የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በመላው የክርስትና ሐይማኖት ተከታዮች እየተከበረ ነው።

በዓሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ-ክርስቲያን፣ በካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን እና በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት÷ በስግደት፣ በጾም፣ በጸሎት እና በዝማሬ እየተከበረ ነው፡፡

በዕለቱ ቀኑን የሚያወሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የሚነበቡ ሲሆን፥ በዕለተ ስቅለት የተከናወኑ ተግባራት እየታሰበም ይሰገዳል።
የጎርጎራ ፕሮጀክትና የዓባይ ድልድይ ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ዕድል ያስገኛሉ – ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቅርብ የሚመረቁት የጎርጎራ ፕሮጀክት እና የዓባይ ድልድይ ለሕዝብ ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ዕድል እንደሚያስገኙ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ማሥተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አደም ፋራህ ከአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች ጋር በመሆን÷ የዓባይ ወንዝ ድልድይን ጨምሮ የተለያዩ አምራች ኢንዱስትሪዎችን እና የሌማት…

https://www.fanabc.com/archives/244611
አቶ አደም ፋራህ በአማራ ክልል ለልማት ሥራዎች ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ሰላም በመስፈኑ ለልማት ሥራዎች ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል ሲሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ማሥተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አደም ፋራህ ገለጹ፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ማሥተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አደም ፋራህ እና የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች÷ በባሕር ዳር ከተማ የተለያዩ አምራች ኢንዱስትሪዎችን፣ የሌማት ትሩፋት እና የልማት ሥራዎች ጎብኝተዋል፡፡…

https://www.fanabc.com/archives/244618
ግብረ-ኃይሉ የትንሣዔ በዓል በሰላም እንዲከበር ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕዝበ ክርስቲያኑ የትንሣዔ በዓልን በሰላም እንዲያከብር በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱ ከተማ አሥተዳደሮች ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ወደ ተግባር መግባቱን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታወቀ፡፡ ሕዝቡም የአካባቢውን ሰላምና ደኅንነት የሚያውኩ አጠራጣሪ ነገሮችን ሲመለከት ለፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠት ከጋራ ግብረ-ኃይሉ ጎን እንዲቆም ተጠይቋል፡፡ ግብረ-ኃይሉ ለመላው የክርስትና ሐይማኖት ተከታዮች የእንኳን…

https://www.fanabc.com/archives/244637
በአሸባሪው ሸኔ ላይ የሚወሰደው ርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል- የደቡብ ዕዝ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው ሸኔ ታጣቂዎች ላይ የሚወሰደው የማያዳግም ርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የደቡብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሰለሞን ኢተፋ ገለጹ። የሽብር ቡድኑን በመደምሰስ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ከምንጩ ለማድረቅ የሚያስችል ውጤታማ ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡ በጥናት ላይ የተመሰረቱ በርካታ ዘመቻዎችን በማድረግ የአሸባሪ ቡድኑን አባላት በቁጥጥር ስር ማዋል…

https://www.fanabc.com/archives/244641
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ፋና ላምሮት! በትንሳኤ ዋዜማ ይጠብቁን!
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አመራሮች የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄን ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አመራሮች እና ሠራተኞች የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄን ተቀላቀሉ፡፡

በዚህም ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር 100 ሺህ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል 5 ሺህ እንዲሁም ሌሎች የተቋሙ አመራሮችና እና ሠራተኞች የተለያየ መጠን ያለው የገንዘብ መጠን ድጋፍ በማድረግ ንቅናቄውን ተቀላቅለዋል፡፡

ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎችም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው የሂሳብ ቁጥር 1000623230248 ድጋፍ በማድረግ ንቅናቄውን መቀላቀል ይችላሉ፡፡

ንቅናቄው ሰዎች በየመንገድ ዳሩ ከመጸዳዳት ወጥተው ንጽህናውን በጠበቀ ቦታ የመጸዳዳት ባህላቸውን እንዲያሳድጉ፣ ለዚህ ደግሞ ደረጃቸውን የጠበቁ መጸዳጃዎች እንዲሠሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ መሆኑ ይታወቃል።
በዓለም የአቪዬሽን ድርጅት ሲንፖዚየም ኢትዮጵያ በርካታ ፋይዳዎች ማግኘቷ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም የአቪዬሽን ድርጅት ሉላዊ አፈፃፀም ድጋፍ ሲንፖዚየም ላይ ኢትዮጵያ ባደረገችው ተሳትፎ በርካታ ፋይዳዎች ማግኘቷን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገለጹ። ባላፉት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የዓለም የአቪዬሽን ድርጅት ሉላዊ የአፈፃፀም ድጋፍ ሲንፖዚየም መጠናቀቁን ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡ በዚህ ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ኢትዮጵያ የአቪዬሽን…

https://www.fanabc.com/archives/244653
Live stream finished (43 minutes)
ፖሊስ 89 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ የተሰረቁ የመኪና ዕቃዎችን ማስመለሱን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 89 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል በተለያየ ጊዜ የተሰረቁ 1 ሺህ 269 የመኪና ዕቃዎችን ማስመለሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በዚህም በልደታ፣ አራዳና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች አዋሳኝ ወረዳዎች የመኪና ዕቃ በሚሰርቁ፣ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድን ሽፋን በማድረግ የተሰረቀውን የመኪና ዕቃ ከሌቦች በሚቀበሉ በአጠቃላይ ወንጀሉን ተደራጅተው ሲፈፅሙ የነበሩ 89 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ብዛታቸው 1 ሺህ 269 የሆነ 33 አይነት የተለያዩ የመኪና ዕቃዎችን ማስመለሱን ገልጿል፡፡

ከተያዙት ዕቃዎች መካከልም÷ 528 ልዩ ልዩ ፍሬቻዎች፣ 187 ስፖኪዮዎች፣ 113 የመኪና መብራቶች፣ 172 የዝናብ መጥረጊያዎች እንደሚገኙበት የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡

የተሰረቁ የመኪና ዕቃዎችን የሚገዙ ለወንጀሉ መስፋፋት ዋና መንስኤ በመሆናቸው በእነሱ ላይ የሚደረገው ቁጥጥር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል፡፡

የመኪና ዕቃ የተሰረቀባቸው ግለሰቦችም በልደታ፣ አራዳና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች ፖሊስ መምሪያዎች በመቅረብ ንብረታቸውን መውሰድ እንደሚችሉ ገልጿል፡፡
የኢየሱስ ክርስቶስ የስቀለት በዓል በዓለም ዙሪያ…

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በዓል በተለያዩ የዓለማችን ሀገራት በሐይማኖታዊ አስተምኅሮዎችና ሥርዓተ-ክዋኔዎች ይከበራል፡፡ ዕለቱ ከሚከበርባቸው በርካታ ሀገራት መካከልም÷ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሩሲያ፣ ግብጽ፣ ግሪክ፣ እስራኤል፣ ቡልጋሪያ እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ በዓሉ የሚከበረውም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ-ክርስቲያን፣ በካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን እና በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት አማኞች ዘንድ ነው፡፡ የአከባበር ሁኔታው እንደየ…

https://www.fanabc.com/archives/244659
2024/05/03 11:21:17
Back to Top
HTML Embed Code: