Telegram Web Link
#ደቡብ_ኢትዮጵያ፦ ኢሰመኮ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ያካሄደው ምክክር
...

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በክልሉ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ አጠቃላይ ምልከታ ላይ ጥቅምት 5 ቀን 2018 ዓ.ም. በአርባ ምንጭ ከተማ ምክክር አካሂዷል። ምክክሩ ኢሰመኮ በክልሉ በተለያዩ ጊዜያት ባደረጋቸው የሰብአዊ መብቶች ክትትሎች እና ምርመራዎች በተለዩ ግኝቶች እና በተሰጡ ምክረ ሐሳቦች ላይ በመወያየት አሳሳቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ለመወትወት ያለመ ነው።

በምክክሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ጥላሁን ከበደ፣ የብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አዳማ ትንዳዬ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝደንት ክቡር አንዷለም አምባዬ እንዲሁም የክልሉ ፍትሕ እና ጸጥታ ቢሮ፣ ፖሊስ እና ማረሚያ ኮሚሽን፣ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር እና የሌሎች ተቋማት ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ ለውይይት መነሻ ባቀረቡት ገለጻ በክልሉ በዳሰነች ወረዳ ያሉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የመብት አያያዝ ሁኔታ፣ በተለያዩ አካባቢዎች በተደጋጋሚ የሚፈጸም ግድያ እና ሌሎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንዲሁም የሕዳጣን መብቶችን ማእከል ያደረጉ ግኝቶችን አብራርተዋል። የሽግግር ፍትሕም ውይይት ከተደረገባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ነው።

🔗 https://ehrc.org/?p=34595

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
#ሶማሊ፦ በክልሉ ያለውን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ለማሻሻል በማለም የተካሄደ ውትወታ
...

የሰብአዊ መብቶች አከባበር ላይ የሚስተዋሉ መሻሻሎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ፤ የጥሰቶች መነሻ የሆኑ ችግሮችም እልባት ሊያገኙ ይገባል

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በሶማሊ ክልል ያለውን አጠቃላይ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ በተመለከተ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጋር ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም. በጅግጅጋ ከተማ ውይይት አካሂዷል። ውይይቱ ኢሰመኮ በክልሉ ያለውን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ በተመለከተ በተለያየ ጊዜ ባካሄዳቸው ክትትሎች የደረሰባቸውን ግኝቶች በማቅረብ መልካም እመርታዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እና አሳሳቢ ጉዳዮች የእርምት እርምጃ እንዲወሰድባቸው ለማሳሰብ ያለመ የኢሰመኮ የውትወታ ተግባር አካል ነው። በውይይቱ ኢሰመኮ የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ሙስጠፋ መሀመድን እና የክልሉ ማረሚያ ቤት ኮሚሽነር በሽር አህመድ ሐሺን ጨምሮ ሌሎች የሥራ ኃላፊዎችን አነጋግሯል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ በሶማሊ ክልል ከሀገራዊ ለውጡ በፊት በማረሚያ ቤቶች እና በፖሊስ ጣቢያዎች ሲፈጸሙ የነበሩ ድብደባ እና ሌሎች የማሰቃየት ተግባራት እንዲሁም ስልታዊ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች መቅረታቸው፣ ለታራሚዎች ከሌሎች ክልሎች የተሻለ የቀን ፍጆታ በጀት መመደቡ፣ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው በመመለስ እና በማቋቋም ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት ጥረቶች መደረጋቸው እና የሽግግር ፍትሕን ተግባራዊ ለማድረግ እርምጃዎች መወሰዳቸው አበረታች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

🔗 https://ehrc.org/?p=34648

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
1
📢 ዝግጁ ናችሁ?!
...

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በ5ኛው ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል በፎቶግራፍ እና በአጫጭር ፊልሞች ዘርፍ እንዲወዳደሩ ይጋብዝዎታል።

በውድድሩ ስለ ትምህርት መብት 📷በፎቶግራፍ እንዲሁም ስለ ነጻነት መብት 🎬በአጭር ፊልም እይታዎን ይሰንዱ ከዚያም ለውድድር ይላኩት፡፡ ለአሸናፊዎች ዳጎስ ያለ ሽልማት፣ ዕውቅና እና ምስጋና ተዘጋጅቷል፡፡

ይወዳደሩ! የኪነጥበብ ዐቅምዎን ተጠቅመው ለሰብአዊ መብቶች መስፋፋት አሻራ ያኑሩ!

ለመሳተፍ እና ለተጨማሪ መረጃ፡- https://filmfest.ehrc.org

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsFilmFestival
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ #HumanRights Concept: ከቤተሰቦቻቸው የተለዩ ሕፃናት ጥበቃ
...

የሕፃናት መብቶች ስምምነት፣ አንቀጽ 20 (1) እና (2)

ለጊዜው ወይም ለዘለቄታው ከቤተሰቡ የተለየ ወይም ለራሱ ጥቅም ሲባል ከቤተሰቡ ጋር እንዲቆይ ሊደረግ የማይችል ሕፃን የመንግሥትን ልዩ ጥበቃ እና ድጋፍ የማግኘት መብት አለው።
አባል ሀገራት በብሔራዊ ሕጎቻቸው መሠረት ከቤተሰቡ የተለየ ሕፃን አማራጭ እንክብካቤ ማግኘቱን ማረጋገጥ አለባቸው።

የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 36 (5)

መንግሥት ለእጓለ ማውታን ልዩ ጥበቃ ያደርግላቸዋል። በጉዲፈቻ የሚያድጉበትን ሥርዓት የሚያመቻቹና የሚያስፋፉ እንዲሁም ደኅንነታቸውንና ትምህርታቸውን የሚያራምዱ ተቋሞች እንዲመሠረቱ ያበረታታል።

🔗 https://ehrc.org/?p=34655

#Ethiopia🇪🇹 #KeepWordSafe #ጤናማቃላት

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
በጋዜጠኞች የሕግ ጥበቃ (ከለላ) ላይ የተካሄደ ውይይት
...

ሐሳብን በነጻነት መግለጽ መሠረታዊ እና በዘፈቀደ ገደብ የማይደረግበት ሰብአዊ መብት ነው

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከኢንተርናሽናል ሚዲያ ሰፖርት (International Media Support) ጋር በመተባበር በጋዜጠኞች የሕግ ጥበቃ (ከለላ) ላይ ጥቅምት 04 ቀን 2018 ዓ.ም. በአርባ ምንጭ ከተማ ውይይት አካሂዷል። በውይይቱ ከማእከላዊ ኢትዮጵያ፣ ከሲዳማ እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች የሕግ አስፈጻሚ አካላት እና ከግልና ከመንግሥት የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

የጥላቻ ንግግርን እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን እንዲሁም የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጡ አዋጆችን ሽፋን በማድረግ የሚፈጸሙ ክልከላዎች እና ገደቦች፣ የመገናኛ ብዙኃን አባላት ስለመብታቸውና ግዴታቸው ያላቸው ግንዛቤ ማነስ እንዲሁም የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ለተወሰኑ የመገናኛ ብዙኃን ብቻ መረጃ የመስጠት አዝማሚያ በተለይም የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ኃላፊዎች ለግል መገናኛ ብዙኃን መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆን በዘርፉ የታዩ ክፍተቶች መሆናቸው በውይይቱ ተነስቷል። በሌላ በኩል የጥላቻ ንግግሮችን፣ ሐሰተኛ መረጃዎችን እንዲሁም ግጭት የሚቀሰቅሱ መልእክቶችን የሚያሰራጩ መገናኛ ብዙኃንን መቆጣጠር አለመቻሉ፣ በበይነ-መረብ ላይ የሚጣሉ ገደቦች እና በመገናኛ ብዙኃን አማካኝነት ተፈጽሟል በተባለ ወንጀል ጋዜጠኞች ከሕግ ውጭ እስራት የሚፈጸምባቸው መሆኑ በውይይቱ ተነስቷል።

🔗 https://ehrc.org/?p=34661

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
4
ፍትሕ የማግኘት መብትን በተመለከተ የተካሄደ ውይይት
...

የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች የተፈጸመባቸው ሰዎች ውጤታማ ፍትሕ እንዲያገኙ የፍትሕ ተቋማት አገልግሎት ተደራሽነት ወሳኝ ነው

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከታኅሣሥ 19 እስከ የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም. በማእከላዊ ኢትዮጵያ፣ በሲዳማ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ፍትሕ የማግኘት መብት ሁኔታን በተመለከተ ባደረገው ክትትል በለያቸው ግኝቶች ላይ ጥቅምት 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ከባለድርሻ አካላት ጋር በአርባምንጭ ከተማ ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱ የሦስቱ ክልሎች ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች እና ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ተወካዮች፣ የመንግሥት ሠራተኞች አስተዳደር ፍርድ ቤቶች ተጠሪ ዳኞች፣ የክልልና የዞን የፍትሕ (ዐቃቤያነ ሕግ)፣ የፖሊስና ማረሚያ ተቋማት እንዲሁም የክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።

በመድረኩ ኢሰመኮ በሦስቱ ክልሎች ያለውን ፍትሕ የማግኘት መብት ሁኔታ አስመልክቶ ባከናወነው ክትትል የለያቸው አሳሳቢ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮችና ምክረ ሐሳቦች ቀርበዋል።  በቁጥጥር ሥራ የዋሉ ተጠርጣሪዎችን በ48 ሰዓት ፍርድ ቤት ሳያቀርቡ ለተራዘመ ጊዜ በእስር ማቆየት እና አቤቱታቸውን ፍርድ ቤት እንዳያቀርቡ በፖሊስ የሚደረግ ክልከላ መኖሩ በውይይቱ ተገልጿል። በተለይም ‘ኮማንድ ፖስት’ በሚል ተግባራዊ በሚደረግ የሕግ ማስከበር እንቅስቃሴ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሰዎችን መደበኛ ባልሆኑ ቦታዎች አስሮ ማቆየት አሳሳቢ የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ 

🔗 https://ehrc.org/?p=34674

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
👍3
2025/10/24 11:13:56
Back to Top
HTML Embed Code: