Telegram Web Link
#ትግራይ፦ ወደ ቀድሞ የመኖሪያ አካባቢያቸው እንዲመለሱ የተደረጉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ የተከናወነ ክትትል
...

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ምክንያት ተፈናቅለው በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተጠልለው ከቆዩ በኋላ በደቡባዊ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች ወደሚገኙ የቀድሞ መኖሪያ አካባቢዎቻቸው እንዲመለሱ የተደረጉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ በተመለከተ ከነሐሴ 19 እስከ ጷጉሜን 1 ቀን 2016 ዓ.ም. ክትትል በማከናወን ያዘጋጀውን ባለ 11 ገጽ ሪፖርት ዛሬ ይፋ አድርጓል። ክትትሉ የተደረገው ኢሰመኮ ከዚህ ቀደም በክልሉ የሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ በተመለከተ ክትትሎችን በማከናወን በተለያዩ ጊዜያት መግለጫዎችን እና ሪፖርቶችን ይፋ ሲያደርግ እንዲሁም ተፈናቃዮች ዘላቂ መፍትሔ በሚያገኙበት ሁኔታ ላይ የሚያደርገውን ክትትልና ውትወታ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ሲገልጽ በቆየው መሠረት ነው።

ጋዜጣዊ መግለጫ፦ https://ehrc.org/?p=32253

ሙሉ ሪፖርቱን ያንብቡ፦ https://ehrc.org/download/?p=32255

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
👍3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ #HumanRights Concept: በሥነ-ጥበብ ሐሳብን የመግለጽ እና የፈጠራ ነጻነት
...

የሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን፣ አንቀጽ 19 (2) እና የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ እና የባህል መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን፣ አንቀጽ 15 (1) (ሐ)

ማንኛውም ሰው በሥነ-ጥበብ መልክ ሐሳቡን በነጻነት የመግለጽ መብት አለው።

አባል ሀገራት የማንኛውንም ሰው ከሥነ-ጽሑፋዊ ወይም ከሥነ-ጥበባዊ የሥራ ውጤቱ የሚመነጨውን የሞራል እና ቁሳዊ ጥቅም የማግኘት መብት ዕውቅና ይሰጣሉ።

የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 41 (9)

መንግሥት የባህልና የታሪክ ቅርሶችን የመጠበቅ እና የመንከባከብ እንዲሁም ለሥነ-ጥበብ መስፋፋት አስተዋጽዖ የማድረግ ኃላፊነት አለበት።

🔗 https://ehrc.org/?p=32361

#Ethiopia🇪🇹 #KeepWordSafe #ጤናማቃላት

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
👍31
Advancing the Business and Human Rights Agenda in Ethiopia
...
The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) in collaboration with the Ministry of Justice, the Danish Institute for Human Rights and Friedrich-Ebert-Stiftung, organized a two-day series of workshops on April 8-9, 2025, focused on the development of Ethiopia’s National Action Plan (NAP) on Business and Human Rights and its methodologies. The events brought together members of the National Action Plan Technical Committee, including representatives from government ministries, the Confederation of Ethiopian Trade Unions, the Confederation of Ethiopian Employers’ Associations and civil society organizations. International partners in attendance included the United Nations Office of the High Commissioner for Human Rights, the Danish Institute for Human Rights and Friedrich-Ebert-Stiftung.

🔗 https://ehrc.org/?p=32408

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
በወንጀል ፍትሕ ሥርዓት የጥቃት ተጎጂ ሴቶች እና ሕፃናት መብቶች አያያዝ ላይ በተሰጡ ምክረ ሐሳቦች አተገባበር ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተካሄደ ውይይት
...

የጥቃት ተጎጂ ሴቶች እና ሕፃናት መብቶች አያያዝ ከመደበኛው የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ በተለየ የሕግ ማዕቀፍ ሊደገፍ ይገባል

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ውስጥ የጥቃት ተጎጂ ሴቶች እና ሕፃናት መብቶች አያያዝን በተመለከተ በ2016 ዓ.ም. ለሕዝብ ይፋ ባደረገው የክትትል ሪፖርት የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች አተገባበር ዙሪያ ባከናወነው ክትትል የተለዩ ግኝቶች ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር መጋቢት 25 ቀን 2017 ዓ.ም. በቢሾፍቱ ከተማ ውይይት አካሂዷል። በውይይቱ የጤና ሚኒስቴር፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተቋማት፣ በሴቶችና እና በሕፃናት መብቶች ላይ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም ከአፋር፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ሐረሪ፣ ኦሮሚያ፣ ሲዳማ እና ሶማሊ፣ ክልሎች እና ከሸገር ከተማ አስተዳድር የተውጣጡ አቻ ተቋማት ተሳትፈዋል።

🔗 https://ehrc.org/?p=32439

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ #HumanRights Concept: ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ የሥራ አካባቢ
...

የዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት ስምምነት ቁጥር 155 –  የሥራ ላይ ደኅንነት እና ጤና ስምምነት፣ አንቀጽ 16 

አሠሪዎች በቁጥጥራቸው ሥር ያሉ የሥራ ቦታዎች፣ ማሽኖች፣ መሣሪያዎች እና የአሠራር ሂደቶች ምክንያታዊና ተግባራዊ ሊሆን በሚችለው መጠን ደኅንነታቸው የተጠበቀ እና ምንም የጤና ሥጋት የማያስከትሉ መሆናቸውን እንዲያረጋግጡ ሊደረጉ ይገባል።

አሠሪዎች ተገቢውን የመከላከያ እርምጃ ሲወስዱ፣ በቁጥጥራቸው ሥር ያሉ ኬሚካላዊ፣ ቁሳዊ እና ሥነ-ሕይወታዊ ንጥረ-ነገሮች እና መሣሪያዎች ምክንያታዊና ተግባራዊ ሊሆን በሚችለው መጠን ለጤና አደጋ የሌላቸው መሆኑን እንዲያረጋግጡ ሊደረጉ ይገባል።

የአደጋ ሥጋትን ወይም አሉታዊ የጤና ተጽዕኖዎችን ምክንያታዊና ተግባራዊ ሊሆን በሚችለው መጠን ለመከላከል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አሠሪዎች በቂ የደኅንነት መጠበቂያ ልብሶችንና መሣሪያዎችን እንዲያቀርቡ ሊደረጉ ይገባል።

🔗 https://ehrc.org/?p=32514

#Ethiopia🇪🇹 #DecentWork #SocialJustice #ThisWayToSocialJustice #KeepWordSafe #ጤናማቃላት

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
👍1
የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ የተካሄደ ውይይት
...

አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን ለማካተት እና ትምህርትን ተደራሽ ለማድረግ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ያስፈልጋል

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በልዩ አዳሪ እና አካቶ ቅድመ መደበኛ፣ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ አስመልክቶ ባከናወነው ክትትል የተለዩ ግኝቶች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ዙር ውይይት አካሂዷል፡፡ በውይይቱ ላይ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ እና ባሕር ዳር ከተሞች የተውጣጡ ባለድርሻዎች ተሳትፈዋል፡፡ ክትትሉ በአዲስ አበባ፣ በአምቦ፣ በባህር ዳር፣ በቢሾፍቱ፣ በባኮ፣ በጋምቤላ፣ በሆሳዕና፣ በመቐለ፣ በሰበታ እና በሻሸመኔ በተመረጡ ትምህርት ቤቶች የተካሄደ ነው።

በውይይት መድረኩ በክትትሉ የተለዩ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን በትምህርት ወቅት የሚያጋጥሟቸው ተግዳሮቶች የቀረቡ ሲሆን ምንም እንኳን በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች የተሻሻሉ ሁኔታዎች ቢኖሩም የትምህርት ቤቶቹ መማሪያ ክፍሎች፣ የአስተዳደር ቢሮዎች እንዲሁም የውስጥ እና የውጭ አካባቢ የተደራሽነት ክፍተት ያለባቸው መሆኑ፣ በአዲሱ የትምህርት ካሪኩለም መሠረት የተዘጋጁ የመማሪያ መጽሐፍት በምልክት ቋንቋ እና በብሬል ተተርጉመው አለመቅረባቸው እንዲሁም በቂ የሰለጠነ የሰው ኃይል አለመኖር ከተጠቀሱ ተግዳሮቶች መካከል ናቸው።

🔗 https://ehrc.org/?p=32542

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
👍1
በክልል ደረጃ ሲካሄድ የቆየው 5ኛው ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሰብአዊ መብቶች ምስለ ችሎት ውድድር ተጠናቀቀ
...

ውድድሩን በበላይነት ካጠናቀቁት 14 ትምህርት ቤቶች መካከል በጽሑፍ ክርክር የላቀ ነጥብ የሚያስመዘግቡ 8 ቡድኖች በግንቦት ወር በአዲስ አባባ ከተማ በሚካሄደው ሀገር አቀፍ ውድድር ተሳታፊ ይሆናሉ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ለ5ኛ ጊዜ የሚያካሂደው ዓመታዊ ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሰብአዊ መብቶች ምስለ ችሎት ውድድር የመጀመሪያው ምዕራፍ በክልል ደረጃ በተካሄደ ውድድር ተጠናቋል። ውድድሩ በ12 ክልሎች እና በ2 ከተማ አስተዳደሮች የተካሄደ ሲሆን ከ77 ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ 154 ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል። እንዲሁም መምህራን፣ የትምህርት ቤቶች ዳይሬክተሮች፣ የትምህርት ቢሮዎች ተጠሪዎች፣ ተማሪዎች እና የተማሪዎች ወላጆች በታዳሚነት ተገኝተዋል። 

የዚህ ዓመት የምስለ ችሎት ውድድር ለልማት ሲባል በግዳጅ ከመፈናቀል ጋር የተያያዙ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች (Development-based Forced Eviction and Human Rights) ላይ የሚያተኩር ነው። ውድድሩም ተማሪዎች ምናባዊ በሆነ ጉዳይ (Hypothetical Case) ላይ በመመርኮዝ የአመልካች እና የተጠሪ ወገንን ወክለው የጽሑፍ እና የቃል ክርክር የሚያደርጉበት ነው። የመደበኛ ፍርድ ቤት የክርክር ሥርዓትን የሚከተለው ይህ ውድድር በተወዳዳሪ ተማሪዎች እና በትምህርት ቤቶች ማኅበረሰብ ዘንድ የሰብአዊ መብቶች ዕውቀትንና ክህሎትን ለመገንባት ያለመ ነው

🔗 https://ehrc.org/?p=32551

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
በኢንዱስትሪ ፓርኮችና ፋብሪካዎች ውስጥ በሚሠሩ ሴቶች መብቶች ላይ አተኩረው በተከናወኑ ክትትሎች ላይ የተካሄደ ውይይት
...

የሴት ሠራተኞች ሰብአዊ መብቶች በተሟላ ሁኔታ መከበራቸውን ለማረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሠሩ ይገባል

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ሸገር ሲቲ እና ሃዋሳ ከተሞች በሚገኙ ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ፋብሪካዎች ውስጥ ተቀጥረው የሚሠሩ ሴቶችን መብቶች አያያዝ በተመለከተ ሚያዝያ 2 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል። ውይይቱ ኢሰመኮ በኅዳር ወር 2017 ዓ.ም. በአዳማ እና ሃዋሳ ከተሞች በሚገኙ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ሥር ባሉ 5 ፋብሪካዎች ባከናወነው ሁለተኛ ዙር የምክረ ሐሳቦች አተገባበር ክትትል እንዲሁም በታኅሣሥ ወር 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ሥር እና በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ በሚገኙ 8 ፋብሪካዎች ባደረገው የሰብአዊ መብቶች ክትትል ግኝቶች ላይ ያተኮረ ነው።

በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የኦሮሚያ እና የሲዳማ ክልሎች ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮዎች፣ የጤና እና የኢንቨስትመንት ቢሮዎች፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች እንዲሁም የሲቪል ማኅበራት ተወካዮች ተሳትፈዋል።

🔗 https://ehrc.org/?p=32615

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
👍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ #HumanRights Concept: የፕሬስ ነጻነት እና ሐሳብን በነጻ የመግለጽ መብት
...

የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 29

ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሐሳቡን የመግለጽ ነጻነት አለው።
የፕሬስ እና የሌሎች መገናኛ ብዙኃን እንዲሁም የሥነ ጥበብ ፈጠራ ነጻነት ተረጋግጧል።
የፕሬስ ነጻነት በተለይ የቅድሚያ ምርመራ በማንኛውም መልኩ የተከለከለ መሆኑን እና የሕዝብን ጥቅም የሚመለከት መረጃ የማግኘት ዕድልን ያካትታል።

የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2021፣ አንቀጽ 86(1)

በመገናኛ ብዙኃን አማካይነት የወንጀል ድርጊት በመፈጸም የተጠረጠረ ማንኛውም ሰው ወይም አካል በወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች መሠረት ለተጨማሪ ምርመራ በእስር እንዲቆይ ሳይደረግ ክሱ በቀጥታ በዐቃቢ ሕግ አማካኝነት ለፍርድ ቤት መቅረብ አለበት።

🔗  https://ehrc.org/?p=32623

#Ethiopia🇪🇹 #WorldPressFreedomDay #WPFD2025 #PressFreedom #KeepWordSafe #ጤናማቃላት

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
👍1
ነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ብሔራዊ ኮንፈረንስ
...

ጥራቱ የተጠበቀ ነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎትን ተደራሽ ማድረግ የሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ኃላፊነት ነው

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ተደራሽነት እና ጥራት ላይ ሚያዝያ 15 እና 16 ቀን 2017 ዓ.ም. ብሔራዊ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ከተማ አካሂዷል። የብሔራዊ ኮንፈረንሱ ዓላማ በፍትሕ ሥርዓቱ በተለይ በወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ሂደት የሚሰጥ ነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት በነባራዊ ጉዳዮች እና በሚስተዋሉ ተግዳሮቶች ዙሪያ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በትብብርና በቅንጅት ለመፍታት የጋራ መወያያ መድረክ መፍጠር ነው።

በኮንፈረንሱ የፍትሕ ሚኒስቴር፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የተከላካይ ጠበቆች ጽሕፈት ቤት፣ ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ የፍትሕ ቢሮና ነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት የሚሰጡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሕግ ትምህርት ቤቶች ተወካዮች እና የሲቪል ማኅበራት እና የግል የጥብቅና ተቋማት ተሳትፈዋል። እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት፣ የአውሮፓ ኅብረት፣ የተባበሩት መንግሥታት የመድኃኒትና የወንጀል ጽሕፈት ቤት፣ የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም፣ የዳኒሽ ሰብአዊ መብቶች ተቋም (DIHR) የአዲስ አበባ እና የዛምቢያ ቢሮ ተወካዮች እና የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ተሳታፊ ሆነዋል።

🔗  https://ehrc.org/?p=32638

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ #HumanRights Concept: የሕይወት፣ የአካል ደኅንነትና የነጻነት መብት
...

የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 14 

 ማንኛውም ሰው ሰብአዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደኅንነትና የነጻነት መብት አለው። 

የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን፣ አንቀጽ 6(1) እና 7

 ማንኛውም ሰው በሕይወት የመኖር ተፈጥሯዊ መብት አለው፡፡ ይህ መብት በሕግ ሊከበር ይገባል፡፡ ማንኛውም ሰው ያለአግባብ ሕይወቱን አያጣም፡፡
ማንኛውም ሰው ለስቃይ ወይም ጭካኔ ለተሞላበት፣ ኢ-ሰብአዊ ወይም ክብርን ለሚያዋርድ አያያዝና ቅጣት ሊዳረግ አይገባም፡፡

🔗 https://ehrc.org/?p=32695 

#Ethiopia🇪🇹 #KeepWordSafe #ጤናማቃላት

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
👍4
Closing the Protection Gap: Advancing the Rights of Older Persons
...

EHRC and GANHRI Call for a Binding International Treaty at UN High-Level Meeting

The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) joined global leaders and human rights advocates at the United Nations Headquarters in New York on May 8, 2025, for a High-Level Meeting convened by the President of the General Assembly on Ageing.

Held under the theme of exchanging views on the recommendations outlined in Decision 14/1 of the Open-ended Working Group on Ageing, the meeting brought together Member States, UN bodies and civil society to address the rights and well-being of older persons and define next steps toward stronger legal protections.

🔗 https://ehrc.org/?p=32721

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
4
Consultation: Strategy for the Participation of Victims and Vulnerable Sections of Society in the Transitional Justice Process in Ethiopia
...

The participation of victims and vulnerable sections of society must be transformative, empowering, and should drive the TJ process based on their lived experiences

The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) and the Office of the High Commissioner for Human Rights—East Africa Regional Office (OHCHR-EARO) in view of their respective mandates to enhance human rights compliance, inclusion, and victim-centeredness in Ethiopia’s transitional justice (TJ) process organized a consultation on the draft Strategy for the Participation of Victims and Vulnerable Sections of Society in the Ethiopian Transitional Justice (TJ) process on April 29, 2025, in Addis Ababa.

🔗 https://ehrc.org/?p=32725

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ #HumanRights Concept: ቤተሰብ የመመሥረት መብት
...

ሁሉ አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ፣ አንቀጽ 16 (1) እና (2)

ዕድሜያቸው ለጋብቻ የደረሰ ወንዶች እና ሴቶች በዘር፣ በዜግነት ወይም በሃይማኖት ልዩነት ሳይደረግባቸው ጋብቻ የመፈጸም እና ቤተሰብ የመመሥረት መብት አላቸው። ጋብቻው ሲፈጸም፣ በጋብቻ ወቅት እና ጋብቻው በሚፈርስበት ጊዜ እኩል መብቶች አሏቸው።

ጋብቻ በተጋቢዎች ነጻ እና ሙሉ ፈቃድ ላይ ብቻ ይመሠረታል።

የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት፣ አንቀጽ 34 (3)

ቤተሰብ የኅብረተሰብ ተፈጥሯዊ እና መሠረታዊ መነሻ ነው። ከኅብረተሰብና ከመንግሥት ጥበቃ የማግኘት መብት አለው።

🔗 https://ehrc.org/?p=32750

#Ethiopia🇪🇹 #KeepWordSafe #ጤናማቃላት

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
👍1
ሰብአዊ መብቶችን ማስፋፋት፦ በ2017 ዓ.ም. በሦስተኛው ሩብ ዓመት የተሰጡ ስልጠናዎች
...

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከጥር 1 እስከ መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም. ባለው ጊዜ በሰብአዊ መብቶች እና በሽግግር ፍትሕ፣ በሕፃናት፣ በታራሚዎች፣ በአረጋውያን እና በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መብቶች ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎችን በተለያዩ ከተሞች ሰጥቷል።

በሰብአዊ መብቶች እና በሽግግር ፍትሕ ዙሪያ የወጣቶችን ሚና ለማሳደግ ያለሙ ስልጠናዎች ከተለያዩ ወጣት ማኅበራት ለተውጣጡ 63 አመራሮች እና አባላት ከየካቲት 10 እስከ 14 ቀን 2017 ዓ.ም. በአርባምንጭ ከተማ እና ከመጋቢት 15 እስከ 19 ቀን 2017 ዓ.ም. በሶዶ ከተማ ተሰጥቷል። በተመሳሳይ የማሕበረሰብ እና የሃይማኖት መሪዎችን ትኩረት ያደረጉ በድምሩ 64 ተሳታፊዎች የተሳተፉባቸው ስልጠናዎች ከየካቲት 4 እስከ 6 ቀን 2017 በጅማ እና ቢሾፍቱ ከተሞች ተከናውነዋል። በስልጠናዎቹ ስለ ሽግግር ፍትሕ ጽንሰ ሐሳብ፣ የሌሎች ሀገራት የሽግግር ፍትሕ ተሞክሮዎች እና በሂደቱ ታሳቢ ሊደረጉ የሚገቡ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች የቀረቡ ሲሆን ክህሎትን የሚያሳድጉ ተግባራዊ ልምምዶች ተካተዋል።

በሰብአዊ መብቶች እና በሽግግር ፍትሕ ዙሪያ ከአዲስ አበባ ከተማ እና ከኦሮሚያ ክልል ለተውጣጡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሠራተኞች እና የሥራ ኃላፊዎች በአዳማ ከተማ ከመጋቢት 1 እስከ 5 ቀን 2017 ዓ.ም. የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጥቷል።

🔗 https://ehrc.org/?p=32785

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
83rd Ordinary Session of the African Commission on Human and Peoples’ Rights in Banjul, The Gambia
...

EHRC will closely follow the African Commission’s recommendations in response to Ethiopia’s report and monitor implementation

The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) delegation, comprising of Chief Commissioner Berhanu Adello, Commissioner for Civil, Political and Socio-Economic Rights Dr. Abdi Jibril and other senior officials, participated in the 83rd Ordinary Session of the African Commission on Human and Peoples’ Rights (African Commission), in Banjul, The Gambia from May 2 to 12, 2025.

🔗 https://ehrc.org/?p=32844

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
Advancing Peace, Justice and Inclusion Through Strengthened Partnerships and Collective Action
...

EHRC took part in the 2025 Sustainable Development Goal 16 (SDG 16) Conference held at UN Headquarters in New York

The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) participated in the 2025 SDG 16 Conference held at UN Headquarters in New York under the theme “Advancing Peace, Justice and Institutions for Sustainable Development” on May 12, 2025. The conference convened global leaders and stakeholders from government, civil society, and multilateral organizations to assess progress and define next steps in delivering on Sustainable Development Goal 16 (SDG 16) as a foundation for broader achievement of the 2030 Agenda. The event was co-hosted by the UN Department of Economic and Social Affairs, the Permanent Mission of Italy, and the International Development Law Organization.

🔗 https://ehrc.org/?p=32848

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
1
የሴት ልጅ ግርዛትን አስመልክቶ በሚካሄድ ግልጽ የምርመራ መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተካሄደ ውይይት
...

በሴቶች ላይ የሚፈጸም ግርዛት እና ተደጋጋሚ ግርዛትን ለማስቆም ማኀበረሰብን ማንቃት፣ ለተጎጂዎች ድጋፍ ማድረግ እና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአፋር እና በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በሴት ልጅ ግርዛት ላይ ስለሚያካሂደው ግልጽ የምርመራ መድረክ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ሚያዝያ 28 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ውይይት አካሂዷል። የውይይቱ ዓላማ የግልጽ ምርመራ መድረኩ ቁልፍ ባለድርሻ አካላትን ማሳወቅ እና አስፈላጊ በሆኑ በትብብርና እገዛዎች ላይ መወያየት ነው።

በውይይቱ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው ፍትሕ ሚኒስቴር፣ ሴቶችና ማኀበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ከአፋር እና ከማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች የሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ ቢሮ፣ ፍትሕ ቢሮ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ጤና ቢሮ፣ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፣ የሀዲያ ዞን ሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ፣ የፍትሕ፣ የፖሊስ እና ጤና ጽሕፈት ቤት የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል። በተጨማሪም በሴት ልጅ ግርዛት ላይ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች እና የኢሰመኮ የከተማ ጽሕፈት ቤቶች የሴቶች እና የሕፃናት መብቶች ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

🔗 https://ehrc.org/?p=32857

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
👍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ #HumanRights Concept: የሴቶች የጤና መብት
...

በሴቶች ላይ የሚደረግ ማንኛውንም አድሎአዊ ልዩነት ለማስወገድ የተደረገ ስምምነት፣ አንቀጽ 12 (1)

አባል ሀገራት የወንዶች እና የሴቶች እኩልነትን መሠረት በማድረግ የቤተሰብ ምጣኔን ጨምሮ የጤና ጥበቃ አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ በጤና ጥበቃ ዘርፍ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን አድልዎ ለማስወገድ ተገቢውን እርምጃ ሁሉ ይወስዳሉ።

የአፍሪካ የሰዎችና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል)፣ አንቀጽ 14 (2) (ሀ)

አባል ሀገራት ለሴቶች በተለይም በገጠር ለሚገኙ የመረጃ፣ የትምህርት እና የግንኙነት መርኃ ግብሮችን ጨምሮ በቂ፣ ተመጣጣኝ እና ተደራሽ የጤና አገልግሎቶችን  ለመስጠት አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ ይወስዳሉ።

🔗 https://ehrc.org/?p=33013

#Ethiopia🇪🇹 #KeepWordSafe #ጤናማቃላት

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
በሕክምና ተቋማት ውስጥ በመካሄድ ላይ የሚገኘውን የሥራ ማቆም አድማ በተመለከተ
...

በሕክምና ተቋማት በመካሄድ ላይ ያሉ የሥራ ማቆም አድማዎች ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች በር እንዳይከፍቱ ትኩረት ሊሰጣቸው እና ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኙ ማድረግ ይገባል

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሕክምና ባለሙያዎች በሕክምና ተቋማት ውስጥ በማድረግ ላይ የሚገኙት የሥራ ማቆም አድማ እንዲሁም ይህንን ተከትሎ በመንግሥት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንዳያስከትሉ ትኩረት ሊሰጣቸው እና አፋጣኝ መፍትሔ ሊያገኙ እንደሚገባ ያሳስባል።

ኢሰመኮ አንዳንድ የሕክምና ባለሙያዎች የደመወዝ እና ከሥራ ሁኔታ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን መንግሥት እንዲመልስ ሰጥተናል ያሉት የ30 ቀናት የጊዜ ገደብ ግንቦት 3 ቀን 2017 ዓ.ም. መጠናቀቁን ተከትሎ በመንግሥት እና በሕክምና ባለሙያዎች በመወሰድ ላይ የሚገኙትን እርምጃዎች በመከታተል ላይ ይገኛል። በዚህም መሠረት ኢሰመኮ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ ከአጋሮ፣ ከአርባ ምንጭ፣ ከባሕር ዳር፣ ከፍቼ፣ ከጎባ፣ ከሃዋሳ እና ከጅማ ከተሞች መረጃ ማሰባሰብ ችሏል።

🔗 https://ehrc.org/?p=33103

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
👍3
2025/10/22 10:21:18
Back to Top
HTML Embed Code: