Telegram Web Link
ይህንን ያውቁ ይሆን!?

በዘፀአት ውስጥ የምናገኘው ትርክት እጅግ የሚያስደምምና ግራ የሚያጋባ ትርክት ይዟል። በአንድ ወቅት እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከግብፁ ንጉስ ፈርዖን ነፃ ለማውጣት ምን ማድረግ እንዳለበት ለሙሴ መመሪያ ሰጠው፥ እግዚአብሔር ለሙሴ በትሩን ወደ እባብ የመቀየርና ይህን መሰል ሌሎች ልዩ ችሎታዎችን ሰጠው። ሆኖም ግን፣ ሙሴ ወደ ግብፅ ሲያቀና፣ እግዚአብሔር ግልብጥ ብሎ ሌላ ሀሳብ ጠነሰሰ።

እርሱም በሚገርም ሁኔታ ሙሴን መግደል ነበር፦

ዘጸአት 4 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁴ ሙሴ በጒዞ ላይ በእንግዳ ማረፊያ ስፍራ ውስጥ ሳለ እግዚአብሔር (ያህዌ) አግኝቶት ሊገድለው ፈልጎ ነበር።



ጥያቄ አንድ፡ እግዚአብሔር ሙሴን ሊገድለው እንደፈለገ የሚተርክልን ሰው ሙሴ ነው ወይስ ሌላ ሰው?

ጥያቄ ሁለት፡ እግዚአብሔር ሙሴን ሊገድለው የፈለገው ምን አጥፍቶ ነው?


ብቻ አንዳንዴ እግዚአብሔር እንዲህ አይነት ግልብጥ ሚያደርግ ኪያል አለበት እንዳትሉኝ!😅


https://www.tg-me.com/ewnet_lehulum
Coming Soon!…🔥
እውነት ለሁሉ [truth for all]
Coming Soon!…🔥
ከአዲሱ መጽሐፍ የተቀነጨበ ነው።


አንዱ አምላክ ስለ ኢየሱስ ሲናገር "ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌ እሰጥሃለሁ" ብሎ ነበር፦
ኢሳይያስ 42፥6 ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌ እሰጥሃለሁ። καὶ ἔδωκά σε εἰς διαθήκην γένους, εἰς φῶς ἐθνῶν
ኢሳይያስ 49፥6 ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌ ሰጥቼሃለሁ። ἰδοὺ δέδωκά σε εἰς διαθήκην γένους, εἰς φῶς ἐθνῶν τοῦ εἶναί σε εἰς.

ሰጪው አንዱ አምላክ ሲሆን ተሰጪው ኢየሱስ ነው፥ ኢየሱስ የተሰጠው "ብርሃን" ሆኖ ነው። "እሰጥካለው" ማለት "እልክካለው" ማለት ከሆነ ዘንዳ ኢየሱስ ከእርሱ በኃላ ስለሚመጣው አጽናኝ ሲናገር "ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል" ብሎ ተንብዮአል፦
ዮሐንስ 14፥16 እኔ አብን እለምናለሁ፥ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል። κἀγὼ ἐρωτήσω τὸν Πατέρα καὶ ἄλλον Παράκλητον δώσει ὑμῖν ἵνα ᾖ μεθ’ ὑμῶν εἰς τὸν αἰῶνα,

"ይሰጣችኋል" የሚለው ይሰመርበት! ሰጪ አንዱ አምላክ ሲሆን ተሰጪ ሌላ አጽናኝ ነው። "ሌላ" የሚለው ቃል "አሎስ" ἄλλος ሲሆን "ሌላ ተመሳሳይ ዓይነት"another the same kind" ማለት ነው፥ ለምሳሌ፦
ማቴዎስ 5፥39 ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ "ሁለተኛውን" ደግሞ አዙርለት። ἀλλ’ ὅστις σε ῥαπίζει εἰς τὴν δεξιὰν σιαγόνα σου, στρέψον αὐτῷ καὶ τὴν ἄλλην·

"ሁለተኛው" ለሚለው የገባው ቃል "አሎስ" ἄλλος ሲሆን የፊተኛው ቀኝ ጉንጭ ከሁለተኛው ግራ ጉንጭ ጋር ተመሳሳይ ናቸው፥ በተመሳሳይ ሁለተኛው አጽናኝ ከፊተኛው አጽናኝ ከኢየሱስ ጋር የሚያመሳስላቸው ብዙ ነገር እንዳለ አመላካች ነው።
ሙታኖች ተነስተው ሄዱ!

በማቴዎስ ዘገባ ላይ የምናገኘው ታሪክ እጅጉን ያስደምማል¡ መቃብሮች ተከፍተው ሙታኖች ተነስተው ወደ ቅድስት ከተማ ገብተው ለብዙዎች ታዩ ይለናል። ይሄ ታሪክ በተቀሩት ሦስቱ ወንጌላቶች ላይ የሌለ ሲሆን፣ በተጨማሪም በታሪክ ምንም አይነት ማረጋገጫ ያልተገኘለት ሐሰተኛ ዘገባ ነው።


ማቴዎስ 27 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵¹ በዚያን ጊዜ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ተቀደደ፤ ምድር ተናወጠች፤ ዐለቶችም ተሰነጣጠቁ፤
⁵² መቃብሮች ተከፈቱ፤ ሞተው የነበሩትም ብዙዎች ቅዱሳን ተነሡ፤
⁵³ ከመቃብርም በመውጣት ከኢየሱስ ትንሣኤ በኋላ ወደ ቅድስት ከተማ ገብተው ለብዙዎች ታዩ።


ለዚህ ተረተረት ጥያቄ ቢጤ ላንሳ!

ስለነዚህ ከሙታን ስለተነሱ ሰዎች ተጨማሪ ማብራሪያ እንፈልጋለን ለምሳሌ፦ ከሞት ከተነሱ በኋላ ምን ነበሩ ስጋ ወይስ መንፈስከዚያ በኋላ ለምን ያህል ጊዜ ኖረዋልየቀድሞ ህይወታቸውን ቀጥለዋልንወይስ እንደ አዲስ መኖር ጀመሩ ከቀድሞ ቤተሰቦቻቸውስጋ ተገናኝተው ይሆን


https://www.tg-me.com/ewnet_lehulum
አምላክ ጌታን ከሞት አስነሳው!


አብዛኛው ወልደ አዳም የፈጠረውን ፈጣሪ ትቶ ፍጡራንን አምላኪ ነው፤ ለእብለት ስር የለው! ለእባብ እግር የለው! እንደሚባለው ሁሉ፥ ያለ ማስረጃና ያለ እውነታ በጨለማ ውስጥ ይዳክራል። ከሁሉ በላይ ደግሞ ላቅ ያለው ቅጥፈት ፈጣሪ ሞቷል ብሎ ማመን ነው። እንደው ጉድ'ኮ ነው! መቼም ለአፍ ለከት የለው! የፈጣሪን ክብርና ባህሪ ከመፅሐፋቸው ቢያነቡና ቢረዱ የተሻለ ነበር። ግና ችግሩ እንኳን ሊያነቡት ትራስ አድርገውታል!

ኢየሱስ እንደሞተ ባይብል ይናገራል ነገር ግን ያ የሞተው ሬሳ 'ጌታ' ተብሏል፦

ዮሐንስ 20 (John)
13፤ እነርሱም፡— አንቺ ሴት፥ ስለ ምን ታለቅሻለሽ? አሉአት። እርስዋም፡— ~ጌታዬን ወስደውታል~ ወዴትም እንዳኖሩት አላውቅም፡ አለቻቸው።
ዮሐንስ 20 (John)
2፤ እየሮጠችም ወደ ስምዖን ጴጥሮስና ኢየሱስ ይወደው ወደ ነበረው ወደ ሌላው ደቀ መዝሙር መጥታ፡— -~ጌታን ከመቃብር ወስደውታል~ ወዴትም እንዳኖሩት አናውቅም፡ አለቻቸው።

ጌታን ከመቃብር ወስደውታል በማለት ሬሳውን ጌታ ብላ መጥራቷን ልብ ይበሉ! ለመጀመሪያ ጊዜ አምላክ ጌታን አስነሣው ብሎ ያስተማረው ጳውሎስ ሲሆን ይህ አስተምህሮ ነቢያት ያልነካኩትና የማያውቁት የጣዖታውያን(የሠይጣን) አስተምህሮ ነው።

“አምላክ ጌታን ከሙታን አንዳስነሣው፣ እኛንም ደግሞ በኀይሉ ከሙታን ያስነሣናል።”
  — 1ኛ ቆሮንቶስ 6፥14 (አዲሱ መ.ት)

ኢየሱስ እንደሞተ ባይብል ይናገራል፣ ኢየሱስ እንደታየም ባይብል ይናገራል። ግን በሚያሳዝን ሁኔታ አይኔን ግንባር ያርገው፣ በማለት ፍጡር የሆነውን ኢየሱስን አምላክ ለማድረግ የሚዳዳቸው አያሌ ናቸው። ይህን አስተሳሰባቸውን ከንቱ የሚያደርግና ፈጣሪ እንደማይሞት እንዲሁም እንዳልሞተ በመፅሐፋቸው ተቀምጧል፦

“እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን፤ አሜን።”
  — 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥16

“ብቻውን አምላክ ለሚሆን ለማይጠፋው ለማይታየውም ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።”
  — 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥17

እውነተኛው አምላክ ብቸኛ ነው፣ አልሞተም፣ ማንም አላየውም ሊያየውም አይቻለውም። ይሄንን እውነታ የሚቀበልና የሚያስተነትን ሰው ኢየሱስ አምላክ ሳይሆን ጌትነቱም ሌሎች ነቢያቶች እንደተጠሩበት የፍጡር ጌትነት እንደሆነ በግልፅ ይረዳል። አንዱና ብቸኛው የአለማት ፈጣሪ ሙታንና ሬሳ ሲሆን አስባችሁታል?! አስታግፊረሏህ!!! ምን አይነት ጭንቅላት ያለው ሰው ነው እንዲ ሚያስበው?


ውድ ወገኖቻችን ሆይ! የተሠጠን አዕምሮ ልናስተነትንበት ነው አይደል? የፈጠረንን ፈጣሪ በእንደዚህ አይነት ተልካሻ ሃሳብ መሳሉ ራሱ እንዴት አዕምሮ ይቀበለዋል?


Al-Furqan 25:58

وَتَوَكَّلْ عَلَى ٱلْحَىِّ ٱلَّذِى لَا يَمُوتُ وَسَبِّحْ بِحَمْدِهِۦۚ وَكَفَىٰ بِهِۦ بِذُنُوبِ عِبَادِهِۦ خَبِيرًا

በዚያም በማይሞተው ሕያው አምላክ ላይ ተመካ፡፡ ከማመስገንም ጋር አጥራው፡፡ በባሮቹ ኀጢኣቶችም ውስጠ ዐዋቂ በእርሱ በቃ፡፡


ንቁ!!! ካላችሁበት ጨለማ ብርሃን ወደሆነው ኢስላም ኑ!


Abdulrauf

https://www.tg-me.com/ewnet_lehulum
መፅሐፋችሁን አምጡ‼️

ኢስላም ጥልልና ጥንፍፍ ባለ መልኩ የፈጣሪ መለኮታዊ መፅሃፍቶች በዘመኑ የተወረደላቸው ሰዎች እንዲጠብቁ ተሰጥተው ከዚያም እንዳልጠበቋቸውና እንዲሁም እንደተበረዙ በግልፅ ሁኔታ ያስተምራል። ክርስትያን ወገኖቻችን ደግሞ ሁሉም የነቢያትን መፅሃፍት በእጃቸው ላይ እንደሚገኝ ሲናገሩና እንደ ጉድ ሲተረተሩ መስማት ፀሐይ የሞቀው ሀገር ያወቀው ዜማ ከሆነ ሰነባብቷል። ያው አፍ ሲናገር አፍንጫ ያሽሟጣልና! እጃቸው ላይ ያሉት መፅሃፍቶች ባለቤትና ፀሃፊያቸውን መርሳታቸው፣ እዳው ገብስ ሆኗል። የፈጣሪ መፅሃፍቶች "ከቁርዓን" ውጭ ያሉት እንደተበረዙና እንደጠፉ ብንናገርም ውሸታም እየተባልን እዚህ ደርሰናል። እኛም ሆደ ሰፊ ነገር አሳላፊ! ሆነን የተሰነዘረብንን የተሳሳተ ክስ ችላ ባለማለት ደጋግመን ለማስረዳት እየጣርን ደከመኝ ወገቤን ሳንል ይሄው አለን። እኛ እውነት ላይ ስለሆንን ወደፊትም እንጥራለን፤ መቼስ ውሸት እውነት ሲመጣበት እሳት የገባ ቅቤ ከመሆን አይተርፍምና! እንግዲህ ቀጠፋችሁ ከተባልን አይቀር፣ ነገሩን የእጅ አዙር አድርገን ጥያቄያችንን እንዲህ እንሰነዝራለን፦

1ኛ፡ የያሻር መፅሃፍ የት ነው የሚገኘው?

“ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመ፥ ጨረቃም ዘገየ። ይህስ በያሻር መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይም በሰማይ መካከል ዘገየ፥ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል ለመግባት አልቸኰለም።”
  — ኢያሱ 10፥13

“የይሁዳንም ልጆች ያስተምሩ ዘንድ አዘዘ። እነሆ፥ ይህ በያሻር መጽሐፍ ተጽፎአል።”
  — 2ኛ ሳሙኤል 1፥18

ይህ የያሻር መፅሃፍ በየትኛውም የመፅሃፍ ቅዱስ ክፍል አይገኝም፤ ይልቁንስ የጠፋ መፅሐፍ እንደሆነና አሁን የትም እንደማይገኝ ይነገርለታል።[1]

2ኛ፡ የእግዚአብሄር የጦርነት መፅሐፍ የት ነው የሚገኘው?

“ስለዚህ በእግዚአብሔር የጦርነት መጽሐፍ እንዲህ ተባለ፦ ዋሄብ በሱፋ፥ የአርኖንም ሸለቆች፥”
  — ዘኍልቁ 21፥14

ይህ መፅሐፍ በየትኛውም የመፅሃፍ ቅዱስ ክፍል ላይ የለም፤ ታዲያ የት ገባ?

3ኛ፡ ሳሙዔል ፅፎ በእግዚአብሄር ፊት ያኖረው 3ኛው የሳሙዔል የሕግ መፅሃፍ የት ገባ?

“ሳሙኤልም ለንጉሥ የሚገባውን ወግና ሥርዐት ለሕዝቡ ገልጦ ካስረዳ በኋላ በመጽሐፍ ጽፎ በእግዚአብሔር ፊት አኖረው። ከዚህ በኋላ ሳሙኤል እያንዳንዱን ሰው ወደየቤቱ አሰናበተ።”
  — 1ኛ ሳሙኤል 10፥25 (አዲሱ መ.ት)

4ኛ፡ የነቢዩ ናታን ታሪክ፣ የኦሒያ ትንቢት፣ የነቢዩ ሻማያና እና የአዶ ራዕይ የተፃፈበት መፅሐፍት የት ገቡ?

“የቀረውም ፊተኛውና ኋለኛው የሰሎሞን ነገር በነቢዩ በናታን ታሪክ፥ በሴሎናዊውም በኦሒያ ትንቢት፥ ስለ ናባጥም ልጅ ስለ ኢዮርብዓም ባየው በባለ ራእዩ በአዶ ራእይ የተጻፈ አይደለምን?”
  — 2 ዜና 9፥29

“የሮብዓምም የፊተኛውና የኋለኛው ነገር በነቢዩ ሸማያና በባለ ራእዩ በአዶ የትውልድ ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? በሮብዓምና በኢዮርብዓም መካከልም በዘመናቸው ሁሉ ሰልፍ ነበረ።”
  — 2 ዜና 12፥15

የአብያም የቀረው ነገርና አካሄዱ የተናገራቸውም ቃሎች በነቢዩ በአዶ መጽሐፍ ተጽፈዋል።”
  — 2 ዜና 13፥22

5ኛ፡ የእስራዔል ነገስታት ታሪክስ የት ይገኝ ይሆን?

“የቀረውም የኢዮርብዓም ነገር፥ እንዴት እንደ ተዋጋ፥ እንዴትም እንደ ነገሠ፥ እነሆ፥ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል።”
  — 1ኛ ነገሥት 14፥19

“የምናሴም የቀረው ነገር፥ ወደ አምላኩም የጸለየው ጸሎት፥ በእስራኤልም አምላክ በእግዚአብሔር ስም የነገሩት የነቢያት ቃል፥ እነሆ፥ በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል።”
  — 2 ዜና 33፥18

“የቀረውም የዘምሪ ነገር፥ ያደረገውም ዐመፅ፥ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?”
  — 1ኛ ነገሥት 16፥20

በእስራኤል ነገሥታት ኢዮርብዓም እና በይሁዳ ሮብዓም ዘመነ መንግሥት ስለተከናወኑት ነገሮችና ስለ ንጉሥ ዘምሪ ይናገራሉ ተብሏል፤ የት ይገኙ ይሆን? አፋልጉን!

6ኛ፡ የነቢዩ ናታንና የጋድ ታሪክ የተፃፈበት የራሳቸው መፅሐፍት የት ገቡ?

“የንጉሡም የዳዊት የፊተኛውና የኋለኛው ነገር፥ እነሆ፥ በባለ ራእዩ በሳሙኤል ታሪክ፥ በነቢዩም በናታን ታሪክ፥ በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ተጽፎአል።”
  — 1 ዜና 29፥29

7ኛ፡ የኢዩ ታሪክ የተፃፈበት መፅሐፍ የት ይገኝ ይሆን?

“የቀረውም የፊተኛውና የኋለኛው የኢዮሣፍጥ ነገር፥ እነሆ፥ በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ውስጥ በሚገኘው በአናኒ ልጅ በኢዩ ታሪክ ተጽፎአል።”
  — 2 ዜና 20፥34

8ኛ፡ ልክ ኢሳይያስ እንደፃፈው ሁሉ ስለ ሕዝቅያስ የሚተርከው የይሁዳ መፅሐፍ የት ገባ?

“የሕዝቅያስም የቀረው ነገር፥ ቸርነቱም፥ እነሆ፥ በአሞጽ ልጅ በነቢዩ በኢሳይያስ ራእይ በይሁዳና በእስራኤልም ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል።”
  — 2 ዜና 32፥32

9ኛ፡ ኤርምያስ ለኢዮስያስ የገጠመለት የልቅሶ ግጥም መፅሐፍ የት ገባ?

“ኤርምያስም ለኢዮስያስ የልቅሶ ግጥም ገጠመለት፤ እስከ ዛሬም ድረስ ወንዶችና ሴቶች መዘምራን ሁሉ በልቅሶ ግጥማቸው ስለ ኢዮስያስ ይናገሩ ነበር፤ ይህም በእስራኤል ዘንድ ወግ ሆኖ በልቅሶ ግጥም ተጽፎአል።”
  — 2 ዜና 35፥25

10ኛ፡ የሜዶንና የፋርስ ነገስታት ታሪክ የት ገባ?

“የኃይሉና የብርታቱም ሥራ ሁሉ ንጉሡም እስከ ምን ድረስ እንዳከበረው የመርዶክዮስ ክብር ታላቅነት፥ በሜዶንና በፋርስ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?”
  — አስቴር 10፥2

ያልታደለ በረዶ ከድንጋይ ላይ ያርፋል ከዚያም ይፈረከሳል እንዲሉ! እንግዲህ ለአሁን ከላይ ላስቀመጥናቸው ጥያቄዎች፤ አጉል መፈራገጥ ለመላላጥና ለመጋጋጥ ስለሆነ! በትህትናና በጨዋነት ደንብ እንድትመልሱልን እንፈልጋለን።

ወሰላሙ ዓለይኩም

Source:🔖
[1]Edward J. Brandt, “The Book of Jasher and the Latter-day Saints,” in Apocryphal Writings and the Latter-day Saints, ed. C. Wilfred Griggs (Provo, UT: Religious Studies Center, Brigham Young University, 1986), 297–318.

🖌ኸድር ኢብኑ ሙሐመድ(Abdulrauf)


https://www.tg-me.com/ewnet_lehulum
Forwarded from Eliyah Mahmoud
እውነት ለሁሉ [truth for all]
Voice message
[ሙስሊሙ ላልኾኑ…ይህንን ካነበቡ ቁርኣን ሰብኣዊ እንዳልኾነ እርግጠኛ ይኾናሉ]

[ሱረቱ ኣነህል]

በኣላህ ስም እጅግ ኣዛኝ እጅግ ሩህሩህ በኾነው እንጀምርና በመቀምቀሚያው ዘመን የመጨረሻ ነብይ ተደርገው በተላኩ ሙሐመድ ላይ የኣላህ ሰላምና እዝነት ይውረድ ብለን ቀጠልን፡፡ ወዳጄ እስኪ ዛሬ ደግሞ ከቁርኣን ቁጥራዊ ተዓምራት ውስጥ ጥቂት እናውራና እንገረም፡፡

ሱረቱ ኣነህል በቁርኣን ምዕራፍ አደራደር ውስጥ ኣስራ ስድስተኛ ምዕራፍ ነው፡፡ የምዕራፉ ስም “የንብ ምዕራፍ” በሚል በግርድፉ ሊቀመጥ ይችላል፡፡ የንብ ሳይንስን (Apiculture) ስናጠና፣ ንግስቲቷ ንብ እንቁላል  ከመጣሏ በፊት ከዳንጉላ (ወንድ) ንቦች ጋር  ወደ ላይ ትበራለች፡፡ ከብዙ ዳንጉላዎች ውስጥ የደረሰባት ከርሷ ጋር ርካቤ ፈጽሞ ብዙም ሳይቆይ ይሞታል፡፡ ንግስቲቷም የዳንጉላውን ፍትወት በውካፈ ፍስ ( spermatheca ፍትወት ማጠራቀሚያ ቀረጢት) አጠራቅማ ጽጌንስቶቹን (እንቁላሎቿን) ለመፈልፈል ወደ ቦይእንቁልእጢ ( ጽንሰት የሚካሄድበት ቦታ oviduct) ጽጌንስቶቹን ከእንቁል እጢ (Ovary) ስታሰወጣ ከወንዴው ፍትውት ጋር ካልቀላቀለችው ዳንጉላ ኾኖ ይፈለፈላል፡፡ ከተቀላቀለ ግን ሴት ሰራተኛ ወይም ንግስት ንብ ይኾናል፡፡ የወንዴው ፍትወትና የንግስቲቷ ጽጌንስቶች ኹለቱም ጽንሰት ሳይፈጠርና ሳይቀላቀሉ በፊት አስራ ስድስት ሃብለበራሂ (chromosomes) ኣላቸው፡፡ ይህ ደግሞ የሱረቱል ነህል የሱራ ቁጥር ነው፡፡ በነገራችሁ ላይ ኣላህ ቁርኣን ውስጥ ስለ ወንድና ሴት ሲያወራ ኹለቱንም 23 ጊዜ በተናጠል ጠቅሷቸዋል፡፡ የሰው ልጅ ከእናቱና ኣባቱ 23፣23 ሃብለበራሂ ይወስዳል፡፡ ያ ደግሞ በትክክል ቁርኣን ውስጥ ከተጠቀሰው ጋር ይስማማል፡፡

ከሱረቱል ነህል ስለ ንብ የሚያወራውን 68ኛ ጥቅስ መቁጠር ጀምረን ልክ አነህል ( النحل (  የሚለው ቃል ጋር ስንደርስ ፣ በኣጠቃላይ ኣስራ ስድስት ፊደላት ናቸው፡፡ ወዳጄ ከመጀመሪያው “ዋው” ፊደል ጀምረው “አነህል” እስከሚለው ቃል የመጨረሻ ፊደል “ላም” ድረስ ይቁጠሩ- ኣስራ ስድስት ፊደላት ናቸው፡፡
وَأَوْحَىٰ رَبُّكَ إِلَى النَّحْلِ أَنِ اتَّخِذِي مِنَ الْجِبَالِ بُيُوتًا وَمِنَ الشَّجَرِ وَمِمَّا يَعْرِشُونَ
ከላይ ያሰፈርነው ጥቅስ ስድሳ ስምንተኛ ጥቅስ ሲኾን በጥቀሱ ውስጥ በኣጠቃላይ ኣስራ ሶስት ቃላት ኣሉ፡፡ 1ኛ) ኣውሓ 2ኛ) ረቡክ 3ኛ) ኢላ 4ኛ) ኣነህሊ 5ኛ) ኣኒ 6ኛ) ኢተኺዚ 7ኛ) ሚን 8ኛ) ኣልጂባሊ 9ኛ) ቡዩተን 10ኛ) ወሚን 11ኛ) ኣሸጀሪ 12ኛ) ወሚማ 13ኛ) የዕሪሹን፡፡ የጥቅሱን ቁጥር በጥቅሱ ውስጥ ባሉ ቃላት ብዛት ስናባዛው 68X13= 884 ይሰጣል፡፡ ይህ ቁጥር ደግሞ ከምዕራፉ የመጀመሪያ ቃል (ኣታ) ከሚለው እስከ 68ኛው ጥቅስ ድረስ እየቆጠርን ሄደን  “ኣነህል” እስከሚለው ቃል ድረስ ያሉ የቃላት ብዛት ናቸው፡፡

በቁርኣን ውስጥ በኣጠቃላይ ኣስራ ስድስትና ከዛ በላይ የጥቅስ ብዛት ያላቸው ምዕራፍች 85 ናቸው፡፡ በነዚህ ሱራዎች ውስጥ ያሉትን ኣስራ ስድስተኛ ጥቅሶችን ኹሉ ሰብስበን በውስጣቸው የያዙትን የቃላት ብዛት ብንቆጥር 884 ይመጣል፡፡ እነዚህ 884 ቃላት ደግሞ በውስጣቸው 3769 ፊደላት ኣላቸው፡፡ ይህ 3769 ደግሞ ከመጀመሪያው የሱረቱል ነህል ጀምረን ስለንብ እስከሚያወራው 68ኛው ጥቅስ መጨረሻ ድረስ ያሉ የፊደል ብዛት ናቸው፡፡
ወዳጄ እስኪ ቁጥሩን ተወት ኣድርገን በሚቀጥለው ጥቅስ ውስጥ ደግሞ ያለውን እንይ ``ከዚያም ከፍሬዎች ሁሉ ብይ፡፡ የጌታሽንም መንገዶች (ላንቺ) የተገሩ ሲኾኑ ግቢ” ይላል፡፡”የጌታሽን” የሚለው ቃልና “የተገሩ” የሚለው ቃል ጋር ትንሽ ቆም ብለው ያስቡ፡፡ “የጌታሽን” የሚለው ቃል በትክክል ከቦታ ቦታ ምትዘዋወራዋ ሰራተኛ ንብ አነስታይ ጾታ እንዳላት ፍንትው ኣድርጎ ያሳያል፡፡ ከ 1400 ዓመታት በፊት  ቁርኣን ይህንን እውነታ ሲገልጽ በነሼክሽፒር ዘመን የነበሩት ኣውሮጳውያን ሰራተኛ ንብ ሴት መኾኗን ኣያውቁም ነበር፡፡ ሼክስፒር በኣንድ የግጥም ስራው ሰራተኛ ንብ ወንድ እንደኾነ ኣድርጎ ገልጾታል፡፡

ሰራተኛ ንብ ሩቅ መንገድ ዞራ ከራሷ ቀፎ ምንም ሳትደናገር ትገባለች፡፡ ይህ የኾነበት ምክንያትም በእያንዳንዱ ቀፎ ውስጥ የምትገኝ ንግስት ንብ የምታመነጨው የራሷ የኾነ ኬሚካል አለ፡፡ የኹሉም ንግስቶች ኬሚካል ይለያያል፡፡ ሰራተኛ ንቦች ዞረው ሲመለሱ የራሳቸው ንግስት ያመነጨችውን ቁሰ-ንግስት ( queen substance ) እየተከተሉ ከቀፎኣቸው ይገባሉ፡፡ ሌላውና በጣም ኣስገራራሚው ነገር ደግሞ ሰራተኛ ንቦች ምግብ በቅርብ ርቀት መኖሩን ለሌሎች ንቦች ለማመላከት በክብ ቅርጽ ይሽከረከራሉ፡፡ ራቅ ካለ ቦታ ምግብ መኖሩን ለማመላከት ደግሚ በዚግዛግ መስመር ይሽከረከራሉ፡፡ ቁርኣን “የጌታሽንም መንገዶች (ላንቺ) የተገሩ ሲኾኑ ግቢ” ሲል ምን ያህል ርቆ እንደሄደ ልብ ይሏል፡፡

ወዳጄ እነኝህ ከላይ የዘረዘርናቸው ሐሳቦች ከብዙ እጅግ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ይህንን ኹሉ ጥልቅ ሒሳብና ሳይንሳዊ ምልከታ ሙሐመድ (ሰለላሁ.ዐለይሂ.ወሰለም) ከየትም ሳይኾን ኹሉን ከፈጠረ ኣምላክ ሰምተው እንዳወሩት ኣልተረዱምን?

ቸር እንሰንብት

https://www.tg-me.com/E_M_ahmoud
እውነት ለሁሉ [truth for all]
[ሙስሊሙ ላልኾኑ…ይህንን ካነበቡ ቁርኣን ሰብኣዊ እንዳልኾነ እርግጠኛ ይኾናሉ] [ሱረቱ ኣነህል] በኣላህ ስም እጅግ ኣዛኝ እጅግ ሩህሩህ በኾነው እንጀምርና በመቀምቀሚያው ዘመን የመጨረሻ ነብይ ተደርገው በተላኩ ሙሐመድ ላይ የኣላህ ሰላምና እዝነት ይውረድ ብለን ቀጠልን፡፡ ወዳጄ እስኪ ዛሬ ደግሞ ከቁርኣን ቁጥራዊ ተዓምራት ውስጥ ጥቂት እናውራና እንገረም፡፡ ሱረቱ ኣነህል በቁርኣን ምዕራፍ አደራደር ውስጥ…
መደመምህን ቀጥል!


ተቆጥረው የማያልቁ የቁርዓን ተዓምሮችን ከቁርዓኑጋ አዋህደህ እያመሳከርክ ስትመለከተው እንደ ሙስሊምነትህ እያለቀስክ አላህን ከማመስገን ውጭ ምን ማድረግ ይቻላል? መንጋጋህን ወደታች ጥለህ፣ አፍህን ከፍተህ ወይም እጆችህን በአፍህ ላይ ጭነህ መገረም ብቻ! ሱብሐን አላህ! ይህን ቀላል ማስተንተን ወገኖቻችን ቢያስተውሉ ምንኛ በተመሩ ነበር?


እዚህጋ አንድ የምጨምርላችሁ ነገር ቢኖር በአረብኛ ቋንቋ "بطن" ወይም "በጥን" ማለት ሆድ ማለት ሲሆን ቁርዓን ግን ለንብ የተጠቀመው ቃል "بُطُونِهَا" ወይም "ቡጡኒሃ" የሚል ቃል ነው። ይህም ትርጉሙ "በሆዶችዋ" ማለት ሲሆን ንብ ከአንድ ሆድ በላይ እንዳላት ገላጭ ቃል ነው። አሁን ላይ ሳይቲስቶች ንብ ሁለት ሆዶች እንዳሏት አረጋግጠዋል።

ثُمَّ كُلِي مِن كُلِّ الثَّمَرَاتِ فَاسْلُكِي سُبُلَ رَبِّكِ ذُلُلًا ۚ يَخْرُجُ مِن بُطُونِهَا شَرَابٌ مُّخْتَلِفٌ أَلْوَانُهُ فِيهِ شِفَاءٌ لِّلنَّاسِ ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ

[ ሱረቱ አል-ነሕል፥ - 69 ]
«ከዚያም ከፍሬዎች ሁሉ ብይ፡፡ የጌታሽንም መንገዶች (ላንቺ) የተገሩ ሲኾኑ ግቢ፡፡» "ከሆዶችዋ" መልኮቹ የተለያዩ መጠጥ ይወጣል፡፡ በእርሱ ውስጥ ለሰዎች መድኃኒት አለበት፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አልለበት፡፡



ይሠመርበት "በዚህ ውስጥ "ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አልለበት፡፡"


وَقُلِ الْحَمْدُ لِلَّهِ سَيُرِيكُمْ آيَاتِهِ فَتَعْرِفُونَهَا ۚ وَمَا رَبُّكَ بِغَافِلٍ عَمَّا تَعْمَلُونَ

[ ሱረቱ አል-ነምል - 93 ]
ምስጋናም ለአላህ ነው፡፡ ተዓምራቶቹን ወደፊት ያሳያችኋል፡፡ «ታውቋትምአላችሁ» በላቸው፡፡ ጌታህም ከምትሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡


وَهُوَ اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ لَهُ الْحَمْدُ فِي الْأُولَىٰ وَالْآخِرَةِ ۖ وَلَهُ الْحُكْمُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ

[ አልቀሶስ - 70 ]
እርሱም አላህ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ምስጋና በመጀመሪያይቱም በመጨረሻይቱም ዓለም ለእርሱ ብቻ ነው፡፡ ፍርዱም የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ወደእርሱም ትመለሳላችሁ፡፡

ሱብሐን አላህ!

https://www.tg-me.com/ewnet_lehulum
وَحَدَّثَنَا عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مُحَمَّدٍ، حَدَّثَنَا عَبْدُ الرَّزَّاقِ، أَخْبَرَنَا مَعْمَرٌ، عَنْ هَمَّامٍ، عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ رَأَى عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ رَجُلاً يَسْرِقُ، فَقَالَ لَهُ أَسَرَقْتَ قَالَ كَلاَّ وَاللَّهِ الَّذِي لاَ إِلَهَ إِلاَّ هُوَ‏.‏ فَقَالَ عِيسَى آمَنْتُ بِاللَّهِ وَكَذَّبْتُ عَيْنِي ‏"‌‏.‏


አቡ ሑረይራህ (ረ.ዐ) እንደተረከው ነቢዩ ሙሐመድ "ﷺ" እንዲህ አሉ፦ ኢየሱስ(ዐ.ሠ) አንድ ሠው ሲሰርቅ አይቶ፣ 'ሠርቀሃልን'? ብሎ ጠየቀው። ሠውዬውም፦ ''ከእርሱ በቀር በሐቅ ሊገዙት የሚገባ አምላክ በሌለው በአላህ ይሁንብኝ አልሰረቅኩም አለው።'' ኢየሱስም(ዐ.ሠ)፦ "በአላህ አምናለሁ እናም አይኖቼንም እንደዋሹኝ እጠራጠራቸዋለሁ አለው።"[📚ሶሂሑል ቡኻሪ መፅሐፍ 55፣ ሐዲስ ቁጥር 653]


የአላህ እዝነትና ሠላም በነቢዩ ኢየሱስ እና በሙሐመድ ላይ ይሁን!
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ራሱን አቃጠለ!

ስለ ጭቁኑ የፍልስጤም ሙስሊም ስለደረበትና ስለሚደርስበት መከራ ለመግለፅ ቃላቶች ራሱ አቅማቸው አይፈቅድላቸውም። የሕፃናት ጭፍጨፋ ከደቂቅ እስከ ትልቅ ያውም በአሰቃቂ ሁኔታ… ነገር ግን አይን ገላጭ ክስተት ሆኖ አለምን አንቅቷል። ኢማን በደም ስራቸው የሞላባቸውን ሙስሊሞች እስከ ጥግ አሳይተውን እኛም በእነርሱ ኮርተን ምንም አካላዊ ተሳትፎ ባለማድረጋችን በራሳችን አፍረናል። ያለን ብቸኛው ኃይል ዱዓችን ብቻ ሲቀር… ፍትህ ከአላህ ነው ከሠውም አይደለምና የአለም ኃያላን ሀገራቶች ሳይቀር ተሰባስበው ፍልስጤም ላይ አደሙባቸው። እስራኤልም በጦርና ወታደራዊ ኃይል በምዕራባውያንና አውሮፓውያን ስትረዳ ብትቆይም መቋቋም አቅቷት መሸሽን መረጠች። ከሕፃናት፣ ሴቶችና አዛውንቶች በቀር የመግደል ሕሊናም ሆነ አቅም በቀር ሌላ ምንም አልነበራትም። ከአለም ጫፍ እስከ ጫፍ ከደቡብ እስከ ሠሜን ከምዕራብ እስከ ምስራቅ ሙሉ በሙሉ ላስተዋሉ ሠዎች የፍሊስጤም ወኔና አልሸነፍ ባይነት ለሐቅ መጋደል የሕይወታቸውን ትልቁን ትምህርት ሠጣቸው። "የፍልስጤም ሙስሊሞች እንዲ በደስታ የሚሞቱለት እምነታቸውና ጥንካሬያቸው ምን ይሆን? በማለት በግርምት ተዋጡ።" ብርሐን ወደ ሆነውም ኢስላም አያሌዎች ቁርዓንን በማንበብ ወደ ኢስላም ጎረፉ። የፍልስጤምን ጉዳይ ቃላቶች ስለማይገልፁት ይህ የአሜሪካ የአየር ኃይል ውስጥ አባል የሆነ ሠው የፍልስጤምን ከመጠን በላይ ጭቆና በተግባር ለማውገዝ የሄደበት እርቀት ክስተቱን ገላጭ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። እየተቃጠለ እንኳን "Free Palestine" ሲል ይደመጣል። ልቡ ምን ያህል እንደታመመና የፍትህን መጓደል የተረዳ ሠው እንደነበረ ጠቋሚም ነው። ልብን ሠባሪ ሞት ሞተ፤ ግን ትልቅ መስዋዕትነትን የከፈለ ታሪካዊ ጀግና ሠው ነው።



አላህ ፍልስጤምን እና ሙስሊሞችን ይጠብቅ!
አሏህና መላእክቱ ለነቢዩ ይሰግዳሉን?


አንዳንዴ በማናውቀውና በማይገባን ነገር ላይ ዘለን ቲፎ የምንገባው ነገር ትርፉ ራሳችንን ለብርድ ማጋለጥ ነው። እኛ ሙስሊሞች የምናመልከው ኃያሉ አምላካችን አላህ ከሁሉ ነገር የተብቃቃና የጠራ ሆኖ ሳለ ለነቢዩ ይሰግዳል(ይፀልያል) እያሉ በየዋህነት የሚደነፉ የጥራዝ ነጠቅ እውቀት ባለቤቶች እጅግ ያሳዝኑኛል። ክሳቸውን ሲተረትሩት እናንተም ሆናችሁ መላእክት ለነቢዩ ትሠግዳላችሁ ይላሉ። አንድ ሠው አሞሃል ስትሉት መልሶ አንተም'ኮ አሞሃል ካለህ መታመሙን አምኗል ማለት ነው። እነሱ ሠው የማምለክ አባዜ የተጠናወታቸውና የተጠመዱ ማህበረሰቦች ስለሆኑ እንዲሁም ይሄን ተግባራቸውን ጠንቅቀው ስለሚያውቁ እኛንም ሠው አምላኪ ብለው ይከሳሉ። ይመስገን እኛ ሙስሊሞች ከአንዱ አምላካችን በቀር ለማንም አንሰግድም፣ አናጎበድድም፣ አምልኮም አናቀርብም። ይሄንን ደግሞ ወገኖቻችንም ቢሆኑ ጠንቅቀው ያውቃሉ፤ ነገሩ ያው! ወስፌ ሲለግም ቅቤ አይወጋም እንዲሉ! እውነቱን ማወቅ አልፈለጉም። ወደ ገደለው ስገባ እነሱ ያመጠቱን ክስ ከዚህ በፊት የተመለሰ ቢሆንም ያልተገላበጠ ያራልና እኛ በጥራዝ ጠለቅ እውቀት እናገላብጠዋለን።

የቋንቋ-ሙገት (Linguistical approach)

በስነ-ቋንቋ ጥናት አንድ ቃል ፍቹን የምናውቅባቸው መንገዶችንና አላማውን በግልፅ ያስተምራል። "definition and their purpose" በሚለው የፍች ጥናት ውስጥ አምስት አበይት ክፍሎች አሉት እነርሱም፦

Stipulative Definition
Persuasive Definition
Precise Definition
Theoretical Definition
Lexical Definition ናቸው።

እነዚህ ስለ ቃላት ፍቾች የሚያጠኑ ክፍሎች ሲሆኑ  እኔ በዚህ ሙግቴ ላይ የምጠቀመው "Lexical Approach Definition" ነው። ይህ የመዝገበ ቃላት ሙግት ሲሆን አላማውም "eliminating ambiguity" አሻሚ ቃላቶችን ወይም ብዙ ትርጉም ያላቸውን ቃላቶች እንድናውቅና እንዳንደናገር በማድረግ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል። ወደ ክሱ ሳልፍ ክሳቸው የሚያርፈው በሡረቱል አሕዛብ አንቀፅ 56 ላይ እንዲህ የሚል ሀሳብ ተቀምጧል፦

إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا

(ሱረቱ አል- አሕዛብ - 56)
አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡

በዚህ አንቀፅ ላይ የተቀመጠው "ዩሶሉነ"يُصَلُّونَ" የሚለው ቃል ስርዎ ቃሉ "ሶሉ"صلو'' ሲሆን እንደየ አውዱ ፀሎት፣ በረከት፣ ምህረት፣ ፀጋ፣ ደግነት፣ መድረስ ወ.ዘ.ተ የሚሉ የተለያዩ ትርጉሞችን ይወክላል። ታዲያ ይሄንን ብዙ ትርጉም ያለውን ቃል ለነቀፋና ለትችት ሲባል አንድ ትርጉም ማስያዝ አግባብ ነውን? ከስነ-አመክንዮ አንፃርስ "ሕፀፅ" መስራት አይሆንባችሁምን? ለናሙና ያህል ከቁርዓን እንመልከት፦


وَالَّذِينَ يَصِلُونَ مَا أَمَرَ اللَّهُ بِهِ أَن ُوصَلَ وَيَخْشَوْنَ رَبَّهُمْ وَيَخَافُونَ سُوءَ الْحِسَابِ

(ሱረቱ አል- ረዕድ፥ - 21)
እነዚያም አላህ እንዲቀጠል በእርሱ ያዘዘውን ነገር የሚቀጥሉ ጌታቸውንም #የሚያከብሩ መጥፎንም ቁጥጥር የሚፈሩ ናቸው፡፡

قَالَ سَنَشُدُّ عَضُدَكَ بِأَخِيكَ وَنَجْعَلُ لَكُمَا سُلْطَانًا فَلَا َصِلُونَ إِلَيْكُمَا ۚ بِآيَاتِنَا أَنتُمَا وَمَنِ اتَّبَعَكُمَا الْغَالِبُونَ

(አልቀሶስ - 35)
(አላህም) «ጡንቻህን በወንድምህ በእርግጥ እናበረታለን፡፡ ለሁለታችሁም ስልጣንን እናደርጋለን፡፡ ወደእናንተም (በመጥፎ) #አይደርሱም፡፡ በተዓምራቶቻችን (ኺዱ)፡፡ እናንተና የተከተላችሁም ሁሉ አሸናፊዎች ናችሁ» አላቸው፡፡

ከላይ በተጠቀሱት የቁርዓን ክፍሎች ውስጥ ቃሉ የወከለውን የተለያየ ትርጉም አንባቢ ልብ ይሏል። እስቲ ከመዝገበ ቃላት ላይ ደግሞ ለነቢዩ ሙሐመድ "ﷺ" ሲውል የሚይዘውን የቃሉን ፍች እንመልከት፦

፨An Arabic-English Vocabulary by D. A. Cameron page 155
《በነቢዩ ሙሐመድ "ﷺ" ላይ ሶለዋት ማውረድ ማለት አላህ ሙሐመድን "ﷺ" ይባርከው ሰላም ይስጠው ማለት ነው።》

፨John L. Esposito, The Oxford Dictionary of Islam. page 274
《በነቢዩ ሙሐመድ "ﷺ" ላይ ሙስሊሞች ሶለዋት ሲያወርዱ የሚጠቀሙት ቃል የአክብሮት ቃል ነው።》

፨Hans Wehr. A Dictionary of Modern written Arabic page 523
《በነቢዩ ሙሐመድ "ﷺ" ላይ የአላህ ሠላምና እዝነት ይሁን የሚለው የሙገሳ አገላለጽ ከነቢዩ "ﷺ" ስም ቡኋለ የሚመጣ ሲሆን አላህ ይባርከው ማለት ነው።》

ከላይ እንደምታዩት በ"Lexical Approach Definition" የወገኖቻችን ሙግት ውሃ የማያነሳና ቆሎ የማይደፋ ሆኖ አግኝተነዋል። ምክንያቱም እነሱ ይሄንን የቡና ወሬያቸውን የሚነዙት ኢስላም ላይ ያለባቸው ጥላቻ እንጂ ማስረጃ ኖሯቸው አይደለም። እኛም መደምደሚያችንን ለማጠናከር ያህል ሐዲስ ላይ ያሉትን እንደ ተጨማሪ መንደርደሪያ እናክላችኋለን።

حَدَّثَنَا عُثْمَانُ بْنُ أَبِي شَيْبَةَ، حَدَّثَنَا مُعَاوِيَةُ بْنُ هِشَامٍ، حَدَّثَنَا سُفْيَانُ، عَنْ أُسَامَةَ بْنِ زَيْدٍ، عَنْ عُثْمَانَ بْنِ عُرْوَةَ، عَنْ عُرْوَةَ، عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏

‏ إِنَّ اللَّهَ وَمَلاَئِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى مَيَامِنِ الصُّفُوفِ ‏"
Narrated Aisha, Ummul Mu'minin:

The Messenger of Allah (ﷺ) said: Allah and His angels bless those who are on the right flanks of the rows.

አዒሻህ ረ.ዐ እንደተረከችው የአላህ መልዕክተኛ "ﷺ" እንዲህ ብለዋል:- ‟አላህ እና መላእክቱ የቀኝ ረድፎች ላይ ሰለዋት ያወርዳሉ”።
(📚Sunan Abi Dawud 676
In-book : Book 2, Hadith 286)


حَدَّثَنَا مُحَمَّدُ بْنُ عِيسَى، حَدَّثَنَا أَبُو عَوَانَةَ، عَنِ الأَسْوَدِ بْنِ قَيْسٍ، عَنْ نُبَيْحٍ الْعَنَزِيِّ، عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ، أَنَّ امْرَأَةً، قَالَتْ لِلنَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم صَلِّ عَلَىَّ وَعَلَى زَوْجِي ‏.‏ فَقَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏

‏ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْكِ وَعَلَى زَوْجِكِ ‏"

‏ ‌‏

Narrated Jabir ibn Abdullah:
A woman said to the Prophet (ﷺ): Invoke blessing on me as well as on my husband. The Prophet (ﷺ) said: May Allah send blessing on you and your husband.

Sahih (Al-Albani)

عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ، أَنَّ امْرَأَةً، قَالَتْ لِلنَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم صَلِّ عَلَىَّ وَعَلَى زَوْجِي ‏.‏ فَقَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏صَلَّى اللَّهُ عَلَيْكِ وَعَلَى زَوْجِكِ
ጃቢር ረ.ዐ እንደተረከው አንዲት ሴት ወደ ነቢዩ "ﷺ" መጥታ በእኔና በባለቤቴ ላይ ሰለዋት አውርድ አለችው፣ እሳቸውም ‟የአላህ ሰላምና እዝነት ባንቺ እና በባለቤትሽ ላይ ይሁን” አሏት።
(📚Sunan Abi Dawud 1533
In-book : Book 8, Hadith 118)

أَخْبَرَنَا قُتَيْبَةُ بْنُ سَعِيدٍ، عَنْ مَالِكٍ، وَالْحَارِثُ بْنُ مِسْكِينٍ، قِرَاءَةً عَلَيْهِ وَأَنَا أَسْمَعُ، عَنِ ابْنِ الْقَاسِمِ، حَدَّثَنِي مَالِكٌ، عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ أَبِي بَكْرِ بْنِ مُحَمَّدِ بْنِ عَمْرِو بْنِ حَزْمٍ، عَنْ أَبِيهِ، عَنْ عَمْرِو بْنِ سُلَيْمٍ الزُّرَقِيِّ، قَالَ أَخْبَرَنِي أَبُو حُمَيْدٍ السَّاعِدِيُّ، أَنَّهُمْ قَالُوا يَا رَسُولَ اللَّهِ كَيْفَ نُصَلِّي عَلَيْكَ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‌‏ قُولُوا اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَأَزْوَاجِهِ وَذُرِّيَّتِهِ ‏"‏ ‏.‏ فِي حَدِيثِ الْحَارِثِ ‏"‏ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ وَبَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَأَزْوَاجِهِ وَذُرِّيَّتِهِ ‏"‏ ‏.‏ قَالاَ جَمِيعًا ‏"‏ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ ‏"‏ ‏.‏ قَالَ أَبُو عَبْدِ الرَّحْمَنِ أَنْبَأَنَا قُتَيْبَةُ بِهَذَا الْحَدِيثِ مَرَّتَيْنِ وَلَعَلَّهُ أَنْ يَكُونَ قَدْ سَقَطَ عَلَيْهِ مِنْهُ شَطْرٌ ‏

Sahih (Darussalam)

በአንድ ወቅት ነቢዩን "ﷺ" ሰለዋት እንዴት እናውርድ? ተብለው ሲጠየቁ፦ ‟አላህ ሆይ በነቢዩ ላይና በባልተቤቶቻቸው እንዲሁም በዝርያወቻቸው ላይ እና በኢብራሂምም ቤተሰብ ላይ አውርድ ብላችሁ ለምኑ” በማለት መለሱ። አል-ሐሪዝም በሌላ ዘገባ አላህ ሆይ በኢብራሒምና በቤተሰቦቹ እንዲሁም በዘሮቹ ሁሉ እንዳወረድክ በሙሐመድና በባለቤቶቹ እንዲሁም በዝርያወቹ ላይ ሠላምን አውርድ ብለው መልሰዋል።
(📚Sunan an-Nasa'i 1294
In-book : Book 13, Hadith 116)


ሌሎችም ሐዲሳቶች በቁና አሉ መዘርዘር ቢቻልም ለጠቢብ አንድ ቃል ብቻ በቂው ነው በሚለው ከላይ የጠቀስናቸው ማስረጃወች ብቻ ወገባቸውን ገትረው ራሳቸው ይከራከራሉ። ከላይ ልብ እንዳላችሁት አምላካችን አላህ በነቢዩ "ﷺ" ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ሰዎች ላይ ሠላምና እዝነቱን ያወርዳል። እንግዲህ ለባለጌ ገድሉ ውርደቱ አይደል ሚባል!? ታዲያ ወገኖቻችን ይሄንን ሲያዩ እሳት እንደ ገባ ቅቤ መቅለጣቸው፣ ውሃ እንደገባች አይጥ መጨባበጣቸው፣ እሳት እንደገባ ፌስታል መኮመታተራቸው ይቀራልን!? እኛም እንግዲህ ይበልህ የእጅህን ነው የሠጠህ! እያልን እነሱ የሠሩትን "ድኩም ሕፀፃት" በዚህ መልኩ "በተጠይቃዊ ፍሰት" መዋቅሩን በጠበቀ መልኩ ሕፀፁን አስወግደናል።


ቸር ሠንብቱ! ወሠላሙ ዓለይኩም!


🖌Kedir Muhammad(Abdulrauf)

https://www.tg-me.com/ewnet_lehulum
Audio
ይህ ሰበር ዜና በጣም አስደንጋጭ ነው

ይህን እርኩስ ተግባር ለማክሸፍ

①.ህብረተሰቡን የማንቃት ስራ መስራት

② የጠዋትና የማታ አዝካር ላይ መበርታት

③ ከቁርአን ጋር ያለንን ግንኙነት ማጠናከር

④ የፆም መያዣና መፍጠሪያ ለተቸገሩ ወገኖቻችን እኛው አለው እንበላቸው

⑤ ይህን የድግምት ስራ በመስራት ላይ ያለን አካል እጅ ከፍንጅ ከያዝነው የማያዳግም እርምጃ የሚወሰድበትን ሁኔታ ማመቻቸት

ሙስሊም ወገኖቻችንን ሁሉ ከከሀዲያን ተንኮል አላህ ይጠብቅልን

T.me/dawudyassin
ሳይንስ የውሐና ምድርን መቶኛ እንዲህ አስቀምጦልናል።

ቁርዓንስ?
እውነት ለሁሉ [truth for all]
ሳይንስ የውሐና ምድርን መቶኛ እንዲህ አስቀምጦልናል። ቁርዓንስ?
የተዓምር ተዓምር የሆነው ቁርዓን!



"ባህር" የሚለው ቃል ቁርዓን ላይ 32 ጊዜ ተጠቅሷል፤ "መሬት" የሚለው ቃል ደግሞ እንዲሁ 13 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ እስቲ ቀለል ባለ የሒሳብ ስሌት ወደ መቶኛ እንቀይረው። ባህር በቁርኣን ውስጥ 32 ግዜ ተጠቅሷል ስለዚህ ወደ መቶኛ ስንቀይረው ራሱን የባህሩን ቁጥር ማለትም 32'ን ለሁለቱ ባህርና መሬት ድምር ማካፈል ከዚያም በ100 ማብዛት ይሆናል። ሚመጣውን ቁጥር Let's See!…
ባህር=32/(32+13 )*100
ባህር=32/45*(100)
ባህር=0.712*100
በመጨረሻም ባህር=71.12% ይመጣልናል።
Les't Go to land's surface area “መሬት” የሚለው ቃል በቁርአን ውስጥ "13" ያህል ጊዜ ተጠቅሷል። ስለዚህ ወደ መቶኛ (percentage) በፐርሰንት ስንቀይረው ከላይ እንዳሰላነው ስሌት በተመሳሳይ ይሆናል።
መሬት=13/(32+13 )x100
መሬት=13/45*(100)
በመጨረሻም መሬት=28.888% ይመጣል፡፡
በሌላ አነጋገር 71.12% አለማችን ክፍል ባህር ሲሆን 28.88% ደግሞ መሬት መሆኑን ቁርዓን ያስረዳናል፡፡ ይህ ማለት "ROUND" ስናደርገው 71% ውሐ እና 29 % መሬት ሲሆን ሳይንስም አሁን ላይ እንዳረጋገጠው 71% ውሐ 29% ያህሉን መሬት እንደደሚሸፍን አረጋግጧል።

ታዲያ አሁንም እርስዎ ይህን መፅሐፍ በአንድ ተራ ግለሰብ የተፃፈ እንደሆነ ያስባሉ ወይስ የፈጣሪ ቃል እንደሆነ? ፍርዱን ለህሊና!


لِّيَعْلَمَ أَن قَدْ أَبْلَغُوا رِسَالَاتِ رَبِّهِمْ وَأَحَاطَ بِمَا لَدَيْهِمْ وَأَحْصَىٰ كُلَّ شَيْءٍ عَدَدًا

[ አል-ጂን - 28 ]
እነርሱ ዘንድ ባለው ነገር ዕውቀቱ የከበበና ነገሩንም ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ ሲኾን የጌታቸውን መልክቶች ያደረሱ መኾናቸውን ያውቅ ዘንድ (ጠባቂ ያደርጋል)፡፡

إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا الذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُ لَحَافِظُونَ

[ ሱረቱ አል-ሒጅር - 9 ]
እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡

تَنزِيلُ الْكِتَابِ لَا رَيْبَ فِيهِ مِن رَّبِّ الْعَالَمِينَ

[ ሱረቱ አል-ሰጅዳህ፣ - 2 ]
የመጽሐፉ መወረድ ጥርጥር የለበትም፡፡ ከዓለማት ጌታ ነው፡፡


ሙስሊም ላደረገን ጌታ ምስጋና ይገባው!

https://www.tg-me.com/ewnet_lehulum
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኧረ እነዚህ ሠዎች!😭😂


ኢየሱስን ሠውነቱን ዳበስኩትት……የምርሽን ነው ሌላስ¡
የተባረከ ወር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥185 የረመዷን ወር በእርሱ ውስጥ ቁርኣን ለሰዎች መሪ፣ የመመሪያ ግልጽ ማስረጃ እና ፉርቃን ሲሆን የተወረደበት ነው። شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ

አምላካችን አሏህ በቁርኣን ከተገለጹት ስሞቹ አንዱ "አል-ከሪም" الْكَرِيم ሲሆን ትርጉሙ "ቸሩ" "ለጋሱ" ማለት ነው፦
82፥6 አንተ ሰው ሆይ! በቸሩ ጌታህ ምን አታለለህ? يَا أَيُّهَا الْإِنسَانُ مَا غَرَّكَ بِرَبِّكَ الْكَرِيمِ
27፥40 እርሱ ዘንድ ረግቶ ባየውም ጊዜ «ይህ ከጌታዬ ችሮታ ነው፥ የማመሰግን ወይም የምክድ መኾኔን ሊፈትነኝ ቸረልኝ፡፡ ያመሰገነም ሰው የሚያመሰግነው ለራሱ ነው፥ የካደም ሰው ጌታዬ ከእርሱ ተብቃቂ ቸር ነው» አለ፡፡ فَلَمَّا رَآهُ مُسْتَقِرًّا عِندَهُ قَالَ هَـٰذَا مِن فَضْلِ رَبِّي لِيَبْلُوَنِي أَأَشْكُرُ أَمْ أَكْفُرُ ۖ وَمَن شَكَرَ فَإِنَّمَا يَشْكُرُ لِنَفْسِهِ ۖ وَمَن كَفَرَ فَإِنَّ رَبِّي غَنِيٌّ كَرِيمٌ

"ከሪም" كَرِيم የሚለው ቃል እንደየ ዐውዱ ዘርፈ ብዙ እና መጠነ ሰፊ ትርጉም አለው፥ "የተባረከ" "የተከበረ" "ቅዱስ" "ክቡር" "ብፁዕ" "ንኡድ" "ውዱስ" "ስቡህ" "እኩት" "እጹብ" የሚል ፍቺ አለው። ለምሳሌ፦ መልአኩ ጂብሪል "ከሪም" كَرِيم ተብሏል፦ 
81፥19 እርሱ የ-"ክቡር" መልእክተኛ ቃል ነው፡፡ إِنَّهُ لَقَوْلُ رَسُولٍ كَرِيمٍ

እዚህ ዐውድ ላይ ጂብሪል "ክቡር" ለተባለበት የገባው ቃል "ከሪም" كَرِيم ሲሆን "ንኡድ"noble" ለማለት እንጂ "ለጋሽ" "ቸር" ለማለት ተፈልጎ አይደለም፥ በተመሳሳይ ነቢያችን"ﷺ" ደግሞ "ከሪም" كَرِيم ተብለዋል፦
69፥40 እርሱ የ-"ተከበረ" መልእክተኛ ቃል ነው፡፡ إِنَّهُ لَقَوْلُ رَسُولٍ كَرِيمٍ

እዚህ ዐውድ ላይ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" "ክቡር" ለተባሉበት የገባው ቃል "ከሪም" كَرِيم ሲሆን "ንኡድ"noble" ለማለት እንጂ "ለጋሽ" "ቸር" ለማለት ተፈልጎ አይደለም። ስለዚህ አንድ ምንነት ወይም ማንነት "ከሪም" كَرِيم ስለተባለ አሏህ ከተወሰፈበትን ወስፍ ጋር ማምታታት አግባብ አይደለም። ቁርኣን "ከሪም" كَرِيم ተብሏል፦ 
56፥77 እርሱ "የከበረ" ቁርኣን ነው። إِنَّهُۥ لَقُرْءَانٌۭ كَرِيمٌۭ

እዚህ አንቀጽ ላይ ቁርኣን "የተከበረ" ለተባለበት የገባው ቃል "ከሪም" كَرِيم ሲሆን ሌላ አንቀጽ ላይ በተለዋዋጭ ቃል "ሙባረክ" مُّبَارَك ተብሏል፦
6፥155 ይህም ያወረድነው የኾነ "የተባረከ" መጽሐፍ ነው፡፡ وَهَـٰذَا كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ مُبَارَكٌ

እዚህ አንቀጽ ላይ ቁርኣን "የተባረከ" ለተባለበት የገባው ቃል "ሙባረክ" مُّبَارَك ሲሆን "ሙባረክ" እና "ከሪም" የቃላት ልዩነት እንጂ የአሳብ ልዩነት የላቸውም። አትክልቶችን እና የሚታጨድን አዝመራ ፍሬ የሚበቅልበት ውኃ "ሙባረክ" مُّبَارَك ተብሏል፦
50፥9 ከሰማይም "ቡሩክን" ውኃ አወረድን፡፡ በእርሱም አትክልቶችን እና የሚታጨድን አዝመራ ፍሬ አበቀልን፡፡ وَنَزَّلْنَا مِنَ السَّمَاءِ مَاءً مُّبَارَكًا فَأَنبَتْنَا بِهِ جَنَّاتٍ وَحَبَّ الْحَصِيدِ

እዚህ አንቀጽ ላይ ውኃ "ቡሩክ(የተባረከ) ለተባለበት የገባው ቃል "ሙባረክ" مُّبَارَك ሲሆን ሌላ አንቀጽ ላይ በተለዋዋጭ ቃል "ከሪም" كَرِيم ተብሏል፦
79፥30 ምድርንም ከዚህ በኋላ ዘረጋት፡፡ وَالْأَرْضَ بَعْدَ ذَٰلِكَ دَحَاهَا
79፥31 ውኃን እና ግጦሿን ከእርሷ አወጣ፡፡ أَخْرَجَ مِنْهَا مَاءَهَا وَمَرْعَاهَا
26፥7 ወደ ምድርም በውስጧ "ከ"መልካም" በቃይ ሁሉ ብዙን እንዳበቀልን አላዩምን?፡፡ أَوَلَمْ يَرَوْا إِلَى الْأَرْضِ كَمْ أَنبَتْنَا فِيهَا مِن كُلِّ زَوْجٍ كَرِيمٍ

እዚህ አንቀጽ ላይ "መልካም" ለሚለው የገባው ቃል "ከሪም" كَرِيم እንደሆነ ልብ አድርግ! "ሙባረክ" እና "ከሪም" ተለዋዋጭ ቃላት እንደሆኑ ለመረዳት ከላይ የቀረቡት ናሙናዎች በቂ ማሳያ ናቸው። እዚህ ድረስ ከተግባባን የረመዷን ወር ቁርኣን የወረደበት ወር ነው፦
2፥185 የረመዷን ወር በእርሱ ውስጥ ቁርኣን ለሰዎች መሪ፣ የመመሪያ ግልጽ ማስረጃ እና ፉርቃን ሲሆን የተወረደበት ነው። شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ

"ፉርቃን" فُرْقَان ማለት "እውነት ከሐሰት፣ ትክክሉን ከስህተት፣ መልካሙን ከክፉ የሚለይ ሚዛን" ማለት ነው። "ሸህሩ ረመዷን" شَهْرُ رَمَضَان ማለት "የረመዳን ወር" ማለት ነው፥ "ረመዷን" رَمَضَان ደግሞ የዘጠነኛው ወር ስም ነው። "ረመዷን" የወር ስም እንጂ የጦም ስም አይደለም፥ ነገር ግን ይህ ወር ቁርኣን የተወረደበት ወር በመሆኑ "ሸህሩ ሙባረክ" شَهْرُ مُّبَارَك ማለትም "የተባረከ ወር" ተብሏል፦
ሡነን ነሣኢይ መጽሐፍ 22, ሐዲስ 17
አቢ ሁራይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የተባረከው ወር ረመዷን መጣላችሁ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ أَتَاكُمْ رَمَضَانُ شَهْرٌ مُبَارَكٌ

ከዚህ አንጻር "ረመዷን ሙባረክ" رَمَضَان مُّبَارَك የሚለውን በቋንቋዬ ተርጉሜ "የተባረከ ረመዷን" ብል የቃላት ልዩነት እንጂ የአሳብ ልዩነት ከሌለው "ረመዷን ከሪም" رَمَضَان كَرِيم ሲባል "መልካም ረመዷን" "የተከበረ ረመዷን" ብል የቃላት እንጂ የአሳብ ልዩነት የለውም። "ኢማን" إِيمَان የሚለውን ቃል ቁርኣን እና ሐዲስ ውስጥ በቁናህ ታገኘዋለህ፥ ቅሉ ግን የኢማን ተለዋዋጭ ቃል "ዐቂዳህ" عَقِيدَة የሚለውን በስም መደብ ቁርኣን ውስጥ አታገኘውም። ነገር ግን ዐቂዳህ እያልን እንማራለን እናስተምራለን፥ "ሙባረክ" እና "ከሪም" የሚለውን በዚህ ስሌት እና ሒሣብ መረዳት ይቻላል። ስለዚህ "ረመዷን ሙባረክ" رَمَضَان مُّبَارَك እና "ረመዷን ከሪም" رَمَضَان كَرِيم ተለዋዋጭ ቃላት እስከሆኑ ድረስ መርጠን መጠቀም እንችላለን።

"አሏሁ አዕለም! ይህ ሙግት የቋንቋን ሙግት ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ሙግት ነው።

"ረመዷን ከሪም" رَمَضَان كَرِيم

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
2024/05/20 00:49:04
Back to Top
HTML Embed Code: