Consultation: Advancing the Right to Food through a Human Rights-Based Approach (HRBA)
...
The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC), in collaboration with the International Institute of Rural Reconstruction (IIRR), held a multi-stakeholder consultation on “The Right to Food and Human Rights-Based Approach” on September 8, 2025, in Addis Ababa. Aimed at promoting the integration of Human Rights-Based Approach (HRBA) principles into Ethiopia’s national food system policies and practices, the consultation brought together a diverse group of stakeholders, including representatives of the House of Peoples’ Representatives (HoPR) standing committees, government institutions, civil society organizations and community-based cooperatives.
🔗 https://ehrc.org/?p=34401
#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

❤1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ #HumanRights Concept: መረጃ የማግኘት መብት
...
ዓለም አቀፍ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን፣ አንቀጽ 19 (2)
ማንኛውም ሰው ሐሳቡን የመግለጽ ነጻነት አለው። ይህ ነጻነት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በጽሑፍ ወይም በሕትመት፣ በሥነ ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ፣ ማንኛውንም ዐይነት መረጃና ሐሳብ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት ነጻነቶችን ያካትታል።
የሰብአዊ መብቶች ኮሚቴ አጠቃላይ ትንታኔ ቁጥር 34፣ አንቀጽ 19
መረጃ የማግኘት መብትን ተግባራዊ ለማድረግ ያመች ዘንድ የቃልኪዳኑ አባል ሀገራት ዜጎች ሊያውቋቸው የሚገቡ መንግሥታዊ መረጃዎችን ለሕዝብ ይፋ ማድረግ ይኖርባቸዋል። የዚህ መረጃ ተደራሽነት ለዜጎች ቀላል፣ ፈጣን፣ ውጤታማ እና ተግባራዊ እንዲሆን አባል ሀገራት ማንኛውንም ጥረት እንዲያደርጉ ይጠበቃል።
🔗 https://ehrc.org/?p=34422
#Ethiopia🇪🇹 #KeepWordSafe #ጤናማቃላት

#ኦሮሚያ፦ በተጠርጣሪዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ ላይ የተካሄደ ውይይት
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በ2017 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል በ156 ፖሊስ ጣቢያዎች እና ኢመደበኛ ማቆያዎች የተጠርጣሪዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝን አስመልክቶ ባካሄደው ክትትል የተለዩ ግኝቶች እና የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር መስከረም 9 ቀን 2018 ዓ.ም. በቢሾፍቱ ከተማ የምክክር መድረክ አካሂዷል። በውይይቱ ከጨፌ ኦሮሚያ፣ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ፍትሕ ቢሮ፣ ፖሊስ መምሪያዎች እና ጣቢያዎች የተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
በመድረኩ ክትትል በተደረገባቸው ፖሊስ ጣቢያዎች በወንጀል ድርጊት የተጠረጠሩ ሰዎች መሠረታዊ መረጃዎች መመዝገባቸው፤ ሃይማኖትን፣ ብሔርን፣ የፖለቲካ አመለካከትን እና ሌሎች ልዩነቶችን መሠረት ያደረጉ እስሮች አለመኖር፤ ስልታዊ የሆነ ድብደባ በተጠርጣሪዎች ላይ የማይፈጸም መሆኑ፤ ተጠርጣሪዎች በቤተሰቦቻቸው፣ በጠበቆቻቸው እና በሌሎች ዘመዶቻቸው እንዳይጎበኙ ክልከላ አለመደረጉ፤ የአዳዲስ ማቆያ ክፍሎች ግንባታ እና ነባር ክፍሎችን የማደስ ሂደት መኖሩ እንዲሁም በተወሰኑ የወረዳ ፖሊስ ጣቢያዎች ዐቅም ለሌላቸው ተጠርጣሪዎች የምግብ አቅርቦት መጀመሩ በተጠርጣሪዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ ላይ የታዩ ጠንካራ ጎኖች መሆናቸው ተገልጿል።
🔗 https://ehrc.org/?p=34427

#ኦሮሚያ፡- በታራሚዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ ላይ የተካሄደ ምክክር
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በ2017 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል በ22 ማረሚያ ቤቶች የታራሚዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝን አስመልክቶ ባካሄደው ክትትል በተለዩ ግኝቶች እና በተሰጡ ምክረ ሐሳቦች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ.ም. በቢሾፍቱ ከተማ የምክክር መድረክ አካሂዷል። በመድረኩ ከጨፌ ኦሮሚያ፣ ከክልሉ ርእሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ፍትሕ ቢሮ እና ማረሚያ ቤቶች የተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
በምክክር መድረኩ ማረሚያ ቤቶች ታራሚዎችን በፍርድ ቤት ትእዛዝ ብቻ የሚቀበሉ መሆናቸው፤ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ተደራሽነት እና የታራሚዎች መረጃ አያያዝ ሥርዓትን ማሻሻላቸው፤ ታራሚዎችን በአመክሮ የሚለቁበት ሁኔታ ሕግን የተከተለ መሆኑ፤ የድብደባ እና ኢ-ሰብአዊ አያያዝ ድርጊቶች አለመኖራቸው እና ለታራሚዎች መለያ አልባሳትን ለማሟላት ጥረት ማድረጋችው አበረታች መሆኑ ተገልጿል።
በሌላ በኩል በቂ፣ ጥራት ያለው እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ችግር፣ የሕክምና አገልግሎት ውስንነት፣ የትምህርት መርጃ መሣሪያዎች እጥረት፣ የታራሚዎች ማደሪያ ክፍሎች የተጨናነቁ መሆናቸው፤ ታራሚዎችን በፈርጅ ለያይቶ አለመያዝ በአሳሳቢነት የቀጠሉ ጉዳዮች መሆናቸው ተመላክቷል።
🔗 https://ehrc.org/?p=34440

የሰብአዊ መብቶች ክበባት አደረጃጀት እና አሠራር ረቂቅ መምሪያ ላይ የተካሄደ ውይይት
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሰብአዊ መብቶች ክበባት በትምህርት ቤቶች ውስጥ እንዲስፋፉ እና በንቃት እንዲንቀሳቀሱ ለማስቻል በተዘጋጀ የአደረጃጀት እና የአሠራር ረቂቅ መምሪያ ላይ መስከረም 13 እና 14 ቀን 2018 ዓ.ም. ከባለድርሻ አካላት ጋር በአዳማ ከተማ ውይይት አካሂዷል። በውይይቱ የትምህርት ሚኒስቴር እና የክልል ትምህርት ቢሮ የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች፣ የተማሪዎች ተወካዮች እንዲሁም በትምህርት ዘርፍ ውስጥ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች ተሳትፈዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር በሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. ያወጣው እና በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ተፈጻሚ በሆነው የተጓዳኝ ትምህርት አደረጃጀት አና አተገባበር መመሪያ መሠረት በትምህርት ቤቶች መቋቋም ከሚችሉ ክበባት መካከል የሰብአዊ መብቶች ክበብ አንዱ ነው። በዚሁ መሠረት የሰብአዊ መብቶች ዕውቀት እና አመለካከት በትምህርት ቤት ማኅበረሰብ ዘንድ እንዲጎለብት ኢሰመኮ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሰብአዊ መብቶች ክበባት አደረጃጀት እና አሠራር ረቂቅ መምሪያ እና ክበባቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ተሰጥቷቸው ከሚከበሩ ቀናት ጋር በማገናኘት የሚያከናውኗቸው ተግባራትን የሚዘረዝር ረቂቅ አጋዥ ሰነድ አዘጋጅቶ ለውይይት አቅርቧል።
🔗 https://ehrc.org/?p=34485

የሳምንቱ #HumanRights Concept: የአረጋውያን ሴቶች ጥበቃ
...
የአፍሪካ የሰዎች እና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር የአረጋውያን መብቶች ፕሮቶኮል፣ አንቀጽ 9
አባል ሀገራት፦
አረጋውያን ሴቶች ከጥቃት፣ ከወሲባዊ ጥቃት እንዲሁም በጾታ ላይ ከተመሠረተ መድልዎ መጠበቃቸውን ማረጋገጥ፤
አረጋውያን ሴቶች ከንብረት እና መሬት መብቶች ጋር ከተያያዙ በደሎች መጠበቃቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሕጎችን ማውጣት እና ሌሎች እርምጃዎችን መውሰድ፤ እንዲሁም
የአረጋውያን ሴቶችን የውርስ መብት ለመጠበቅ ተገቢውን ሕግ ማውጣት አለባቸው።
🔗 https://ehrc.org/?p=34481

የሳምንቱ #HumanRights Concept: የአደጋ ሥጋት እና ሰብአዊ መብቶች
...
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 89 (3)
መንግሥት የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋ እንዳይደርስ መከላከልና አደጋው ሲደርስም ለተጎጂው እርዳታ በወቅቱ እንዲደርስ ማድረግ አለበት።
የሴንዳይ የአደጋ ሥጋት ቅነሳ ማዕቀፍ (እ.ኤ.አ. 2015 – 2030)፣ አንቀጽ 19 (ሐ)
የአደጋ ሥጋት አመራር ዓላማ የልማት መብትን ጨምሮ ሁሉንም ሰብአዊ መብቶችን በማስፋፋት እና በመጠበቅ፣ ሰዎችን እና ንብረታቸውን፣ ጤናቸውን፣ መተዳደሪያቸውን እና ምርታማ ንብረቶቻቸውን እንዲሁም የባህልና የአካባቢ ሀብቶችን መጠበቅ ነው።
🔗 https://ehrc.org/?p=34512

👍1
የመንቀሳቀስ ነጻነት
...
የመንቀሳቀስ ነጻነት ምንድነው?
የመንቀሳቀስ ነጻነት በዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ (Universal Declaration of Human Rights)፣ በሲቪልና ፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን (International Covenant on Civil and Political Rights)፣ በአፍሪካ የሰዎችና የሕዝቦች መብቶች ቻርተር (African Charter on Human and Peoples’ Rights) እንዲሁም በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ጥበቃ የተደረገለት ሰብአዊ መብት ነው። በውስጡም በአንድ ሀገር ውስጥ በመረጡት አካባቢ የመዘዋወር እና የመኖሪያ ቦታ የመመሥረት ነጻነትን፣ የራስን ጨምሮ ከማንኛውም ሀገር የመውጣት ነጻነትን፣ እንዲሁም ወደ ራስ ሀገር የመግባት (entry to one’s own country) ነጻነትን ያካትታል።
የሲቪልና ፖለቲካ መብቶችን ተፈጻሚነት የሚከታተለው የሰብአዊ መብቶች ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ በሰጠው አጠቃላይ ትንታኔ እንዳመለከተው የመንቀሳቀስ ነጻነት ለሌሎች ሰብአዊ መብቶች ተግባራዊነት ወሳኝ ቅድመ ሁኔታ ነው። በዚህም ምክንያት ለምሳሌ በሕይወት የመኖር፣ የመሥራት፣ የንብረት፣ የምግብ፣ የመኖሪያ ቤት፣ የቤተሰብ፣ የትምህርትና የጤና መብቶች ዕውን እንዲሆኑ ሰዎች ከቦታ ቦታ የመዘዋወር መብታቸው ሊከበርላቸው ይገባል።
የመንቀሳቀስ ነጻነት በውስጡ ምን ምን ጥበቃዎችን ይዟል?
🔗 https://ehrc.org/?p=34519

የሰዎችን ከቦታ ቦታ የመዘዋወር ነጻነት በተሟላ ሁኔታ መፈጸም የሚያስችሉ እርምጃዎች በአፋጣኝ ሊወሰዱ ይገባል
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኢትዮጵያ በግጭት ዐውድ ውስጥና ከግጭት ዐውድ ውጪ ባሉ አካባቢዎች ያሉ አሳሳቢ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታዎችን ለመለየት እና ለመሰነድ ከሚያዝያ ወር 2017 ዓ.ም. እስከ መስከረም ወር 2018 ዓ.ም. በተለያዩ ክልሎች የሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ ሲያከናውን ቆይቷል። በዚህም መሠረት በአማራ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ እና በኦሮሚያ ክልሎች የሚገኙ ነዋሪዎችን፣ የዓይን ምስክሮችን፣ የተጎጂ ቤተሰቦችን እንዲሁም የሚመለከታቸውን የመንግሥት አካላትን በማነጋገር መረጃ እና ማስረጃዎችን በማሰባሰብ ከለያቸው አሳሳቢ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች መካከል የሰዎችን ከቦታ ቦታ የመዘዋወር ነጻነትን የተመለከቱ ግኝቶች ከዚህ በታች ቀርበዋል።
ይህ መግለጫ በክትትል እና ምርመራ በተሸፈነው ጊዜ እና ቦታ የተለዩ ሁሉንም ግኝቶች የሚይዝ ሳይሆን የመዘዋወር መብት አፈጻጸምን የሚሸረሽሩ እና የተከሰቱ አሳሳቢ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በመለየት የሰብአዊ መብት ሁኔታውን ለማሳየት ታስበው የተመረጡ ጉዳዮችን ያካተተ ነው።
ኢሰመኮ በሐምሌ ወር 2017 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ላይም ከቦታ ቦታ የመዘዋወር ነጻነት በበጀት ዓመቱ አሳሳቢ ሆኖ መቀጠሉን መግለጹ የሚታወስ ነው።
🔗 https://ehrc.org/?p=34533

❤4
#ማእከላዊ_ኢትዮጵያ፦ በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ የተካሄደ ውይይት
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በመጋቢት እና በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. ከኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን አመያ ወረዳ እና ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ተፈናቅለው በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ እና ሀበሽጌ ወረዳ ዳርጌ ከተማ ከማኅበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው የሚኖሩ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን አስመልክቶ ከኅዳር 16 እስከ 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ባከናወነው ክትትል፣ በለያቸው ግኝቶች እና ባቀረባቸው ምክረ ሐሳቦች ላይ መስከረም 22 ቀን 2018 ዓ.ም. በሆሳዕና ከተማ ውይይት አካሂዷል።
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች በውይይቱ ተሳትፈዋል። በውይይቱ ኢሰመኮ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ ባከናወነው ክትትል የለያቸው ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ለውይይት ቀርበዋል። በዚህም መሠረት ከአመያ እና ኖኖ ወረዳዎች ወደ ወልቂጤ ከተማ እና ሀበሽጌ ወረዳ የተፈናቀሉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ምዝገባ አለመደረጉ፣ ተፈናቃዮች መብቶቻቸውን ለመጠቀም የሚያስችሉ ሰነዶች አለማግኘታቸው፣ የጸጥታና ደኅንነት ሥጋት ያለባቸው መሆኑ፣ የሰብአዊ ድጋፍ እና መሠረታዊ አገልግሎትን ጨምሮ ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ተፈናቃዮች የተመቻቸ ሁኔታ አለመኖሩ እንዲሁም የዘላቂ መፍትሔ አማራጮችን የማፈላልግ ሥራ በመንግሥት በኩል አለመጀመሩ ተገልጿል።
🔗 https://ehrc.org/?p=34544

#አዲስ_አበባ፡ በአካል ጉዳተኞች የትምህርት መብቶች ዙሪያ ለቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ተቋማት ባለሙያዎች የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ተቋማት ለሚሠሩ ባለሙያዎች በአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች መብቶች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መስከረም 27 እና 28 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ አካሂዷል። መድረኩ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ከጉዳት አልባ አቻዎቻቸው እኩል የትምህርት መብታቸው እንዲጠበቅላቸው፣ የአካቶ ትምህርት ማእከላት በቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ተቋማት ውስጥ እንዲስፋፉ፣ እንዲሁም በዘርፉ የሚታየውን የአመለካከት ክፍተት ለማጥበብ የሚያስችል ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ነው።
በመድረኩ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩትን ጨምሮ በአዲስ አበባ ከሚገኙ ስድስት የመንግሥት የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የተውጣጡ መምህራን፣ ርዕሳነ መምህራን እና ሠራተኞች የተሳተፉ ሲሆን በዋናነት የሰብአዊ መብቶች መሠረታዊ ፅንሰ ሐሳቦች እና የአካል ጉዳተኞች የትምህርት መብትን አስመልክቶ ግንዛቤ ተሰጥቷል።
በተጨማሪም፣ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት ውስጥ የሚጋጥሟቸው ተግዳሮቶች፣ የአካል ጉዳተኞች አካቶ ቴክኒክ እና ሙያ መመሪያ ይዘት፣ እንዲሁም የመፍትሔ ሐሳቦች ቀርበው ከተሳታፊዎች ጋር ውይይት ተደርጓል።
🔗 https://ehrc.org/?p=34557

ሰብአዊ መብቶችን ማስፋፋት፦ በ2018 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተሰጡ ስልጠናዎች
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሐምሌ 2017 ዓ.ም. እስከ መስከረም 2018 ዓ.ም. ባሉት ሦስት ወራት በተለያዩ ከተሞች ለሚገኙ የወጣቶች ማኅበራት፣ ለሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እንዲሁም ለማረሚያ ቤት ፖሊሶች እና አመራሮች በሰብአዊ መብቶች እና በሽግግር ፍትሕ፣ በወንጀል የተጠረጠሩ እና ተፈርዶባቸው በመታረም ላይ የሚገኙ ሰዎች ሰብአዊ መብቶች ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎችን ሰጥቷል።
ኢሰመኮ በሰብአዊ መብቶች እና በሽግግር ፍትሕ ዙሪያ በአርባ ምንጭ፣ በበደሌ፣ በዲላ፣በመቱ እና በሮቤ ከተሞች ከሐምሌ 14 እስከ ነሐሴ 23 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ የአምስት የአምስት ቀናት የስልጠና መድረኮችን በማዘጋጀት ለ166 ወጣቶች የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጥቷል። ስልጠናው ወጣቶች በሰብአዊ መብቶች ፅንሰ ሐሳብ እና እሴቶች ላይ ያላቸውን ዕውቀት እና ክህሎት በማሳደግ የሰብአዊ መብቶች መከበር ለሰላም እና አብሮ መኖር ያላቸውን ዋጋ ተረድተው የበኩላቸውን እንዲወጡ ለማድረግ ያለመ ነው።
በስልጠናዎቹ የሌሎች ሀገራት የሽግግር ፍትሕ ተሞክሮዎች የቀረቡ ሲሆን የወጣቶችን ጉልህ ሚና ለማሳደግ የሚረዱ ተግባራዊ ልምምዶች የተካተቱበት ነው። በዚህ የአሰልጣኞች ስልጠና ላይ የተሳተፉ ወጣቶች በየከተማቸው ለሚገኙ 113 ወጣቶች እና የማኅበር አባላት የመልሶ ስልጠና ሰጥተዋል።
🔗 https://ehrc.org/?p=34565

ለ5ኛው የኢሰመኮ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል የኪነጥበብ ሥራዎች ውድድር ተጀመረ
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀን ጋር በማስተሳሰር በየዓመቱ የሚያካሂደው የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል 5ኛ ዙር የፎቶግራፍ እና የአጫጭር ፊልም ሥራዎች ውድድር ዛሬ ጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም. በይፋ ተጀምሯል። ውድድሩ በኢሰመኮ የ2017 በጀት ዓመት የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርት በከፍተኛ ደረጃ አሳሳቢ በመሆን ከተለዩት ጉዳዮች መካከል በነጻነት መብት እና በትምህርት መብት ላይ ያተኩራል።
ውድድሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚደረግ ሲሆን አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በሁሉም ክልሎች የሚገኙ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። ከግለሰቦች በተጨማሪ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ማለትም የመገናኛ ብዙኃን፣ የኮሙኒኬሽን፣ የሲቪክ ማኅበረሰብ፣ የትምህርትና ስልጠና ድርጅቶች ወዘተ. በውድድሩ መሳተፍ ይችላሉ።
ከ2014 ዓ.ም. ጀምሮ በኢሰመኮ አዘጋጅነት የሚካሄደው ዓመታዊ ፊልም ፌስቲቫል ዓላማ በኪነ ጥበብ ሥራዎቻቸው ስለ ሰብአዊ መብቶች የሚያወሱ እና የሰብአዊ መብቶች መከበር፣ ጥበቃና መስፋፋትን የሚያበረታቱ ሰዎችን፣ ተቋማትን እና ድምፆችን ማሰባሰብ ነው።
ስለ ፌስቲቫሉ እና ውድድሩ ተጨማሪ ማብራሪያ፦ https://filmfest.ehrc.org
🔗 https://ehrc.org/?p=34586
#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll #HumanRightsFilmFestival

#ደቡብ_ኢትዮጵያ፦ ኢሰመኮ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ያካሄደው ምክክር
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በክልሉ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ አጠቃላይ ምልከታ ላይ ጥቅምት 5 ቀን 2018 ዓ.ም. በአርባ ምንጭ ከተማ ምክክር አካሂዷል። ምክክሩ ኢሰመኮ በክልሉ በተለያዩ ጊዜያት ባደረጋቸው የሰብአዊ መብቶች ክትትሎች እና ምርመራዎች በተለዩ ግኝቶች እና በተሰጡ ምክረ ሐሳቦች ላይ በመወያየት አሳሳቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ለመወትወት ያለመ ነው።
በምክክሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ጥላሁን ከበደ፣ የብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አዳማ ትንዳዬ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝደንት ክቡር አንዷለም አምባዬ እንዲሁም የክልሉ ፍትሕ እና ጸጥታ ቢሮ፣ ፖሊስ እና ማረሚያ ኮሚሽን፣ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር እና የሌሎች ተቋማት ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ ለውይይት መነሻ ባቀረቡት ገለጻ በክልሉ በዳሰነች ወረዳ ያሉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የመብት አያያዝ ሁኔታ፣ በተለያዩ አካባቢዎች በተደጋጋሚ የሚፈጸም ግድያ እና ሌሎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንዲሁም የሕዳጣን መብቶችን ማእከል ያደረጉ ግኝቶችን አብራርተዋል። የሽግግር ፍትሕም ውይይት ከተደረገባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ነው።
🔗 https://ehrc.org/?p=34595

#ሶማሊ፦ በክልሉ ያለውን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ለማሻሻል በማለም የተካሄደ ውትወታ
...
የሰብአዊ መብቶች አከባበር ላይ የሚስተዋሉ መሻሻሎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ፤ የጥሰቶች መነሻ የሆኑ ችግሮችም እልባት ሊያገኙ ይገባል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በሶማሊ ክልል ያለውን አጠቃላይ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ በተመለከተ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጋር ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም. በጅግጅጋ ከተማ ውይይት አካሂዷል። ውይይቱ ኢሰመኮ በክልሉ ያለውን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ በተመለከተ በተለያየ ጊዜ ባካሄዳቸው ክትትሎች የደረሰባቸውን ግኝቶች በማቅረብ መልካም እመርታዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እና አሳሳቢ ጉዳዮች የእርምት እርምጃ እንዲወሰድባቸው ለማሳሰብ ያለመ የኢሰመኮ የውትወታ ተግባር አካል ነው። በውይይቱ ኢሰመኮ የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ሙስጠፋ መሀመድን እና የክልሉ ማረሚያ ቤት ኮሚሽነር በሽር አህመድ ሐሺን ጨምሮ ሌሎች የሥራ ኃላፊዎችን አነጋግሯል።
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ በሶማሊ ክልል ከሀገራዊ ለውጡ በፊት በማረሚያ ቤቶች እና በፖሊስ ጣቢያዎች ሲፈጸሙ የነበሩ ድብደባ እና ሌሎች የማሰቃየት ተግባራት እንዲሁም ስልታዊ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች መቅረታቸው፣ ለታራሚዎች ከሌሎች ክልሎች የተሻለ የቀን ፍጆታ በጀት መመደቡ፣ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው በመመለስ እና በማቋቋም ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት ጥረቶች መደረጋቸው እና የሽግግር ፍትሕን ተግባራዊ ለማድረግ እርምጃዎች መወሰዳቸው አበረታች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
🔗 https://ehrc.org/?p=34648

📢 ዝግጁ ናችሁ?!
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በ5ኛው ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል በፎቶግራፍ እና በአጫጭር ፊልሞች ዘርፍ እንዲወዳደሩ ይጋብዝዎታል።
በውድድሩ ስለ ትምህርት መብት 📷በፎቶግራፍ እንዲሁም ስለ ነጻነት መብት 🎬በአጭር ፊልም እይታዎን ይሰንዱ ከዚያም ለውድድር ይላኩት፡፡ ለአሸናፊዎች ዳጎስ ያለ ሽልማት፣ ዕውቅና እና ምስጋና ተዘጋጅቷል፡፡
ይወዳደሩ! የኪነጥበብ ዐቅምዎን ተጠቅመው ለሰብአዊ መብቶች መስፋፋት አሻራ ያኑሩ!
ለመሳተፍ እና ለተጨማሪ መረጃ፡- https://filmfest.ehrc.org
#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsFilmFestival

የሳምንቱ #HumanRights Concept: ከቤተሰቦቻቸው የተለዩ ሕፃናት ጥበቃ
...
የሕፃናት መብቶች ስምምነት፣ አንቀጽ 20 (1) እና (2)
ለጊዜው ወይም ለዘለቄታው ከቤተሰቡ የተለየ ወይም ለራሱ ጥቅም ሲባል ከቤተሰቡ ጋር እንዲቆይ ሊደረግ የማይችል ሕፃን የመንግሥትን ልዩ ጥበቃ እና ድጋፍ የማግኘት መብት አለው።
አባል ሀገራት በብሔራዊ ሕጎቻቸው መሠረት ከቤተሰቡ የተለየ ሕፃን አማራጭ እንክብካቤ ማግኘቱን ማረጋገጥ አለባቸው።
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 36 (5)
መንግሥት ለእጓለ ማውታን ልዩ ጥበቃ ያደርግላቸዋል። በጉዲፈቻ የሚያድጉበትን ሥርዓት የሚያመቻቹና የሚያስፋፉ እንዲሁም ደኅንነታቸውንና ትምህርታቸውን የሚያራምዱ ተቋሞች እንዲመሠረቱ ያበረታታል።
🔗 https://ehrc.org/?p=34655
#Ethiopia🇪🇹 #KeepWordSafe #ጤናማቃላት
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
...
የሕፃናት መብቶች ስምምነት፣ አንቀጽ 20 (1) እና (2)
ለጊዜው ወይም ለዘለቄታው ከቤተሰቡ የተለየ ወይም ለራሱ ጥቅም ሲባል ከቤተሰቡ ጋር እንዲቆይ ሊደረግ የማይችል ሕፃን የመንግሥትን ልዩ ጥበቃ እና ድጋፍ የማግኘት መብት አለው።
አባል ሀገራት በብሔራዊ ሕጎቻቸው መሠረት ከቤተሰቡ የተለየ ሕፃን አማራጭ እንክብካቤ ማግኘቱን ማረጋገጥ አለባቸው።
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 36 (5)
መንግሥት ለእጓለ ማውታን ልዩ ጥበቃ ያደርግላቸዋል። በጉዲፈቻ የሚያድጉበትን ሥርዓት የሚያመቻቹና የሚያስፋፉ እንዲሁም ደኅንነታቸውንና ትምህርታቸውን የሚያራምዱ ተቋሞች እንዲመሠረቱ ያበረታታል።
🔗 https://ehrc.org/?p=34655
#Ethiopia🇪🇹 #KeepWordSafe #ጤናማቃላት
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
በጋዜጠኞች የሕግ ጥበቃ (ከለላ) ላይ የተካሄደ ውይይት
...
ሐሳብን በነጻነት መግለጽ መሠረታዊ እና በዘፈቀደ ገደብ የማይደረግበት ሰብአዊ መብት ነው
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከኢንተርናሽናል ሚዲያ ሰፖርት (International Media Support) ጋር በመተባበር በጋዜጠኞች የሕግ ጥበቃ (ከለላ) ላይ ጥቅምት 04 ቀን 2018 ዓ.ም. በአርባ ምንጭ ከተማ ውይይት አካሂዷል። በውይይቱ ከማእከላዊ ኢትዮጵያ፣ ከሲዳማ እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች የሕግ አስፈጻሚ አካላት እና ከግልና ከመንግሥት የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
የጥላቻ ንግግርን እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን እንዲሁም የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጡ አዋጆችን ሽፋን በማድረግ የሚፈጸሙ ክልከላዎች እና ገደቦች፣ የመገናኛ ብዙኃን አባላት ስለመብታቸውና ግዴታቸው ያላቸው ግንዛቤ ማነስ እንዲሁም የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ለተወሰኑ የመገናኛ ብዙኃን ብቻ መረጃ የመስጠት አዝማሚያ በተለይም የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ኃላፊዎች ለግል መገናኛ ብዙኃን መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆን በዘርፉ የታዩ ክፍተቶች መሆናቸው በውይይቱ ተነስቷል። በሌላ በኩል የጥላቻ ንግግሮችን፣ ሐሰተኛ መረጃዎችን እንዲሁም ግጭት የሚቀሰቅሱ መልእክቶችን የሚያሰራጩ መገናኛ ብዙኃንን መቆጣጠር አለመቻሉ፣ በበይነ-መረብ ላይ የሚጣሉ ገደቦች እና በመገናኛ ብዙኃን አማካኝነት ተፈጽሟል በተባለ ወንጀል ጋዜጠኞች ከሕግ ውጭ እስራት የሚፈጸምባቸው መሆኑ በውይይቱ ተነስቷል።
🔗 https://ehrc.org/?p=34661

ፍትሕ የማግኘት መብትን በተመለከተ የተካሄደ ውይይት
...
የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች የተፈጸመባቸው ሰዎች ውጤታማ ፍትሕ እንዲያገኙ የፍትሕ ተቋማት አገልግሎት ተደራሽነት ወሳኝ ነው
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከታኅሣሥ 19 እስከ የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም. በማእከላዊ ኢትዮጵያ፣ በሲዳማ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ፍትሕ የማግኘት መብት ሁኔታን በተመለከተ ባደረገው ክትትል በለያቸው ግኝቶች ላይ ጥቅምት 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ከባለድርሻ አካላት ጋር በአርባምንጭ ከተማ ውይይት አካሂዷል።
በውይይቱ የሦስቱ ክልሎች ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች እና ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ተወካዮች፣ የመንግሥት ሠራተኞች አስተዳደር ፍርድ ቤቶች ተጠሪ ዳኞች፣ የክልልና የዞን የፍትሕ (ዐቃቤያነ ሕግ)፣ የፖሊስና ማረሚያ ተቋማት እንዲሁም የክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
በመድረኩ ኢሰመኮ በሦስቱ ክልሎች ያለውን ፍትሕ የማግኘት መብት ሁኔታ አስመልክቶ ባከናወነው ክትትል የለያቸው አሳሳቢ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮችና ምክረ ሐሳቦች ቀርበዋል። በቁጥጥር ሥራ የዋሉ ተጠርጣሪዎችን በ48 ሰዓት ፍርድ ቤት ሳያቀርቡ ለተራዘመ ጊዜ በእስር ማቆየት እና አቤቱታቸውን ፍርድ ቤት እንዳያቀርቡ በፖሊስ የሚደረግ ክልከላ መኖሩ በውይይቱ ተገልጿል። በተለይም ‘ኮማንድ ፖስት’ በሚል ተግባራዊ በሚደረግ የሕግ ማስከበር እንቅስቃሴ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሰዎችን መደበኛ ባልሆኑ ቦታዎች አስሮ ማቆየት አሳሳቢ የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
🔗 https://ehrc.org/?p=34674

👍3