Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ #HumanRights Concept: ከአስገድዶ መሰወር የመጠበቅ መብት
...
ሁሉንም ሰው ከአስገድዶ መሰወር ለመጠበቅ የወጣ መግለጫ፣ አንቀጽ 1
ማንኛውም የአስገድዶ መሰወር ተግባር ሰብአዊ ክብርን የሚጥስ ድርጊት ነው። ይህ ተግባር የተባበሩት መንግሥታት ቻርተር ዐላማዎችን የሚጣረስ እንዲሁም በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ እና በዘርፉ ባሉ ዓለም አቀፍ ሰነዶች ውስጥ የተደነገጉ እና ተጨማሪ ዕውቅና ያገኙ ሰብአዊ መብቶች እና መሠረታዊ ነጻነቶች ላይ የሚፈጸም ከባድ እና ግልጽ ጥሰት ተደርጎ ይወሰዳል።
የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት፣ አንቀጽ 28(1)
ኢትዮጵያ ባጸደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እና በሌሎች የኢትዮጵያ ሕጎች በሰው ልጅ ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ተብለው የተወሰኑትን ወንጀሎች፣ የሰው ዘር የማጥፋት፣ ያለፍርድ የሞት ቅጣት እርምጃ የመውሰድ፣ በአስገዳጅ ሰውን የመሰወር፣ ወይም ኢ-ሰብአዊ የድብደባ ድርጊቶችን በፈጸሙ ሰዎች ላይ ክስ ማቅረብ በይርጋ አይታገድም። በሕግ አውጪው ክፍልም ሆነ በማንኛውም የመንግሥት አካል ውሳኔዎች በምሕረት ወይም በይቅርታ አይታለፍም።
🔗 https://ehrc.org/?p=34311
#Ethiopia🇪🇹 #KeepWordSafe #ጤናማቃላት
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

❤3
ለኢሰመኮ የቀድሞ ኮሚሽነሮች የተዘጋጀ የምስጋና መድረክ
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ኃላፊነታቸውን በራሳቸው ፈቃድ ለለቀቁት የቀድሞ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ እና የቀድሞ የሴቶች፣ የሕፃናት፣ የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋርያ ነሐሴ 22 ቀን 2017 ዓ.ም. የምስጋናና ዕውቅና መርኃ ግብር በአዲስ አበባ ዋናው መሥሪያ ቤት አካሂዷል፡፡ የኢሰመኮ ዋና መሥሪያ ቤት እና የከተማ ጽሕፈት ቤቶች የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በአካል እንዲሁም በበይነ-መረብ በመርኃ ግብሩ ተሳትፈዋል፡፡
በመድረኩ ከኢሰመኮ የተለያዩ የሥራ ክፍሎች የተውጣጡ ሠራተኞች ለተሰናባች ኮሚሽነሮች ምስጋና እና መልካም ምኞታቸውን አቅርበዋል፡፡ በቀድሞ ኮሚሽነሮች የአገልግሎት ጊዜ ኢሰመኮ በርካታ ስኬቶችን እንዳስመዘገበ፣ በተለይም የቀድሞ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ከአጋር ድርጅቶች ጋር ኢሰመኮ ያለውን ግንኙነት በማጠናከር ተልዕኮውን ለመወጣት የሚያግዘውን ፋይናንስ በማፈላለግ እና ለሰብአዊ መብቶች ጠበቃ በመሆን ከፍተኛ አስተዋጽዖ ማበርከታቸው ተነግሯል። እንዲሁም የቀድሞ የሴቶች፣ የሕፃናት፣ የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ተጋላጭ የማኅበረሰብ ክፍሎች መብቶችን ከማስከበር አንጻር ውጤታማ የውትወታ ተግባራትን በማከናወን መንግሥት የአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን መብቶችን ለማረጋገጥ አስተዋጽዖ ያላቸውን የሕግ እና የፖሊስ እርምጃዎች እንዲወስድ በማድረግ ረገድ የማይተካ ሚና እንደተጫወቱ ተገልጿል፡፡
🔗 https://ehrc.org/?p=34321
#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll

የሳምንቱ #HumanRights Concept: ትምህርትን ከጥቃት መጠበቅ
...
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ 74/275፤ “ትምህርትን ከጥቃት የመጠበቅ ዓለም አቀፍ ቀን”፣ አንቀጽ 2
የተ.መ.ድ. ጠቅላላ ጉባኤ:-
የሁሉም ሰዎች የትምህርት መብትን እንዲሁም በሰብአዊነት ቀውስ ሁኔታ ውስጥ ደኅንነቱ የተጠበቀና አስቻይ የትምህርት ከባቢን እና በሁሉም ደረጃዎች የትምህርት ጥራትን የማስፈን አስፈላጊነትን በድጋሚ ያረጋግጣል።
በትምህርት ቤቶች ላይ የሚሰነዘሩ ማናቸውም ጥቃቶችን እና ከዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ በሚጻረር መልኩ ትምህርት ቤቶችን ለወታደራዊ አገልግሎት ማዋልን አጥብቆ ያወግዛል፤ በሰብአዊነት ቀውስ ሁኔታ ውስጥ አስተማማኝ እና ጥበቃ የሚያስገኝ የትምህርት ቤት አካባቢን ለማስፋፋት የሚደረጉ ጥረቶችን ያበረታታል።
🔗 https://ehrc.org/?p=34351

❤4
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ #HumanRights Concept: ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እና ዴሞክራሲ
...
ሁሉ አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ፣ አንቀጽ 19
ማንኛውም ሰው በነጻነት የመሰለውን አመለካከት የመያዝ እና ሐሳቡን የመግለጽ መብት አለው፤ ይህ መብት ያለጣልቃ ገብነት አመለካከት የመያዝ እና በሀገራት ድንበር ሳይወሰኑ በማናቸውም ዐይነት የመገናኛ ዘዴዎች መረጃዎችና ሐሳቦችን የማፈላለግ፣ የመቀበል እና የማሰራጨት ነጻነትን ይጨምራል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ውሳኔ 44/12፤ “የአመለካከት እና ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት”፣ አንቀጽ 7
ዴሞክራሲያዊ ማኅበረሰብ የአመለካከት እና ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ጨምሮ ሰብአዊ መብቶችን በማክበር ላይ የተመሠረተ ሲሆን፤ መረጃን በማፈላለግ፣ በመቀበል እና በማሰራጨት ነጻነት ላይ አላግባብ የሚጣሉ ገደቦች የመንግሥት ባለሥልጣናትን ተጠያቂ ለማድረግ እና ሙስናን ለማጋለጥ የሚደረጉ ጥረቶችን በማስቀረት ዴሞክራሲን እና የሕግ የበላይነትን ያዳክማሉ።
🔗 https://ehrc.org/?p=34359

በትምህርት ቤቶች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ እና ምቹነት ላይ የተካሄደ የውይይት መድረክ
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ምቹ መሆናቸውን እና የተማሪዎች የሰብአዊ መብቶች አጠባበቅ ሁኔታን አስመልክቶ በአዲስ አበባ፣ አፋር፣ አማራ፣ ጋምቤላ፣ ኦሮሚያ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች በሚገኙ 61 የመንግሥት እና የግል 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ባደረገው ክትትል የተለዩ ግኝቶች እና ምክረ ሐሳቦች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ነሐሴ 27 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ የውይይት መድረክ አካሂዷል። በውይይቱ የትምህርት ሚኒስቴር፣ የክልሎች የትምህርት እና የገንዘብና ኢኮኖሚ ቢሮ ኃላፊዎችና ተወካዮች እንዲሁም የትምህርት ቤቶች ርዕሰ መምህራን ተሳትፈዋል።
በመድረኩ ኢሰመኮ በክትትሉ የለያቸው ቁልፍ እመርታዎች፣ አሳሳቢ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች እና የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል። በአብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች የመጠጥ እና የንጽሕና መጠበቂያ ውሃ እና በጾታ የተለዩ መጸዳጃ ቤቶች መኖር፣ ከጤና ተቋማት ጋር በሽታ የመከላከልና ክትባት የመስጠት ሥራዎች የሚከናወን መሆኑ፣ የተማሪዎች እና የሠራተኞች የሥነ ምግባር ደንብ መኖር እንዲሁም በአብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች ሴት ተማሪዎች እኩል ተሳትፎ እንዲኖራቸው ጥረት መደረጉ ክትትሉ በአበረታችነት ከለያቸው ጉዳዮች መካከል ናቸው።
🔗 https://ehrc.org/?p=34378

👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ #HumanRights Concept: ተመጣጣኝ ማመቻቸት
...
የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነት፤ አንቀጽ 5 (3) እና (4)
እኩልነትን ለማስፋፋትና አድሎዊ ልዩነትን ለማስወገድ ዓላማ ተዋዋይ ሀገራት ተመጣጣኝ ማመቻቸት መደረጉን ለማረጋገጥ ተገቢ የሆነውን ማንኛውንም እርምጃ መውሰድ አለባቸው።
የአካል ጉዳተኞችን ተጨባጭ እኩልነት ለማፋጠን ወይም ለማሳካት አስፈላጊ በመሆናቸው የሚወሰዱ የተለዩ እርምጃዎች በዚህ ስምምነት ድንጋጌዎች መሠረት አድሎአዊ ልዩነቶች ተደርገው አይወሰዱም።
የአካል ጉዳተኞች መብቶች ኮሚቴ አጠቃላይ ትንታኔ ቁጥር 6፤ አንቀጽ 23
ተመጣጣኝ ማመቻቸት በአካል ጉዳተኝነት ዐውድ ውስጥ ወዲያውኑ ተፈጻሚ ሊሆን የሚገባው አድሏዊ ልዩነት ያለማድረግ ግዴታ አካል ነው። የተመጣጣኝ ማመቻቸት ምሳሌዎች ነባር መገልገያዎችን እና መረጃዎችን ለአካል ጉዳተኛው ተደራሽ የማድረግ፤ መሣሪያዎችን የማስተካከል፤ ተግባራትን እንደገና የማደራጀት፤ የሥራ መርኃ ግብሮችን የማሻሻል፤ የትምህርት ሥርዓትን፣ የመማሪያ ቁሳቁሶችን እንዲሁም የማስተማሪያ ስልቶችን የማስተካከል፤ የሕክምና ሂደቶችን የማስተካከል ወይም ኢ-ተመጣጣኝ ወይም አግባብ ያልሆነ ግዴታን በማያስከትል ሁኔታ አካል ጉዳተኛው ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞችን እንዲያገኝ የማስቻል እርምጃዎችን ይጨምራሉ።
🔗 https://ehrc.org/?p=34394

❤2
Consultation: Advancing the Right to Food through a Human Rights-Based Approach (HRBA)
...
The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC), in collaboration with the International Institute of Rural Reconstruction (IIRR), held a multi-stakeholder consultation on “The Right to Food and Human Rights-Based Approach” on September 8, 2025, in Addis Ababa. Aimed at promoting the integration of Human Rights-Based Approach (HRBA) principles into Ethiopia’s national food system policies and practices, the consultation brought together a diverse group of stakeholders, including representatives of the House of Peoples’ Representatives (HoPR) standing committees, government institutions, civil society organizations and community-based cooperatives.
🔗 https://ehrc.org/?p=34401

❤1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሳምንቱ #HumanRights Concept: መረጃ የማግኘት መብት
...
ዓለም አቀፍ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን፣ አንቀጽ 19 (2)
ማንኛውም ሰው ሐሳቡን የመግለጽ ነጻነት አለው። ይህ ነጻነት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በጽሑፍ ወይም በሕትመት፣ በሥነ ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ፣ ማንኛውንም ዐይነት መረጃና ሐሳብ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት ነጻነቶችን ያካትታል።
የሰብአዊ መብቶች ኮሚቴ አጠቃላይ ትንታኔ ቁጥር 34፣ አንቀጽ 19
መረጃ የማግኘት መብትን ተግባራዊ ለማድረግ ያመች ዘንድ የቃልኪዳኑ አባል ሀገራት ዜጎች ሊያውቋቸው የሚገቡ መንግሥታዊ መረጃዎችን ለሕዝብ ይፋ ማድረግ ይኖርባቸዋል። የዚህ መረጃ ተደራሽነት ለዜጎች ቀላል፣ ፈጣን፣ ውጤታማ እና ተግባራዊ እንዲሆን አባል ሀገራት ማንኛውንም ጥረት እንዲያደርጉ ይጠበቃል።
🔗 https://ehrc.org/?p=34422

#ኦሮሚያ፦ በተጠርጣሪዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ ላይ የተካሄደ ውይይት
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በ2017 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል በ156 ፖሊስ ጣቢያዎች እና ኢመደበኛ ማቆያዎች የተጠርጣሪዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝን አስመልክቶ ባካሄደው ክትትል የተለዩ ግኝቶች እና የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር መስከረም 9 ቀን 2018 ዓ.ም. በቢሾፍቱ ከተማ የምክክር መድረክ አካሂዷል። በውይይቱ ከጨፌ ኦሮሚያ፣ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ፍትሕ ቢሮ፣ ፖሊስ መምሪያዎች እና ጣቢያዎች የተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
በመድረኩ ክትትል በተደረገባቸው ፖሊስ ጣቢያዎች በወንጀል ድርጊት የተጠረጠሩ ሰዎች መሠረታዊ መረጃዎች መመዝገባቸው፤ ሃይማኖትን፣ ብሔርን፣ የፖለቲካ አመለካከትን እና ሌሎች ልዩነቶችን መሠረት ያደረጉ እስሮች አለመኖር፤ ስልታዊ የሆነ ድብደባ በተጠርጣሪዎች ላይ የማይፈጸም መሆኑ፤ ተጠርጣሪዎች በቤተሰቦቻቸው፣ በጠበቆቻቸው እና በሌሎች ዘመዶቻቸው እንዳይጎበኙ ክልከላ አለመደረጉ፤ የአዳዲስ ማቆያ ክፍሎች ግንባታ እና ነባር ክፍሎችን የማደስ ሂደት መኖሩ እንዲሁም በተወሰኑ የወረዳ ፖሊስ ጣቢያዎች ዐቅም ለሌላቸው ተጠርጣሪዎች የምግብ አቅርቦት መጀመሩ በተጠርጣሪዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ ላይ የታዩ ጠንካራ ጎኖች መሆናቸው ተገልጿል።
🔗 https://ehrc.org/?p=34427

#ኦሮሚያ፡- በታራሚዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ ላይ የተካሄደ ምክክር
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በ2017 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል በ22 ማረሚያ ቤቶች የታራሚዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝን አስመልክቶ ባካሄደው ክትትል በተለዩ ግኝቶች እና በተሰጡ ምክረ ሐሳቦች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ.ም. በቢሾፍቱ ከተማ የምክክር መድረክ አካሂዷል። በመድረኩ ከጨፌ ኦሮሚያ፣ ከክልሉ ርእሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ፍትሕ ቢሮ እና ማረሚያ ቤቶች የተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
በምክክር መድረኩ ማረሚያ ቤቶች ታራሚዎችን በፍርድ ቤት ትእዛዝ ብቻ የሚቀበሉ መሆናቸው፤ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ተደራሽነት እና የታራሚዎች መረጃ አያያዝ ሥርዓትን ማሻሻላቸው፤ ታራሚዎችን በአመክሮ የሚለቁበት ሁኔታ ሕግን የተከተለ መሆኑ፤ የድብደባ እና ኢ-ሰብአዊ አያያዝ ድርጊቶች አለመኖራቸው እና ለታራሚዎች መለያ አልባሳትን ለማሟላት ጥረት ማድረጋችው አበረታች መሆኑ ተገልጿል።
በሌላ በኩል በቂ፣ ጥራት ያለው እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ችግር፣ የሕክምና አገልግሎት ውስንነት፣ የትምህርት መርጃ መሣሪያዎች እጥረት፣ የታራሚዎች ማደሪያ ክፍሎች የተጨናነቁ መሆናቸው፤ ታራሚዎችን በፈርጅ ለያይቶ አለመያዝ በአሳሳቢነት የቀጠሉ ጉዳዮች መሆናቸው ተመላክቷል።
🔗 https://ehrc.org/?p=34440

የሰብአዊ መብቶች ክበባት አደረጃጀት እና አሠራር ረቂቅ መምሪያ ላይ የተካሄደ ውይይት
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሰብአዊ መብቶች ክበባት በትምህርት ቤቶች ውስጥ እንዲስፋፉ እና በንቃት እንዲንቀሳቀሱ ለማስቻል በተዘጋጀ የአደረጃጀት እና የአሠራር ረቂቅ መምሪያ ላይ መስከረም 13 እና 14 ቀን 2018 ዓ.ም. ከባለድርሻ አካላት ጋር በአዳማ ከተማ ውይይት አካሂዷል። በውይይቱ የትምህርት ሚኒስቴር እና የክልል ትምህርት ቢሮ የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች፣ የተማሪዎች ተወካዮች እንዲሁም በትምህርት ዘርፍ ውስጥ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች ተሳትፈዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር በሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. ያወጣው እና በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ተፈጻሚ በሆነው የተጓዳኝ ትምህርት አደረጃጀት አና አተገባበር መመሪያ መሠረት በትምህርት ቤቶች መቋቋም ከሚችሉ ክበባት መካከል የሰብአዊ መብቶች ክበብ አንዱ ነው። በዚሁ መሠረት የሰብአዊ መብቶች ዕውቀት እና አመለካከት በትምህርት ቤት ማኅበረሰብ ዘንድ እንዲጎለብት ኢሰመኮ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሰብአዊ መብቶች ክበባት አደረጃጀት እና አሠራር ረቂቅ መምሪያ እና ክበባቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ተሰጥቷቸው ከሚከበሩ ቀናት ጋር በማገናኘት የሚያከናውኗቸው ተግባራትን የሚዘረዝር ረቂቅ አጋዥ ሰነድ አዘጋጅቶ ለውይይት አቅርቧል።
🔗 https://ehrc.org/?p=34485

የሳምንቱ #HumanRights Concept: የአረጋውያን ሴቶች ጥበቃ
...
የአፍሪካ የሰዎች እና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር የአረጋውያን መብቶች ፕሮቶኮል፣ አንቀጽ 9
አባል ሀገራት፦
አረጋውያን ሴቶች ከጥቃት፣ ከወሲባዊ ጥቃት እንዲሁም በጾታ ላይ ከተመሠረተ መድልዎ መጠበቃቸውን ማረጋገጥ፤
አረጋውያን ሴቶች ከንብረት እና መሬት መብቶች ጋር ከተያያዙ በደሎች መጠበቃቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሕጎችን ማውጣት እና ሌሎች እርምጃዎችን መውሰድ፤ እንዲሁም
የአረጋውያን ሴቶችን የውርስ መብት ለመጠበቅ ተገቢውን ሕግ ማውጣት አለባቸው።
🔗 https://ehrc.org/?p=34481

የሳምንቱ #HumanRights Concept: የአደጋ ሥጋት እና ሰብአዊ መብቶች
...
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 89 (3)
መንግሥት የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋ እንዳይደርስ መከላከልና አደጋው ሲደርስም ለተጎጂው እርዳታ በወቅቱ እንዲደርስ ማድረግ አለበት።
የሴንዳይ የአደጋ ሥጋት ቅነሳ ማዕቀፍ (እ.ኤ.አ. 2015 – 2030)፣ አንቀጽ 19 (ሐ)
የአደጋ ሥጋት አመራር ዓላማ የልማት መብትን ጨምሮ ሁሉንም ሰብአዊ መብቶችን በማስፋፋት እና በመጠበቅ፣ ሰዎችን እና ንብረታቸውን፣ ጤናቸውን፣ መተዳደሪያቸውን እና ምርታማ ንብረቶቻቸውን እንዲሁም የባህልና የአካባቢ ሀብቶችን መጠበቅ ነው።
🔗 https://ehrc.org/?p=34512

👍1
የመንቀሳቀስ ነጻነት
...
የመንቀሳቀስ ነጻነት ምንድነው?
የመንቀሳቀስ ነጻነት በዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ (Universal Declaration of Human Rights)፣ በሲቪልና ፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን (International Covenant on Civil and Political Rights)፣ በአፍሪካ የሰዎችና የሕዝቦች መብቶች ቻርተር (African Charter on Human and Peoples’ Rights) እንዲሁም በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ጥበቃ የተደረገለት ሰብአዊ መብት ነው። በውስጡም በአንድ ሀገር ውስጥ በመረጡት አካባቢ የመዘዋወር እና የመኖሪያ ቦታ የመመሥረት ነጻነትን፣ የራስን ጨምሮ ከማንኛውም ሀገር የመውጣት ነጻነትን፣ እንዲሁም ወደ ራስ ሀገር የመግባት (entry to one’s own country) ነጻነትን ያካትታል።
የሲቪልና ፖለቲካ መብቶችን ተፈጻሚነት የሚከታተለው የሰብአዊ መብቶች ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ በሰጠው አጠቃላይ ትንታኔ እንዳመለከተው የመንቀሳቀስ ነጻነት ለሌሎች ሰብአዊ መብቶች ተግባራዊነት ወሳኝ ቅድመ ሁኔታ ነው። በዚህም ምክንያት ለምሳሌ በሕይወት የመኖር፣ የመሥራት፣ የንብረት፣ የምግብ፣ የመኖሪያ ቤት፣ የቤተሰብ፣ የትምህርትና የጤና መብቶች ዕውን እንዲሆኑ ሰዎች ከቦታ ቦታ የመዘዋወር መብታቸው ሊከበርላቸው ይገባል።
የመንቀሳቀስ ነጻነት በውስጡ ምን ምን ጥበቃዎችን ይዟል?
🔗 https://ehrc.org/?p=34519

የሰዎችን ከቦታ ቦታ የመዘዋወር ነጻነት በተሟላ ሁኔታ መፈጸም የሚያስችሉ እርምጃዎች በአፋጣኝ ሊወሰዱ ይገባል
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኢትዮጵያ በግጭት ዐውድ ውስጥና ከግጭት ዐውድ ውጪ ባሉ አካባቢዎች ያሉ አሳሳቢ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታዎችን ለመለየት እና ለመሰነድ ከሚያዝያ ወር 2017 ዓ.ም. እስከ መስከረም ወር 2018 ዓ.ም. በተለያዩ ክልሎች የሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ ሲያከናውን ቆይቷል። በዚህም መሠረት በአማራ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ እና በኦሮሚያ ክልሎች የሚገኙ ነዋሪዎችን፣ የዓይን ምስክሮችን፣ የተጎጂ ቤተሰቦችን እንዲሁም የሚመለከታቸውን የመንግሥት አካላትን በማነጋገር መረጃ እና ማስረጃዎችን በማሰባሰብ ከለያቸው አሳሳቢ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች መካከል የሰዎችን ከቦታ ቦታ የመዘዋወር ነጻነትን የተመለከቱ ግኝቶች ከዚህ በታች ቀርበዋል።
ይህ መግለጫ በክትትል እና ምርመራ በተሸፈነው ጊዜ እና ቦታ የተለዩ ሁሉንም ግኝቶች የሚይዝ ሳይሆን የመዘዋወር መብት አፈጻጸምን የሚሸረሽሩ እና የተከሰቱ አሳሳቢ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በመለየት የሰብአዊ መብት ሁኔታውን ለማሳየት ታስበው የተመረጡ ጉዳዮችን ያካተተ ነው።
ኢሰመኮ በሐምሌ ወር 2017 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ላይም ከቦታ ቦታ የመዘዋወር ነጻነት በበጀት ዓመቱ አሳሳቢ ሆኖ መቀጠሉን መግለጹ የሚታወስ ነው።
🔗 https://ehrc.org/?p=34533

#ማእከላዊ_ኢትዮጵያ፦ በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ የተካሄደ ውይይት
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በመጋቢት እና በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. ከኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን አመያ ወረዳ እና ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ተፈናቅለው በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ እና ሀበሽጌ ወረዳ ዳርጌ ከተማ ከማኅበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው የሚኖሩ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን አስመልክቶ ከኅዳር 16 እስከ 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ባከናወነው ክትትል፣ በለያቸው ግኝቶች እና ባቀረባቸው ምክረ ሐሳቦች ላይ መስከረም 22 ቀን 2018 ዓ.ም. በሆሳዕና ከተማ ውይይት አካሂዷል።
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች በውይይቱ ተሳትፈዋል። በውይይቱ ኢሰመኮ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ ባከናወነው ክትትል የለያቸው ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ለውይይት ቀርበዋል። በዚህም መሠረት ከአመያ እና ኖኖ ወረዳዎች ወደ ወልቂጤ ከተማ እና ሀበሽጌ ወረዳ የተፈናቀሉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ምዝገባ አለመደረጉ፣ ተፈናቃዮች መብቶቻቸውን ለመጠቀም የሚያስችሉ ሰነዶች አለማግኘታቸው፣ የጸጥታና ደኅንነት ሥጋት ያለባቸው መሆኑ፣ የሰብአዊ ድጋፍ እና መሠረታዊ አገልግሎትን ጨምሮ ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ተፈናቃዮች የተመቻቸ ሁኔታ አለመኖሩ እንዲሁም የዘላቂ መፍትሔ አማራጮችን የማፈላልግ ሥራ በመንግሥት በኩል አለመጀመሩ ተገልጿል።
🔗 https://ehrc.org/?p=34544

#አዲስ_አበባ፡ በአካል ጉዳተኞች የትምህርት መብቶች ዙሪያ ለቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ተቋማት ባለሙያዎች የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ተቋማት ለሚሠሩ ባለሙያዎች በአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች መብቶች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መስከረም 27 እና 28 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ አካሂዷል። መድረኩ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ከጉዳት አልባ አቻዎቻቸው እኩል የትምህርት መብታቸው እንዲጠበቅላቸው፣ የአካቶ ትምህርት ማእከላት በቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ተቋማት ውስጥ እንዲስፋፉ፣ እንዲሁም በዘርፉ የሚታየውን የአመለካከት ክፍተት ለማጥበብ የሚያስችል ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ነው።
በመድረኩ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩትን ጨምሮ በአዲስ አበባ ከሚገኙ ስድስት የመንግሥት የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የተውጣጡ መምህራን፣ ርዕሳነ መምህራን እና ሠራተኞች የተሳተፉ ሲሆን በዋናነት የሰብአዊ መብቶች መሠረታዊ ፅንሰ ሐሳቦች እና የአካል ጉዳተኞች የትምህርት መብትን አስመልክቶ ግንዛቤ ተሰጥቷል።
በተጨማሪም፣ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት ውስጥ የሚጋጥሟቸው ተግዳሮቶች፣ የአካል ጉዳተኞች አካቶ ቴክኒክ እና ሙያ መመሪያ ይዘት፣ እንዲሁም የመፍትሔ ሐሳቦች ቀርበው ከተሳታፊዎች ጋር ውይይት ተደርጓል።
🔗 https://ehrc.org/?p=34557

ሰብአዊ መብቶችን ማስፋፋት፦ በ2018 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተሰጡ ስልጠናዎች
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሐምሌ 2017 ዓ.ም. እስከ መስከረም 2018 ዓ.ም. ባሉት ሦስት ወራት በተለያዩ ከተሞች ለሚገኙ የወጣቶች ማኅበራት፣ ለሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እንዲሁም ለማረሚያ ቤት ፖሊሶች እና አመራሮች በሰብአዊ መብቶች እና በሽግግር ፍትሕ፣ በወንጀል የተጠረጠሩ እና ተፈርዶባቸው በመታረም ላይ የሚገኙ ሰዎች ሰብአዊ መብቶች ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎችን ሰጥቷል።
ኢሰመኮ በሰብአዊ መብቶች እና በሽግግር ፍትሕ ዙሪያ በአርባ ምንጭ፣ በበደሌ፣ በዲላ፣በመቱ እና በሮቤ ከተሞች ከሐምሌ 14 እስከ ነሐሴ 23 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ የአምስት የአምስት ቀናት የስልጠና መድረኮችን በማዘጋጀት ለ166 ወጣቶች የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጥቷል። ስልጠናው ወጣቶች በሰብአዊ መብቶች ፅንሰ ሐሳብ እና እሴቶች ላይ ያላቸውን ዕውቀት እና ክህሎት በማሳደግ የሰብአዊ መብቶች መከበር ለሰላም እና አብሮ መኖር ያላቸውን ዋጋ ተረድተው የበኩላቸውን እንዲወጡ ለማድረግ ያለመ ነው።
በስልጠናዎቹ የሌሎች ሀገራት የሽግግር ፍትሕ ተሞክሮዎች የቀረቡ ሲሆን የወጣቶችን ጉልህ ሚና ለማሳደግ የሚረዱ ተግባራዊ ልምምዶች የተካተቱበት ነው። በዚህ የአሰልጣኞች ስልጠና ላይ የተሳተፉ ወጣቶች በየከተማቸው ለሚገኙ 113 ወጣቶች እና የማኅበር አባላት የመልሶ ስልጠና ሰጥተዋል።
🔗 https://ehrc.org/?p=34565

ለ5ኛው የኢሰመኮ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል የኪነጥበብ ሥራዎች ውድድር ተጀመረ
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀን ጋር በማስተሳሰር በየዓመቱ የሚያካሂደው የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል 5ኛ ዙር የፎቶግራፍ እና የአጫጭር ፊልም ሥራዎች ውድድር ዛሬ ጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም. በይፋ ተጀምሯል። ውድድሩ በኢሰመኮ የ2017 በጀት ዓመት የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርት በከፍተኛ ደረጃ አሳሳቢ በመሆን ከተለዩት ጉዳዮች መካከል በነጻነት መብት እና በትምህርት መብት ላይ ያተኩራል።
ውድድሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚደረግ ሲሆን አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በሁሉም ክልሎች የሚገኙ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። ከግለሰቦች በተጨማሪ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ማለትም የመገናኛ ብዙኃን፣ የኮሙኒኬሽን፣ የሲቪክ ማኅበረሰብ፣ የትምህርትና ስልጠና ድርጅቶች ወዘተ. በውድድሩ መሳተፍ ይችላሉ።
ከ2014 ዓ.ም. ጀምሮ በኢሰመኮ አዘጋጅነት የሚካሄደው ዓመታዊ ፊልም ፌስቲቫል ዓላማ በኪነ ጥበብ ሥራዎቻቸው ስለ ሰብአዊ መብቶች የሚያወሱ እና የሰብአዊ መብቶች መከበር፣ ጥበቃና መስፋፋትን የሚያበረታቱ ሰዎችን፣ ተቋማትን እና ድምፆችን ማሰባሰብ ነው።
ስለ ፌስቲቫሉ እና ውድድሩ ተጨማሪ ማብራሪያ፦ https://filmfest.ehrc.org
🔗 https://ehrc.org/?p=34586
#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll #HumanRightsFilmFestival

#ደቡብ_ኢትዮጵያ፦ ኢሰመኮ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ያካሄደው ምክክር
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በክልሉ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ አጠቃላይ ምልከታ ላይ ጥቅምት 5 ቀን 2018 ዓ.ም. በአርባ ምንጭ ከተማ ምክክር አካሂዷል። ምክክሩ ኢሰመኮ በክልሉ በተለያዩ ጊዜያት ባደረጋቸው የሰብአዊ መብቶች ክትትሎች እና ምርመራዎች በተለዩ ግኝቶች እና በተሰጡ ምክረ ሐሳቦች ላይ በመወያየት አሳሳቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ለመወትወት ያለመ ነው።
በምክክሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ጥላሁን ከበደ፣ የብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አዳማ ትንዳዬ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝደንት ክቡር አንዷለም አምባዬ እንዲሁም የክልሉ ፍትሕ እና ጸጥታ ቢሮ፣ ፖሊስ እና ማረሚያ ኮሚሽን፣ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር እና የሌሎች ተቋማት ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ ለውይይት መነሻ ባቀረቡት ገለጻ በክልሉ በዳሰነች ወረዳ ያሉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የመብት አያያዝ ሁኔታ፣ በተለያዩ አካባቢዎች በተደጋጋሚ የሚፈጸም ግድያ እና ሌሎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንዲሁም የሕዳጣን መብቶችን ማእከል ያደረጉ ግኝቶችን አብራርተዋል። የሽግግር ፍትሕም ውይይት ከተደረገባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ነው።
🔗 https://ehrc.org/?p=34595