በጎዳና ላይ ያሉ ሰዎችን ያለፈቃዳቸው መያዝና ወደ ማቆያ ማእከላት ማስገባት የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ስለሚያስከትል ሊቆም ይገባል
...
ከጎዳና ላይ ለሚነሱና ወደማቆያ ለሚገቡ ሰዎች ሰብአዊ መብቶችን ያማከለ ዘላቂ መፍትሔ መስጠት ያስፈልጋል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በሚያዝያ 27 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ በጎዳና ላይ ያሉ ሕፃናት በጅምላ ተይዘው የሚቆዩበትን ሁኔታ በተመለከተ እንዲሁም መስከረም 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በሸገር ከተማ ገላን ክፍለ ከተማ ሲዳ አዋሽ ወረዳ በሚገኘው ማቆያ ማእከል ተይዘው የነበሩ ውሎና አዳራቸውን በጎዳና ያደረጉ ሰዎችን (በተለምዶ አጠራር ‘‘ጎዳና ተዳዳሪዎች’’ ተብለው የሚታወቁ) ሁኔታ አስመልክቶ ክትትል በማድረግ የተለዩ ክፍተቶችን እና ምክረ ሐሳቦችን የያዘ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል።
ኢሰመኮ በታኅሣሥ ወር 2017 ዓ.ም. ባደረጋቸው ክትትሎች በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ “ቃሊቲ አካባቢ” ተብሎ በሚጠራው የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ አካባቢ ባለ ሰፊ መጋዝን ውስጥ ከጎዳና ላይ የተነሱ በርካታ ሰዎች መኖራቸውንና ይህ ሰዎችን የመያዝና ወደ ማቆያ ማእከል/ቦታ የማስገባት ድርጊት አሁንም መቀጠሉን ተገንዝቧል፡፡ ወደ ማቆያው ከገቡት ሰዎች መካከል በማእከሉ ከመቆየት እና የእርሻ ሥራ ከመሥራት እንዲመርጡ በማድረግ፤ የእርሻ ሥራ ለመሥራት የመረጡ ሰዎች በተለያዩ አካባቢዎች ወደሚገኙ እርሻ ጣቢያዎች ተወስደው እንዲሠሩ እንደሚደረግ ለመገንዘብ ተችሏል።
🔗 https://ehrc.org/?p=30998
#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

👍2
የሳምንቱ #HumanRights Concept: ቤተሰብ የመመሥረት መብት
…
ሁሉ አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ፣ አንቀጽ 16 (1) እና (2)
ዕድሜያቸው ለጋብቻ የደረሰ ወንዶች እና ሴቶች በዘር፣ በዜግነት ወይም በሃይማኖት ልዩነት ሳይደረግባቸው ጋብቻ የመፈጸም እና ቤተሰብ የመመሥረት መብት አላቸው። ጋብቻው ሲፈጸም፣ በጋብቻ ወቅት እና ጋብቻው በሚፈርስበት ጊዜ እኩል መብቶች አሏቸው።
ጋብቻ በተጋቢዎች ነጻ እና ሙሉ ፈቃድ ላይ ብቻ ይመሠረታል።
የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት፣ አንቀጽ 34 (3)
ቤተሰብ የኅብረተሰብ ተፈጥሯዊ እና መሠረታዊ መነሻ ነው። ከኅብረተሰብና ከመንግሥት ጥበቃ የማግኘት መብት አለው።
🔗 https://ehrc.org/?p=31006
#Ethiopia🇪🇹 #KeepWordSafe #ጤናማቃላት

👍6
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ #HumanRights Concept: የመማር መብት
...
ሁሉ አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ፣ አንቀጽ 26
ማንኛውም ሰው የመማር መብት አለው፡፡ ቢያንስ የአንደኛ ደረጃና መሠረታዊ ትምህርት በነጻ ሊሰጥ ይገባል፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ግዴታ ሊሆን ይገባል።
ትምህርት ለሰው ልጅ የተሟላ የስብእና እድገትን ለማምጣት እና የሰብአዊ መብቶችንና መሠረታዊ ነጻነቶች መከበርን ለማጠናከር ያለመ መሆን አለበት፡፡ ትምህርት በሁሉም ሀገራት፣ በተለያዩ ዘሮችና ሃይማኖቶች መካከል መግባባትን፣ መቻቻልን እና ወዳጅነትን ሊያጎለብት ይገባል።
🔗 https://ehrc.org/?p=31049
#Ethiopia🇪🇹 #EducationDay #RightToEducation #KeepWordSafe #ጤናማቃላት

❤3
የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ወደቀድሞ ቀያቸው የመመለስ እና ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኙ የማድረግ ሂደት ሰብአዊ መብቶችን መሠረት ያደረገ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በትግራይ ክልል ወደቀድሞ ቀያቸው የተመለሱ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ አስመልክቶ በክልሉ ከሚገኙ የሚመለከታቸው መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም የፌደራል መንግሥት ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ጋር ኅዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም. በመቐለ ከተማ ተወያይቷል።
ውይይቱ በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በትግራይ ክልል ተፈናቅለው በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ተጠልለው ከቆዩ በኋላ የፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነትን ተከትሎ ጦርነቱ በመቆሙ ወደ ቀድሞ የመኖሪያ አካባቢያቸው ማለትም ወደ ኮረም ከተማ፤ ኦፍላ ወረዳ፣ ሕጉም ቡርዳ እና ፋላ ቀበሌ፤ ራያ አላማጣ ወረዳ፣ ዋጃ ጡሙጋ ቀበሌ፤ በአላማጣ ከተማ 02 እና 03 ቀበሌ እንዲሁም ጸለምት፣ ላዕላይ ጸለምት እና ማይፀብሪ ከተማ እንዲመለሱ የተደረጉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ለመረዳት እና ለማሻሻል ይረዳ ዘንድ ኢሰመኮ ከነሐሴ 19 እስከ ጳጉሜን 1 ቀን 2016 ዓ.ም. ባከናወነው የሰብአዊ መብቶች ክትትል የለያቸው ግኝቶች እና የሰጣቸው ምክረ ሐሳቦች ላይ ያተኮረ ነው።
በውይይት መድረኩ ከጸጥታ እና ደኅነነት፣ ከመሠረታዊ አገልግሎት እና ከሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት እዲሁም ከማኅበራዊ አገልግሎት አንጻር የተለዩ ግኝቶች ቀርበዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ከተመለሱ በኃላ መሠረታዊ አገልግሎት እና የሰብአዊ ድጋፍ አለማግኘታቸውን እና በጸጥታ ሥጋት ምክንያት ተመላሾቹ ወደ ቀያቸው ሳይመለሱ አሁንም ድረስ በትምህርት ቤቶች ተጠልለው ለመኖር ስለመገደዳቸው ተናግረዋል። በተጨማሪም አስፈላጊ ማኅበራዊ አገልግሎት ማግኘት አለመቻላቸውን፤ በአንዳንድ አካባቢዎች በፈረቃ ትምህርት መስጠት የተጀመረ ቢሆንም ትምህርት ያልጀመሩ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን፤ የመንግሥት አገልግሎቶችን ለማግኘት መቸገራቸውን እና ቅሬታ የሚያቀርቡበት አካል አለመኖሩን አንስተዋል።
ከአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የተገኙ ተሳታፊዎች በመሠረታዊ አገልግሎት እና በሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት ረገድ ያለውን ክፍተት ለመሙላት እና በቀጣይ የምግብ አቅርቦቱን ለማሻሻል በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች ጋር የሚሠሩ መሆኑን ገልጸዋል። ከትምህርት እና ከጤና ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የተገኙ የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በግጭት ለተጎዱ አካባቢዎች ቅድሚያ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይ በእነዚህ አካባቢዎች የሚገኙ የትምህርት እና የጤና ተቋማትን ወደ ሥራ ለማስገባት ዕቅድ ተይዞ እየተሠራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
የኢሰመኮ የስደተኞች፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና የፍልሰተኞች መብቶች ሥራ ክፍል ዳይሬክተር እንጉዳይ መስቀሌ፣ በቀጣይ የሚከናወኑ ተፈናቃዮችን ወደቀድሞ ቀያቸው የመመለስ ተግባር እና ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኙ የማድረግ ሂደት የሰብአዊ መብቶች መስፈርቶችን መሠረት ያደረገ እና ያሟላ መሆኑ በቅድሚያ ሊረጋገጥ እንደሚገባ አስረድተዋል።
🔗 https://ehrc.org/?p=31066
#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll #Tigray

👍3
በ 2017 ዓ.ም. በሁለተኛው ሩብ ዓመት የተሰጡ የሰብአዊ መብቶች ስልጠናዎች
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከጥቅምት እስከ ታኅሣሥ ወር 2017 ዓ.ም. በሰብአዊ መብቶች እና በሽግግር ፍትሕ እንዲሁም በሴቶች መብቶች፣ በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መብቶች፣ በአረጋውያን መብቶች፣ በተጠርጣሪዎች እና በሕግ ታራሚዎች መብቶች ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎችን እና የአሰልጣኞች ስልጠናዎችን ለወጣቶች፣ ለማረሚያ ቤት ፖሊሶች፣ ለፖሊስ አባላት እና ሥራ ኃላፊዎች፣ ለአረጋውያን፣ ለሲቪል ማኅበራት እና ለመንግሥት ተቋማት ሠራተኞች ሰጥቷል፡፡
ኢሰመኮ ከሰላም፣ አብሮነት እና መቻቻል አንጻር የወጣቶችን ሚና ለማሳደግ ያለመ የሰብአዊ መብቶች ስልጠና በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተለያዩ የወጣት ማኅበራት ለተውጣጡ 32 ወጣት አመራሮች እና አባላት በቡታጂራ ከተማ ከኅዳር 9 እስከ 13 ቀን 2017. ዓ.ም ሰጥቷል። በሌላ በኩል ኢሰመኮ ዮዝ አዌርነስ ኤንድ ማይንድሴት ግሮውዝ (Youth Awareness and Mindset Growth -YAMG) ከተባለ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ጋር በመተባበር በሰብአዊ መብቶች እና በሽግግር ፍትሕ ፅንሰ ሐሳብ፣ ሂደቶችና አላባዎች ዙርያ ወጣቶች በቂ ዕውቀት እንዲያገኙ እና በሂደቱ ለመሳተፍ ተነሳሽነት እንዲያዳብሩ በጅማ ከተማ ከጥቅምት 25 እስከ 29 ቀን 2017 ዓ.ም. የአሰልጣኞች ስልጠና አካሂዷል። በስልጠናው ከወልቂጤ፣ ከዋቻሞ፣ ከጅማ፣ ከቦንጋ እና ከወራቤ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ 30 የዩኒቨርሲቲ ሰላም ፎረምና የተማሪዎች መማክርት አመራሮችና አባላት ተሳትፈዋል። በተመሳሳይ ከአዲስ አበባ እና ከቢሾፍቱ ከተሞች ለተውጣጡ 33 የወጣት ማኅበራት አመራሮች እና አባላት ከታኅሣሥ 21 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም. የአሰልጣኞች ስልጠና በቢሾፍቱ ከተማ ተሰጥቷል። ስልጠናዎቹ የሌሎች ሀገራት የሽግግር ፍትሕ ተሞክሮዎች የቀረቡበት ሲሆን የወጣቶችን ጉልህ ሚና ለማሳደግ የሚረዱ ተግባራዊ ልምምዶች የተካተቱበት ነው።
በተመሳሳይ ኢሰመኮ የሰብአዊ መብቶች ፅንሰ ሐሳብ እና የሽግግር ፍትሕ ምንነትን በተመለከተ በራሱ እና ከፕሮጀክት ኤክስፒዲየት ጀስቲስ (Project Expedite Justice) ጋር በመተባበር ከትግራይ ክልል 25፣ ከአማራ ክልል 26 እና ከሲዳማ ክልል 35 ለተውጣጡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ሠራተኞች እና የሥራ ኃላፊዎች ከታኅሣሥ 1 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዳማና በሃዋሳ ከተማ ስልጠና አካሂዷል።
ኢሰመኮ ባለፉት 3 ወራት የአረጋውያን ሰብአዊ መብቶች እንዲሁም መብቶቹን ለማስከበርና ለማስፋፋት የሚያስችሉ ክህሎቶችን በተመለከተ ከኢትዮጵያ አረጋውያንና ጡረተኞች ማኅበር፣ ከደቡብ ምዕራብ ክልል እና ከጅማ ከተማ አረጋውያን ማኅበራት ለተወጣጡ 61 አረጋውያን እና አመራሮች በተለያዩ ጊዜያት በአዳማ እና በጅማ ከተሞች ስልጠናዎችን ሰጥቷል። በስልጠናው አረጋውያን ላይ የሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶች ለሚመለከተው አካል ሪፖርት እና አቤቱታ ለማቅረብ እንዲሁም ውትወታ ለማድረግ የሚያስችሏቸውን ክህሎቶች ለማዳበር እንዲችሉ ተግባራዊ ልምምድ አድርገዋል። በተመሳሳይ ኢሰመኮ የሴቶችን መብቶች በተመለከተ በአዳማ፣ በአዲስ አበባ እና በቢሾፍቱ ከተሞች ከሚንቀሳቀሱ ኢ-መደበኛ ከሆኑ አደረጃጀቶች ለተወጣጡ 35 ተሳታፊዎች ከታኅሣሥ 7 እስከ 11 ቀን 2017 ዓ.ም. ለ5 ተከታታይ ቀናት በአዳማ ከተማ የአሰልጣኞች ስልጠናው ሰጥቷል። የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ ስለሴቶች መብቶች ዕውቀት ማስጨበጥ፣ አመለካከትን ማጎልበት እንዲሁም ተሳታፊዎች ያገኙትን ዕውቀትና አመለካከት ወደ ተግባር እንዲቀይሩ ማስቻል ነው፡፡ በሌላ በኩል ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች አገልግሎት ከሚሰጡ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት ለተውጣጡ 30 የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ከኅዳር 23 እስከ 27 ቀን 2017 ዓ.ም. በአርባ ምንጭ ከተማ ስልጠና ተሰጥቷል። ስልጠናው የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በቅድመ መፈናቀል፣ በመፈናቀል እና በድኅረ መፈናቀል ወቅት በዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊ እና ብሔራዊ የሕግ ማዕቀፎች ላይ ስላሏቸው መብቶች፣ ከሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጋር በተያያዘ የመንግሥት ግዴታዎች እና መንግሥታዊ ያልሆኑ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ኃላፊነትን በተመለከተ ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ ያለመ ነው። ተሳታፊዎች በስልጠናው ያገኙትን የሰብአዊ መብቶች ዕውቀት፣ አመለካከት እና ክህሎት በመጠቀም ተግባራዊ እርምጃ ለመውሰድ ያላቸውን ተነሳሽነት ገልጸዋል፡፡
የኢሰመኮ የሰብአዊ መብቶች ትምህርት ሥራ ክፍል ዳይሬክተር ዶ/ር መቅደስ ታደለ የሰብአዊ መብቶች ትምህርት እና ስልጠና መርኃ ግብር የመብቶች ባለቤቶችን እና ባለግዴታዎችን የሰብአዊ መብቶች ዕውቀት፣ ክህሎት እና አመለካከት በማጎልበት የሰብአዊ መብቶች ባህልን ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ገልጸዋል። አያይዘውም የስልጠና ተሳታፊዎች የቀሰሙትን የሰብአዊ መብቶች ዕውቀትና ክህሎት በሥራ በመተርጎምና ለሌሎች ባልደረቦቻቸው ምሳሌ በመሆን ሰብአዊ መብቶችን በማስፋፋት የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ አሳስበዋል።
🔗 https://ehrc.org/?p=31080

🥰5👍2❤1
Strengthening collaboration among stakeholders is essential to ensure effective protection of refugees’ and asylum seekers’ rights
...
The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) organized a consultative workshop on December 26, 2024, in Harar city to discuss the current challenges faced by refugees and asylum seekers in Awbare, Shedder and Kebribeyah refugee camps located in the Jigjiga area. The workshop aimed to share the key findings from EHRC’s human rights situation monitoring with stakeholders and advocate for better protection of refugees’ and asylum seekers’ rights. The event brought together representatives from governmental and non-governmental organizations, refugee representatives and UN agencies working in the three camps.
During the consultation, EHRC presented its monitoring findings on the human rights situation of refugees and asylum seekers in the three refugee camps, highlighting both positive developments and persistent challenges. While peace and security within the camps have been relatively stable, creating a conducive environment for refugee protection, the monitoring highlighted multiple challenges. These include delays in the refugee status determination process and limited access to essential documentation, restricted access to justice mechanisms, and inadequate access to basic services such as food, non-food items, shelter, healthcare and education.
The monitoring also identified specific vulnerabilities faced by children, women, older persons and persons with disabilities. Additionally, it revealed gaps in implementing the Kebribeyah Inclusion Plan, a five-year Road Map (2023-2027) designed to foster a more inclusive and prosperous community in Kebribeyah town in the Somali region of Ethiopia.
Participants raised concerns about budget constraints and resource shortages that hinder the provision of services to refugee communities. Gaps in humanitarian assistance were also highlighted, along with the limited capacity of government institutions in Kebribeyah to effectively implement the Inclusion Plan.
The event concluded with a renewed commitment from stakeholders to collaborate effectively in addressing the multifaceted challenges exacerbating protection risks of refugees and asylum seekers in the three refugee camps.
Enguday Meskele, Director of the Department of the Rights of Refugees, IDPs, and Migrants at EHRC reaffirmed EHRC’s commitment to collaborate with stakeholders and advocate for the rights and well-being of refugees and asylum seekers.
🔗 https://ehrc.org/?p=31139

❤2👍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ #HumanRights Concept: የነጻነት መብት
...
የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን፣ አንቀጽ 9 (1) (4)፣ 10 (1)
ማንኛውም ሰው በዘፈቀደ ሊያዝ ወይም ሊታሰር አይችልም። ማንኛውም ሰው በሕግ ከተደነገገው ምክንያትና ሥርዓት ውጭ ነጻነቱን አይነፈግም፡፡
በመያዙ ወይም በመታሰሩ ምክንያት ነጻነቱን የተነፈገ ማንኛውም ሰው ፍርድ ቤቱ ሳይዘገይ ስለእስራቱ ሕጋዊነት እንዲወስንለትና ያለአግባብ መታሰሩን ካረጋገጠም በነጻ እንዲለቀቅ እንዲያዝለት ጉዳዩን ለፍርድ ቤት የማቅረብ መብት አለው፡፡
ነጻነታቸውን የተነፈጉ ሰዎች ሁሉ ሰብአዊ አያያዝ ሊደረግላቸውና በተፈጥሮ የተጎናጸፉት ሰብአዊ ክብር ሊጠበቅላቸው ይገባል፡፡
🔗 https://ehrc.org/?p=31153

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ሹመትን በተመለከተ
...
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም. ባካሄደው 17ኛ መደበኛ ስብሰባ አቶ ብርሃኑ አዴሎን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር አድርጎ ሾሟል። የዋና ኮሚሽነር ሹመት በኢሰመኮ ማቋቋሚያ አዋጅ 210/1992 (በአዋጅ ቁጥር 1224/2012 እንደተሻሻለው) አንቀጽ 10፣ 11 እና 12 በተደነገገው መሠረት የተካሄደ ነው።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሾሙት አቶ ብርሃኑ አዴሎ ከዚህ ቀደም በተለያዩ መንግሥታዊ ኃላፊነቶች ያገለገሉ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር፣ እንዲሁም የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ሚኒስትርና የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ነበሩ።
የኢሰመኮ የቀድሞ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የሥራ ዘመን መጠናቀቁን ተከትሎ ከሐምሌ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ኢሰመኮን በተጠባባቂ ዋና ኮሚሽነርነት ራኬብ መሰለ፣ ዶ/ር አብዲ ጅብሪል በሲቪል፣ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚያዊ እና በማኅበራዊ መብቶች ኮሚሽነርነት፣ እንዲሁም ርግበ ገብረሐዋሪያ በሴቶች፣ በሕፃናት፣ በአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን መብቶች ኮሚሽነርነት ሲመሩ ቆይተዋል።
ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ሹመቱን በማስመልከት ባስተላለፉት መልእክት ወቅታዊ የሀገሪቱ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ጠንካራ አመራር እና ውጤታማ የሰብአዊ መብቶች ሥራ የሚጠይቅ መሆኑን በማስታወስ የኢሰመኮን ኮሚሽነሮች እና ባልደረባዎች በመወከል ለዋና ኮሚሽነር አቶ ብርሃኑ አዴሎ ከወዲሁ “መልካም የሥራ ዘመን እመኝላቸዋለሁ” ብለዋል።
🔗 https://ehrc.org/?p=31197

Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ሹመትን በተመለከተ - Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) is an independent federal state body established by Parliament as the national human rights institution with the mandate for the promotion and protection of human rights.
በኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር እና በምክትል ዋና ኮሚሽነር መካከል የሥራ ርክክብ ተደረገ
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ በኢሰመኮ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 210/1992 (በአዋጅ ቁጥር 1224/2012 እንደተሻሻለው) አንቀጽ 19 በተደነገገው መሠረት በዋና ኮሚሽነር ሥልጣንና ኃላፊነት ሥር የሚወድቁ ሥራዎችን ከምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ጥር 26 ቀን 2017 ዓ.ም. ተረክበዋል። በመርኃ ግብሩ ዶ/ር አብዲ ጅብሪል የሲቪል፣ የፖለቲካ፣ የማኅበራዊ እና የኢኮኖሚያዊ መብቶች ኮሚሽነር እንዲሁም ርግበ ገብረሐዋሪያ የሴቶች፣ የሕፃናት፣ የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ተገኝተዋል።
በርክክብ መርኃ ግብሩ ኢሰመኮን ላለፉት ስድስት ወራት በተጠባባቂ ዋና ኮሚሽነርነት ከመሩት ምክትል ዋና ኮሚሽነር የተከናወኑ፣ በመከናወን ላይ ያሉ እና ወደፊት ለማከናወን በዕቅድ ስለተያዙ ተግባራት ማብራሪያ ተሰጥቷል። በተመሳሳይ ኮሚሽነር አብዲ ጅብሪል እና ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋሪያ በየዘርፋቸው ማብራሪያ ሰተዋል።
ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ የሰብአዊ መብቶች ሥራ የኢሰመኮ ሠራተኞችን እና የሁሉም ባለድርሻ አካላትን ትብብርና ቅንጅታዊ ሥራን የሚጠይቅ መሆኑን ጠቁመው ዋና ኮሚሽነር የሰብአዊ መብቶችን በማስፋፋት፣ በማስጠበቅ እና በማስከበር ረገድ ለሚሠሩት ሥራዎች የሚያስፈልገውን ድጋፍ ለማድረግ ከጎናቸው መሆናቸውን ገልጸዋል። በድጋሚ መልካም የሥራ ዘመንም ተመኝተውላቸዋል።
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ ለተደረገላቸው ገለጻ እና ለመልካም ምኞት ምሥጋና አቅርበው ኢሰመኮ በአዋጅ የተጣለበትን ሰብአዊ መብቶችን የማስፋፋት፣ የመጠበቅና እንዲከበሩ የመወትወት ሥራዎች በከፍተኛ ኃላፊነት ለመፈጸም እንደሚተጉ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም. ባካሄደው 17ኛ መደበኛ ስብሰባ ብርሃኑ አዴሎ ኢሰመኮን በዋና ኮሚሽነርነት እንዲመሩ የሾማቸው መሆኑ ይታወሳል።
🔗 https://ehrc.org/?p=31224

👍4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ #HumanRights Concept: የሴት ልጅ ግርዛት
...
የአፍሪካ የሰዎችና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል፣ በአንቀጽ 5
አባል ሀገራት የሴቶች ሰብአዊ መብቶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ከተሰጣችው መስፈርቶች ጋር የሚጣረሱ ሁሉንም ዐይነት ልማዳዊ ድርጊቶች መከልከልና ማውገዝ አለባቸው።
አባል ሀገራት ቅጣትን የሚያስከትሉ ሕጎችን በማውጣት ማንኛውንም ዐይነት የሴት ልጅ ግርዛትን መከልከል አለባቸው።
የሴት ልጅ ግርዛት እና ተያያዥ ድርጊቶች በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ፣ አንቀጽ 565 እና አንቀጽ 566 ላይ የሚያስቀጡ ተግባራት ናቸው።
🔗 https://ehrc.org/?p=31238
#Ethiopia🇪🇹 #EndFGM #EndFemaleGenitalMutilation #Unite2EndFGM #KeepWordSafe #ጤናማቃላት
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
...
የአፍሪካ የሰዎችና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል፣ በአንቀጽ 5
አባል ሀገራት የሴቶች ሰብአዊ መብቶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ከተሰጣችው መስፈርቶች ጋር የሚጣረሱ ሁሉንም ዐይነት ልማዳዊ ድርጊቶች መከልከልና ማውገዝ አለባቸው።
አባል ሀገራት ቅጣትን የሚያስከትሉ ሕጎችን በማውጣት ማንኛውንም ዐይነት የሴት ልጅ ግርዛትን መከልከል አለባቸው።
የሴት ልጅ ግርዛት እና ተያያዥ ድርጊቶች በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ፣ አንቀጽ 565 እና አንቀጽ 566 ላይ የሚያስቀጡ ተግባራት ናቸው።
🔗 https://ehrc.org/?p=31238
#Ethiopia🇪🇹 #EndFGM #EndFemaleGenitalMutilation #Unite2EndFGM #KeepWordSafe #ጤናማቃላት
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
👍1
በ4ኛ ዙር የሁሉ-አቀፍ ግምገማ መድረክ (Universal Periodic Review – UPR) የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች ላይ የተደረገ ምክክር
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተ.መ.ድ.) የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት (United Nations Human Rights Council – UNHRC) በጥር ወር 2017 ዓ.ም. በተካሄደው 4ኛው ዙር ሁሉ-አቀፍ ወቅታዊ የግምገማ መድረክ (Universal Periodic Review- UPR) ወቅት በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ለማሻሻል የተሰጡ ምክረ ሐሳቦችን ሀገር ውስጥ ካለው ነባራዊ ዐውድ ጋር በማዛመድ ሀገራዊ የሰብአዊ መብቶች አጀንዳ አድርጎ በጋራ ለመደገፍ ያለመ የምክክር መድረክ ጥር 20 እና 21 ቀን 2017 ዓ.ም. አካሄደ። በመድረኩ በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ የሚሠሩ የመንግሥት አካላት፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ የጥናትና የምርምር ተቋማት፣ ሚዲያዎች እና ዩኒሴፍን ጨምሮ መንግሥታዊ ያልሆኑ ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ተሳትፈዋል።
ከዚህ ቀደም ከኅዳር 3 እስከ 6 ቀን 2017 ዓ.ም. በተ.መ.ድ. የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት 47ኛው መደበኛ ስብሰባ ወቅት የኢትዮጵያ 4ኛው ዙር ሁሉ-አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ግምገማ በጄኔቫ፣ ስዊዘርላንድ መካሄዱ ይታወሳል። በዚህ ስብሰባ ኢትዮጵያ በ3ኛው ዙር የግምገማ መድረክ የተሰጧትን ምክረ ሐሳቦች ከመተግበር አንጻር እና የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን በማሻሻል ረገድ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያከናወነቻቸውን ተግባራት አስመልክቶ ሪፖርት አቅርባ በተ.መ.ድ. አባል ሀገራት የአቻ ለአቻ ግምገማ ሂደት አልፋለች። በዚህ ሂደት በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ለማሻሻል መንግሥት ሊወስዳቸው የሚገቡ እርምጃዎችን በተለመከተ 114 የተ.መ.ድ. አባል ሀገራት 316 ምክረ ሐሳቦችን ሰጥተዋል። በዚህም መሠረት ከቀጣዩ 58ኛው የተ.መ.ድ. የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ስብሰባ አስቀድሞ ኢትዮጵያ ከእነዚህ 316 ምክረ ሐሳቦች ውስጥ የተቀበለቻቸውን ለይታ እንደምታሳውቅ ይጠበቃል፡፡
በምክክር መድረኩ የሁሉ-አቀፍ ወቅታዊ ግምገማ ሂደት ለሰብአዊ መብቶች መከበር እና መስፋፋት ያለውን ጉልህ ጠቀሜታ እንዲሁም በኢሰመኮ፣ በተለያዩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና መንግሥታዊ ባልሆኑ ዓለም አቀፍ ተቋማት ቀርበው የነበሩ ሪፖርቶች ላይ ገለጻ ተሰጥቷል። ይህንንም ተከትሎ በሴቶች እና ሕፃናት፣ በሲቪል እና ፖለቲካዊ መብቶች፣ በማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶች፣ በሽግግር ፍትሕና ተጠያቂነት እና የቀሩ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን ማጽደቅ ላይ ውይይት ተደርጓል። እንዲሁም እንደ ኢሰመኮ ያሉ ነጻ ተቋማትን ማጠናከር፣ በመንግሥት ተቋማት፣ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና በዓለም አቀፍ ድርጅቶች መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከርን በተመለከተ የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች በውይይቱ ተዳስሰዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች የምክረ ሐሳቦቹ ተቀባይነት ማግኘት በመንግሥት እየተወሰዱ ያሉ መልካም እርምጃዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል እንዲሁም አሳሳቢ በሆኑ እና ትኩረት በሚሹ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች ላይ የሕግ፣ የፖሊሲ እና የአሠራር ማሻሻያዎችን በማድረግ ተጨባጭ እርምጃዎች እንዲወሰዱ በማገዝ ሰብአዊ መብቶችን በኢትዮጵያ ለማስፋፋት እና ለማስከበር ጉልህ አስተዋጽዖ እንዳለው ገልጸዋል። በተጨማሪም ምክረ ሐሳቦቹን ከመቀበል ባለፈ በሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት እቅዶች ውስጥ እንዲካተቱ ማድረግ፣ ተጨባጭ የሆኑ እርምጃዎች እንዲወሰዱ እና አፈጻጸማቸውን በተሟላ ሁኔታ መከታተል እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።
የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ በ4ኛው ዙር የሁሉ-አቀፍ ወቅታዊ የግምገማ መድረክ የተሰጡ ምክረ ሐሳቦችን ተቀብሎ መተግበር በኢትዮጵያ ያለው የሰብአዊ መብቶች ዐውድ ላይ አወንታዊ አስተዋጽዖ እንደሚያበረክት ግምት ውስጥ በማስገባት መንግሥት በተቻለ መጠን አብዛኛዎቹን ምክረ ሐሳቦች እንዲቀበል በዕለቱ ጥሪ አቅርበዋል። ኢሰመኮ የኢትዮጵያ መንግሥት የሚቀበላቸውን ምክረ ሐሳቦች በመጪው ዓመታት ለመተግበር የሚከናወኑ ተግባራትን ለመደገፍ ከመንግሥት እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር እንደሚሠራም ገልጸዋል።
🔗 https://ehrc.org/?p=31265

ሰመራ፦ ለአስርት ዓመታት አገልግሎት መስጠት ያልጀመረ የአካል ጉዳተኞች ተሐድሶ ማእከልን ለማስጀመር የተካሄደ ውይይት
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ግንባታው ተጠናቆ ለአስርት ዓመታት ወደ ሥራ ሳይገባ የቆየው የሰመራ የአካል ጉዳተኞች ተሐድሶ ማእከል አገልግሎት መስጠት መጀመር በሚችልበት ሁኔታ ላይ ትኩረቱን ያደረገ የውይይት መድረክ ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም. በሰመራ ከተማ አካሂዷል። በውይይቱ የኢትዮጵያ አካል ድጋፍ አገልግሎትን ጨምሮ የክልሉ ፕሬዚደንት ጽሕፈት ቤት፣ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ፣ የጤና ቢሮ፣ የአፋር አካል ጉዳተኞች ማኅበራት ፌዴሬሽን፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተወካዮች እና ሌሎች አጋር አካላት ተሳትፈዋል።
ኢሰመኮ በ2014 ዓ.ም. በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ተከስቶ የነበረው ግጭት በአፋር እና አማራ ክልሎች በሚኖሩ አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን ላይ ያሳደረውን ተጽእኖ አስመልክቶ ክትትል በሚያካሂድበት ወቅት የሰመራ ተሐድሶ ማእከል ሁኔታን ለመገንዘብ የቻለ ሲሆን ይህንኑ ተከትሎም ሚያዚያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ከአፋር ክልል ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር በጉዳዩ ላይ ሰፊ ውይይት አካሂዷል። በተጨማሪም በጷጉሜን 1 ቀን 2016 ዓ.ም. ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲሁም በጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም. ለ2ተኛ ጊዜ ይፋ ያደረጋቸው የአካል ጉዳተኞችና አረጋውያን ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርቶች ላይ የሰመራ የአካል ጉዳተኞች ተሐድሶ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን የገለጸ ሲሆን ምክረ ሐሳቦቹን ለማስፈጸም በርካታ የውትወታ ሥራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል። እንዲሁም በጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም. ማእከሉ ያለበትን ሁኔታ በአካል በመገኘት ከክልሉ ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር ተመልክቷል፤ ውይይትም አካሂዷል።
በውይይቱም በክልሉ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ እና ጤና ቢሮ መካከል ባለው የይዞታ ይገባኛል ክርክር ምክንያት ማእከሉ እስከአሁን ድረስ ወደ ሥራ አለመግባቱ እና ያለጥቅም ተዘግቶ በመቆየቱ ቀድሞ ከነበረበት ሁኔታ በእጅጉ መጎዳቱን ኢሰመኮ በአካሄደው ምልከታ መገንዘቡ ተገልጿል። የክልሉ የአካል ጉዳተኞች ማኅበራት ፌዴሬሽን እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተወካዮች በበኩላቸው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በክልሉ የሚገኙ አካል ጉዳተኞች የአካል ድጋፍ እና የተሐድሶ አገልግሎት ለማግኘት በአማራ ክልል፣ ደቡብ ወሎ ዞን፣ ደሴ ከተማ ወደሚገኘው የደሴ የአካል ጉዳተኞች ተሐድሶ ማእከል እንደሚላኩ ጠቁመዋል። በዚህም ምክንያት በአየር ንብረት ለውጥ፣ የማኅበረ- ሥነልቦና ድጋፍ አለማግኘት እንዲሁም የአካባቢውን ምግብ አለመላመድ ጋር በተያያዘ አካል ጉዳተኞች ጤናቸው መስተጓጎሉ እና አገልግሎቱን በአግባቡ ማግኘት እንዳይችሉ ተግዳሮት እንደሆነባቸው ተናግረዋል። በመጨረሻም ማእከሉን ወደ ሥራ ለማስገባት የክልሉን ፕሬዚደንት ጽሕፈት ቤት ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሊያበረክቱ የሚችሏቸውን አስተዋጽዖዎች ያካተተ የድርጊት መርኃ ግብር ተዘጋጅቷል።
የኢሰመኮ አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን መብቶች ሥራ ክፍል ዳይሬክተር ሜቲ አቶምሳ ኢሰመኮ ማእከሉ ሊሰጥ የሚገባውን አገልግሎት ለማስጀመር ከዚህ ቀደም ያደረጋቸውን ጥረቶች ጠቅሰው ይህ በርካታ የሕዝብ እና የመንግሥት ሀብት የፈሰሰበት ተቋም ከአስርት ዓመታት በላይ ለታለመለት ዓላማ አለመዋሉ በክልሉ አካል ጉዳተኞች ላይ እየፈጠረ ያለውን ጫና ከግምት በማስገባት ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። አክለውም ማዕከሉ አገልግሎት መስጠት እስከሚጀምር ድረስ ኢሰመኮ የውትወታ ሥራውን አጠንክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል።
🔗 https://ehrc.org/?p=31290
#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll #Samara #DisabilityInclusion

ሰመራ፦ ለአስርት ዓመታት አገልግሎት መስጠት ያልጀመረ የአካል ጉዳተኞች ተሐድሶ ማእከልን ለማስጀመር የተካሄደ ውይይት - Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) is an independent federal state body established by Parliament as the national human rights institution with the mandate for the promotion and protection of human rights.
👍1
Workshop: The role of the Judiciary in the Transitional Justice (TJ) Process
...
The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) in collaboration with the Federal Supreme Court of Ethiopia (FSCE), organized an awareness raising workshop on Transitional Justice (TJ) and Human Rights for the Judiciary on February 1, 2025, in Addis Ababa. The workshop brought together judges and experts from the Federal Supreme and High Courts, along with EHRC’s representatives. The workshop aimed to enhance the capacity of Ethiopian judges to engage in TJ processes and uphold international legal standards.
The workshop provided an in-depth overview of key human rights instruments and relevant provisions from International Humanitarian Law (IHL) and International Criminal Law (ICL). It particularly focused on the African human rights system, the African Charter on Human and Peoples’ Rights, international experiences and the implementation of Ethiopian TJ Policy. The overview placed special emphasis to the judiciary’s role in ensuring justice and accountability for gross human rights violations and international crimes.
The Office of the High Commissioner for Human Rights (OHCHR) detailed the international human rights obligations in the context of TJ, addressing international human rights principles, the intersection of TJ and human rights law and key components of Ethiopia’s TJ Policy. In addition, Justice Susan Okalany, Deputy Head of the International Crimes Division at the High Court of Uganda, presented a virtual overview of Uganda’s approach to prosecuting international crimes.
During the discussion, participants exchanged views on various criminal tribunal models, including international tribunals, hybrid courts and domestic mechanisms, drawing on comparative experiences from countries like Uganda, Sierra Leone and the Gambia. They also raised questions regarding international legal instruments, Ethiopia’s TJ Policy and its implementation, fostering dialogue on how different states have integrated TJ principles and international criminal law within their national legal frameworks.
In her opening remark, Her Excellency Lelise Desalegn, President of the Federal High Court, underscored the pivotal role of judges in implementing TJ in Ethiopia. She emphasized the workshop’s significance in enhancing judicial knowledge, deepening understanding of international standards and best practices in human rights protection and TJ, as well as equipping judges to navigate the complexities of TJ with dedication and integrity.
Rakeb Messele, Deputy Chief Commissioner of EHRC, reaffirmed EHRC’s commitment to promoting an inclusive, victim-centered, human rights-compliant TJ process. She highlighted EHRC’s ongoing engagement in the TJ process, stressing the importance of drawing lessons from both international and African experiences as TJ is an ever evolving process.
🔗 https://ehrc.org/?p=31301

የሳምንቱ #HumanRights Concept: ሴቶችን በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ማብቃት
...
የአፍሪካ የሰዎችና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል)፣ አንቀጽ 12(2) እና አንቀጽ 18 (2)(ለ)
አባል ሀገራት፦
በሴቶች ዘንድ ማንበብ እና መጻፍን ለማስፋፋት፣
በሁሉም ደረጃዎችና በሁሉም የትምህርት ዘርፎች በተለይም በሳይንስና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ለሴቶች የሚሰጡ ትምህርትና ስልጠናዎችን ለማስፋፋት ዝርዝር አወንታዊ እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው።
አባል ሀገራት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂዎችን ጨምሮ በአዲስና ታዳሽ የኃይል ምንጮች እንዲሁም አስፈላጊ ቴክኖሎጂዎች ላይ ምርምርንና ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት፣ በዚሁም ላይ የሴቶችን ተደራሽነት እና የቁጥጥር ተሳትፎ ለማመቻቸት ተገቢውን እርምጃ ሁሉ መውሰድ ይገባቸዋል።
🔗 https://ehrc.org/?p=31321
#Ethiopia🇪🇹 #WomenInScience #IDWGS #WomenInSTEM #WomenInScienceDay #KeepWordSafe #ጤናማቃላት

5ኛው ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሰብአዊ መብቶች የምስለ-ችሎት ወድድርን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተካሄደ ውይይት
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የሚያካሄደውን 5ኛ ዙር ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሰብአዊ መብቶች የምስለ-ችሎት ውድድር (National High Schools Human Rights Moot Court Competition – NHSHRMCC) መጀመሩን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ ጥር 21 እና 22 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ አካሂዷል። በውይይቱ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር፣ የሁሉም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችና እና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
ኢሰመኮ በየዓመቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚያካሂደው የሁለተኛ ደርጃ ትምህርት ቤቶች የሰብአዊ መብቶች የምስለ-ችሎት ውድድር ከሞላ ጎደል የመደበኛ ፍርድ ቤት የክርክር ሥርዓትን የሚከተል ውድድር ሲሆን በተመረጠ ምናባዊ የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ (hypothetical case) ላይ በመመሥረት ተማሪዎች የአመልካች እና ተጠሪ ወገንን በመወከል የጽሑፍ እና የቃል ክርክር ያደርጉበታል። ውድድሩ በተወዳዳሪ ተማሪዎች እና በትምህርት ቤት ማኅበረሰብ ዘንድ የሰብአዊ መብቶች ዕውቀትን እና ክህሎትን ለማጎልበት፤ አመለካከትን እና ባሕርይን ለመቅርጽ ያለመ ነው። ውድድሩ በክልል እና ከተማ አስተዳደር ደረጃ በትምህርት ቢሮዎች አስተባባሪነት ተጀምሮ ፍጻሜውን በአዲስ አበባ ከተማ የሚያደርግ ሲሆን ምናባዊ ጉዳዩም ወቅታዊ እና ለተማሪዎች ቅርብ በሆነ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች ላይ ያተኩራል።
በመድረኩ በ2016 ዓ.ም. የተካሄደው 4ኛው ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሰብአዊ መብቶች የምስለ-ችሎት ውድድር ሂደት የተገመገመ ሲሆን ውድድሩን አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን እና ተግዳሮቶችን በመለየት ውይይት ተደርጓል። እንዲሁም ባለፉት ውድድሮች ላይ ተሳታፊ የነበሩ እና በአሁን ወቅት በዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት በመከታተል ላይ የሚገኙ 3 ተማሪዎች የነበራቸውን መልካም ተሞክሮዎች አጋርተዋል። በተጨማሪም ውድድሩ የሚመራባቸውን መመሪያዎች እንዲሁም የውድድሩ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ በማድረግ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
በውይይት መድረኩ የተገኙት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የትምህርት ሚኒስቴር የሥርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ቴዎድሮስ ሸዋረገጥ በአዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት የግብረገብ እና የሥነዜጋ ትምህርቶች መካተታቸው ቀጣዮ ትውልድ እንደ ራስን ማወቅ፣ ሰብአዊነት፣ መከባበር፣ እኩልነት፣ ኃላፊነት እና በመሳሰሉ ዕሴቶች እንዲታነጽ ዕድል የሚሰጥ መሆኑን ጠቅሰው፣ የሰብአዊ መብቶች ምስለ ችሎት ውድድሩ በተማሪዎች፣ በመምህራን እንዲሁም በማኅበረሰቡ ዘንድ ተጽዕኖ ለመፍጠር አስተዋጽዖው የጎላ እንደሆነ ተናግረዋል።
የኢሰመኮ የሴቶች፣ የሕፃናት፣ የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋሪያ በበኩላቸው ኢሰመኮ ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ እና እንዲስፋፉ የምስለ-ችሎት ውድድርን ጨምሮ በርካታ ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን አስታውሰው፣ ቀደም ባሉ ውድድሮች ከአካታችነት አንጻር የሴቶችን እኩል ተሳትፎ ማረጋገጥ መቻሉን ገልጸዋል። ነገር ግን አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን በማሳተፍ ረገድ ክፍተት መታየቱን ጠቁመው በዘንድሮው ውድድር አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን በተወዳዳሪነት ወደ ውድድሩ ለማመጣት የሚመለከታቸው ሁሉ በተለይም ትምህርት ቢሮዎች እና ትምህርት ቤቶች ተገቢውን ጥረት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
በመጨረሻም የዚህ ዓመት ውድድር ምናባዊ ጉዳይ “ለልማት ሲባል በግዳጅ ከመፈናቀል ጋር የተያይዙ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች” ላይ እንደሚያተኩር ይፋ አድርገዋል።
🔗 https://ehrc.org/?p=31335

አማራ ክልል፦ የዳኞች ያለመከሰስ መብት የሕግ ከለላ ማግኘቱን በተመለከተ
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት በ6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 9ኛ መደበኛ ጉባኤ የዳኞች ያለመከሰስ መብት የሕግ ከለላ የሚሰጥ የአማራ ብሔራዊ ክልል ፍርድ ቤቶች የማጠናከሪያ አዋጅ ማጽደቁን እንደ በጎ ጅማሮ ይመለከተዋል። ኢሰመኮ በክልሉ በየደረጃው በሚገኙ ዳኞች ላይ የሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን አስመልክቶ በተደጋጋሚ ከደረሱት አቤቱታዎች በመነሳት በክልሉ ያለው የዳኝነት ነጻነት እንዲከበር እና ለዚህም ጠንካራ የሕግ ማዕቀፍ እንዲዘጋጅ ምክረ ሐሳቦችን ማቅረቡ እና ውትወታ ሲያደርግ መቆየቱ የሚታወስ ነው።
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ “የዳኝነት ነጻነት ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እና ለሰብአዊ መብቶች መከበር መሠረት በመሆኑ የዳኞች ያለመከሰስ መብት የሕግ ከለላ ማግኘቱ በክልሉ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እና ለሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ወሳኝ ነው” ብለዋል። አክለውም አዋጁ እንዲጸድቅ አዎንታዊ ሚና ለተጫወቱ ሁሉ ምስጋና አቅርበው፤ የአዋጁን ውጤታማ አተገባበር ለማረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት መሥራት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
🔗 https://ehrc.org/?p=31346

❤2👏2
የመገናኛ ብዙኃን የቁጥጥር ሥራዎች ከሴቶች ሰብአዊ መብቶች አንጻር ያላቸውን አተገባበር በተመለከተ የጥናት ግኝቶች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተካሄደ ውይይት
...
የመገናኛ ብዙኃን የቁጥጥር ሥራዎች አተገባበር ለሴቶች መብቶች መከበር ተገቢውን ትኩረት ሊሰጥ ይገባል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የመገናኛ ብዙኃን የቁጥጥር ሥራዎች ከሴቶች መብቶች አንጻር ያላቸውን አተገባበር በተመለከተ ባከናወነው ጥናት ላይ ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል። በውይይት መድረኩ በጥናቱ የተለዩ ግኝቶች እና ምክረ ሐሳቦች ለውይይት የቀረቡ ሲሆን፣ የቴሌቪዥን እና የሬዲዮ ብሮድካስት መገናኛ ብዙኃን ተቋማት፣ የመገናኛ ብዙኃን ተቆጣጣሪ አካላት እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሌሎች መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተወካዮች ተሳትፈዋል።
🔗 https://ehrc.org/?p=31349
#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
...
የመገናኛ ብዙኃን የቁጥጥር ሥራዎች አተገባበር ለሴቶች መብቶች መከበር ተገቢውን ትኩረት ሊሰጥ ይገባል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የመገናኛ ብዙኃን የቁጥጥር ሥራዎች ከሴቶች መብቶች አንጻር ያላቸውን አተገባበር በተመለከተ ባከናወነው ጥናት ላይ ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል። በውይይት መድረኩ በጥናቱ የተለዩ ግኝቶች እና ምክረ ሐሳቦች ለውይይት የቀረቡ ሲሆን፣ የቴሌቪዥን እና የሬዲዮ ብሮድካስት መገናኛ ብዙኃን ተቋማት፣ የመገናኛ ብዙኃን ተቆጣጣሪ አካላት እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሌሎች መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተወካዮች ተሳትፈዋል።
🔗 https://ehrc.org/?p=31349
#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ #HumanRights Concept: የሕፃናት ከጉልበት ብዝበዛ የመጠበቅ መብት
...
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 36(1) (መ)
ማንኛውም ሕፃን ጉልበቱን ከሚበዘብዙ ልማዶች የመጠበቅ፤ በትምህርቱ፣ በጤናውና በደኅንነቱ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሥራዎችን እንዲሠራ ያለመገደድ ወይም ከመሥራት የመጠበቅ መብት አለው።
ዓለም አቀፉ የሕፃናት መብቶች ስምምነት፣ አንቀጽ 32(2) (ሀ-ሐ)
ተዋዋይ ሀገራት በተለይ፡-
ዝቅተኛ የቅጥር ዕድሜን ወይም ዕድሜዎችን ይወስናሉ፤
የሥራ ሰዓትንና የቅጥር ሁኔታዎችን በተመለከተ ተገቢውን ደንብ ያወጣሉ፤
ይህ አንቀጽ በሚገባ በሥራ ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ ተገቢ ቅጣቶችን ወይም ሌሎች ክልከላዎችን ያስቀምጣሉ።
🔗 https://ehrc.org/?p=31359
#Ethiopia🇪🇹 #EndChildLabour #KeepWordSafe #ጤናማቃላት
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
...
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 36(1) (መ)
ማንኛውም ሕፃን ጉልበቱን ከሚበዘብዙ ልማዶች የመጠበቅ፤ በትምህርቱ፣ በጤናውና በደኅንነቱ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሥራዎችን እንዲሠራ ያለመገደድ ወይም ከመሥራት የመጠበቅ መብት አለው።
ዓለም አቀፉ የሕፃናት መብቶች ስምምነት፣ አንቀጽ 32(2) (ሀ-ሐ)
ተዋዋይ ሀገራት በተለይ፡-
ዝቅተኛ የቅጥር ዕድሜን ወይም ዕድሜዎችን ይወስናሉ፤
የሥራ ሰዓትንና የቅጥር ሁኔታዎችን በተመለከተ ተገቢውን ደንብ ያወጣሉ፤
ይህ አንቀጽ በሚገባ በሥራ ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ ተገቢ ቅጣቶችን ወይም ሌሎች ክልከላዎችን ያስቀምጣሉ።
🔗 https://ehrc.org/?p=31359
#Ethiopia🇪🇹 #EndChildLabour #KeepWordSafe #ጤናማቃላት
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
👍1
በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ የተካሄደ ውይይት
...
የታራሚዎችን የተሻለ የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ለማረጋገጥ በባለድርሻዎች የሚደረገው ድጋፍ በትብብር መርሕ ሊቀጥል ይገባል
በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ እና ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ የተመራ ቡድን የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ከሚያስተዳድራቸው 6 ማረሚያ ቤቶች መካከል በቃሊቲ ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማእከል በተለምዶ “አባ ሳሙኤል” በመባል በሚጠራው ማረሚያ ቤት የካቲት 11 ቀን 2017 ዓ.ም. የሥራ ጉብኝት አድርጓል። ቡድኑ በጉብኝቱ የተመለከታቸውን በጎ ጅማሮዎች፣ የታዘባቸውን ቀሪ ክፍተቶች እና ኢሰመኮ ከዚህ በፊት በማረሚያ ቤቶች ባካሄደው የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል በለያቸው ግኝቶች መነሻነት የሰጣቸው ምክረ ሐሳቦች አፈጻጸም ላይ ከፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ ጋር ተወያይቷል።
🔗 https://ehrc.org/?p=31373

Workshop: CSOs Engagement in Ethiopia’s Transitional Justice Process
...
The active participation and collaboration of NHRIs and CSOs is key in promoting an inclusive, victim-centered and human rights compliant transitional justice process
The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) hosted a sensitization workshop on February 6, 2025, at its head office in Addis Ababa, focusing on Ethiopia’s Transitional Justice (TJ) process. The event gathered representatives from EHRC alongside fifteen Civil Society Organizations (CSOs) actively engaged in TJ initiatives.
The workshop aimed to enhance the participants’ understanding of TJ principles, relevant legal frameworks and Ethiopia’s international obligations. It also sought to facilitate the integration of these elements into participants’ thematic areas of work and strategies.
🔗 https://ehrc.org/?p=31431