Telegram Web Link
ዋጋቸው 1300 ብር
ብዛት ከአስር ያነሰ ብቻ ነው ያለው
ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ዉሹ ፌዴሬሽን በሃገር ውስጥ የሚገኙ ስፖርተኞችን የዘመናት ጥያቄ ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል።በዚህም መሰረት ቁጰጥራቸው ቀላል የማይባል ስፖርተኞችን ከተለያዩ ክልሎች በተለያዩ ጊዜያት ወደ ቻይና በመላክ የረጅምና የአጭር ጊዜ ስልጠናዎችን እንዲወስዱ መደረጉ ይታወሳል።በቀጣይም ይህን ስልጠናን በቋሚነት ለማስቀጠል እና የበለጠ ተደራሽ እንዲሆን ከሚመለከታቸው ጋር እየተሰራ ነው።ይህ በእንዲህ እንዳለ የስራ አስፈፃሚ ቦርዱ በወሰነው መሰረት ወደ ውጪ ልኮ የማሰልጠን ሂደቱ እንዳለ ሆኖ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን ከውጪ ባለሙያዎችን በማስመጣት በዕቅድ የተያዙ ቀዳሚ ተግባራት ተፈፃሚ እንዲሆኑ በተላለፈው አቅጣጫ መሠረት ክፍተቶችን በመፈተሽ እና በቀጣይ በሀገር ውስጥ የሳንሹ/ፋይት/የማሰልጠን ሂደትን ወጥ እና ዘመናዊ ለማድረግ ከአለም አቀፉ ተቋም ጋር በመነጋገር ከመጋቢት 8-10/2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ አለም አቀፍ ታላቅ ስልጠና ለመስጠት ዝግጅታችንን የጨረስን ሲሆን ስልጠናው በዋናነት ሳንሹ ላይ የሚያተኩር ሆኖ በቀጣይ በማሰልጠን ስራ ላይ አውንታዊ ለውጥ የሚያመጣ መሆኑን ሁሉም አሰልጣኝ ተገንዝቦ በክልላችሁ በኩል እንድትመዘገቡ እናሳስባለን ።
ለስልጠናው የሚበቁ መስፈርቶች
1. ከህጋዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ጥቁር ቀበቶ ያለው መረጃ ማቅረብ የሚችል
2. ከኢትዮጵያ ዉሹ ፌዴሬሽን ዳን የወሰደ
3. በክለቡ:በክልሉ ወይም በሀገር አቀፍ ደረጃ ቅጣት ያልተላለፈበት
4. አሰልጣኝ ከሆነ ህጋዊ እውቅናና ፍቃድ ያለው

ማሳሰቢያ
_ ስልጠናው የደረጃ እና ዓለም አቀፋዊ እውቅና ያለው ሲሆን ስልጠናውን ለሚያጠናቅቁ ሁሉ ደረጃውን የጠበቀ እና የተመዘገበ ህጋዊ ሰርቲፌኬት ከውጭ ሀገር ተዘጋጅቶ እንደሚመጣ መግለፅ እንወዳለን።
_ ክፍያን በተመለከተ አቅምን ባገናዘበ መልኩ 2000.00/ሁለት ሺ ብር/መሆኑን እየገለፅን ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ 913618715/911673538/ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል ።
uniform mgzat mtflgu @sanwushu lay yanagrun
የኢትዮጵያ ዉሹ ፌዴሬሽን ከነሀሴ 29/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት ሊሰጥ የነበረው ዓለም አቀፍ የታኦሉ ስልጠና ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ።ከክልሎች ጋር በተደረገው የጋራ ውይይትና ውሳኔ ስልጠናው እንዲራዘም ተደርጓል።በዋናነት ለመራዘሙ እንደምክንያት ከተነሱት ነጥቦች ውስጥ ለስልጠናው የተመረጠው ቀን ከአዲስ አመት መቀበያ ወቅት ጋር የገጠመ በመሆኑ ለስልጠናው ከተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች የሚመጡ ሰልጣኞች በተለይ ለመመለስ ከፍተኛ የትራንስፖርት እክል የሚገጥማቸው በመሆኑ ለተጨማሪ ወጪ እና እንግልት እንዳይዳረጉ በማሰብ ወደፊት እንዲራዘም የተወሰነ ሲሆን ለተፈጠረው የፕሮግራም ለውጥ ይቅርታ እየጠየቅን ተለዋጭ ፕሮግራሙን በቅርቡ የምናሳውቅ ይሆናል።
Forwarded from Tibebe Belay
2024/05/29 09:11:39
Back to Top
HTML Embed Code: