. #ይህችን_ስህተት_አርም
✒️🖌✒️🖌✒️🖌✒️🖌✒️🖌✒️🖌
بسم الله الرحمن الرحيم

አንዳንድ ስህተቶች ከሌላ ባህል ወደኛ አስተሳሰብ ሰርገው ገብተዋል። ኢስላም ግን ከነዚህ ስተቶች የጠራ ነው።
🍃በማስቀደም #ሴት ልጅ ምንድናት?
ሴት ልጅ ማለት፦
❄️ውዷና የምትራራላት እናት ናት
❄️ጣፋጯና ተወዳጇ ሚስት ናት
❄️ደስ ምትልና ተናፋቂዋ እህት ናት
❄️አሊያም በሙስሊም ዘንድ ትልቅ ክብርና ቦታ ያላት ናት።

ኢሄ ሁሉ ክብርና ቦታ እያላት አንድ አንድ ሰዎች በሌላ ነገር ሲተረጉሟት ይደመጣሉ። እነርሱ፦
❄️በሕብረተሰቡ ውስጥ ለሚከሰት ጥፋት ዋነኛ ተጠያቂዋ እንስት ናት።
❄️እንስት የየትኛውም ክፋት (በላእ) ሰበብ ናት።
❄️እንስት አእምሮዋም ዲኗም ጐዶሎ ነው።
«ይህ ወንድሞቼ ስህተት ነው»። አንቺም እህቴ እራስሽን ዝቅ አርገሽ አትገምቺ ። ይህ ስተት የመነጨው በዚህ ረገድ የተነገረውን ሀዲስ በወጉ ካለመረዳት ነው።
❄️ለነዚህ ስህተቶ አሁን መልስ አልሰጥም ። ግን ከአንዳንድ እውነታዎች ጋር አስታውቅካለሁ።
❄️ከአላህ መልክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በኋላ ለአላህ መጀመሪያ የሰገደችው እንስት ናት። እሷም ከድጃ መሆኗን ኡለሞች በአንድ ድምፅ አፅድቀዋል።
❄️ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አይሻን (ረ.ዐ) በማስመልከት እንዲህ ብለዋል፦የሀይማኖታቹሁን ግማሽ ከዚህች ሴት ያዙ።
❄️ሴት ልጅ በተፈጥሮዋ አእምሮዋም ዲኗም ጐዶሎ ቢሆን ኖሮ ግማሽ ሀይማኖትን ከሷ መማር ተገቢ አይሆንም ነበር።

@fikr_eska_jenat
💁‍♂@fikr_eska_jenat
@fikr_eska_jenat
. የሼክ አል-ኡሰይሚን መግቢያ
✒️🖌✒️🖌✒️🖌✒️🖌✒️🖌✒️🖌
بسم الله الرحمن الرحيم

🍃#የተውሂድ_ትርጓሜ

ተውሂድ በአረበኛ ቋንቋ መሰረት አንድ ማድረግ መሆን በሸሪዓ ደግሞ አላህን (ሱ.ወ) በሚነጠልባቸው ነገራቶች (በጌትነቱ ፤ በአምላክነቱ ፤ በስሞቹና ባህሪያቱ ) አንድ ማድረግ (መነጠል ) ማለት ነው።

🍃#የተውሂድ_ክፍሎች

ተውሂድ ለሶስት ይከፈላል። እነሱም፦

1.ተውሂድ አል-ሩቡቢያ (የጌትነቱ አንድነት)
2.ተውሂድ አል-ኡሉሂያ (የአመላክነቱ አንድነት)
3.ተውሂድ አል-አስማኢ ወ ሲፋት (የስሞቹና ባህሪያቱ አንድነት)

እነዚያን የተውሂድ ክፍሎች በአንድ የቁርኣን አንቀፅ ተጠቃለው እናገኛቸዋለን። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፦

{رَّبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا فَاعْبُدْهُ وَاصْطَبِرْ لِعِبَادَتِهِ ۚ هَلْ تَعْلَمُ لَهُ سَمِيًّا}

«(እርሱ) የሰማያትና የምድር በሁለቱም መካከል ላለው ሁሉ ጌታ ነውና ተገዛው፡፡ እርሱን በመገዛትም ላይ ታገስ፡፡ ለእርሱ ሞክሼን ታውቃለህን?» (መርየም :65)

1.#ተውሂድ አል-ሩቡቢያ (አላህን በጌትነቱ አንድና ብቸኛ ማድረግ)

ተውሂድ አል-ሩቡቢያ ማለት አላህን (ሱ.ወ) በመፍጠሩ ፤ በባለቤትነቱና ነገሮችን በማስተናበሩ መነጠል (አንድ ማድረግ) ማለት ነው።

💦በመፍጠሩ መነጠል፦ ይህ ማለት ከአላህ በስተቀር ፈጣሪ እንደሌለ ማመን ማለት ነው። መፍጠር ለሱ ብቻ የተነጠለ መሆኑን የገልፅ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፦

{ۗ أَلَا لَهُ الْخَلْقُ وَالْأَمْرُ}
«ንቁ! መፍጠርና ማዘዝ የእርሱ ብቻ ነው፡፡» (አዕራፍ፡54)

በአረብኛ ቋንቋ ሰዋሰው (ነህው) ሙብተደዕ (አሰሪዎች ያልቀደሙት የንግግራችን መጀመሪያ የሆነ ስም) ከበሩን (ስለ ሙብተዲኡ አናን በመናገር ንግግሩን ጠቃሚ የሚያደርግ) ተቀድሞ ይመጣል። ከበሩን ለመገደብ ሲፈልግ ግን ከሙብተደኡ ይቀድማል። ስለዚህ ከበሩ መተርጎም «የእርሱ ብቻ ነው» ይባላል።
የእውነት ጌታ እሱ ብቻ መሆኑን ሲገልፅ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ፦

{فَذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمُ الْحَقُّ ۖ فَمَاذَا بَعْدَ الْحَقِّ إِلَّا الضَّلَالُ ۖ فَأَنَّىٰ تُصْرَفُونَ}

«እርሱ እውነተኛ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእውነትም በኋላ ጥመት እንጂ ሌላ ምን አለ? (ከውነት) እንዴት ትዞራላችሁ?» (ዩኑስ፡32)

ከቋንቋ አንፃር ከአላህ ውጭ ያለ አካል ፈጠረ ሊባል ይችላል። ለምሳሌ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፦

{فَتَبَارَكَ اللَّهُ أَحْسَنُ الْخَالِقِينَ}

«ከፈጣሪዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ፡፡» (ሙዕሚኑን :14)

ቡካሪና ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የሰዓሊዎችን ቅጣት መናገሩ እንዲህ ይላሉ፦ «የፈጠራችሁትን ህያው አድርጉ ይባላሉ።»
ይ...ቀ...ጥ...ላ...ል...

@fikr_eska_jenat
💁‍♂@fikr_eska_jenat
@fikr_eska_jenat
. የሼክ አል-ኡሰይሚን መግቢያ
✒️🖌✒️🖌✒️🖌✒️🖌✒️🖌✒️🖌
بسم الله الرحمن الرحيم
🍃ክፍል-2

ቡካሪና ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የሰዓሊዎችን ቅጣት መናገሩ እንዲህ ይላሉ፦ «የፈጠራችሁትን ህያው አድርጉ ይባላሉ።»

ይህ እውነተኛው መፈጠር አይደለም። ምከንያቱም እውነተኛ መፈጠር ማለት ካልነበረ በኋላ ማስገኘት ነው ፤ ከአላህ ውጭ ያሉ አካላት ፈጠሩ ስንል ግን የአላህን ፍጥረቶች በማዋሀድ የተለየ መልክና ቅርፅ አስያዙት ለማለት ብቻ ነው። ይህም የተለየ መልክ ማስያዝ አላህ (ሱ.ወ) በሰጣቸው ውስን ዕውቀትና ችሎታ የተገደበ ሲሆን አላህ (ሱ.ወ) ግን ያለገደብ ያሻውን ፈጣሪ የሆነ ሃያል ጌታ ነው። ስለዚህ ከአላህ በስተቀር ፈጣሪ የለም ከሚለው እምነታችን ጋር ፈፅሞ አይቃረንም።

🍃ባለቤትነቱ (ንግስናው) መነጠል፦ ይህ ማለት የፉጡራን ባለቤት ፈጣሪያቸው ብቻ መሆኑን ማመን ማለት ነው። ይህን አስመልክቶ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፦

{وَلِلَّهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ}

«የሰማያትና የምድር ንግሥና ለአላህ ብቻ ነው፡፡» (አል-ኢምራን :189)

ከአላህ ውጭ ያሉ አካላት በአላህ መፍቀድ ውስን ለሆኑ ነገራት ባለቤት ሊሆኑ ይችላሉ። ይህንን በማረጋገጥ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፦

{إِلَّا عَلَىٰ أَزْوَاجِهِمْ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُمْ فَإِنَّهُمْ غَيْرُ مَلُومِينَ}

«በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዟቸው (ባሪያዎች) ላይ ሲቀር፡፡ እነርሱ (በነዚህ) የማይወቀሱ ናቸውና፡፡»
(ሙዕሚኑን :6)

ነገር ግን ይህ ባለቤትነት እጅግ በጣም የተገደበና በአላህ (ሱ.ወ) መፍቀድ ብቻ የሚሆን ነው። አንድ ሰው በራሱ ስር ባለ ንብረት ላይ ባለቤት ሊሆን ሲችል በሌላው ሰው ንብረት ላይ ግን ባለቤት መሆን አይችልም ፤ የራሱ ንብረትንም ቢሆን ሸሪዓው በፈቀደለት መሠረት እንጂ ማንቀሳቀስ አይችልም። ለምሳሌ አንድ ሰው ለማቃጠል ወይንም የሚሰራባቸውን እንስሳ ለማሰቃየት ቢፈልግ አይበቃልህም እንለዋለን። አላህ (ሱ.ወ) ግን የፉጡራን ሁሉ ባለቤትና በነሱም ላይ ያሻቸውን ሰሪ ነው።

🍃በማስተናበሩ መነጠል፦ ይህ ማለት ከአላህ (ሱ.ወ) በስተቀር አስተናባሪ እንደሌለ ማመን ማለት ነው። አላህ (ሱ.ወ) አንዲህ ይላል፦

{قُلْ مَن يَرْزُقُكُم مِّنَ السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ أَمَّن يَمْلِكُ السَّمْعَ وَالْأَبْصَارَ وَمَن يُخْرِجُ الْحَيَّ مِنَ الْمَيِّتِ وَيُخْرِجُ الْمَيِّتَ مِنَ الْحَيِّ وَمَن يُدَبِّرُ الْأَمْرَ ۚ فَسَيَقُولُونَ اللَّهُ ۚ فَقُلْ أَفَلَا تَتَّقُونَ ¤ فَذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمُ الْحَقُّ ۖ فَمَاذَا بَعْدَ الْحَقِّ إِلَّا الضَّلَالُ ۖ فَأَنَّىٰ تُصْرَفُونَ}

«ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረ ማን ነው ከሙትም ሕያውን የሚያወጣ ከሕያውም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው» በላቸው፡፡ «በእርግጥም አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ (ለምን ታጋራላችሁ) አትፈሩትምን» በላቸው፡፡ «እርሱ እውነተኛ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእውነትም በኋላ ጥመት እንጂ ሌላ ምን አለ (ከውነት) እንዴት ትዞራላችሁ።» (ዩኑስ :31-32)

የሰው ልጅ ማስተናበር ግን እጅግ በጣም የተገደበና ሸሪዓው በፈቀደው መንገድ ብቻ የሚሆን ነው።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የተላኩባቸው ሙሽሪኮች በዚህ የተውሂድ ክፍል (ተውሂድ አል-ሩቡቢያ) ያረጋግጡ ነበር። አላህ (ሱ.ወ) አንዲህ ይላል፦
ይ...ቀ...ጥ...ላ...ል...

@fikr_eska_jenat
💁‍♂@fikr_eska_jenat
@fikr_eska_jenat
. የሼክ አል-ኡሰይሚን መግቢያ
✒️🖌✒️🖌✒️🖌✒️🖌✒️🖌✒️🖌
بسم الله الرحمن الرحيم
🍃ክፍል-3

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የተላኩባቸው ሙሽሪኮች በዚህ የተውሂድ ክፍል (ተውሂድ አል-ሩቡቢያ) ያረጋግጡ ነበር። አላህ (ሱ.ወ) አንዲህ ይላል፦

{وَلَئِن سَأَلْتَهُم مَّنْ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ لَيَقُولُنَّ خَلَقَهُنَّ الْعَزِيزُ الْعَلِيمُ}

«ሰማያትንና ምድርንም ማን ፈጠራቸው» ብለህ ብትጠይቃቸው «አሸናፊው ዐዋቂው (አላህ) በእርግጥ ፈጠራቸው» ይላሉ፡፡

ሙሽሪኮቹ የነገሮች አስተናባሪ አላህ ብቻ መሆኑን ያምናሉ። ከሰው ልጅ በጣም ኢምንቶች ሲቀሩ ይህንን የተውሂድ ክፍል ያሰተባበለ የለም ፤ ለዚህች ዓለም ሁለት እኩል ፈጣሪዎች አሏት ያለ አንድም የለም። ፊርዓውንና ተከታዮቹ በሰተቀር ተውሂድ አል-ሩቡቢያን ከአላህ (ሱ.ወ) ያስወገደ የለም ፤ ፊርዓውን ከኩራተ የተነሳ በምላሱ የአላህን (ሱ.ወ) ጌትነትና መኖር አስተባብሏል። አላህ ስለ ፊርዓውን ሲተርክልን እንዲህ ይላል፦

فَقَالَ أَنَا رَبُّكُمُ الْأَعْلَىٰ

«እኔ ታላቁ ጌታችሁ ነኝ፡፡» "አለም» (ናዚዓት :24)

{مَا عَلِمْتُ لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرِي}

«ከእኔ ሌላ ለእናንተ አምላክን ምንም አላወቅሁም፡፡» (አለም)» (ቀሰስ:38)

ይህ ክህደት ከኩራት የመጣ እንጂ አላህ (ሱ.ወ) ብቸኛ ፈጣሪ መሆኑን በውስጡ ያረጋገጥ ነበር። ይህን በማስመልከት ሃያሉ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፦

{وَجَحَدُوا بِهَا وَاسْتَيْقَنَتْهَا أَنفُسُهُمْ ظُلْمًا وَعُلُوًّا}

«ነፍሶቻቸውም ያረጋገጧት ሲኾኑ ለበደልና ለኩራት በእርሷ ካዱ፡፡» (ነምል፡14)

ሙሳ (ዐ.ሰ) ለፊርዓውን የተናገረውን አላህ (ሱ.ወ) ሲተርክ አንዲህ ይላል፦


{قَالَ لَقَدْ عَلِمْتَ مَا أَنزَلَ هَٰؤُلَاءِ إِلَّا رَبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ}

«(ሙሳም) «እነዚህን (ተዓምራቶች) መገሰጫዎች ሲኾኑ የሰማያትና የምድር ጌታ እንጂ ሌላ እንዳላወረዳቸው በእርግጥ ዐውቀሃል፡፡ (አለ)» (ኢስራእ :102)

መጁሶች ለዓለም ሁለት ፈጣሪዎች አሏት ባሉ ጊዜ በአላህ (ሱ.ወ) ጌትነት ላይ አጋርተዋል። ሁለት ፈጣሪዎች የሚሏቸውም ብርሃንንና ፅልመትን ነው። ከመሆኑም ጋር ሁለቱን እኩል አላደረጉም ፤ ብርሃን ከፅልመት ይበልጣል ይላሉ። ምክንያቱም ብርሃን ጥሩን ነገር ሲፈጥር ፅልመት ደግሞ ክፉን ነገር ይፈጥራል ፤ ብርሃን ያለና የሚያበራ ሲሆን ፅልመት ደግሞ የሚዳሰስ የሆነ የራሱ ምንጭ የሌለው ነው ብለው ስለሚያምኑ ነው። አክለውም ፈላስፋዎች በብርሃን ነባርነት ሲስማሙ በፅልመት ጉዳይ ግን ተለያይተዋል። ይህ የብርሃንን በላጭነት ያሳያል ይላሉ። ይህን በማለታቸው ነገራትን ሁሉ ፈጣሪ በሆነው አላህ (ሱ.ወ) ጌትነት (ሩቡቢያ) አጋርተዋል።

🍃#የአለማት_ፈጣሪ_አንድ_ብቻ_የመሆኑ_አዕምሯዊ_ምልከታ ፦ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፦
ይ...ቀ...ጥ...ላ...ል...

@fikr_eska_jenat
💁‍♂@fikr_eska_jenat
@fikr_eska_jenat
🗝እምነትን ከእውነት🗝

. የሼክ አል-ኡሰይሚን መግቢያ
✒️🖌✒️🖌✒️🖌✒️🖌✒️🖌✒️🖌
بسم الله الرحمن الرحيم
🍃ክፍል-4

🍃#የአለማት_ፈጣሪ_አንድ_ብቻ_የመሆኑ_አዕምሯዊ_ምልከታ ፦ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፦

{مَا اتَّخَذَ اللَّهُ مِن وَلَدٍ وَمَا كَانَ مَعَهُ مِنْ إِلَٰهٍ ۚ إِذًا لَّذَهَبَ كُلُّ إِلَٰهٍ بِمَا خَلَقَ وَلَعَلَا بَعْضُهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ}

አላህ ምንም ልጅን አልያዘም (አልወለደም)፡፡ ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም፡፡ ያን ጊዜ (ሌላ አምላክ በነበረ) አምላክ ሁሉ በፈጠረው ነገር በተለየ ነበር፡፡ ከፊላቸውም በከፊሉ ለይ በላቀ ነበር፡፡»
(የምእመናን ምዕራፍ المؤمنون 23:91)

አንድ ሰው ለዚህች አንድ አለም ሁለት ፈጣሪዎች አሏት ቢል ኖሮ እንደ ነገስታት ልማድ ሁለቱም ፈጣሪዎች የፈጠሩትን ነገር ይዘው በተገነጠሉና ተጋሪ የሌለበትን ሙሉ ስልጣን በፈለጉ ነበር። በዚህ ጊዜ አለም አንድ ስርዓቷም አንድ ነውና አንዳቸው በሌላኛው ላይ የበላይ በመሆን ብቸኛ ጌትነቱን ያረጋግጣል። አንዳቸው በሌላኛው ላይ የበላይ መሆን ካልቻለ ግን የሁለቱም ጌትነት ይወገዳል። ምክንያቱም ችሎታ የሌለውና ደካማ የሆነ አካል ጌታ ሊሆን ስለማይችል ነው።

. 2⃣. ተውሂድ አል-ኡሉሂያ (አላህን በአምላክነቱ መነጠል)

ተውሂድ አል-ኡሉሂያ ማለት አላህን (ሱ.ወ) በአምኮ መነጠል (አንድ ማድረግ ) ማለት ነው። ይህ የተውሂድ ክፍል ተውሂድ አል-ኢባዳ (የአምልኮ ተውሂድ ) በመባልም ይጠራል። ይህንን ተውሂድ ወደ አላህ (ሱ.ወ) ስናስጠጋው ተውሂድ አል-ኡሉሂያ (የአምላክነቱ ወይም የተመላኪነቱ አንድነት) በመባል ይጠራል። ወደ ባሮች (ፉጡራን) ስናስጠጋው ደግሞ ተውሂድ አል-ኢባዳ (የአምልኮ ተውሂድ ) በመባል ይጠራል።

ለአምልኮ ተገቢው ሁሉን ፈጣሪና ሰያሽ (ረዛቂ) የሆነው አላህ (ሱ.ወ) ብቻ ነው። ሃያሉ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፦

{ذَٰلِكَ بِأَنَّ اللَّهَ هُوَ الْحَقُّ وَأَنَّ مَا يَدْعُونَ مِن دُونِهِ الْبَاطِلُ وَأَنَّ اللَّهَ هُوَ الْعَلِيُّ الْكَبِيرُ}

ይህ አላህ እርሱ እውነት ከእርሱም የሚግገዙት (ጣዖት) ውሸት በመሆኑና አላህም እርሱ የበላይ ታላቅ በመሆኑ ነው፡፡»
(የሉቅማን ምዕራፍ لقمان 31:30)

{لَوْ كَانَ هَٰؤُلَاءِ آلِهَةً مَّا وَرَدُوهَا ۖ وَكُلٌّ فِيهَا خَالِدُونَ}

እነዚህ (ጣዖታት) አማልክት በነበሩ ኖሮ አይገቧዋትም ነበር፡፡ ግን ሁሉም በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡»
(የነቢያት ምዕራፍ الأنبياء 21:99)

ኢባዳ (አምልኮ) ሁለት ነገሮችን ሊወክል ይችላል። እነሱም፦
ይ...ቀ...ጥ...ላ...ል...

@fikr_eska_jenat
💁‍♂@fikr_eska_jenat
@fikr_eska_jenat
ያ አላህ ማረን:
🕌 የ 13 አመቱህፃኑ ልጅ
.
.
አንድ ሸይኽ ምን ይላሉ...
ከፈጅር ሰላት ቡሀዋላ አንድ የ13 አመት ህፃን እኔ ጋር
ይመጣና አባቴ ከባድ ለሆነ ጉዳይ ስለሚፈልግህ በፍጥነት
እንድትመጣ ይለኛል
*
ተከትየውም ሄድኩኝ እንደደረስንም አንድ 50 አመት
የሚሞላቸው አዛውንት ብቅ ይላሉ ....
ልጄን በጣም እያመማት ነውና እባክህ ቁርአን ቅራባት
ይሉኛል ቤት ውሰጥ ስገባም የልጅቷ ፊት ላይ ሻሽ ነገር አለ
ለሞት እያጣጣረች መሆኗንም ተመለከትኩ ወዲያውም
(ላኢላሀኢለላህ) በይ አልኳት ብዙ ጊዜም ደጋጌሜ
ላኢላሀኢለላህ በይ አልኳት
ምን ትላለች የህች ወጣት ልጅ...*ዋ !! ጉዴ ደረቴ ላይ
ጠበበኝ.....ዋ!! ጉዴ ደረቴ ላይ ጠበበኝ ትል ጀመር፡፡
ወእንደ መብረቅ ሆኖ ከወረደብኝ ነግግሮቿ መሀል ....
"ወላሂ በአላህ ይሁንብኝ ከእሳት መቀመጫዬን እያየሁት
ነው...........ወላሂ በአላህ ይሁንብኝ ከእሳት መቀመጫዬን
እያየሁት ነው፡፡**
ይህን እየተናገረች ዱንያን ለቃ አኺራ ሄደች...
መጨረሻዋ ለምን እንዳላማረ ስጠይቃቸው እንዲህ ሲሉ
መለሱልኝ...
ዱንያ ላይ እያለች በሙዚቃ ፍቅር ያበደች ነበረች
አሉኝ...በቁርአን ቦታም ሙዚቃን ታዳምጥ እንደነበር ነገሩኝ...
ሱብሀነላህ አላህ ይጠብቀን ወላሂ በቁርአን ቦታ የሙዚቃ
ፍቅር ሊያሳብደን ነው፡፡
አንድ ዶክተር ምን ይላል...
ሆስፒታላችን ውስጥ ወደ 24 ሰዎች ሞተዋል ከ24 አንዱ
ብቻ ነበር ሸሀዳ ይዞ የሞተው፡፡
ሱብሀነላህ ወላሂ አላህ መጨረሻችንን ያሳምርልን
አሚን ያረብ
አስተማሪ ስለሆነ ሼርማረጉን እንዳይረሱ
♻️ይቀላቀሉን♻️
🔽🔽🔽🔽

⚡️ @fikr_eska_jenat ⚡️
🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰
🗝እምነትን ከእውነት🗝

. የሼክ አል-ኡሰይሚን መግቢያ
✒️🖌✒️🖌✒️🖌✒️🖌✒️🖌✒️🖌
بسم الله الرحمن الرحيم
🍃ክፍል-5

ኢባዳ (አምልኮ) ሁለት ነገሮችን ሊወክል ይችላል። እነሱም፦

1.አላህን የሚገዙበት የአምልኮ ስርዓት ፦ ሸይኩል-ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ሲተረግሙት እንዲህ ይላል፦ "ኢባዳ (የአምልኮ ስርዓት) ጥቅል ስም ሲሆን አላህ (ሱ.ወ) የሚወዳቸውና የሚቀበላቸውን ውጫዊና ውስጣዊ የሆነ ንግግሮችና ስራዎችን ያጠቃልላል።"

2.መገዛት (መዋደቅ)፦ አላህን (ሱ.ወ) በመውደድና በማተለቅ ያዘዘውን መታዘዝ ፤ የከለከለውን መከልከል ።

ለምሳሌ ሰላት የአምልኮ ስርዓት ሲሆን ሰላትን መስገድ ደግሞ አላህን (ሱ.ወ) መገዛትና ለሱ መዋደቅ ነው። ሁለቱም (ሰላቱና መስገድ) ኢባዳ (አምልኮ) ናቸው።

በዚህኛው ተውሂድ አላህን (ሱ.ወ)መነጠል ማለት በመውደድና ማተለቅ ለሃያሉ አላህ ብቻ ባሪያ (ተገዥ) መሆንህ ፤ እሱን በመዋደቅ መነጠልህ ፤ እሱ በደነገገው መንገድ እሱን ብቻ ማምለክህ ነው። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል ፦

{لَّا تَجْعَلْ مَعَ اللَّهِ إِلَٰهًا آخَرَ فَتَقْعُدَ مَذْمُومًا مَّخْذُولًا}

«ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ አታድርግ የተወቀስክ ረዳት የሌለህ ትኾናለህና፤»
(የሌሊት ጉዞ ምዕራፍ الإسراء 17:22)

እንዲህም ተብሏል፦

{الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ}

«ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው፤ የአለማቱ ጌታ»
(መክፈቻ الفاتحة 1:2)

{يَا أَيُّهَا النَّاسُ اعْبُدُوا رَبَّكُمُ الَّذِي خَلَقَكُمْ}

«እናንተ ሰዎች ሆይ! የፈጠራችሁን እነዚያንም ከናንተ በፊት የነበሩትን (የፈጠረውን) ጌታችሁን ተገዙ»
(የላሚትዋ ምዕራፍ البقرة 2:21)

አላህ (ሱ.ወ) ብቻ የዓለማት ጌታና ፈጣሪ መሆኑ ለአምላክነቱ (የተመላኪነቱ) መረጋገጡና እሱ ብቻ በአምልኮ ለመነጠሉ እንደ ምክንያትና መረጃ ነው። ምክንያቱም ካልነበረ በኋላ የተገኘን ወደ መጥፋትም ተመላሽ የሆነን ፍጡር ሚመለክ አምላክ አድርጎ መያዝ ከቂልነት ነው። ትብያ ወደሆነ የአንድ ግለሰብ ቀብር በመሄድ ያንተን ዱኣ ከጃይ ሲሆን እሱን መለመንና ማምለክ ከቂልነት ነው። በእርግጥ ይህ ፉጡር ላንተ በማስገኘት ፣ በማዘጋጀትና በማብዛት መቼም አይጠቀምህም። ነገሩ እራሱን መጥቀምና መጉዳት የማይችል ፍጡር እንዴት ሌላውን መጥቀምና መጉዳት ይችላል!

ከፉጡራን አብዛኞቹ በዚህ የተውሂድ ክፍል ክደዋል አስተባብለዋልም። በዚህም ሳቢያ አላህ (ሱ.ወ) መልክተኞችን ልኳል ፤ በነሱም ላይ መፅሃፍቱን አውሩዷል። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፦
ይ...ቀ...ጥ...ላ...ል...

@fikr_eska_jenat
💁‍♂@fikr_eska_jenat
@fikr_eska_jenat
ዐብደሏህ ኢብን ዐምር (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ ነቢይ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡ “ሙስሊም የሚባለው በምላሱና በእጁ ሙስሊሞችን ከመጉዳት የታቀበ (ነጻ የሆነ) ሰው ነው። “ሙሃጂር' ' (ስደተኛ) የሚባለው ደግሞ አላህ የከለከለውን ነገር ሁሉ የተወ ነው።
♻️ይቀላቀሉን♻️
🔽🔽🔽🔽

⚡️ @fikr_eska_jenat ⚡️
🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰
Forwarded from mahfuz
🗝እምነትን ከእውነት🗝

. የሼክ አል-ኡሰይሚን መግቢያ
✒️🖌✒️🖌✒️🖌✒️🖌✒️🖌✒️🖌
بسم الله الرحمن الرحيم
🍃ክፍል-6

ከፉጡራን አብዛኞቹ በዚህ የተውሂድ ክፍል ክደዋል አስተባብለዋልም። በዚህም ሳቢያ አላህ (ሱ.ወ) መልክተኞችን ልኳል ፤ በነሱም ላይ መፅሃፍቱን አውሩዷል። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፦

{وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ}

«ከአንተ በፊትም እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ በማለት ወደርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡»

(የነቢያት ምዕራፍ الأنبياء 21:25)

3⃣. ተውሂድ አል-አስማኢ ወ ሲፋት

ይህ ማለት አላህን(ሱ.ወ) ባሉት ባህሪያትና ስሞቹ መነጠል (አንድ ማድረግ) ማለት ነው። ይህም ሁለት ነገሮችን በውስጡ ያካትታል። እነርሱም፦

1ኛ. ማረጋገጥ፦ ይህ ማለት አላህ(ሱ.ወ) በቁርኣን ወይንም በነቢዩﷺ ሱና (ሶሂህ ሐዲስ) ውስጥ ለራሱ ያረጋገጠውን ባህሪያትና ስሞች ሁሉንም ማረጋገጥ ማለት ነው።

2ኛ. ማመሳሰልን ማስወገድ፦ ይህ ማለት በባህሪያቱና ስሞቹ ለአላህ(ሱ.ወ) አምሳያን አለማድረግ ማለት ነው። አላህ(ሱ.ወ) በጉዳዩ እንዲህ ይላል፦

{لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ۖ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ}

«የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡»

(የመመካከር ምዕራፍ الشورى 42:11)

ይህ አንቀፅ አላህ(ሱ.ወ) ባሉት ባህሪያት ሁሉ አንድም ፍጡር እንደማይመሳሰለው ያመላክታል። አላህ(ሱ.ወ) ለራሱ ያረጋገጠውን የማያረጋግጥ ሙአጢል (አስወጋጅ) ይባላል። ይህ ማስወገዱ ከፊርዓውን የማስወገድ ክህደት ጋር ይመሳሰላል። ከማመሳሰል ጋር ያረጋገጠ ደግሞ ከአላህ ጋር ሌላን አካል ካመለኩ አጋሪዎች (ሙሽሪኮች) ጋር ተመሳስሏል። ያለማመሳሰል ያረጋገጠ ደግሞ ከመውሂዶች (አላህን ብቻ ከሚያመልኩ) ነው።

ይህ የተውሂድ ክፍል የተወሰኑ ሙስሊሞች የተሳሳቱበትና የጠመሙበት ነው። ወደ ብዙ አንጃዎችም ተከፋፍለውበታል ፤ ከነሱ "አላህን(ሱ.ወ) የማጠራ ነኝ" በሚል ሙገታ የአላህን ባህሪያት ያስወገደ አለ። በእርግጥ ጠሟል ፤ ምክንያቱም ይ...ቀ...ጥ...ላ...ል ...
♻️ይቀላቀሉን♻️
🔽🔽🔽🔽

⚡️ @fikr_eska_jenat ⚡️
🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰
••••••የእብድ ኹጥባ•••••
በጁሙዐ ቀን ኹጥባ የሚያደርጉት የመስጅድ ኢማም በጊዜ አልመጡም ( ዘግይተው) ነበርና አንድ እብድ መጣና ሚንበሩ ላይ ወጣ። የተወሰኑ ሰዎች ሊያስወርዱት ሞከሩ። በመስጅዱ ውስጥ ሀላፊነት ካላቸው ሰዎች መካከል አንዱ ባለበት እንድተውትና ኹጥባ እንድያደርግ አዘዘ። እብዱም ኹጥባ ማድረግ ጀመረ:_
" ምስጋና ለአሏህ ይገባው። ያ ከሁለት አይነት የፈጠራችሁና ለሁለት አይነት አድርጎ ለከፈላችሁ። ከናንተ ውስጥ ልታመሰግኑ ዘንድ ሀብታሞችን አደረገ። ከናንተም ውስጥ ትታገሱ ዘንድ ድሆችን አደረገ።
ከናንተ ውስጥ ሀብታም የሆነውም አላመሰገነ፣ ድሀ የሆነውም አልታገሰ።
የአሏህ እርግማን በሁላችሁም ላይ ይሁን!
ቁሙ ወደ ሶላታችሁ!"
👍👍👍ንግግሩ የእብድ ንግግር አደለም ሀቅ ነው ያወራው
እንኳን ደህና መጣህ
♻️ይቀላቀሉን♻️
🔽🔽🔽🔽

⚡️ @fikr_eska_jenat ⚡️
🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰
እቺን መልዕክት ወላሂ ሼር አደርገዋለሁ እርግጠኛ ነኝ ሼር ልታደርገው ነው
ምክንያቱም ወላሂ ብለሀል!!

ስትወለድ ከእናትህ ሆድ ማህፀን ያወጣህን ፈፅሞ አታውቅም
ስትሞት ማን ወደ ቀብርህ እንደሚያስገባህ ፈፅሞ አታውቅም

የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ
ስትወለድ ትታጠባለህ ትፀዳለህ ስትሞት ትታጠባለህ ትፀዳለህ
ስትወለድ ማን እንዳዘነና ማን እንደተደሰተ አታውቅም
ስትሞትም ጊዜ ማን እንደሚያለቅስልህ ማን እንደሚቀብርህ አታውቅም

የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ
በእናትህ ሆድ ውስጥ በጠባብ ቦታና በጨለማ ውስጥ ነበርክ
ስትሞት ጊዜ በጠባብ ቦታና በጨለማ ውስጥ ትሆናለህ።

የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ
ስትወለድ በጨርቅ ትጠቀለላለህ ሊሸፍኑህ ስትሞት በከፈን ይጠቀልሉሃል ሊሸፍኑህ

የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ
በተወለድክና በአደክ ጊዜ ሰዎች ምስክር ወረቀት ስለሙያህ ይጠይቁሀል
በሞትክም ጊዜ በመላኢካዎች ስለመልካም ስራህ ይጠይቁሀል
_ለመጨረሻው ሀገርህ ምን አዘጋጀህ

ከልብህ ይህቺን ቃል ለመናገር ሞክር
ከአላህ ሌላ በፍፁም የሚመለክ አምላክ እንደሌለ መስክር እንዲሁም ሙሀመድﷺ የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውን መስክር

ይህቺን መልእክት ፍፁም ሳታነባት እንዳትልካት

قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ اللَّهُ الصَّمَدُ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ وَلَمْ يَكُن لَّهُ كُفُوًا أَحَدٌ
(#ሱረቱ_አል_ኢኽላስ)
((በል እርሱ አላህ አንድ ነው አላህ የሁሉ መጠጊያ ነው አልወለደም አልተወለደምም ለእርሱ አንድም ብጤ የለውም))
መልዕክቱን ሼር አድርገው በአንተ ሠበብ የቁርአን አንድ ሶስተኛውን ይቀራሉ ያነባሉ ነፍስህን አጅር አትከልክላት!!

ሼር አድርጉት ♻️ይቀላቀሉን♻️
🔽🔽🔽🔽

⚡️ @fikr_eska_jenat ⚡️
🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰
Forwarded from mahfuz
💙 አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ)
ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ሲገልፃቸው እንዲህ አለ‥

﴿وَما أَرسَلناكَ إِلّا رَحمَةً لِلعالَمينَ﴾
" ለዓለማት እዝነት አድርገን እንጂ
አልላክንህም ፡፡"
 [አል-አንቢያእ 107]

እንዲሁም ረሱል(ሰዐወ) እራሳቸውን
ሲገልፁ እንዲህ አሉ " إنما أنا رحمة مهداة "
⇘ ረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) ተከታይ የሆነ ሰው
ባህሪውንና ተግባሩን በእዝነት ሚዛን ያድርጋቸው ። የዛኔ ረሱልን መከተሉ በአፍ ወይ በተግባር እንደሆነ ይታወቃል ።
                ♻️ይቀላቀሉን♻️
🔽🔽🔽🔽

⚡️ @fikr_eska_jenat ⚡️
🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰
አሠላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ🖐🖐🖐🖐
እደሞት እና እደቀብር ማን መካሪ አለ፡😭😭😭
ወላሂ ሞት ሲታሰብ
ልቡ ያልታወረ ካልሆነ
አይኑ ያለቅሳል
ልቡ ይደማል
አረ ሁሉም አካል ይፈራል
እደዚ የምንሆነው ሞት አስፈርቶን መሆን የለበትም!!"!!!!!!!!
ቀብርን ፈርተን ቢሆን እጂ😭😭 ሞትማ አይፈራም የቀብር ነገር ያሳስባል 😭😭😭
ያስጨንቃል😭😭😭
ያስለቅሳል ወላሂ ልብ ይሠብራል
😭😭😭😭
ዛሬ ኸይር ስራ ካልሰራን
ዛሬ በአላህ መገድ ካልፀናን
ዛሬ የነብዩን መገድ ካልተከተልን
ሞት መቶ ጒሮሮዋችንን ሲይዘን
ጊዜው እረፍዶብን
ሰአታችን አልፎ 😭😭😭
ኢሄን ጊዜ ተውበትም አይቻል
ምን ሊውጠን ነው ወድሜ😭😭
ምን ሊውጠን ነው እህቴ😭😭
ዱንያ ከአሁን ወዲ አታታለን!"!"!!!!
ለቀብር እኮ
ሀብት አይጠቅምም
ቤተሠብ አይጠቅምም
የሚጠቅመን !
ኸይር ስራችን
በአላህ መንገድ መፅናታችን
የነብዩን ጒዳና(ፈለግ)መከተላችን
ጊዜው ሣይረፍድ ተውበት ማድረጋችን ነው😭😭😭😭
እና ምን እየጠበቅን ነው😭
ሞት ሣይመጣ ለምን አንቶብትም!!
የቀብርን ቅጣት ያሰበ
ቀብር ውስጥ ምን እደሚጠብቀን ያሰበ😭😭😭😭
አላህ ልቡን ያወረበት ካልሆነ
ወላሂ ፡ወቢላሂ ፡ወተላሂ
የማይቶብት😭😭
ቀብርን አስቦ የማያለቅስ😭
ሞትን አስቦ የማይመከር የለም😭
እና እህት ወድሞቼ ጊዜው አስፈርቷል😭😭
ድገተኛ ሞት በዝቷል😭😭
ስለዚ ሁላችንም እንንቃ
ሁላችንም እንቶብት
ሁላችንም እናልቅስ
አላህ ተቆጣ
መስጊዶች ተዘጉ 😭😭😭😭😭
ቤቴ አትሂዱ አለ 😭😭😭😭
እና አናለቅስም😭😭
እና አንቶብትም😭😭
አረ ይብቃን ፡
መገላለጥ ልታይ ልታይ ማለት
አራዳ አራዳ ነኝ ከማለት
ፎቶ በየ ሚዲያው ከመልቀቅ
አለመስገድ ፡😭😭😭😭
የአላህን ትእዛዝ መተላለፍ
የነቢዩን ትእዛዝ መተላለፍ
ዛሬ ይብቃ 😭😭😭😭
ሁላችንም ወደ አላህ እንመለስ😔
የአላህ መጨረሻችንን አሳምረህ🙏
የአላህ ከቀብር ቅጣት ጠብቀህ🙏
የአላህ የቂያማ ቀን ሚዛናችንን ከፍ አርገህ፡፡ 🙏🙏🙏🙏 ጀነትን ሰተህ አበስረን🙏🙏
የአላህ ሱ ወ ፊት ጠግበው ከሚያዩት አርገን🙏🙏🙏🙏 ከነቢዩ ሙሀመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ጒረቤት አርገን🙏🙏🙏

እና ሙስሊም እህት ወድሞቼ
ዱአ አድርጉ እላችኋለው!!!!!!!!!!!!
ወሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ በዱአ አንረሳሳ😔😔


⚡️ @fikr_eska_jenat ⚡️
🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
ከታጋሽነት በስተቀር የማናቸውም መልካም ነገር ሽልማቱ ምን እንደሆነ ይታወቅ ይሆናል፡፡ ታጋሽነት ግን ሽልማቱ የማይታወቅ ትልቅ እና መልካም ነገር ነው፡፡
                ♻️ይቀላቀሉን♻️
@Halal_2Tube
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
የአንድ ሙስሊም ወንድ ከሁሉ የበለጠ ቅዱስነት/ንጹህነት፣ ምላሱን፣ ወሲባዊ አካሉን እና አስተያየቱን ሲጠብቅ ነው፡፡
               ♻️ይቀላቀሉን♻️
@Halal_2Tube
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
════════ ∘◦❁◦∘ ═════════
ወረተኛ አትሁን
◕———✷_✿_✷———◕

አሽ-ሸብሊ በአንድ ወቅት፦ "#ከረጀብና #ከሸዕባን የሚበልጠው የትኛው ነው?" የሚል ጥያቄ ቀረበላቸው። እርሳቸውም፦ "ሁሌም አላህን #የምታመልኩ ሰዎች ሁኑ እንጂ #ወረተኛ አትሁኑ።" ሲሉ መለሱ።

ይህ ንግግራቸው ጫፍ ላይ ሆኖ አላህን የሚያመልክ፣ ሸዕባን ወር ላይ አላህን ተገዝቶ ቀሪውን ወራት አላህን የሚረሳን ሰው ለማሳሰብ ነው። #በረመዳን ወር እንባውን ሲያፈስ የነበረንና ከረመዷን ውጭ ባሉት ወራት እንባው #የደረቀውን ሰውም ይመለከታል።

ሁሉም የህይወት ዘመናቸው #ረመዷን የሆነላቸው የአላህ ምርጥ ባሮች ከወረተኞች ምንኛ የላቀ ደረጃ ላይ ናቸው?! የሌሊት ግዚያቸው #በሶላት ያልፋል፤ ቀናቸው በፆምና በዒባዳ።

#ወንድሜ_ሆይ! የአላህን መልትክኛ (ሰ.ዕ.ወ) ኮቴ ተከተል። ውድድርህን እስከምታጠናቅቅ ሥራህ ያለመቋረጥ ይቀጥል። በዚህ ሁኔታ ሆነህ ወደ #አኺራ ተጓዝ። የህይወትህ ፍጻሜ ይሁን።

"እውነትም (ሞት) እስኪመጣ ድረስ ጌታህን ተገዛ።" (አል-ሒጅር ፡99)

               ♻️ይቀላቀሉን♻️
@Halal_2Tube
════════ ∘◦❁◦∘ ═════════
🌾ከጃቢር ኢብን አብዱላህ (ረ.ዐ) በተላለፈው ሐዲስ፦ "የአላህ መልክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ #ሚንበር ወጡ። የመጀመሪያውን ደረጃ በሚወጡበት ጊዜ አሚን! አሉ ሁለተኛውን ደረጃ በሚወጡበት ጊዜም አሚን! አሉ። (እንዲሁም) ሦስተኛውን ደረጃ በሚወጡበት ጊዜ አሚን! አሉ። አንቱ የአላህ መልዕክተኛ! ሦስት ጊዚ አሚን! ስትሉ #ሰማንዎት ለምን ይሆን? ተብለው ተጠየቁ። (እርሳቸውም) የመጀመሪያውን ደረጃ በምወጣበት ሰዓት ጅብሪል (ዐ.ሰ) ወደኔ መጣና፦ ረመዷንን አጊኝቶ ምህረት ሳያገኝበት የተለየው ሰው ዕድለ-ቢስ ይሁን አለኝ፤ አሚን! አልኩት። ከዚያም ሁለቱም ወላጆቹ ወይም አንዳቸው በህይወት ኖረውለት በነርሱ ሰበብ #ጀነት ያልገባ ሰው ዕድለ-ቢስ ይሁን አለ፣ እኔም አሚን! አልኩ። ቀጠለና ደግሞ፣ ያንተ ስም ሲወሳ ሰምቶ #ሶለዋት ያላወረደ ሰው ዕድለ-ቢስ ይሁን አለ፣ እኔም አሚን! አልኩ። " (ቡካሪ)

@fikr_eska_jenat
@fikr_eska_jenat
@fikr_eska_jenat
ተስሀሩ ተስሀሩ ተሰሀሩ ተሰሀሩ
ፈኢነ ፊስሁር በረካህ

ትንሽም ቢሆን ሰሑር መብላት በረካ አለው (አንድ ጉንጭ ውሀ ቢሆንም)....እናም በሰሑር አስታውሳችኀለሁ!
ኒያ አትርሱ...

@fikr_eska_jenat
@fikr_eska_jenat
2024/05/17 04:44:00
Back to Top
HTML Embed Code: