Telegram Web Link
የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የሸሸና የተመዘበረ ሃብትን ለማስመለስ በጋራ እንዲሰሩ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ቅንጅታዊ አሰራርን በመፍጠር ከሀገር የሸሸና የተመዘበረ ሃብትን ለማስመለስ እንዲሁም በተያያዥ ወንጀሎች ላይ በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባ ተመላከተ፡፡ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የሸሸ እና የተመዘበረ ሃብትን ለማስመለስ እንዲሁም በተያያዥ ወንጀሎች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ጥምረት መስርተዋል፡፡ በመድረኩ የተገኙት በፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ኃላፊ ምክትል…

https://www.fanabc.com/archives/244470
ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ትስስር ከፍተኛ ሚና ትጫወታለች – አቶ አሕመድ ሺዴ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በቀጣናው ሀገራት ደህንነትና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ዙሪያ ቁልፍ ሚና ትጫወታለች ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ ገለጹ። አቶ አሕመድ በሳዑዲ ዓረቢያ ሪያድ በተደረገ የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም መድረክ ላይ በነበራቸው ተሳትፎ እንደገለጹት÷ በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ እያደገ የመጣውን ፈተና ለመቋቋም የደቡብ ደቡብ ትብብር ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። ኢትዮጵያ…

https://www.fanabc.com/archives/244473
Live stream finished (58 minutes)
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለ1 ሺህ 455 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ1 ሺህ 455 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ÷ መጪውን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ የክልሉ መንግስት የይቅርታ አዋጁን መስፈርት ላሟሉ 1 ሺህ 455 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

ይቅርታ የተደረገላቸው የህግ ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ቆይታቸው መልካም ሥነ-ምግባር ያሳዩ እና በሕግ በተደነገገው የይቅርታ መስፈርትን ማሟላታቸው በክልሉ የይቅርታ ቦርድ ተጣርቶ የቀረቡ ናቸው ብለዋል። https://www.fanabc.com/archives/244487
ለትንሳኤ በዓል ወደ ሀገር ለሚገቡ 2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን አቀባበል እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለትንሳኤ በዓል ወደ ሀገር እየገቡ ለሚገኙ 2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል እየተደረገ ነው፡፡

በአቀባበል ሥነ -ስርዓቱ ላይ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

“ባክ ቱ ዩር ኦሪጂንስ” የሚል ስያሜ የተሰጠው እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በውጭ ለሚኖሩ የ2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ያቀረቡት ጥሪ በሶስት ዙሮች እንደሚካሄድ ይታወቃል፡፡https://www.fanabc.com/archives/244490
የስቅለትና የትንሳዔ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጎ ወደ ሥራ መግባቱን የጋራ ግብረ ኃይሉ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የስቅለትና የፋሲካ በዓላት ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲከበሩ ለማስቻል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጎ ወደ ስራ መግባቱን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ፡፡ በክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ በሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓት ከሚከበሩ ታላላቅ ሐይማኖታዊ በዓላት መካከል አንዱና ዋንኛው የሆነው የ2016 ዓ.ም የስቅለትና የፋሲካ በዓላት በሰላም እንዲከበር ለማስቻል አስፈላጊውን…

https://www.fanabc.com/archives/244493
የሐረሪ ክልል መስተዳድር ም/ቤት የ9 ወራት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት የ2016 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ መካሄድ ጀምሯል። በግምገማው መሰረት የክልሉ አስፈፃሚ መሥሪያ ቤቶች ሪፖርታቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በተገኙበት እያቀረቡ ነው። አቶ ኦርዲን በድሪ እንደገለፁት÷ በመድረኩ በክልሉ ባለፉት በዘጠኝ ወራት ለማከናወን የታቀዱ ስራዎች ይገመገማሉ። በተለይም ነባርና…

https://www.fanabc.com/archives/244502
የኢትዮጵያን የአቪዬሽን ዘርፍ ለማሳደግ የሚያስችሉ ውይይቶች ተካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን የአቪዬሽን ዘርፍ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ እና በዘርፉ አብሮ ለመሥራት የሚያስችሉ የሁለትዮሽ ውይይቶች በዶሚኒካ ሪፐብሊክ ፑንታካና ከተማ ተካሂደዋል፡፡ በዶሜኒካ ሪፐብሊክ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ድርጅት (አይ ሲኤኦ) ሲምፖዚየም ላይ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ከተለያዩ ተቋማትና ሀገራት ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል። ሚኒስትሩ ከዓለም…

https://www.fanabc.com/archives/244507
ከ374 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት 374 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሤ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት የሚኒስቴሩ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 391 ነጥብ 34 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 374 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን…

https://www.fanabc.com/archives/244510
በሚቀጥሉት ቀናት ከቀላል እስከ ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ በአብዛኛው የሀገሪቱ አካባቢ ላይ ይኖራል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሚቀጥሉት 30 ቀናት ወቅታዊው ዝናብ ከበልግ አብቃይ የሀገሪቱ ክፍሎች እየቀነሰ ከክረምት ዝናብ ሰጪ የሚቲዎሮሎጂ ክስተቶች መጠናከር ጋር ተያይዞ ወደ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ እንደሚስፋፋ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገለፀ፡፡ በመጪው ወር ለዝናብ መፈጠር አስተዋጽኦ የሚያደርጉ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በአብዛኛዎቹ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ…

https://www.fanabc.com/archives/244517
አምባሳደር ስለሺ በቀለ በአጎዋ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከአሜሪካ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር ኢ/ር) በአጎዋ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከተለያዩ የአሜሪካ የኮንግረስ አባላት ጋር ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ የአሜሪካ የኮንግረስ አባልና በኮንግረሱ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የአፍሪካ ንዑስ ኮሚቴ አባል ሺላ ቼርፊለስ-ማኮርሚክ ጋር ኢትዮጵያን ከአጎዋ ማግለሉ የሚፈጥረው ኢኮኖሚያዊ ቀውስን አስመልክተው መወያየታቸውን አንስተዋል፡፡

ሲያብራሩም አጎዋ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ባሉ ዜጎች ላይ ተጽዕኖው ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም በአሜሪካ ባለሃብቶች ላይ የሚያደርሰው ተጽዕኖ ቀላል እንዳልሆነም አስገንዝበዋል አምባሳደሩ፡፡

ከዚህ በተጨማሪም እየታዩ ያሉ ግጭቶች፣ የአንዳንድ ቡድኖች ስርዓት አልበኝነት በኢትዮጵያ መረጋጋት ላይ እና...https://www.fanabc.com/archives/244485
ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶችን ስራ የማስኬድ ተግባር ለኢትዮጵያ አየር መንገድ አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተከናወኑት የ'ገበታ ለሀገር' ፕሮጀክቶችን ስራ የማስኬድ ተግባር ዛሬ ለኢትዮጵ አየር መንገድ ስካይላይት ሆቴል አስረክቧል፡፡

በገበታ ለሀገር የተገነቡ ሎጆችን ስራ የማስኬድ ተግባርን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በስካይ ላይት ሆቴል ተቋሙ በኩል እንዲወጣ የስምምነት ፊርማ ሥነሥርዓት ተካሂዷል።

ከአራቱ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች ሶስቱ ማለትም ሃላላ ኬላ ሎጅ፣ ጨበራ ጩርጩራ የዝሆን ዳና ሎጅ እና ወንጪ ኢኮ ሎጅ በቅርቡ መመረቃቸው የሚታወሰ ሲሆን የጎርጎራ ፕሮጀክት ስራም በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።

በጠቅላይ ሚኒስሩ ከፍተኛ ትኩረት እና አመራር የተከናወነው የ’ገበታ ለሀገር’ ስራ የብሔራዊው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አንዱ ማዕዘን የሆነውን ቱሪዝምን የማሳደግ አላማ ያለው መሆኑ ተመላክቷል።

ፕሮጀክቶቹ በመጀመሪያው ፋይናንስ የማሰባሰብ ምዕራፍ የኅብረተሰቡን ድጋፍ በሰፊው ያሰባሰቡ፣ በግንባታቸው ምዕራፍ ግዙፍ የስራ ዕድል የፈጠሩ ብሎም ታላላቅ ... https://www.fanabc.com/archives/244515
ጸሎተ ሐሙስ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጸሎተ ሐሙስ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች እየተከበረ ነው፡፡ መስዋዕተ ቅዳሴ፣ የቅባ ቅዱስ ቡራኬና ህፅበተ እግር የዚሁ አካል ሲሆኑ ቀኑ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ ትህትናና መተሳሰብን ያስተማረበት መሆኑ ተገልጿል። በፒያሳ ልደታ ማርያም ካቴድራል የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሀነኢየሱስ ሱራፌልን ጨምሮ ካህናት፣…

https://www.fanabc.com/archives/244531
ጸሎተ ሐሙስ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ኢየሱስ ክርስቶስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የመጨረሻውን እራት የበላበት እና እግራቸውን በትሕትና ያጠበበት ዕለት ነው፡፡ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዐቢይ ጾም በተለይ ደግሞ በዚህ በህመማት ሳምንት የተለያዩ ሥነ-ሥርዓቶች ይከወናል፡፡ እያንዳንዱ የሳምንቱ ቀናት የየራሳቸው ትርጉም ያላቸው ሲሆን ÷ እለተ ሐሙስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዘንድ በብዙ ስያሜ…

https://www.fanabc.com/archives/244530
2024/06/01 18:24:15
Back to Top
HTML Embed Code: