Telegram Web Link
የብዙዎች ጥያቄ የሆነው ተሰርቶ ያለቀ ጣራ የጣራ ክዳን EGA quantity በAutocad ቀለል ባለ መልኩ እንዴት ሰርተን ማዘዝ እንዳለብን የሚያሳይ screenshot ነው።

በተለይ ለጀማሪ የሳይት መሀንዲሶች ጠቃሚ ነው።
እንበልና ተሰርቶ ሞራሌ ተመቶ ያለቀ የአንድ ቪላ የጣራ ልባስ ቆርቆሮ roof tiles  ለማልበስ ፈልገን ከሆነ እንደምትመለከቱት ሁሉንም የጣራው section sketch አድርገን actual measurement ከወሰድን በኋላ የያዝነውን መረጃ በአውቶካድ በመሳል እንደምናዘው የቆርቆሮ ስፋት መከፋፈል ነው
አብዛኞቹ ፋብሪካዎች የሚያመርቱት ስፋት ሁለት አይነት ሲሆን እነዚህም ባለ90ሳ.ሜና ባለ 110ሳ.ሜ ሲሆን በፎቶ የምታዩት የተሰራው ክፍልፋይ ለባለ 90ሳ.ሜ ነው
ርዝመት እስከ ስድስት ሜትር ድረስ ወጥ ማዘዝ ይቻላል።
ምንም እንኳን ባለ 90cm ስፋት ብንጠቀምም ክፍልፋይ በ80cm የሚታየው 10cm overlap ስለሚደረግ ስናከፋፍል 10cm ተቀናሽ ተደርጎ ነው።
ባለ110cm ስፋት ማዘዝ ከፈለግን ደግሞ በ1m እናከፋፍላለን ማለት ነው።

በአሁን ሰዐት በአብዛኛው በየ40cm ርቀት ክርክር የተረገላቸው የዚህ አይነት ወጥ የቤት ክዳን ቆርቆሮዎች እየተመረቱ እየቀረቡ ነው።
የዚህ አይነቱ የቤት ክዳን ትልቁ ደካማ ጎኑ ብዙ ብክነት (waste) መኖሩ ነው እንደምትመለከቱት ከጣራው section ውጪ የሚታዩት በሙሉ waste ነው በአንፃሩ ለስራ ደግሞ በጣም ምቹና ቀላል ነው  ለምን ቢባል በቦታ ልክ የሚታዘዝ ስለሆነ አስቀምጦ መትቶ በግራይንደር መቁረጥ ብቻ ነው።
ሌላኛው (48cm×110cm) ይመረት የነበረ ሲሆን ብዙ waste  ባይኖረውም ለስራ እየቀጣጠሉ መምታት አመቺ ካለመሆኑም በላይ too many overlap ስላለው ተጨማሪ የቤት ክዳን ቆርቆሮ ያስጨምራል።


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍415🙏2👏1
ኮንትራክተር ለመሆን ምን ያስፈልጋል?

👉What we need to have to be
contractor?
🇪🇹

1.የንግድ ስያሜ በ ዌብሳቱ 👇👇 በመግባት መመዝገብ እና የ ድርጅቱን መዋቅር መወሰን
https://www.business.gov.et

ሀ. Sole proprietorship/ አንድ ግለሰብ ብቻ ባለቤት የሆነበት

ለ. PLC ( private limited company)/ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር

ሐ.SC(share company)/ አክሲዮን ማህበር


2. ውል እና ማስረጃ ( document authentication) በመሄድ መመስረቻ እና መተዳደሪያ ማፀደቅ

3.ክፍለከተማ ንግድ ቢሮ በመሄድ በባንክ ዝግ አካውንት በማሳየት ካፒታል ማፀደቅ

4. ሰነዶች ማረጋገጫ በመሄድ በ ቤት ኪራይ ውል ማዘጋጀት

5. በአቅራቢያ ባለው ገቢዎች TIN number ማውጣት

6.የንግድ ምዝገባ እና ንግድ ፈቃድ
https://www.business.gov.et በዚ ዌብ ሳይት በመግባት ማውጣት

7. ደረሰኝ ማሳተም

8. ኮንስራክሽን ቢሮ በመሄድ ደረጃ ማውጣት

➡️ባላችሁ ብቃት (ልምድ ፣የሰው ሀይል፣ማሽን) የደረጃ እርከን ይወጣላችኋል!

https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍8323😍4
የውሃ ማፍሰሻ (Drainage) ንድፍ የሲቪል ምህንድስና፣ የከተማ ፕላን እና የመሬት ገጽታ አርክቴክቸር ወሳኝ ገጽታ ነው።

የውኃ ፍሰትን በተለይም የዝናብ ውሃን፣የጎርፍ መጥለቅለቅን፣የአፈር መሸርሸርን እና የውሃ መቆራረጥን ለመከላከል ስርዓቶችን ማቀድ እና መተግበርን ያካትታል።

የፍሳሽ ማስወገጃ ንድፍ አጠቃላይ ሂደቶች ከዚህ በታች ቀርበዋል

⭐️1. የፕሮጀክት ምዘና እና መረጃ ማሰባሰብ

    - የሳይት ዳሰሳ፡ የመሬት አቀማመጥን፣ ተዳፋትን እና የተፈጥሮ ፍሳሽን ሁኔታ ለመረዳት የመሬት አቀማመጥ ዳሰሳ ያካሂዱ።
    - የሃይድሮሎጂካል መረጃ፡ የዝናብ መረጃን ይሰብስቡ፣ የዝናብ መጠን፣ የቆይታ ጊዜ እና የአውሎ ነፋሶች ብዛት (ለምሳሌ ታሪካዊ የአየር ሁኔታ መረጃን በመጠቀም)።
    - የአፈር ባህሪያት፡ የአፈር አይነት፣ የመተላለፊያ አቅም እና የሰርጎ መግባት መጠንን ይተንትኑ።
    - የመሬት አጠቃቀም፡ የውሃ ፍሳሽን ለመገመት ነባሩን እና የታቀደውን የመሬት አጠቃቀም (ለምሳሌ የመኖሪያ፣ የንግድ፣ የግብርና) ይለዩ።
    - የቁጥጥር መስፈርቶች *: የአካባቢ ደንቦችን, ኮዶችን እና የአካባቢ መመሪያዎችን ይከልሱ።

⭐️2. የንድፍ መስፈርቶችን ይወስኑ

- Design Storm፡ በፕሮጀክቱ አስፈላጊነት እና አደጋ ላይ በመመስረት ተገቢውን የአውሎ ነፋስ መመለሻ ጊዜ (ለምሳሌ፡ 10-አመት፣ 25-አመት፣ ወይም 100-አመት አውሎ ነፋስ) ይምረጡ።
    - Runoff Coefficient *: በመሬት አጠቃቀም፣ በአፈር አይነት እና በገፀ ምድር ባህሪያት ላይ በመመስረት የፍሳሹን መጠን (C) አስላ።
    - ከፍተኛ ፍሰት መጠን *: ከፍተኛ ፍሰት መጠኖችን ለመገመት እንደ ምክንያታዊ ዘዴ ወይም ሃይድሮሎጂካል ሞዴሎችን ይጠቀሙ።
    - የፍጥነት ገደቦች፡ የአፈር መሸርሸርን ወይም ደለልን ለመከላከል የፍሰት ፍጥነቶች ተቀባይነት ባለው ገደብ ውስጥ መሆናቸውን ያረጋግጡ።

⭐️3. ሀይድሮሎጂካል ትንተና
   
- Run off Estimation፡ እንደ ምክንያታዊ ዘዴ፣ የኤስ.ሲ.ኤስ ከርቭ ቁጥር ዘዴ ወይም የሃይድሮሎጂ ሞዴሊንግ ሶፍትዌር (ለምሳሌ HEC-HMS፣ SWMM) ያሉ ዘዴዎችን ተጠቀም።
    - Time of Concentration*: ውሃ ከተፋሰሱ ከሩቅ ቦታ ወደ መውጫው ለመጓዝ የሚፈጀውን ጊዜ ያሰሉ ።
    - የፍሰት መንገዶች፡ ጅረቶችን፣ ስዋሎችን እና ያሉትን የፍሳሽ ማስወገጃ ዘዴዎችን ጨምሮ የተፈጥሮ እና አርቲፊሻል ፍሰት መንገዶችን ይለዩ።

⭐️4. የሃይድሮሊክ ዲዛይን
  
- የቧንቧ መጠን *: ቧንቧዎችን ፣ ቧንቧዎችን እና ሰርጦችን ለመለካት የማኒንግ እኩልታ ወይም ሌላ የሃይድሮሊክ ቀመሮችን ይጠቀሙ።
    - ግራዲየንት እና ተዳፋት: ከመጠን በላይ ፍጥነቶችን በማስወገድ ትክክለኛ ተዳፋትን ለስበት ኃይል ፍሰት ያረጋግጡ።
    - መግቢያዎች እና መውጫዎች *: ውሃን በብቃት ለመሰብሰብ እና ለማውጣት የመግቢያ እና መውጫ መዋቅሮችን ይንደፉ።
    - የማጠራቀሚያ ተቋማት *፡ ከፍተኛ ፍሰቶችን ለመቆጣጠር እና የታችኛው ተፋሰስ ተፅእኖዎችን ለመቀነስ አስፈላጊ ከሆነ ማቆያ ወይም ማቆያ ገንዳዎችን ዲዛይን ያድርጉ።

⭐️5. የስርዓት አቀማመጥ

    - የአውታረ መረብ ንድፍ *: የቧንቧዎችን, የሰርጦችን እና ሌሎች የፍሳሽ ክፍሎችን አቀማመጥ ያቅዱ.
    - ከነባር ስርዓቶች ጋር ውህደት *: አሁን ካለው የፍሳሽ መሠረተ ልማት ጋር ተኳሃኝነትን ያረጋግጡ።
    - አካባቢያዊ ጉዳዮች፡ ዘላቂነትን ለማጎልበት አረንጓዴ መሠረተ ልማትን (ለምሳሌ የዝናብ ጓሮዎች፣ ተላላፊ መንገዶችን) ማካተት።

⭐️6. መዋቅራዊ ንድፍ

    - የቁሳቁሶች ምርጫ *: ለቧንቧዎች, ለቆሻሻ ማጠራቀሚያዎች እና ለሌሎች መዋቅሮች (ለምሳሌ, ኮንክሪት, HDPE, ቆርቆሮ ብረት) ተስማሚ ቁሳቁሶችን ይምረጡ.
    - የጭነት ትንተና : የአፈርን ግፊት እና የትራፊክ ጭነቶችን ጨምሮ መዋቅሮች የሚጠበቁ ሸክሞችን መቋቋም እንደሚችሉ ያረጋግጡ.
    - የአፈር መሸርሸርን መቆጣጠር *: እንደ መሸርሸር, ጋቢን ወይም እፅዋትን የመሳሰሉ የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል የንድፍ እርምጃዎች.

⭐️ 7. ሞዴሊንግ እና ማስመሰል

    - የሶፍትዌር መሳሪያዎች *: በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ የስርዓት አፈፃፀምን ለማስመሰል የውሃ ማፍሰሻ ሞዴሊንግ ሶፍትዌርን ይጠቀሙ (ለምሳሌ ፣ SWMM ፣ Civil 3D ፣ AutoCAD)።
    - የትዕይንት ትንተና * ስርዓቱን በተለያዩ አውሎ ነፋሶች እና ውድቀት ሁኔታዎች ውስጥ ይሞክሩት።

⭐️8. የግንባታ ሰነድ

    - ድሮዊንግ *: እቅዶችን, መገለጫዎችን እና መስቀሎችን ጨምሮ ዝርዝር የግንባታ ንድፎችን ያዘጋጁ.
    - መግለጫዎች *: የቁሳቁስ እና የግንባታ ዝርዝሮችን ያቅርቡ.
    - የወጪ ግምት *: የውሃ መውረጃ ስርዓት ወጪ ግምት ያዘጋጁ.

⭐️9. አተገባበር እና ጥገና

    - የግንባታ ቁጥጥር *: የፍሳሽ ማስወገጃ ክፍሎችን በትክክል መጫኑን ያረጋግጡ.
    - ፍተሻ እና ሙከራ *: የስርዓት አፈፃፀምን ለማረጋገጥ ምርመራዎችን እና ሙከራዎችን ያካሂዱ።
    - የጥገና እቅድ *: የረጅም ጊዜ ተግባራትን ለማረጋገጥ የጥገና እቅድ ማዘጋጀት, ማጽዳትን, ጥገናዎችን እና ማሻሻያዎችን ያካትታል.

⭐️10. ክትትልና ግምገማ

    - የአፈጻጸም ክትትል *: ስርዓቱን በማዕበል ጊዜ እና በኋላ ይቆጣጠሩ ውጤታማነቱን ለመገምገም.
    - ተስማሚ አስተዳደር *: በታዩ አፈጻጸም እና በተለዋዋጭ ሁኔታዎች ላይ በመመስረት ማስተካከያዎችን ያድርጉ።

📜ቁልፍ ጉዳዮች

- ዘላቂነት *: ዘላቂ የፍሳሽ ማስወገጃ ዘዴዎችን (SuDS) ወይም ዝቅተኛ-ተፅእኖ ልማት (LID) ልምዶችን ማካተት።
- የአየር ንብረት ለውጥ *: በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በዝናብ መጠን ላይ ሊደረጉ የሚችሉ ለውጦችን ግምት ውስጥ ያስገቡ።
- የህዝብ ደህንነት፡ ስርዓቱ እንደ ጎርፍ ወይም መዋቅራዊ ውድቀት ባሉ የህዝብ ደህንነት ላይ አደጋዎችን እንደማይፈጥር ያረጋግጡ።

እነዚህን ቅደም ተከተሎች በመከተል, መሐንዲሶች እና ዲዛይነሮች ሁለቱንም ተግባራዊ እና አካባቢያዊ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ውጤታማ እና ተከላካይ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓቶችን መፍጠር ይችላሉ።


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍5210💯2👏1🙏1
በአሜሪካ ኬንቲኪ Grace Farms ውስጥ በወንዝ አምሳያ የተገነባው  "River building" ጥልፍልፍ ሕንፃ በምህንድስና ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ያለው እንደሆነ የተመሠከረለት ነው‼️

https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍403🤔2
10x📏 ለካ አንድ ጊዜ ቁረጥ🪚🤔🤔🤔

https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍34🤔63
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን፣

ዒድ ሙባረክ!

መልካም በዓል!

https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
11👍6
በጋራ የኮንስትራክሽን ሥራ ንግድ ፍቃድ ስታወጡ ስለስያሜው     {ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (PLC) እና የአክሲዮን ማህበር (SC) ተመሳሳይነትና ልዩነት}

በኮንስትራክሽን ሥራ ውስጥ አክሲዮን ማኅበር፣ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ ሽርክና የሚባሉ ከአንድ በላይ የሆኑ አባላት በጋራ ሆነ ንግድ ፍቃድ የሚያወጡባቸው ዘርፎች አሉ እነዚህ ስያሜዎች በኢትዮጵያ ንግድ ህግ ዉስጥ ካሉት የንግድ ማህበራት መካከል የሚጠቀሱ ሲሆን በዚህ ክፍል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር—ኃ.የተ.የግ.ማ (Private Limitted Company - PLC) እና የአክሲዮን ማህበር - አ.ማ (Social Company - SC) ያላቸውን አንድነትና ልዩነት እንመለከታለን። ሁለቱም ማህበራት አክሲዮን ያላቸዉ ወይም ካምፓኒዎች ሲሆኑ ተመሳሳይነትና ልዩነት አላቸዉ።


ተመሳሳይነታቸዉ:-
• ህጋዊ ሰዉነት ያላቸዉ መሆኑ ፣
• የራሳቸዉ ንብረት ያላቸዉ መሆኑ፣
• የራሳቸዉን ትርፍና ኪሳራ ተጠያቂነት ያለባቸዉ መሆኑ፣
• ሁለቱም ትንሹ የአባላት ብዛትና የመነሻ ካፒታል ያላቸዉ መሆኑ፣
• ሁለቱም በቦርድና በማናጀር መመራት የሚችሉ መሆኑ ነገር ግን ለ PLC አሰገዳጅ አለመሆኑ፣
• የሁለቱም ተጠያቂ በተዋጣዉ የገንዘብ መጠን (አክሲዮን ) መሆኑ ፣
• ሁለቱም የሙያ መዋጮን የማይቀበሉ መሆኑ
• በሁለቱም ካፒታል ማሳደግና መቀነስ የሚቻል መሆኑ ፣
• በሁለቱም አክሲዮኖች በመያዣ /በዋስትና / መያዝ ሚችሉ መሆኑ ፣


ልዩነታቸዉ:-
አንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር / PLC/ private Limited Company/ ለማቋቋም የአባላት ብዛት ከሁለት ማነስ የማይችሉ መሆኑ እንዲሁም ከሀምሳ መብለጥ እንደማይችሉ በንግድ ህጉ ተገልጿል። የአክሲዮን ማህበርን (share company) በተመለከተ ለማቋቋም ከ5 አባላት ማነስ የማይችል ሲሆን ብዛት ግን ገደብ የሌለዉ መሆኑን በንግድ ህጉ ላይ ይገኛል።

〰️ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መነሻ ካፒታል 15000 ሺህ ብርና ከዚያ በላይ ሲሆን የአንድ አክሲዮን ዋጋም በኢትዮጵያ ብር አንድ በመቶ ማነስ አይችልም።
〰️ አክሲዮን ማህበር መነሻ ካፒታል 50000 ሺህ እና ከዚያ በላይ ሲሆን የአንድ አክሲዮን ዋጋ ከአንድ መቶ ብር በታች መሆን አይችልም
〰️ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ካፒታሉ ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ የተከፈለ ሲሆን የአክሲዮን ማህበር ግን ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ የሚከፈል አይደለም ነገር ግን ከተፈረሙ አክሲዮኖች ቢያንስ 1/4 (25%) መከፈል አለበት የቀረዉ በሂደት የሚከፈል ይሆናል
〰️ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የአክሲዮኖች ሽያጭ ለህዝብ ክፍት የሚደርግ አይደለም  ነገር ግን አክሲዮን ማህበር ለህዝብ ክፍት የሚደረግ ነዉ
〰️ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ( PLC) ላይ አክሲዮን ማህበር ዉስጥ ያለ ሰዉ አክሲዮኑን ለሶስተኛ ሰዉ ማስተላለፍ አይችልም ምክንያቱም መተዳደሪያ ደንቡ ላይ አባላት ይህን እስካልፈቀዱ ድረስ በህጉ መሰረት sale freely transfrable አይደለም። ነገር ግን አክሲዮን ማህበር ላይ አክሲዮን ማስተላለፍን በተመለከተ አክሲዮን የገዛ ሰዉ አክሲየኑን ለሌላ አባል ላልሆነ ሰዉ በቀላሉ ማስተላለፍ ይችላል ። ስለዚህ አክሲዮን ማስተላለፍ ከተፈለገ በቀላሉ የአክሲዮን ማህበርን መምረጥ ያስፈልጋል ማለት ነዉ።
〰️ አስተዳደራዊ አካል (ቦርድ) ን በተመለከተ አክሲዮን ማህበራት ሁሉ ከ3-12 ሰዉ የሚይዝ ቦርድ ኦፍ ዳይሬክተር ሲቋቋም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (plc) ዉስጥ የቦርድ መዋቅር ግዴታ አይደለም።


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍578
ባለ ፌሮ አርማታ (RC) የምናረገው ሁለት ነገሮችን ለመቋቋም ነው🏗

1. መኮማተርን(compression)
2. መለጠጥን (tension)

ፌሮ የመለጠጥ ጥንካሬ አለው ductile property አለው ስለዚህ ሲለጠጥ እና deform ሲያረግ ጊዜ ይወስድበታል

አርማታ ደግሞ የ መኮማተር ጥንካሬ አለው ለመለጠጥ ከጠጋለጠ ወዲያው ይቀነጠሳል ለምን ቢባል brittle ስለሆነ

ስለዚህ አርማታ በዝቶ ብረት ካነሰ tensile failure occur ያረጋል በተቃራኒው ደግሞ ብረት በዝቶ አርማታ ካነሰ compression failure በዚህ ግዜ ፈጠን ያለ ምላሽ እናገኛለን ከ tensile failure አንፃር።

ስለዚህ Balanced የሆነ structure design ማረግ አለብን።


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
👍766👏4🔥2
🔶Advanced Structural Design
( ዲዛይነሮችንና ግንባታ ፈቃድ ባለሙያዎችን በተለየ የሚጠቅም )
New Class Schedule, On Saturday Afternoon
👆These are the Checklists We'll Discuss for the 2 Months Structural Design Course. It Covers👇
🔹Mainly Concrete Structure (Ordinary & High rise)
🔹Also Steel Structure
🔸4 Software : Etabs, Sap, Safe
, Idea Statica
Class Options
I) 7:30-10:00 LT
II) 10:30-1:00 LT
Class Starts on April 26/2025
🔹To Register Fill the Form 👇
https://forms.gle/cgetEcy5c1uYtBNJ7
📞 +251920933016
https://www.tg-me.com/BeGetEngineering
👍278🔥2👏1😍1
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም በዓል ይሁንላችሁ፣ ይሁንልን።


https://www.tg-me.com/ethioengineers1
👍29
የኮንስትራክሽን_ብቃት_ማረጋገጫ_ምዝገባ_መመሪያ_1.pdf
50.8 MB
አዲሱ የኮንስትራክሽን ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ መመሪያ

https://www.tg-me.com/ethioengineers1
👍321👏1
📢 Official Class Start Announcement
The Advanced Structural Design course will officially begin with Class 1 this Saturday, May 3, 2025!
🔹 Topics Covered:
✔️ Concrete Structures (Ordinary & High-Rise)
✔️ Steel Structures
✔️ Structural Design Software: ETABS, SAP2000, SAFE, IDEA StatiCa
Class Time Options:
- Afternoon Session: 7:30 - 10:00 LT
- Late Afternoon Session: 10:30 - 1:00 LT

💡 Get ready to strengthen your structural design skills with practical applications and expert guidance. See you in class! 🚀

📞 +251911890392
https://www.tg-me.com/BeGetEngineering
👍182👏1
2025/10/21 23:51:16
Back to Top
HTML Embed Code: