንባታ እንዲገባ ፈርመው ይሰጣሉ።

ገንቢውም በዚህ ተመስርቶ እንዲገነባ ይጠበቅበታል።

የህንጻ መዋቅር ዲዛይን ታሳቢዎች
በመዋቅር ዲዛይን ታሳቢ የሚደረጉ ጭነቶች (Action loads) መካከል መሰረታዊ የሚባሉት Dead load, Live load Wind Load እና Seismic actions ሲሆኑ እንደ ሁኔታው እየታየ የተዘረዘሩት loadዎች በጋራ የሚያመጡት ጉዳት ከግንዛቤ የሚያስገባ እንደ አስፈላጊነቱ ከ 100 load combination ይሰራል።

ወደ መሬት መንቀጥቀጡ ስንገባ ለህንጻ ዲዛይንም በሬክተር ስኬል እየተለካ ሳይሆን ቀድሞ በተጠና አካባቢያዊ ተጠባቂ ሁኔታ የተከፋፈሉ ዞኖችን ታሳቢ አድርጎ በዚያ አካባቢ የሚጠበቀውን ከፍተኛ የምድር እንቅስቃሴ (Peak Ground Acceleration)  ታሳቢ በማድረግ በተሰሩ ቀመሮችና ለመቀመሪያ በተዘጋጁ Software በመታገዝ ነው።

ወደ ዲዛይን ታሳቢዎች ስንገባ

፩) ህንጻው የሚገባበት አካባቢ ለመሬት መንቀጥቀጥ ያለው ተጋላጭነትን ያገናዘበ ዞን (Seismic Zone) ( አዲስ አበባ ዞን 3 ሲሆን የሰሞኑ የአብዛኛው መሬት መንቀጥቀጥ መነሻ አፋር ክልል ብዙው ዞን 5 ነው)

፪) እያንዳንዱ ህንጻ ስንመለከተው በአርማታ በመሰራቱ ግትር ቢሆንም የመሬት መንቀጥቀጥን ለመከላከል እንዲችል የተወሰነ ያክል ተለማጭ እንዲሆን የሚያስችል ስሌት (Elastic Analysis) ይሰራለታል።

፫) የህንጻው መሰረት የሚያርፍበት የመሬት (አፈር/አለት)
ሁኔታ ( Ground Type) ታሳቢ ይደረጋል።

፬) የሚገነባው ህንጻ መዋቅር ዓይነት ( Structural Type and Behavioral Factor) የጥናቱ አካል ነው።

፭) የህንጻው ቅርጽና ቁመና (Structural Regularity) ከግምት ውስጥ ይገባል።

፮) የህንጻው መዋቅር አካላት Beam, Slab, Column, Wall, Number of Story, Number of Bays እና Foundation Types በልዩ ሁኔታ ታሳቢ ይደረጋሉ።

፯) ለግንባታ የምንጠቀማቸው ቁሶችና ጥራታቸው ( በተለይ የአርማታ የብረት ) በየመስፈሪያቸው የዲዛይኑ ግብዓት ሆነው ያገለግላሉ።

⭐️ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ታሳቢዎች ታክለው በተሰራው የኮምፒውተር ሞዴል በሚሰጣቸው ከመቶ በላይ load combinations የከፋ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉትን እንዲቋቋም ተደርጎ ፣ የተለያዩ ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸው Modifier Factors ተካተው፣ የ Stability Check ተደርጎ የስትራክቸራል ዲዛይን ድሮዊንግ ይሰራል።

ለምን እንንቀጠቀጣለን?

እንዲህ ተሰርቶ ለምን እንንቀጠቀጣለን? ለሚለው መልሱ ከላይ የዘረዘርኩት ማስረጃዎችን ታሳቢ ተደርጎ ከተሰራ ዲዛይን ላይ ሶስት ሞዴሎች ተያይዘዋልና ተመልከቷቸው።

እንቅስቃሴዎቹ በተለያዩ load combinations ህንጻው ራሱን ሲከላከል የሚያሳይ የትክክለኛ ዲዛይን animation ነው።

ይህ እንቅስቃሴ በአይናችን ልናየው ባንችልም የተሰቀሉ መብራቶች ሲንቀሳቀሱ፣የተቀመጠ ዕቃ ሲወድቅ፣ የተከፈተ መስኮት/በር ሲዘጋ...እንመለከታለን እኛም ህንጻው ላይ እንደተቀመጡት ዕቃዎች ንዝረቱ ይሰማናል እንጂ የህንጻውን እንቅስቃሴ ልንመለከት አንችልም ግን እየተንቀሳቀሰ ነው።

ህንጻው ተንቀሳቀሰ ማለት ዲዛይኑ ትክክል አይደለም ማለት ወይም ይፈርሳል ማለት አይደለም። ዲዛይን በተደረገው ሞዴል መሰረት እራሱን እየተከላከለ ነው።

💫ምን ያሰጋናል?

፩) የግንባታ ጥራት
፪) ከዲዛይን ውጪ የተጨመሩ ወለሎች ያሏቸው ህንጻዎች
፫) የመሬት መንቀጥቀጥ የሚነሳባቸው አካባቢ ያሉ ቤቶች
፬) ሳይት ላይ መዋቅሮች የተደረጉ ማሻሻያዎች
፭) በተኛንበት ወይም በተቀመጥንበት የተንጠለጠሉ ቁሶች አናታችን ላይ ወድቀውብን አደጋ እንዳያደርሱብን!

Via ደሳለኝ ከበደ ህንጻ መሀንዲስ፣ ገንቢ፣ ሪል ስቴት አማካሪ


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የአፈር ጥቅጠቃ (Fill or Embankment)

በሀገራችን የቀድሞው ባትኮዳ (Building and Transport Construction Design Authority - BaTCoDA) Specification እና በ 'AASHO T147' መሰረት የአፈር ጥቅጠቃ ወይም መረምረም በተቆጣጣሪው መሐንዲስ የጸደቀ ግብአት መሆን ያለበት ሲሆን፦

1ኛ) ቢያንስ 95% የመጠቅጠቅ ብቃትን (95% compaction) ያሟላ መሆን አለበት

2ኛ) የጥቅጠቃ ሥራው ቢበዛ ከ20 ሳንቲሜትር ባልበለጠ የንጣፍ ውፍረት (not ecmxceeding 20cm layers) መጠቅጠቅ አለበት

3ኛ) እያንዳንዱ ንጣፍ በቂ ውሃ እየጠጣ መጠቅጠቅ (watered compaction) አለበት


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
መሀንዲስ ስራ ለመቀጠር ሲሄድ የሚጠየቃቸው ጥያቄዎች እና መልሶች?

1. የስላምፕ ቴስት ውጤት ምን ይነግርሀል?
ኮንክሪታችን ምን ያህል ፈሳሽ እና ወጥ እንደሆነ ፣water- cement ratio ከፍተኛ እንደሆነ እና እንዳልሆነ፣ የ batchingኣችንን ጥራት እና ወጥነት የስላፕ ቴስት ውጤት ይነግረናል፡፡


2. ካሊፐር ምንድነው?
ስፋት፣ውፍረት ፣ጥልቀት እና ወርድ የምንለካበት መሳሪያ ሲሆን በ ኮንስትራክሽን የ 6.ሮ diameter እና ለ ስቲል ሴክሽን ውፍረት ምንለካበት ነው።


3. C25 ምን ማለት ነው?
አርማታው ከተሞላ በ 28 ቀን የመኖረው የ 25 ሜጋፓስካል (25MPa) 99% የመኮማተር አቅም Characteristics compressive strength (fck)


4. ህንፃ ስንሰራ ፌሮ አስተዋፅኦ ምንድነው?
(deformable bar)RC (reinforced concrete) structure የ Tensile stressን ለመቆጣጠር ፌሮ እንጠቀማለን እንደየ ስትክቸሩ የተለያዩ አገልግሎቶች አሉት ለምሳሌ ቢም ላይ ለ tension zone ላይ እንጠቀማን ለ ሺር (ስታፋ) እንጠቀማለን፣ መሬት ላይ ለምንሰራው (Ground supported slab) minimum rebar a temperature (ሙቀት ሲያጋጥመው እንዳይሰነጠቅ) እንጠቀማለን።

Tiktok

https://www.tiktok.com/@ethiocons

እናመስግናለን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ባለ ፌሮ አርማታ (RC) የምናረገው ሁለት ነገሮችን ለመቋቋም ነው

1. መኮማተርን(compression)
2. መለጠጥን (tension)

ፌሮ የመለጠጥ ጥንካሬ አለው ductile property አለው ስለዚህ ሲለጠጥ እና deform ሲያረግ ጊዜ ይወስድበታል

አርማታ ደግሞ የ መኮማተር ጥንካሬ አለው ለመለጠጥ ከጠጋለጠ ወዲያው ይቀነጠሳል ለምን ቢባል brittle ስለሆነ

ስለዚህ አርማታ በዝቶ ብረት ካነሰ tensile failure occur ያረጋል በተቃራኒው ደግሞ ብረት በዝቶ አርማታ ካነሰ compression failure በዚህ ግዜ ፈጠን ያለ ምላሽ እናገኛለን ከ tensile failure አንፃር።
ስለዚህ Balanced የሆነ structure design ማረግ አለብን።

Tiktok

https://www.tiktok.com/@ethiocons
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የሲሚንቶ ቤተሙከራዎች »
  { Cement Tests }


A) የመኮማተር ጥንካሬ (Compressive Strength)፡-

ይህ ምዘን ሲሚንቶ ከደረቀ በኋላ ያለምንም መኮማተር  ወይም መፈረካከስ የሚተገበርበትን ክብደት የመሸከም አቅሙን የምንለይበት ነው።

በመሆኑም ሲሚንቶው ምን ያህል ክብደትን ወይን ጭነትን (loads) የመቋቋም አቅም እንዳለው የምንለይበት ነው።

B) የመለጠጥ ጥንካሬ (Tensile strength)፡


ይህ ሙከራ የሲሚንቶን የመለጠጥ ጥንካሬን የምንመዝንበት ሲሆን ለጭንቀት ሊጋለጥ ለሚችልበትን የጭነት ትግበራ ለማወቅ ጠቃሚ ነው።

C) ጤናማነት ፍተሻ (Soundness):  ይህ የምዘና ሥራ ሲሚንቶ ከውሃ ጋር ሲዋሃድ የሚኖረውን የመጠን ለውጥ እና መሰነጣጠቅን ለመቋቋም ያለውን ክህሎት (ጥንካሬ) የምናይበት ነው።

D) የመጠንከሪያ ሰዓት (Setting Time)፡

ይህ ሙከራ ሲሚንቶ የሚጠበቅበትን ጥንካሬ  የሚይዝበትን ወይን የሚደርቅበትን የሰዓት መጠን (ለማጠንከር የሚፈጀውን ጊዜ) ለማወቅ የሚደረግ ምዘና ነው።

ይህ ሂደት የቀረበው የሲሚንቶ አይነት ልንጠቀምበት ላቀድነው የሥራ ክፍል (application to intended works) ተስማሚ የሆነ የመጠንከሪያ ጊዜ መሆኑን ለመለየት ይጠቅማል።

E) ጥቃቅንነት ወይም ልመት (Fineness): 

ይህ የሲሚንቶ ቤተሙከራዊ ምዘና የሲሚንቶውን ቅንጣት መጠን (particle size) ለመወሰን የምንሰራው ሲሆን ከውሃ ጋር የመዋሐድ (hydration) ምጣኔን እና በውኅደት ሂደት የሚኖረውን ጥንካሬ እድገት የምንለካበት ነው።

F) ከውሃ ጋር የሚዋሃድበትን የሙቀት መጠን (Heat of Hydration)

ይህ የምዘና ሂደት ሲሚንቶ ከእርጥበት ወይም ከውሃ ጋር ለሚያደርገው አጸግብሮት የሚያስፈልገውን የሙቀት መጠን ለማወቅ ይጠቅማል። ይህ ፍተሻ በእርጥበት ሂደት ውስጥ የሚፈጠረው ሙቀት በሲሚንቶው ላይ ስንጥቅ ወይም ሌላ ጉዳት እንዳይደርስበት መጠኑን ለመወሰን ወይም ለማረጋገጥ ጠቃሚ ነው።

G) የኬሚካል ይዘት (Chemical Analysis)፡ ይህ ሙከራ ሲሚንቶው የተመረተበትን የኬሚካል ስብጥር ለማወቅ የሚጠቅም ሲሆን በውስጡ ያሉ ኬሚካሎችና መጠናቸው ለሚፈለገው ሥራ ተስማሚ መሆኑንና አለመሆኑን ወይም የኬሚካል መመዘኛዎች የሚያሟላ መሆኑን እና ምንም ዓይነት ጎጂ ንጥረ ነገሮችን እንደሌለው ለማረጋገጥ ጠቃሚ ነው።


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የኮንስትራክሽን ጨረታ በተመለከተ!

⚡️ውድ የቻናላችን ቤተሰብዎች

በአሁን ሰዓት ብዙ ኮንትራክተሮች ከ technical ግምገማ ውጪ እየሆኑ እናያለን የ ቻናላችን ቤተሰቦች በሰበሰቡት መረጃ መሰረት አንዱ ምክንያት የግዢ አዋጁ ከደነገገው መመሪያ በላይ requirement ስለሚቀመጥ ነው።


ለምሣሌ የግንባታ የተሻሻለው መመሪያ ላይ ስለ turnover እንዲህ ያስቀምጣል:-

👌ለሀገር ውስጥ ተጫራቾች peak annual turn over እንዲያዝ ሲያዝ ለውጪ ተቋራጮች ደግሞ average turnover  እንዲያዝ ያዛል ነገር ግን የሀገር ውስጥ ተቋራጭ average ባለሟሟላቱ ውድቅ ይደረጋል።

Turnover amount የሚሰላው የሚገነባው ፕሮጀክት ዋጋ ለሚፈጀው ወራት በማካፈልና በ12 በማብዛት ሲሆን አንድ ፕሮጀክት engineering estimation 100 million ሆና duration 3 አመት ቢሆን መጠየቅ ያለበት peak 33.3 million birr ለሀገር ውስጥ ተቋራጭ እና 100 million ለውጪ ተቋራጭ እንደ ማለት ነው።

👌ስለዚህ የ ቻናላችን ቤተሰቦች ጨረታ ሲገዙ ይህንን አዋጅ በመጥቀስ clarification እየጠየቁ ቢሞሉ ጨረታውን የማለፍ እድልዎ እንደሚጨምር እየገለፅን ተመሳሳይ አስተማሪ የሆኑ መልእክቶችን ለወደፊቱ እናሳውቃለን።


እናመስግናለን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2025/06/29 17:25:09
Back to Top
HTML Embed Code: