Telegram Web Link
በሕክምና ተቋማት ውስጥ በመካሄድ ላይ የሚገኘውን የሥራ ማቆም አድማ በተመለከተ
...

በሕክምና ተቋማት በመካሄድ ላይ ያሉ የሥራ ማቆም አድማዎች ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች በር እንዳይከፍቱ ትኩረት ሊሰጣቸው እና ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኙ ማድረግ ይገባል

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሕክምና ባለሙያዎች በሕክምና ተቋማት ውስጥ በማድረግ ላይ የሚገኙት የሥራ ማቆም አድማ እንዲሁም ይህንን ተከትሎ በመንግሥት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንዳያስከትሉ ትኩረት ሊሰጣቸው እና አፋጣኝ መፍትሔ ሊያገኙ እንደሚገባ ያሳስባል።

ኢሰመኮ አንዳንድ የሕክምና ባለሙያዎች የደመወዝ እና ከሥራ ሁኔታ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን መንግሥት እንዲመልስ ሰጥተናል ያሉት የ30 ቀናት የጊዜ ገደብ ግንቦት 3 ቀን 2017 ዓ.ም. መጠናቀቁን ተከትሎ በመንግሥት እና በሕክምና ባለሙያዎች በመወሰድ ላይ የሚገኙትን እርምጃዎች በመከታተል ላይ ይገኛል። በዚህም መሠረት ኢሰመኮ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ ከአጋሮ፣ ከአርባ ምንጭ፣ ከባሕር ዳር፣ ከፍቼ፣ ከጎባ፣ ከሃዋሳ እና ከጅማ ከተሞች መረጃ ማሰባሰብ ችሏል።

🔗 https://ehrc.org/?p=33103

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
👍3
ጥገኝነት የመጠየቅ መብት ስንል ምን ማለታችን ነው?
...

ጥገኝነት የመጠየቅ መብት ማለት ከግጭት ወይም አደጋ የሚያመልጡ ሰዎች በሌላ ሀገር ከለላ የሚያገኙበት ሥነ ሥርዓት ነው። ሰዎች ለጥገኝነት ሲያመለክቱ በዘራቸው፣ በሃይማኖታቸው፣ በብሔራቸው፣ በፖለቲካ አስተሳሰባቸው ወይም በአንድ የተወሰነ ማኅበራዊ ቡድን ውስጥ አባል በመሆናቸው ምክንያት የሚፈጸም ጥቃት ስለሚያስፈራቸው ጥበቃ እንዲደረግላቸው ነው። ከለላ ለማግኘትም ወደ ሀገራቸው ቢመለሱ በእርግጥ ወይም በተጨባጭ ሊደርስባቸው የሚችል ማሳደድ፣ ማሠቃየት፣ መንገላታት ስለመኖሩ ማሳየት አለባቸው።

ጥገኝነት የመጠየቅ መብት የሕግ መሠረቶች ምንድን ናቸው?

ዓለም አቀፍ እና ብሔራዊ የሕግ ማዕቀፎች ተጨባጭ ከሆነ ጥቃት/ጭቆና ጥበቃ ለማግኘት ጥገኝነት የመጠየቅ መብትን እና ሂደቶችን ይደነግጋሉ። ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ (Universal Declaration of Human Rights) አንቀጽ 14 ከጥቃት/ጭቆና ሸሽቶ በሌሎች ሀገሮች ጥገኝነት የመጠየቅ መብትን እውቅና ሰጥቷል። ማን እንደ ስደተኛ እንደሚቆጠር እና ሀገራት ለጥገኝነት ጠያቂዎች ከለላ ለመስጠት ያለባቸውን ግዴታዎች ከመዘርዘር አኳያ እ.ኤ.አ. በ1951 የወጣው የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ስምምነት እና እ.ኤ.አ. በ1967 የስደተኞች ሁኔታን ለመደንገግ የወጣው ፕሮቶኮል ጥገኝነትን ለተመለከቱ ሕጎች መሠረት በመሆን ያገለግላሉ።

🔗 https://ehrc.org/?p=33120

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
👍5
የትምህርት መብት፡- በአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ የተካሄደ ውይይት
...

የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን የትምህርት መብት ለማረጋገጥ የትምህርት ግብአት አቅርቦት፣ ከባቢያዊ እና የመረጃ ተደራሽነት እንዲሁም የአመለካከት ክፍተቶች ላይ መሥራት ያስፈልጋል

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በልዩ አዳሪ እና አካቶ ቅድመ መደበኛ፣ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን አስመልክቶ ከአዲስ አበባ፣ አምቦ፣ ባሕር ዳር፣ ቢሾፍቱ፣ ባኮ፣ ጋምቤላ፣ ሆሳዕና፣ መቐለ፣ ሰበታ እና ሻሸመኔ በተመረጡ ትምህርት ቤቶች ባከናወነው ክትትል የተለዩ ግኝቶች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሁለት የምክክር መድረኮች በአዲስ አበባ እና ሃዋሳ ከተሞች አካሂዷል።

በውይይት መድረኮቹ የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጨምሮ የማእከላዊ ኢትዮጵያ፣ የጋምቤላ፣ የኦሮሚያ እና የሲዳማ ክልሎች ትምህርት ቢሮዎች፣ ጽሕፈት ቤቶች እና ክትትል የተደረገባቸው ትምህርት ቤቶች ተወካዮች ተሳትፈዋል።

ኢሰመኮ በአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ሰብአዊ መብቶች ዙሪያ የአዲስ አበባ እና የባሕር ዳር ከተሞች ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት ተመሳሳይ የውይይት መድረክ በመጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ማካሄዱ ይታወሳል።

🔗 https://ehrc.org/?p=33164

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

‎በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
👍52
5ኛው ዓመታዊ ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሰብአዊ መብቶች ምስለ-ችሎት (Human Rights Moot Court) ፍጻሜ ውድድር ተካሄደ
...

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) 5ኛውን ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሰብአዊ መብቶች ምስለ-ችሎት (5th National High Schools Human Rights Moot Court Competition) ፍጻሜ ውድድር ግንቦት 22 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ አካሂዷል። ከሚያዚያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲካሄድ በቆየው ውድድር በ12 ክልሎች እና በ2 ከተማ አስተዳደሮች ከሚገኙ 90 ትምህርት ቤቶች 180 ተወዳዳሪ ተማሪዎች ተሳትፈዋል።

በዚሁ መሠረት ተማሪ ሲፈን ደረጄ እና ተማሪ ሚልኬሳ ንጋቱ ከቢሾፍቱ ከተማ የኦሮሚያ ልማት ማኅበር ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ቢሾፍቱ ቅርንጫፍ የፍጻሜ ውድድሩ አሸናፊ ሆነዋል። በተጨማሪም የውድድሩ ምርጥ የቃል ተከራካሪ በመሆን ተማሪ ሲፈን ደረጄ ከኦሮሚያ ልማት ማኅበር ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ቢሾፍቱ ቅርንጫፍ ያሸነፈች ሲሆን በምርጥ የጽሑፍ ክርክር ደግሞ በተመሳሳይ ከኦሮሚያ ልማት ማኅበር ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ቢሾፍቱ ቅርንጫፍ የመጡት ተማሪ ሲፈን ደረጄ እና ተማሪ ሚልኬሳ ንጋቱ አሸናፊዎች ሆነዋል።

🔗  https://ehrc.org/?p=33257

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
👍32🔥1
በማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ በሚገኙ ሕፃናት መብቶች አያያዝ ላይ የተካሄደ ውይይት
...

በማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ሕፃናትን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ለማሻሻል ሁሉም ባለድርሻዎች ምክረ ሐሳቦችን በቅንጅት ሊተገብሩ ይገባል

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ሃዋሳ፣ ሻሸመኔ እና ወላይታ ከተሞች በሚገኙ 21 የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማት ባከናወነው የምክረ ሐሳቦች አፈጻጸም ክትትል ግኝቶች ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ግንቦት 8 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ውይይት አካሂዷል። በውይይቱ የሐረሪ፣ የኦሮሚያ፣ የሲዳማ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች እንዲሁም የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የሴቶች፣ የሕፃናት እና የማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮዎች ኃላፊዎች እንዲሁም የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማት ተወካዮች ተሳትፈዋል።

ኢሰመኮ በማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ ከሚገኙ ሕፃናት መብቶች አያያዝ ጋር በተያያዘ ያከናወነው ክትትል ዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊ እና ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ማዕቀፎችን መሠረት ያደረገ ሲሆን፤ በተለይም የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማት የቅበላ መሥፈርቶች እና መረጃ አያያዝ፣ የሕፃናት ከጥቃት የመጠበቅ መብት፣ የቅጣት (የዲሲፕሊን) እርምጃዎች​፣ የጤና፣ የሥነ ልቦና፣ የትምህርት፣ የጨዋታ እና የመዝናኛ አገልግሎቶች፣ የእምነት ነጻነት እና የተሳትፎ መብቶችን በተመለከተ የተለዩ ግኝቶች፣ አሳሳቢ ሁኔታዎች እና የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

🔗 https://ehrc.org/?p=33299

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ #HumanRights Concept: በሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች የተጎዱ ሕፃናት
...

የሕፃናት መብቶች ስምምነት፣ አንቀጽ 39

ተዋዋይ ሀገራት የማናቸውም ዐይነት የእንክብካቤ እጦት፣ ብዝበዛ፣ ያልተገባ አያያዝ፣ ማሰቃየት ወይም ሌላ ማናቸውም ዐይነት ጭካኔ የተሞላበት፣ ኢ-ሰብአዊ የሆነ ወይም ክብርን የሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት ወይም የትጥቅ ግጭት ሰለባ የሆነን ሕፃን በአካልና በሥነ ልቦና ከደረሰበት ጉዳት እንዲያገግምና ከኅብረተሰቡ ጋር እንዲቀላቀል ለማድረግ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳሉ።

ይህ ዐይነቱ ሕፃኑን ከጉዳቱ እንዲያገግም እና ወደ ኅብረተሰቡ እንዲቀላቀል የማድረግ ተግባር የሕፃኑን ጤንነት፣ ለራስ ዋጋ የመስጠት ስሜት እና ክብር ለማዳበር በሚያመች ሁኔታ ውስጥ መከናወን አለበት።

🔗 https://ehrc.org/?p=33355

#Ethiopia🇪🇹 #KeepWordSafe #ጤናማቃላት

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
1
ሀገር አቀፍ ውይይት፦ የሰብአዊ መብቶች ክትትል፣ ምርመራ እና ስነዳ
...

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከፕሮጀክት ኤክስፔዳይት ጀስቲስ (Project Expedite Justice, PEJ) ጋር በመተባበር በሰብአዊ መብቶች ክትትል፣ ምርመራ እና ስነዳ ላይ ሀገር አቀፍ የውይይት መድረክ ግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ አካሂዷል።

በኢሰመኮ፣ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና ሌሎች ባለድርሻዎች መካከል ያለውን ትብብርና ቅንጅት ማጠናከርን ዓላማ ባደረገው ውይይት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በሲዳማ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች በሰብአዊ መብቶች ላይ የሚሠሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እና ነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ሰጪ አካላት ተሳትፈዋል።

በውይይት መድረኩ ኢሰመኮን ጨምሮ የሦስት ተቋማት የሰብአዊ መብቶች ክትትል፣ ምርመራ እና ስነዳን የተመለከቱ ገለጻዎች፣ መልካም ተሞክሮዎች እና ተግዳሮቶች ቀርበዋል። በኢሰመኮ የሰብአዊ መብቶች ክትትል፣ ምርመራ እና ስነዳ ፅንሰ ሐሳባዊ ማብራሪያ፣ የሰብአዊ መብቶች ስነዳ ዐይነቶች፣ የስነዳ አስፈላጊነት፣ በሰብአዊ መብቶች ጥበቃ እና ማስፋፋት ላይ ኢሰመኮ እና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የሚጋሯቸው ጉዳዮች፣ በሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ መካከል ያለው ልዩነት እና አንድነት እንዲሁም ተግባራዊ ሊሆኑ የሚገቡ የሰብአዊ መብቶች መርሖች፣ የሰብአዊ መብቶች ክትትል፣ ምርመራ እና ስነዳ ወሰን (scope) እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ገለጻ ተድርጓል።


🔗 https://ehrc.org/?p=33387

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
1👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ #HumanRights Concept: የሕፃናት ከጉልበት ብዝበዛ የመጠበቅ መብት
...

የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 36(1) (መ)

ማንኛውም ሕፃን ጉልበቱን ከሚበዘብዙ ልማዶች የመጠበቅ፤ በትምህርቱ፣ በጤናውና በደኅንነቱ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሥራዎችን እንዲሠራ ያለመገደድ ወይም ከመሥራት የመጠበቅ መብት አለው።

ዓለም አቀፉ የሕፃናት መብቶች ስምምነት፣ አንቀጽ 32(2) (ሀ-ሐ)

ተዋዋይ ሀገራት በተለይ፡-

ዝቅተኛ የቅጥር ዕድሜን ወይም ዕድሜዎችን ይወስናሉ፤
የሥራ ሰዓትንና የቅጥር ሁኔታዎችን በተመለከተ ተገቢውን ደንብ ያወጣሉ፤
ይህ አንቀጽ በሚገባ በሥራ ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ ተገቢ ቅጣቶችን ወይም ሌሎች ክልከላዎችን ያስቀምጣሉ።

🔗 https://ehrc.org/?p=33411

#Ethiopia🇪🇹 #EndChildLabour #KeepWordSafe #ጤናማቃላት

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
👍21
Regional Meeting on Family Law Reform and Women’s Rights in the Greater Horn of Africa (GHOA)
...

The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) participated in the Regional Conference on Revitalizing Advocacy for Family Law Reform and Strengthening Regional Collaboration to Counter Backlash Against Women’s Rights in the Greater Horn of Africa, held in Kampala, Uganda, from May 28-29, 2025.

Organized by Strategic Initiative for women in the Horn of Africa (SIHA) and partners of the Africa Family Law Network (AFLN), the conference brought together government representatives, national human rights institutions, scholars specializing in family law, women’s rights organizations, grassroots activists, community and religious leaders, persons with disabilities and influential community actors across GHOA.

🔗 https://ehrc.org/?p=33416

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
👍21
በነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ላይ የተካሄደ የባለሙያዎች ውይይት
...

በሀገር አቀፍ ደረጃ የነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎትን ጥራት እና ተደራሽነት ለማሻሻል የተጀመሩ ጥረቶች ውጤት እንዲያስገኙ ኢሰመኮ የበኩሉን አስተዋጽዖ ማድረጉን ይቀጥላል

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ጥራት እና ተደራሽነት ረገድ የተጀመሩ ጥረቶችን ለማጠናከር ያለመ የባለሙያዎች ውይይት ግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ አካሂዷል።

ኢሰመኮ ሚያዝያ 15 እና 16 ቀን 2017 ዓ.ም. የነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎትን አስመልክቶ ባካሄደው ብሔራዊ ኮንፈረንስ ማጠቃለያ ላይ በዘርፉ ከሚሠሩ የፌዴራል እና የክልል መንግሥት ተቋማት፣ የዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤቶች፣ የአዲሰ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰብአዊ መብቶች ማእከል እና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ተውጣጥቶ የተቋቋመው የባለሙያዎች ኮሜቴ አባላት እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት የምሥራቅ አፍሪካ ቢሮ እና የዴንማርክ ሰብአዊ መብቶች ተቋም ተወካዮች በውይይቱ ላይ በአማካሪነት ተሳትፈዋል።

በመድረኩ ፍትሕ ሚኒስቴር በተለያዩ የውይይት መድረኮች በተሰጡ አስተያየቶችና ግብአቶች መሠረት ያሻሻላቸው የነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ረቂቅ አዋጅ ይዘቶች ለኮሚቴው ቀርበው ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ውይይት ተደርጎባቸዋል።

🔗 https://ehrc.org/?p=33424

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ #HumanRights Concept: በትጥቅ ግጭቶች ውስጥ የሴቶች ጥበቃ
...

የአፍሪካ የሰዎችና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል)፣ አንቀጽ 1(በ)፣ 4(2)(ለ) እና 11(1)

አባል ሀገራት በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ሁሉም ዐይነት ጥቃቶችን የሚከለክሉ ሕጎችን ለማውጣት እና ለማስፈጸም ተገቢ እና ውጤታማ እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው። በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃት በሰላም ጊዜ እንዲሁም በትጥቅ ግጭት ወይም ጦርነት ጊዜ የሚፈጸሙ የጥቃት ድርጊቶችን ያጠቃልላል።

አባል ሀገራት በሕዝብ በተለይም በሴቶች ላይ ተጽዕኖ በሚያደርሱ የትጥቅ ግጭት ሁኔታዎች ውስጥ ተፈጻሚነት ያላቸውን ዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ ደንቦች የማክበር እና የማስከበር ግዴታ አለባቸው።

🔗 https://ehrc.org/?p=33463

#Ethiopia🇪🇹 #KeepWordSafe #ጤናማቃላት

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
1
Consultation: Ethiopia’s draft state report on the implementation of the International Covenant on Economic, Social and Cultural Rights (ICESCR)
...

The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) in collaboration with the Ministry of Justice (MoJ), organized a Consultation Meeting on Ethiopia’s 4th and 5th draft state report on the implementation of the International Covenant on Economic, Social and Cultural Rights (ICESCR) on June 13, 2025, in Bishoftu City.

The meeting brought together members of the state report drafting team (Inter-Ministerial Team) and non-state actors including civil society organizations (CSOs), unions and associations to ensure that the report preparation process is inclusive, participatory and consultative.

🔗 https://ehrc.org/?p=33539

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
5👍1
Event_Update_በተባበሩት_መንግሥታት_ድርጅት_የሰብአዊ_መብቶች_ኮሚቴ_ለኢትዮጵያ_የተሰጡ_የማጠቃለያ.png
1.7 MB
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ኮሚቴ ለኢትዮጵያ የተሰጡ የማጠቃለያ ምልከታዎች እና የማራኬሽ መግለጫ ላይ የተካሄደ ውይይት
...

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ኮሚቴ ለኢትዮጵያ የሰጣቸው የማጠቃለያ ምልከታዎች እና የማራኬሽ መግለጫ ላይ ከመንግሥት አስፈጸሚ አካላት ጋር ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ውይይት አካሂዷል። ውይይቱ ኮሚቴው ለኢትዮጵያ የሰጣቸውን ምልከታዎች እና የማራኬሽ መግለጫን ይዘት ለባለድርሻ አካላት ለማስገንዘብ እና በአፈጻጸም ሁኔታ ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ያለመ ነው።

በመድረኩ የዓለም አቀፍ የሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን አፈጻጸምን በተመለከተ ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ ያቀረበችውን ወቅታዊ ሪፖርት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ኮሚቴ ጥቅምት 7 እና 8 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው ግምገማ ላይ በመመሥረት ጥቅምት 21 ቀን 2015 ዓ.ም. የሰጣቸው የማጠቃለያ ምልከታዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

🔗 https://ehrc.org/?p=33557

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
1👍1
በአረጋውያን ላይ የሚደርስ ጥቃትን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተካሄደ ውይይት
...

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በየዓመቱ የሚታሰበውን “በአረጋውያን ላይ የሚደርስ ጥቃት ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን” በማስመልከት ከአረጋውያንና ጡረተኞች ብሔራዊ ማኅበር እና ሄልፕኤጅ ኢንተርናሽናል (HelpAge International) ጋር በመተባበር መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ባለድርሻ ተቋማት እና የአረጋውያን ማኅበራት ተወካዮች የተሳተፉበት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ አካሂዷል።

ውይይቱ የዚህ ዓመት ዓለም አቀፍ መሪ ቃል በሆነው “በመንከባከቢያ ማዕከላት የሚገኙ አረጋውያን ላይ ለሚደርሱ ጥቃቶች በመረጃ እና እርምጃ ምላሽ መስጠት” (“Addressing Abuse of Older Adults in Long Term Care Facilities: Through Data and Action”) እንዲሁም የኢትዮጵያ አረጋውያን እና ጡረተኞች ብሔራዊ ማኅበር “በየትኛውም ቦታ እና ሁኔታ የአረጋውያን ጥቃትን በጋራ እንግታ!” በሚለው መሪ ቃል ላይ በመመርኮዝ አረጋውያን ላይ የሚደርሱ የጥቃት ዐይነቶችን የሚያሳዩ እና ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን የሚያስረዱ ገለጻዎች ቀርበው የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱ ተሳታፊ የነበሩ የአረጋውያን ማኅበራት ተወካዮች አረጋውያን ለዘርፈ ብዙ የመብት ጥሰቶች ተጋላጭ እንደሚሆኑ እና በተለይም የኢኮኖሚ ጥገኛ መሆናቸው የጥቃት ተጋላጭታቸውን በእጅጉ እንደሚያሰፋው ተናግረዋል።

🔗 https://ehrc.org/?p=33575

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
👍41
Transitional Justice and Early Warning: EHRC Holds Consultations and Advocacy in Dire Dawa and Harari
...

The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) in collaboration with the United Nations Office of the High Commissioner for Human Rights – East Africa Regional Office (OHCHR-EARO), carried out a series of activities in the Dire Dawa City Administration and Harari Region from June 16 to 20, 2025.

From June 16 to 19, EHRC and OHCHR-EARO held two consecutive consultation sessions with victims of human rights violations. These consultations aimed to raise awareness among victims’ groups about the ongoing Transitional Justice (TJ) process in Ethiopia, highlight the central role of victims, and assess their capacity and local context. The sessions also created a platform for victims’ associations to share experiences and explore opportunities for collaboration across regions.

🔗 https://ehrc.org/?p=33597

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
1
ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር የተካሄደ ስልጠናዊ ውይይት
...

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በዋና ዋና ተግባራት እና ኃላፊነቶቹ እንዲሁም ትኩረት በሚሹ የሰብአዊ መብቶች ዘርፎች ዙሪያ ሰኔ 22 እና 23 ቀን 2017 ዓ.ም. ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ተቋማት ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች እና አባላት ጋር ስልጠናዊ ውይይት አካሂዷል። ስልጠናዊ ውይይቱ ኢሰመኮ ከምክር ቤቱ ጋር ያለውን የሥራ ግንኙነት ለማሳደግ፣ በአዋጅ በተሰጡት ተግባራትና ኃላፊነቶች ላይ ግልጽነት ለመፍጠር፣ እያከናወናቸው የሚገኙ ዋና ዋና ተግባራትን ማስገንዘብ እና ትኩረት በሚሹ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባትን ለመፍጠር ያለመ ነው፡፡

በመድረኩ በብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ተቋማት ምንነት፣ በኢሰመኮ የሪፎርም ሥራዎች፣ የትኩረት መስኮች እና ተግዳሮቶች፣ የሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ ሥራ፣ ኮሚሽኑ የሚሰጣቸው ምክረ ሐሳቦች አፈጻጸም እንዲሁም በሽግግር ፍትሕ ላይ የኢሰመኮ ሚና እና እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት፣ በኢሰመኮ የተለያዩ የዘርፍ መብቶች የሥራ ክፍሎች እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች እንዲሁም ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን የሚመለከት ገለጻ የቀረበ ሲሆን ኢሰመኮ ሰብአዊ መብቶችን ይበልጥ ለማስፋፋት እና ለማስጠበቅ ውጤታማ ሥራ ማከናወን በሚችልባቸው መንገዶች ላይ ከቋሚ ኮሚቴው አባላት ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡

🔗 https://ehrc.org/?p=33613

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
1
የዳኝነት ነጻነትና የፍትሕ አካላት ለሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ያላቸውን ሚና እና የሽግግር ፍትሕን በተመለከተ የተሰጠ ስልጠና
...

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የዳኝነት ነጻነት እና የፍትሕ አካላት ለሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ያላቸውን ሚና እንዲሁም የሽግግር ፍትሕን የተመለከተ ስልጠና ከሰኔ 15 እስከ 18 ቀን 2017 ዓ.ም. በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ቦንጋ እና ሚዛን አማን ከተሞች ሰጥቷል። በስልጠናው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ዳኞች፣ የክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች እንዲሁም የተለያዩ የፍትሕ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

በስልጠናው በሰብአዊ መብቶች ጥበቃ፣ መከበር እና መስፋፋት ረገድ የፍርድ ቤቶች ሚና፣ የዳኝነት ነጻነት፣ የዳኞች ያለመከሰስ መብት የሕግ ማዕቀፍ፣ በሴቶች እና ሕፃናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች እና የባለግዴታዎች ምላሽ አሰጣጥ እንዲሁም የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ በተመለከተ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ የተሞከሩ የሽግግር ፍትሕ ሂደቶችና የተለያዩ ሀገራት ተሞክሮዎችን ጨምሮ የክልሎችና የፍትሕ አካላት ሚና ላይ ሰፊ ገለጻ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች በስልጠናው በተነሱ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ጥያቄዎችን በማንሳት ውይይት እንዲያደርጉ እድል የሰጠ በመሆኑ በርዕሰ ጉዳዮቹ ላይ ጠለቅ ያለ ግንዛቤ እንዲይዙ እንደረዳቸው ገልጸው ተመሳሳይ ስልጠናዎች እና ትብብሮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

🔗 https://ehrc.org/?p=33664

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
4
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ #HumanRights Concept: የማሠቃየት ተግባር ተጎጂዎች መብት
...

የማሠቃየት እና ሌሎች የጭካኔ፣ ኢ-ሰብአዊ የሆነና ክብርን የሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት ለማስቀረት የተደረገ ስምምነት፣ አንቀጽ 14

እያንዳንዱ አባል ሀገር በሕግ ሥርዓቱ ውስጥ የማሠቃየት ተግባር ሰለባ የሆነ ሰው መፍትሔ እንደሚያገኝ እንዲሁም በተቻለ መጠን የተሟላ ማገገሚያን ጨምሮ ተፈጻሚነት ያለው ፍትሐዊና በቂ ካሳ የማግኘት መብት እንዳለው ማረጋገጥ አለበት።

ተጎጂው በደረሰበት የማሠቃየት ተግባር ምክንያት የሞተ እንደሆነ በእርሱ ኃላፊነት እና ድጋፍ ይተዳደሩ የነበሩ ሰዎች ካሳ ሊያገኙ ይገባል።

🔗 https://ehrc.org/?p=33736

#Ethiopia🇪🇹 #KeepWordSafe #ጤናማቃላት

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
1
#አፋር እና #ማእከላዊኢትዮጵያ:- በሴት ልጅ ግርዛት ላይ የተካሄደ የመጀመሪያው ግልጽ የአቤቱታ መቀበያ መድረክ
...

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአፋር እና በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በሚፈጸም የሴት ልጅ ግርዛት ላይ ያተኮረ ሕዝባዊ መሰማት ወይም ግልጽ የአቤቱታ መቀበያ መድረክ በሰኔ 18 እና 19 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ አካሂዷል። በአቤቱታ መቀበያ መድረኩ ጥቃት የደረሰባቸው ተጎጂዎች፣ ምስክሮች፣ የሚመለከታቸው የመንግሥት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

መድረኩ ከአፋር እና ከማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመጡ 10 ተጎጂዎች ያቀረቡትን አቤቱታ እና ደርሶብናል ያሉትን የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች፣ እንዲሁም የ2 ባለሙያዎችን እና የ3 ምስክሮችን ቃል አዳምጧል። በአፋር ክልል 3 የግርዛት ዓይነቶች የሚፈጸሙ መሆኑን ምስክሮች አብራርተዋል። እነዚህ የግርዛት ዓይነቶች የተፈጸሙባቸው ተጎጂዎች በመድረኩ ላይ ተገኝተው ግርዛቱ ትዳራቸው ላይ ተጽዕኖ እንደፈጠረባቸው፣ በግንኙነት እና በወር አበባ ጊዜ ሕመም እና ሥቃይ እንደሚሰማቸው እና የሥነ ልቦና ጉዳት እንዳስከተለባቸው አስረድተዋል። ሴትን ልጅ ማስገረዝ የሴቶች ወይም የእናቶች ኃላፊነት መሆኑን፣ እንዲሁም ግርዛቱ የሚፈጸመው በድብቅ መሆኑን በመድረኩ መስክረዋል። በግርዛት ምክንያት በቅድመ ወሊድና በወሊድ ወቅት ለረጅም ሰዓታት ለሚቆይ ምጥ እና ሕመም ከመጋለጣቸው የተነሳ በቀዶ ሕክምና ለመውለድ እንደተገደዱም ገልጸዋል።

🔗 https://ehrc.org/?p=33750

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
3
#ጋምቤላ፦ በታራሚዎች እና በተጠርጣሪዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተካሄደ ውይይት
...

የታራሚዎች እና የተጠርጣሪዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝን ለማሻሻል ባለድርሻ አካላት የተሰጡ ምክረ ሐሳቦችን መተግበር ይጠበቅባቸዋል

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በጋምቤላ ክልል በሚገኙ 4 ማረሚያ ቤቶች፣ 21 ፖሊስ ጣቢያዎች እና 5 ኢ-መደበኛ ማቆያዎች ላይ ባከናወነው የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ክትትል የተለዩ ግኝቶች ላይ ሰኔ 20 እና 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋምቤላ ከተማ ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱ የክልሉ ምክር ቤት የፍትሕ እና የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢን እና የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ጋምቤላ ቅርንጫፍ ተወካዮችን ጨመሮ በየደረጃው የሚገኙ የክልሉ የፍትሕ፣ የጸጥታ እና የአስተዳደር አካላት የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

በውይይት መድረኩ ታራሚዎች እና የጊዜ ቀጠሮ እስረኞች በፍርድ ቤት ትእዛዝ ወይም ውሳኔ ብቻ ወደ ማረሚያ ቤት እንደሚገቡ፣ ተጠርጣሪዎች በሕግ ሥልጣን በተሰጣቸው አካላት ብቻ በቁጥጥር ሥር እንደሚውሉ፣ በማረሚያ ቤቶች እና ፖሊስ ጣቢያዎች የመጎብኘት መብት ላይ የሚጣል ገደብ አለመኖሩ፣ የእምነት ነጻነት መከበሩ፣ ተጠርጣሪዎችና ታራሚዎች በግዳጅ ሥራ እንዲሠሩ አለመደርጉ፣ በፍርድ ቤት የተፈቀደ ዋስትና በፖሊስ ጣቢያዎች መከበሩ፣ እንዲሁም ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ሲውሉ የተያዙበት ምክንያት የሚገለጽላቸው መሆኑ በክትትሉ በመልካም እመርታነት ከተለዩት መካከል ተነስተዋል።

🔗 https://ehrc.org/?p=33767

#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
4
2025/10/21 21:52:53
Back to Top
HTML Embed Code: