Telegram Web Link
#ሶማሊ፦ በክልሉ ያለውን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ለማሻሻል በማለም የተካሄደ ውትወታ
...

የሰብአዊ መብቶች አከባበር ላይ የሚስተዋሉ መሻሻሎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ፤ የጥሰቶች መነሻ የሆኑ ችግሮችም እልባት ሊያገኙ ይገባል

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በሶማሊ ክልል ያለውን አጠቃላይ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ በተመለከተ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጋር ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም. በጅግጅጋ ከተማ ውይይት አካሂዷል። ውይይቱ ኢሰመኮ በክልሉ ያለውን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ በተመለከተ በተለያየ ጊዜ ባካሄዳቸው ክትትሎች የደረሰባቸውን ግኝቶች በማቅረብ መልካም እመርታዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እና አሳሳቢ ጉዳዮች የእርምት እርምጃ እንዲወሰድባቸው ለማሳሰብ ያለመ የኢሰመኮ የውትወታ ተግባር አካል ነው። በውይይቱ ኢሰመኮ የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ሙስጠፋ መሀመድን እና የክልሉ ማረሚያ ቤት ኮሚሽነር በሽር አህመድ ሐሺን ጨምሮ ሌሎች የሥራ ኃላፊዎችን አነጋግሯል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ በሶማሊ ክልል ከሀገራዊ ለውጡ በፊት በማረሚያ ቤቶች እና በፖሊስ ጣቢያዎች ሲፈጸሙ የነበሩ ድብደባ እና ሌሎች የማሰቃየት ተግባራት እንዲሁም ስልታዊ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች መቅረታቸው፣ ለታራሚዎች ከሌሎች ክልሎች የተሻለ የቀን ፍጆታ በጀት መመደቡ፣ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው በመመለስ እና በማቋቋም ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት ጥረቶች መደረጋቸው እና የሽግግር ፍትሕን ተግባራዊ ለማድረግ እርምጃዎች መወሰዳቸው አበረታች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

🔗 https://ehrc.org/?p=34648

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
📢 ዝግጁ ናችሁ?!
...

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በ5ኛው ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል በፎቶግራፍ እና በአጫጭር ፊልሞች ዘርፍ እንዲወዳደሩ ይጋብዝዎታል።

በውድድሩ ስለ ትምህርት መብት 📷በፎቶግራፍ እንዲሁም ስለ ነጻነት መብት 🎬በአጭር ፊልም እይታዎን ይሰንዱ ከዚያም ለውድድር ይላኩት፡፡ ለአሸናፊዎች ዳጎስ ያለ ሽልማት፣ ዕውቅና እና ምስጋና ተዘጋጅቷል፡፡

ይወዳደሩ! የኪነጥበብ ዐቅምዎን ተጠቅመው ለሰብአዊ መብቶች መስፋፋት አሻራ ያኑሩ!

ለመሳተፍ እና ለተጨማሪ መረጃ፡- https://filmfest.ehrc.org

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsFilmFestival
2025/10/22 16:59:29
Back to Top
HTML Embed Code: