Telegram Web Link
ስለዘገየን ትልቅ ይቅርታ እየጠየቅን ትውውቅ ክፍል 4ን ጀባ አልናቹ።🙏

መልካም ምሽት

#ህብረ_ቀለማት_ግጥሞች
#ከአእምሮ የበለጠ መዝገብ፥ከእውነት የቀና መልክተኛ የለም፥ከእውነት የበለጠ መንገድ መሪ፥ዝም ከማለት የበለጠ ጠባቂ የለም፥መናገር እንኳን ብር ቢሆን አለመናገር ወርቅ ነው ተብሏል።

#የተገኘ ነገር ሁሉ ጥሩ ነው፥ነገር ግን፥ሰዎች የታጣውንና ተፈልጎ ያልተገኘውን ነገር ይፈልጉታል። ያገኙትን ንቀው የማያገኙትን ለማግኘት ይደክማሉ። (የቆጡን አውርድ ብላ የብብቷን ጣለች)እንዲሉ

#ከብዙ ድልብ ይልቅ ትዕግሥት ገንዘብ አድርግ። ትዕግሥት የተድላ ደስታ መክፈቻ ነውና።

#share
@ethiopiagna
@ethiopiagna11
ኩራዝ ቡክስ
ስብሃት ገብረእግዚአብሄር አንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር፥

"በህይወት እስካለህ ልትሳሳት ፣ ልትወድቅ ትቸላለህ፤ ሰዎች ላይቀበሉህ ይችላሉ፤ ወይም ሀሳብህን ላይረዱህ ፣ ቦታ ላይሰጡህ ይችላሉ፤ በእጅህ ላይ ያለው ሙሉ በሙሉ አመድ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ፤ ሰዎች ሊጠሉህ ፣ ሊያሙህ ፣ ወይ ስም ሊያወጡልህ ፣ አሊያም ሊስቁብህ ፣ ይችላሉ።

"በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው። መልካም ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሀል። አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ባዶነታቸውን ስለምትገልጥባቸው አብዝተው ይፀየፉሀል። ብርሃናዊ ራዕይ ቢኖርህ የጨለምተኞችን ጨለማ ስለምታሳይ መኖርህ ያንገበግባቸዋል። ነፃ አውጭ ብትሆን ጨቋኞች ያሳድዱሀል።

"ምናለፋህ በአለም ስትኖር በሙሉ ድምፅ ልትወደድም፣ ልትጠላም አትችልም። ስለዚህ በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደ ውሃ ቅርፅህን አትቀያይር! ከምንም በላይ በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን!"

አንድ ነገር ልንገራችሁ፥ በህይወታችሁ ማንንም አትውቀሱ፤ ጥሩ ሰዎች ደስታን ይሰጡልችሀል፤ መጥፎ ሰዎች ልምድ ይሆኑችሁዋል። ክፉ ሰዎች ማስጠንቀቂያ ይሆናቹኋል፤ ምርጥ ሰዎች ትዝታ ይሆኑላችሁዋል።

መልካም ቀን🙏

#share
@ethiopiagna
@ethiopiagna
ዛሬ ትውውቅ ክፍል 5ትን ልናደርሳቹ ባለመቻላችን ይቅርታ።

ዛሬ ከናንተ የመጡ እና የሚመጡ አስተያየቶችን በመቀበል እናሳልፋለን።

@lanchi_new11 ላይ አስተያየታችሁን ፃፉልን
"ማንም ሰው የበላይም የበታችም አይደለም። ግን ደግሞ እኩልም አይደለም። በቃ! ሰዎች የተለያዩ ናቸው። አይወዳደሩም ፤ አይነፃፀሩም። አንተ አንተን ወይንም ራስህን ነህ። እኔ ደግሞ እኔን ነኝ። "
•••
ባግዋን ራጅኒሽ (ኦሾ)
@ethiopiagna
@ethiopiagna11
https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAE0Qfz9KF9rNtu3p4Q

ትውውቅ 5

የመጨረሻ ክፍል

ዝብርቅርቅ ምክክር

ለአንባቢ ሁሉ ግልፅ እንዲሆን የፈለኩት ትውውቃችን አሁን ድረስ መጨረሻ የለውም። እኔም ብቻዬን ግዙፍ መሬት ማረሱን ለምጄዋለው። የህይወቴ አጋር መቅረት ብዙም እየደነቀኝ አደለም። እሷም ከአዲሱ እና ከብዙዎቹ አንዱ ከነበረው ጋር ያላትን ጥምረት መርጣለች። የኔ መቅረት ምን እያረጋት ይሆን? ይሄን አላቅም።

በኛ ትውውቅ ላይ እጃችሁን ሳንፈቅድ ያስገባቹ ሁሉ ደርሶባችሁ ታዩት ዘንድ መልካም ምኞቴ ነው። ይቅናቹ

ትንሽ መሬት ላይ ያለረፍት ተዘርቶም ትርፍ ይገኛል። ግዙፍ መሬትም ብቻን ተሁኖ ይታረሳል። ማስተዋልን ብቻ ነው እሚፈልጉት። ትልቅነትንም ይፈልጋሉ። አበቃ

ትውውቃችን አራት ነጥብ መፈለጉ ብቻ ካለበት ለመቆም በቂ ምክንያት ነበር። እኔ አልሰጠውም ስላልኩ ስላላልኩ አደለም። ትውውቃችን በኛ እንጂ በኔ ብቻ አይፀናም። ምንም በልቤ ትዕግስትን ይዤ ብጓዝ በይሉኝታ እና በሌለ በማይኖር ፍቅር ስም ስታለል አልኖርም።

በመጣ በሄደው ላለመሸነፍ እራሴን እንዲ እመክረዋለው

የተፃፈልህን መኖር ትተህ ራስህ የፃፍከውን ኑር። የፃፍከው ከሌለህ ደሞ ፃፍ። ምናልባት እኮ ህይወትክን ፅፈህ እንድትኖራት ተፅፎ ይሆናል። ተስፋ ፣ ትዕግስት ፣ ብልሀት ፤ ሁሉን ባሟላ መልኩ ኑሮህን ፃፈው። እንደፃፍከው ካልኖርክ ግን ምክንያትህ አንተ ሳትሆን ሌሎች መሆን አለባቸው። የፃፍከውን ላለመኖር አንተ ምክንያት ልትሆን አይገባም። ይልቁን ኑሮህን ስትፅፍ የራሳቸውን ኑሮ ያልፃፉትን ፣ ላንዱ በተፃፈው የሚኖሩትን(ሰዎች) እያሰብክ ፃፈው።

ትውውቃችንን ፅፌው ነበር።

አሁን ደሞ ፅፌው እንደነበር እየፃፍኩ ነው።

አስተውል ፤ አይምሮህ ሳያስብብህ በፊት አንተ አስብበት። ሁሉም ነገር እዛው ውስጥ ነው የሚካሄደው። አይምሮህን ከተቆጣጠርክ ሙሉ ሰው ነህ። ምንም ፣ ማንም አይገዛህም። ፍቅር የሚባለው ክንውንም በልብ ይመሰል እንጂ በአይምሮህ ነው የሚሰፈረው።

በማይረካ የስሜት አይነት የተወጠነ

አሁን አሁን ካለው የሰው ፍቅር በጣም የላቀ

የፍቅር አይነት አለ። መጠሪያም የለውም። ብዙዎቹም አይሰማቸውም። ይሄ ከተሰማህ እድለኛ ነህ።

ደስ የሚል ስቃይ ብሎ ሲዘፍን ድምፃዊው ፤ ይሄን ስሜት ያሰበ ይመስለኛል።

ሀሳቦቹን በቦታ ቦታቸው ካስገባህ በኃላ ምክሩን ተመከር።

አጭር ፅሁፍ "ትውውቅ"
ፀሀፊ "የጊዜ ልጅ"
ህብረ ቀለማት ግጥሞች pinned «https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAE0Qfz9KF9rNtu3p4Q ትውውቅ 5 ። የመጨረሻ ክፍል ። ዝብርቅርቅ ምክክር ። ለአንባቢ ሁሉ ግልፅ እንዲሆን የፈለኩት ትውውቃችን አሁን ድረስ መጨረሻ የለውም። እኔም ብቻዬን ግዙፍ መሬት ማረሱን ለምጄዋለው። የህይወቴ አጋር መቅረት ብዙም እየደነቀኝ አደለም። እሷም ከአዲሱ እና ከብዙዎቹ አንዱ ከነበረው ጋር ያላትን ጥምረት መርጣለች። የኔ መቅረት ምን እያረጋት…»
የሱፍ አበባ "
ከሚለው መጽሐፍ የተቆነጠሩ ገፆች...

"ጎበዝ ሰው ለጥያቄዎች በሚሰጠው መልስ ይታወቃል። ብልህ ሰው ግን በሚጠይቀው ጥያቄ ይመዘናል።"
/ የሱፍ አበባ...ገጽ 56 /

"ድርቅ የተፈጥሮ ምክንያት አለው። ርሀብ ግን ሁሌም የተዛባ ፖለቲካዊ መስመርና ፖሊሲ ውጤት ነው። "
/ የሱፍ አበባ...ገጽ 66 /

"...ሞኝ አትሁን! ፍቅር፣ ወሲብ፣ ምናምን ቀድሞ የተዘጋጀ ቀመር የለውም። የምክንያትና የሎጂክ ጣጣም አያውቅ። ድንገት ብቅ ይላል፣ ሀሴት አዝንቦልህ መልሶ ይሰወራል። እንደገና ትናፍቀዋለህ። ይሄንን የተፈጥሮ ሕግ እንኳንስ አንተ የፍቅር አማልክት ሊለውጡት አይችሉም ።..."
/ የሱፍ አበባ...ገጽ 119 /

"ምሥጢር በትክክል ምሥጢር የሚሆነው የአንተ እስረኛ ሲሆን ነው። ሌላ ሰው ጆሮ ከደረሰ ግን አንተ የምሥጢርህ እስረኛ ትሆናለህ!..."
/ የሱፍ አበባ...ገጽ 128 /

"የሚኖሩለት ዓላማ አለ ማለት ከእንስሳዊ ተፈጥሮ እየወጡ...እየራቁ...አየመጠቁ መሄድ ማለት ነው ። "
/ የሱፍ አበባ...ገጽ 131 /

#share
@ethiopiagna
@ethiopiagna11
አስተውል ይሄ እውነታ ነው ‼️

•| ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትወደቅ ማለት አይደለም !ወድቀህ መነሳትን ልመድ ማለት እንጂ ።

•| ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ! ሌሎችን ለመስማትም ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ ።

•| ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም ! በሰዎች ሃቅ ላይ አትለፍ ማለት እንጂ ።

•| አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም !ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ ።

•| ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም ! በሆድ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ ።

•| ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም !ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ እንጂ ።

•| ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ! ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ ።

•| ስራህን ወደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ! ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ወደድ ማለት እንጂ ::

#share
Join @ethiopiagna
#የኤደን ደምግባት!

(ሚካኤል አስጨናቂ)

።።።።።።

በአረንጓዴ ቢጫ በቀይ ጥለት ሸማ

አደባባይ መሀል ተውቦ በግርማ

ቃላትን ሰድሮ ... እያሰማመረ

እሰይ የምስራች !

ብሎ የሚናገር ፥ አዝማሪ ነበረ።

።።።

እሰይ የምስራች !

የድል ብስራት ዜና...

ቁጭትን ሸርሽሮ ፥ መንፈስ የሚያረካ

አዲስ ፀሀይ ወጣች ፥ ይኸው ሰማይ ፈካ

የዘመን መብሰልሰል ፥ ብሶት ረገበ 

ዓባይ ሀገሩ ላይ ፥ ሰክኖ ተገደበ ።

.

ከእንግዲህ መቆዘም እንባን ዘግኖ መዝራት

በጭስ ተለብልቦ ማዘጋጀት ራት 

ታሪክ ሆኖ ሊቀር መንገድ ተጀምሯል

እናቴ ሆይ ሳቂ ያንቺም ቀን ተውቧል።

.

እሰይ የምስራች!

የድል ብስራት ዜማ

ፋኖስ ያልዘለቀው ፥ ድቅድቁ ጨለማ

በኤክትሪክ አምፖል ፥ ቅጥሩ ተጥሶ

ወከክ ብሎ በራ ፥ ጎጆሽ ብርሀን ለብሶ።

።።።።።።

እናቴ ሆይ ሳቂ !

ከንፈርሽን ገልጠሽ ፥ በስድር ጥርሶችሽ

አምናና ካቻምና ...

ዘር ብሄር ሳይለዩ ፥ አብረው ልጆችሽ

ሕብረት ባጀገነው

አንድነት በዋጀው

በፍቅር ሰንሰለት ...

ዛሬም ደግመውታል ፥ የአደዋውን እውነት።

።።።።።

እናቴ ሆይ ሳቂ !

ደምቀሽ አሸብርቂ.. .

ትግሬ አማራ ኦሮሞ ...

ጋምቤላ ጉራጌ እንዲሁም ሀድያ 

ቤንሻንጉል ሱማሌ አፋርና ራያ

ቋንቋቸው ቢለያይ እንደ ብሄር ስሙ

ሁሉም ኢትዮጵያ ነው መቋጠርያ ደሙ።

።።።

እሰይ የምስራች !

የድል ብስራት ዜና ...

ዓመቱ ተስፋ ነው ...ዕድገት ብልፅግና

....

እናቴ ሆይ ተነሽ !

የተከዘ ፊትሽ ፥ የተከፋ ገፅሽ

በሸክምሽ ብዛት ፥ የዛለ ወገብሽ

ዳግም ቀና ይበል በአዲስ ቀን መሻት

አባይ ቤትሽ ውሏል ጎጆሽን ለማልማት።

.

ብሎ እየዘፈነ ፥ ክሩን እየቃኘ

በሰንደቅ ተውቦ ፥ መሀል የተገኘ

ቃላቱን ከሽኖ ፥ ዜማውን ያሳመረ

ከእናቱ ጋራ ፥ የተነጋገረ ...

የምስራች የሚል አዝማሪ ነበረ!

@ethiopiagna
ራቁት ሰማይ

ጨለማው ለምዶናል
ከጨረቃ በላይ እኛን ይወደናል

ሁል ጊዜ ሳገኝሽ አመሻሽ ጠብቄ
ከፀሀይ ፍጥጫ ላይሽ ተደብቄ

ብርሀን በሌለው ጨለማ ሳገኝሽ
የሞት ሞቴን ቆሜ አይኖችሽን ሳይሽ

እጆችሽን ይዤ በፍቅርሽ ስረታ
ጨረቃ ነበረች ከላይ የዛን ለታ

ደስ ይላት ነበረ እኛን መመልከቱ
የፍቅራችን ግለት ስንቱን መመከቱ

ታድያ የዛን እለት
ፍቅራችን ሲፀና የተሰማኝ ስሜት
ጨረቃ ን ፣ ጨለማን ተሰምቷቸው ኑሮ
መንጋት ተሳናቸው አንድ ለሊት አድሮ

ከዋክብት ፣ ጨረቃ የምሽቱ ድምቀት የነበሩ ሁሉ
ድምቀታቸው ሁነን እኛን እኛን ሲሉ
እነሱን እነሱን ማለት በተራችን ቢከብደን መድመቁ
መገናኘት ስንተው የሰማይ ከዋክብት አንድ ባንድ አለቁ

ጨለማን የጣለው ጨረቃን ያዘለው ሰማይ ተራቆተ
በኮከቦች ፈንታ የኔን ያንቺን ናፍቆት በላዩ አቆተ።

አኒታ

@ethiopiagna
የማስተጋባት ክፉ ደዌ
.
ደብረ ሊባኖሳዊው ባለ ቅኔ ካህሊል ጅብራን እንዲህ ይላል:-"አንዱ ሰው በውስጡ ሁለት ሰዎችን ነው፤አንዱ በብርሃን ሲተኛ ሌላው በጨለማ ይነቃል" ይላል ይህቺን ይዘን ሌላ ከፈለጋችን እንጭለፍ። ሳንሞቀው የጠለቀው ፀሀያች አያ ሙሌ ሙሉ -ጌታ ተስፋዬ(አያዬ) ደግሞ " ለካ ሰው ጥንድ ነው የአንድ ራስ መንትያ
አንድ ነው ሲካፈል" ይለናል እያወዳደርኩ አይደለም። ግን ቢያንስ ያለንን እንወቅ። ማንም ማንንም አልቀደመም አልበለጠምም ራሱን እስካልቀደመ በቀር።ነገ ስም ያለው ተነስቶ ስለ አያ ሙሌ ቢያወራ አሽቃብጠን እና አለ ልክ አውርተን ዝም ነን። አድናቂ ከማድነቁ በፊት የሚያደንቀውን ሰው እና ግብሩን ቢያንስ በአረዳዳችን መጠን እንኳን እንወቀው ግድ የለም ጥበብ መንጋነት አትደግፍም። የሚገርመው ግን የሀገራችን የስነ ፅሁፍ አለም በመንጋ የሀሳብ ዳራ ተተብትቧል።አንድ ጫፍ ይዞ ስለ አንድ ሰው ብቻ መለፈፍ ታሪክ ገደላ ነው።
ምን አይነት የዘመኑ ዘዴ አለ መሰላችሁ የባዕድ ቋንቋ በንግግር መሃል መደብለቅ የአዋቂነት ልክ እንደሆነው ሁሉ በስነ ፅሁፍ ችሎታቸው ገዘፍ ያሉትን ስም እየጠቀሱ ገሳ መጠለል ደግሞ አዋቂነት ሆኗል።እኔ ግን አይመስለኝም። ቀድሞ ነገር የገባን ራሱ አልገባንም።የጥበብ ሰው ደግሞ ጣዎስ ወይም ኮፒ ማሽን አይደለም ከሌላው የሰማውን ለማሰማት በስማ በለው አይጋልብም።ኢትዮጵያዬ ሆይ ጥበበኞችን ስንጠራ ብቅ የሚሉትን አንድ በይልኝ እኛ ጥበበኞችን እንጂ የቡና ወረኞችን አልጠራንም።ለማንኛውም ይህን ያልኩት በማያቸው መደጋገሞች ነው። ስጋ ቤት ሲከፈት መደዳውን ስጋ ቤት መክፈት ንግድ ነው። ስጋ ቤት ሲከፈት ከጎኑ እንጀራ ቤት ፣ ቢላ መሞረጃ ቤት እና የመሳሰሉትን መክፈት ደግሞ ጥበብ ነው።
በረሃ ላይ ውሃ ፍለጋ አንዲት ቦታ ላይ ቆፍረህ ውሃ ስታገኝ ኩባያ ይዞ ከሚመጣው ሰው ይልቅ የተገኘውን ምንጭ ደግሞ ለመቆፈር የሚመጣው ይበዛል። የገጠመን ይህ ነው። ወይ ለመጠጣት ኩባያ ይዘህ ና ወይም ፈቅ ብለህ ቆፍር። ብዙዎቻችን ሰው ከሚተቸን ተኩሶ ቢገድለን እንመርጣለን እና በማወቅም ባለማወቅም የተቀየመ ካለ ይቅር ይበለኝ። እኔም ይቅርታን ጠይቄያለሁ። ቸር ሰንብቱማ
ያለንን እንወቅ!!
አድናቂነት በግርድፉ ሳይሆን ሰርፆ ይግባን!!
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
©ሲራክ
@ethiopiagna
@ethiopiagna
ቀጠሮ🤷‍♂

ፈጣሪ ከወጉ ለአንተም ይድረስ ቢለኝ፣
በቀጥር ሰአት ላይ ከአንዲት ኮረዳ ጋር
ቀጠሮ ነበረኝ፤
አምላኬ በልኬ ለእኔም ስጠኝ ብዬ፣
ከታቦት ማደሪያው ቆሜ ከበተስኪያን
የገባሁት ስለት፣
የደራ መሠለኝ በተክሊል ዝማሜ
በመቋሚያው ቁመት፤

ኋላ ጨለማው ተረቶ እንዲያው ሊነጋጋ
ጎህ ሲቀድ ማለዳ፣
በወረብ ነካክቶ ተነስ ቀድስ በሚል በቅዳሴው ዜማ
ድንገት ነቃሁና፤
በላብ የጠቆረ ፊቴን እያባበስኩ አልጋው ካረፈበት
ከወለሉ ንጣፍ እግሬን እንዳወረድኩት፣
አፌ በረጅሙ ሲያዛጋ ሰማሁት፤

ተነሳ ረሀቤ ደሞ ጀማመረው፣
አፌ በአቤቱታ በማዛጋት መልኩ
የሆዴ መራቡን ለሆዴ ቢነግረው፤

ማለዳ ሠንጥቆ ልቆ ንሮ ንሮ ከሩቁ ሲሰማ
የሆዴ አቤቱታ፣
እጄን ወደ ኪሴ ዘለቅ አደረኩት ረሀቤን ሚገቱ
ሳንቲሞች ላወጣ፤
እነዛ እጆቼ ሲያሻው ለዝነጣ
ደሞ ግፍ ካለ ሙቀትን ፍለጋ መዝለቅ የለመዱ፣
ዛሬም እንደወትሮ ወና ሆነው ወጡ፤

የሚያነባን አይተ ከቶ ላታፅናናው ስለሚብስበት፣
ሆዴም እንዲያው ሆኖ ወና መሆኑን ሲያውቀው
መራቡ ባሰበት፤

ደሞ በዚህ በኩል በደብሮች ዙሪያ ገብቼ ስለት
ያስያሰኩት ቀጠሮ፣
በአፍ ብቻ ቃላት የፍቅር ድንኳኑን
አመሳቅሎ ጥሎ፤
ረሀቤ በሹክሹክታ እንኳን ለቀጠሮ
ለሆድ የለው ቢለው፣
ልቤ በአመፅ መልኩ ድንኳኑን ሰበረው፤

የ40 ቀን ዕድሌ ለካ እንዲ ኖርዋል፣
በእንጀራ ጉዳይ ገፆቹን ቀያይሮ
ሊያስቀረኝ ያለመው ከጉብልዋ ጋራ
ያለኝን ቀጠሮ፤

በስተመጨረሻም አውራጅ ያጣ ቋንጣ
ተሰቅሎ እንደሚያድር፣
እኔም በተራዬ አስታዋሽ አጥቼ
ባዶ ሆዴን ከማድር፤
ዳግም ወደ አልጋዬ ሰተት ብዬ ወጣው
አይኖቼን ከዳደንኩ የቱንም ሳልሰማ፤
የሆዴንም ጩሀት ማለዳ ሰንጥቆ የሚሰማውንም
ያሬዳዊ ዜማ፤


ተፃፈ በአዶኒያስ(LikeTed)
23/12/2012
Forwarded from 🔥BE_C TATTOO🔥
ለበዓል ታላቅ ቅናሽ አድርገናል😁👍

አዲሱን አመት ካለዎት ውበት ላይ ጨምረው ጨማምረው ይቀበሉት።

ማንኛውንም Tattoo ለመሰራት ከፈለጉ መደወል ብቻ ነው።
ቅርብ ላሉ ቤታቸው ድረስ ሄደን እንሰራለን።

ጥራት ያለው ስራ በ be_c tattoo
+251923880303
+251965928512
የሴተኛ አዳሪ ልጅ ነኝ by yoas
<unknown>
#የሴተኛ አዳሪ ልጅ ነኝ
(በላይ በቀለ ወያ)
#size 📂 1.2mb
@ethiopiagna
@ethiopiagna11
በቻናላችን አዲስ እና ለየት ያለ ምክር አዘል ፅሁፍ ልንጀምር አስበናል። ፅሁፉ ፍቅረኛ ላለውም(couples) ሆነ ብቸኛ ለሆነ(singles) በየአይነቱ የተዘጋጀ ነው። አንዱን እንድናስቀድም ግን ምን ያህል ፍቅረኛ ያለው እና የሌለው ተከታይ እንዳለን ማወቅ እንፈልጋለን።
anonymous poll

ፍቅረኛ የለኝም – 119
👍👍👍👍👍👍👍 67%

ፍቅረኛ አለኝ – 59
👍👍👍 33%

👥 178 people voted so far.
ቀደምት ጥበባት

#በርባኖስ (the Black hole) ምንድን ነዉ?

የአለማትን የሳይንሱን ዘረፍ የፈተነዉ ፍንጩ እንኳ ለመስጠት የሚያስቸግረዉ በርባኖስ ምንድን ነዉ?
ቀደምት ኢትዮጵያዉያን ስለ በርባኖስ ምን ብለዋል?
ብራናወቻችን አለም ተመራምሮ ስላልደረሰበት የሚስጥራት ሁሉ ሚስጥር ስለሆነዉ ስለ አለማት አፈጣጠርና አመሰራረት እንዲሁም በርባኖስ ምን ይላሉ?

መልካም ንባብ.......
ቀደምት ኢትዮጵያዉያን አባቶቻችን የእግዚአብሔርን ጥበብና ሚስጥር ተመግበዉ በዘመኑ ለሳይንስ ለቴክኒዎሎጂ እንቆቅልሽ የሆነ ምስጥራዊ እዉቀቶችን ና ጥበቦችን ትተዉልን አልፈዋል፡፡
እንዲሁም መለስ ብለን ታሪክን ስንመረምር፤ የተፃፉ ዶሴወችን ስናገላብጥ፤ የብራና መፃሆፍቶቻችንን ስንመረምር፤ አሁን ድረስ አለም ያልፈታቸዉ በረቀቀና በመጠቀ መልኩ ተብራርተዉና ተቀምጠዉ የሚገኙ አያሌ እዉቀቶች አሉ፡፡
ከነዚህም መካከል በምላት ና በስፋት ተብራርቶ የምናገኛቸዉ የአለማት አፈጣጠር ሚስጥራትን ነዉ፡፡
በዚህም የተነሳ የሚስጥር ማህበረሰብ የሚባሉት የምዕራቡ አለም ነገስታት አለምን አንድአድርጎ ለመግዛት ካላቸዉ ጉጉት የተነሳ የአዳም ልጆች ከሰለጠኑባት ከ ኢትዮጵያ ምድር ዉስጥ የሚገኙትን የአራቱን አለማት አፈጣጠር ሚስጥራትና ጥበባት ለመበዝበዝ ያላሰቡት ሀሳብ ያለፈነቀሉትም ድንጋይ አልነበረም፡፡

ከሰማያዊዉ ህብረት ሃይላት ህብረት መፍጠር የቻሉት ኢትዮጵያዉያን በየዘመኑ ከአራቱም አለማት ሚስጥራትና በመረዳታቸዉ በዘመናቸዉ ብርቱና ሀያል ሁነዉ ከማለፋቸዉ ባሻገር በመንፈሳዊ ፅናትና አቋማቸዉ ምክኒያት ወደ ሀገራቸወ ሲመጡ ለነበሩት ቅዱሳን ይህኔን ጥበባት አስተምረዋል፡፡
በምዕራባዉያን ሳይንስና ቴክንሎጂ የህዋ ምርምር ተቋማት ሚስጥራቸዉ አልፈታም ብለዉ ከተዘረዘሩት አንዱና ዋናዉ በርባኖስ ወይም ብላክ ሆል በመባል ይታወቃል፡፡
ስለዚህ ሚስጥራዊ ቦታ የተለያዩ ተመራማሪወች ሀሳባዊ መላምቶቻቸዉን አስቀምጠዋል ሁኖም ግን ከመላምታዊ ድምዳሜ የዘለለ አንዳችም ተጨባጭ ነገር ለመናገር አልቻሉም፡፡
ነገር ግን ቀደመት ኢትዮጵያዉያን ምሁራን በሚደንቅ እና በሚረቅ ትንታኔ አስቀምጠዉልን አልፈዋል፡፡
በአጠቃላይ አለማት 20 ሲሆኑ 14ቱ የሳትና የምድር ሲሆኑ 6 ደግሞ የነፍስና የዉሃ ናቸዉ፡፡
የሳት ፣የምድር፣ የነፋስ፣ እንዲሁም የዉሃ አለማት በመባል የሚታወቁ ጠቅለል ሲሉ አራት አለማት በመባል ይታወቃሉ፡፡
የሳት አለማት የሚባሉት 9 ሲሆኑ የምድር አለማት ደግሞ 5 ናቸዉ ፡፡
በ14 አለማት ዉስጥ የሚገኙት ፍጥረታት አንዳቸዉ ከአንዳቸዉ ግንኙነት የሚፈጠርባቸዉ ህቡዕ መንገዶች የሀይላቸዉ ማረፊያና ማደሪያ የሆኑ 12 የተለያዩ ቦታወች አሉ፡፡
እነዚህ የአለም ሀገራት black hool ብለዉ የሚጠሯቸዉ ከእነዚህ የተለያዩ ቦታወች 6ቱን ነዉ፡፡
የሳት አለማት የሚባሉት እጂግ በሚያንፀባርቅና በነበልባል በተከበበ ከፍተኛ በሆነ የሃይል መጠን የሚገኙባቸዉ አለማት ናቸዉ፡፡
እኒህ 20 አለማት በዝርዝር እንደሚከተለዉ ተቀምጠዋል፡፡
ዘጠኝ የእሳት: አምስት የመሬት: አራት የውሃና ሁለት የንፋስ ዓለማት ናቸው።

ሀ. የእሳት ዓለም ( በቁጥር 9 ዘጠኝ ናቸው ) ከላይ
ወደ ታች ሲቆጠሩ :-
1 ጽርሐ አርያም ( የእግዚአብሔር የምስጋናው አዳራሽ )
2 መንበረ መንግሥት/ስብሐት ( የጌታ ዙፋን ያለባት )
3 ሰማይ ውዱድ( በአራቱ እንስሳዎች ክንፎች ላይ የተዘረጋ ሰማይ )
4 ኢየሩሳሌም ሰማያዊት/ ዛዶር ( በመጀመሪያ
ሳጥናኤል የተፈጠረባት በኋላም ከእሱ ተነጥቃ ለአዳም ልጆች የተሰጠች )
5 ኢዮር ( የአርባው ነገድ የመላእክት ከተማ )
6 ራማ ( የሠላሳው ነገድ የመላእክት ከተማ )
7 ኤረር ( የሠላሳው ነገድ የመላእክት ከተማ )
8 ምጽናተ ሰማይ ( ባህረ እሳት )
9 ገሀነመ እሳት ናቸው።
አዳም አባታችን በዚች እኛ በምንኖርባት ምድር ከመሰልጠኑ አስቀድሞ ምድር ለሰባት ተቆርሳ ወይንም ተከፍላ ነበር። ይህ ማለት እንግዲህ ከምድራችን ጋር ተመሳሳይ የሀይል የጊዜና የግዝፈት መጠን ያላቸው ነገር ግን የማናውቃቸው ስድስት የመሬት ክፍሎች አሉ። እነዚህ በስድስት የተከፈሉ ሰባት የምድር ክፍሎች
የሚከተሉት ናቸው:፡
1,መሬት(እኛ አሁን የምንገኝበት)
2, ብሔሞት
3, አራዊት ብቻ የሚገኙበት
4, እሳት ብቻ የሚገኝበት
5, በረድ ብቻ የሚገኝበት
6, ሌዋታን
7, በርባኖስ (ጨለማ ስፍራና እስርቤት)
የስነፍጥረት አንድምታ መፅሐፍ እንደሚያስረዳው ኢዮር ራማና ኤረር አሰራራቸዉ አራት ማዕዘን ሲሆን ሰባት የሳት ቅፅርና ሰባት የሳት መጋረጃ የጋረዳቸዉ የሳት አለማት ናቸዉ፡፡ እኒህ አለማት ከሰዉ በተሰወረና ከመላእክት እንኳ በረቀቀ መልኩ ይገናኛሉ፡፡
አራት ማአዘን ቅርፅ ይዛ የተፈጠረችው ምድር ለሰባት ከተከፈለች በኃላ
ውሃ መላት። አንዳቸውን ከአንዳቸው እንዲሁ ውሃ ለያቸው።
በዚህ የተነሳ መሬትን እኛ የምንገኝባትን ውሃ ከበባት በዚህ
የተነሳ መሬት ክብ ናት የሚል ግንዛቤ ኖረን።
ከአራቱ አለማት አንዱ የሆነው መሬት አምስት ሰማያትን
ጠቅልሎ ይዟል እነርሱም ሲዖል ፣ መሬት፣ ብሔረ ብፁአን፣
ብሔረ ሕያዋን፣ ገነት ናቸው።
ከነዚህ መካከል መሬት ከላይ
እንዳየነው የሰው ልጅ በቅጡ ያልተረዳቸው ስድስት ክፍሎችን
ይዛለች።

Source-Kuraz books🙏

@ethiopiagna
@ethiopiagna11
ህብረ ቀለማት ግጥሞች via @vote
በቻናላችን አዲስ እና ለየት ያለ ምክር አዘል ፅሁፍ ልንጀምር አስበናል። ፅሁፉ ፍቅረኛ ላለውም(couples) ሆነ ብቸኛ ለሆነ(singles) በየአይነቱ የተዘጋጀ ነው። አንዱን እንድናስቀድም ግን ምን ያህል ፍቅረኛ ያለው እና የሌለው ተከታይ እንዳለን ማወቅ እንፈልጋለን። anonymous poll ፍቅረኛ የለኝም – 119 👍👍👍👍👍👍👍 67% ፍቅረኛ አለኝ – 59 👍👍👍 33% 👥 178 people voted…
እዚጋ በሰጣችሁት ድምፅ መሰረት ለወንዶች እንዴት ከሴቶች ጋር መግባባት እንዳለባቸው ፤ ለሴቶችም ወንድን ልጅ እንዴት መቅረብ እንዳለባቸው የሚያሳይ አጠር ያለ ፅሁፍ በመጪዎቹ ሶስት ቀናት እናደርሳችኃለን።

እስከዛ ግን ከፅሁፉ የተወሰደች አንዲት አጭር ንግግር ጀባ ልበላቹ።

መልካም ንባብ

ሁሉም ሰው ፤ ሴትም ወንድም ይሁን ማንኛውም ፆታ የግሉ ሰው ነው። የሰው ልጅ በገፁ በጣም ይመሳሰላል። ውስጡ ግን የግሉ ነው። ማንም የማንንም የሚመስል የውስጥ ማንነት የለውም። ሁሉም የየራሱ ማንነት አለው።

ሰው ስንቀርብ በላይ ገፅታው ተማርከን ሊሆን አይገባም። መማረክ ያለብን በያዘው ማንነት ነው። በርግጥ የማናቀውን ሰው በገፁ እንጂ በማንነቱ ልንማረክ አንችልም። ግን መማረክ ሳይሆን ያለብን በቃላሉ መሳብ ነው ያለብን። በገፁ ተስበሽ በማንነቱ ብትማረኪ ምንም አደለም። ለዚ ነው ብዙ ጊዜ የተሳካ ጓደኝነት ሲመሰረት የማናየው። በውበቷ ተደመም እንጂ አትገዛ። ውበት ማድነቅ ጥሩ ነገር ነው።

እያንዳዱ ሰው ውስጡ ልዩ ማንነት አለው ይህን ማንነት ለማየት ብለህ እንጂ ቆንጆ ስለሆነች ብቻ አትገዛ። ያን ልዩ ማንነቷን ልታሳይህ ፍቃደኛ ካልሆነች በቀላሉ ተዋት። ሌላ ብዙ ያንተን አይነት ሰው እሚፈልጉ ሴቶች ማንነታቸውን ሊያሳዩህ ዝግጁ ናቸው።

ወደኛ ሀገር ሴቶች ስመለስ ደሞ ሁላችሁም ባይባል አብዛኞቸችሁ ሁሉም ወንድ አንድ ነው በሚል ታምናላቹ። ይሄ አስተሳሰብ በሴቶች ይጉላ እንጂ ሁሉም ሴቶች አንድ መሆናቸውን የሚያምኑ ወንዶችም አሉ። ይሄ ነገር ደሞ በጭራሽ ልክ ያልሆነ ፣ ሊሆንም የማይችል የወደቀ አስተሳሰብ ነው። ይህን የወደቀ አስተሳሰብ ደሞ ቅድም ሁሉም የግሉ የሆነ ልዩ እና ምርጥ ማንነት አለው ያልኩት ያነሳዋል። ወንድ ሁሉ የሚያመሳስለው ነገር አለ ግን በገፁ እንጂ በማንነቱ አደለም። ሴት ሁሉ የሚያመሳስላቸው ነገር ካላይ ይኑር እንጂ ውስጣቸው በጣም ይለያያል።

ምናልባት ሴቶቹ የሚለያዩ ከሆነ አሁን በቀጣይ የሚለቀቀው ፅሁፍ እንዴት ከማንኛውም ሴት ጋር ያቀራርበኛል ብለህ እንዳትሰጋ። የሚፃፈው ፅሁፍ በአጠቃላይ ስለሰው መቀራረብ ነው። ግን ሴቶች ጋር ስትሄድ እና አብረሀት ስትሆን ምን ማረግ እንዳለብህ ይነግርሀል።

ማንነትህን ግን አቀይርም።

ከቀናት በኃላ በዋናው ፅሁፍ እንገናኛለን።
ጥሩ ቀን ተመኘውላቹ
የጊዜ ልጅ
@ethiopiagna
@yegtmmaebel
Forwarded from Rosie Shita
የጦቢያ ትንሳኤ

ምንድነው ማንባቱ ዕንባህን መዘርገፍ
ጠላትህ ሲጋልብ እንደማለት ዘራፍ
ከቶ አይችልምና መሞቱ ሊያባባህ
ሸልል ፎክር እና ስደደው አርቀህ
ግርማህን አሳየው ዝናርህን ታጥቀህ
ሰማይ ሆይ አድምጠኝ ስማኝ አስተውለህ
ከጷግሜ በኋላ ዝናብ ነው ጠላትህ
ወዝህን ማድረቂያ መርዛማ ነው ዕንባህ።
ፀሀይም አትሞኝ አትበይ አልወጣም
ቀንሽን ብሪበት ድመቂበት በጣም
ባክሽን ጦቢያዬ ልብሽን አይክፋው
አብቅቷል ወጀቡ የፀደይ ነው ተራው።
ደዌውን ሊያጠፋ ፌጦው ተፈትፍቷል
የእናቶችም አንጀት ለፀሎት ተፈቷል
ልጆች ሽክ ብለዋል አምረዋል በእጅጉ
አባቶች ባርከዋል ተሰውቷል በጉ።
ዕድልሽ ይታደል ደስታሽም ይደሰት
ችግርሽ ይቸገር ሞትሽ ቀድሞሽ ይሙት
እንደ አሸዋ ውሀ በኖ ተኖ ይጥፋ
ምድርሽ በአደይ እና በፍቅርሽ ይሰፋ
በአዲስ አመት መንበር በነገ ድልድይ ላይ
የፍቅር አክሊልን ደፍተሽ በላይሽ ላይ
ደምቀሽ ፈክተሽ ይታይ
መአዛሽ ይታወድ ከርቤሽ ያረስርሰን
በአዲስ እኛ አንኑር አሮጌውን ትተን።


ተፃፈ በ ግሩም ነን መቼም(ሮዛ)

የመለያ ቁጥር - ET-068

Like and join @eshidigital
@tibeb_drawing_and_poem
እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ

ህብረ ቀለማት ግጥሞች ከናንተ ጋር አመታትን አብሮ አሳልፏል። ከወራት በኃላ 4ተኛ አመቱን ይይዛል። በነዚ ጉዚያት ውስጥ ወጣ ገባ ያለ ነገር ነበር የነበረው ባሁኑ አመት ለየት ባለ መልኩ አድሚኖችን በማብዛት ስራውን ለማስቀጠል እንሞክራለን።

አዲሱን አመት በተስፋ ተቀበሉት። አዲስ አመት የቀን እና የዓ/ም ለውጥ ነው። ለውጥ አለ የሚባለው ራሳችን አሻሽለን ስንገኝ ነው። የዓምናው አይነት ስብዕና ይዘን ከነጉድለቱ አዲስ አመት ማክበር ይቅር እንለወጥ። ለሰው እናስብ። ሰው መሆናችንን አንዘንጋው።

ለየት ያለ ዓመት ተመኘውላቹ
እናት ጊዜ ነበርኩ ተሳትፏቹ አይለየን

እንኳን አደረሰህ/አደረሰሽ ማለት ለምትፈልጉት ሰው ቻናላችን መስመሩ ክፍት ነው ማለት የምትፈልጉትን በ @lanchi_new11 ላኩልን እኛ እንለቅላቹሀለን።

መልካም ቀን
2024/05/16 03:12:57
Back to Top
HTML Embed Code: