Channel name was changed to «የአላህን ውዴታ ፍለጋ»
የመቃብር ሰዎችን ተጎራበትኩ!
ከክፋት የሚያቅቡ፣ቀጣዪን ዓለም የሚያስታውሱ እውነተኛ ጎረቤቶች ሆነው አገኘዃቸው!!!
___ሰዪዱና ዐሊይ(كرم الله وجهه)

https://www.tg-me.com/finding_hubullah
ሽማግሌ ልከህ… አባትየው መስጂድ ግን አይቼህ አላቅም ያለህ ትዝ ሲልህ😂😂😂

https://www.tg-me.com/finding_hubullah
#ከዓሪፎቹ ተሞክሮ
የላቁት፣የበቁት ሸይኽ፣ሰዪዲ ዩሱፍ አን ነብሃኒይ(قدس سره)
እንዲህ ብለዋል:–
ሰዪዳችንን ﷺ በህልሙ መመልከት የፈለገ፣ሁለት ረከዓ ሶላት ይስገድ፣ከዛም ተከታዩን ዱዓእ መቶ ጊዜ ይበል
"يا نور النور يا مدير الأمور، بلغ عني روح سيدنا محمد صلى الله تعالى عليه وسلم تحية وسلامًا.
አባባል:–
"ያ ኑረን–ኑር፣ያ ሙዲረል–ኡሙር፣በል’ሊጝ ዐን’ኒ ሩሐ ሰዪዲና ሙሐመዲን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለመ ተሒይ’የተን ወሰላማ"
__
(( مفرج الكروب ومفرح القلوب ))
አቡ ሱሀይል
https://www.tg-me.com/finding_hubullah
# መረሳት የሌለበት እውነታ!!!

https://www.tg-me.com/finding_hubullah
#ከወደ ህንድ የተሰማው ዘገባ፣እንዲህም አለ እንዴ? !!! ያስብላል… !!!🤔
ህንዳዊቷ ሴት ባሏ ለሷ ካለው ከልክ ያለፈ ፍቅር የተነሳ ፍቺ ጠየቀች ይላል፤እንዲህ ስትልም ስሞታዋን አቅርባለች “በጣም ይወደኛል፣አይከራከረኝም፣አይጮኽብኝም
፣ምግብ ያበስልልኛል፣ቤት ውስጥ ባሉ ስራዎች እንዳለ ይረዳኛል.. !!!
የምከራከረውን ሰው እፈልጋለው፣ባል በሁሉም ነገር የሚስማማበትን ህይወት አልፈልግም!!!
___
በጣም ካዝናኑኝ ኮመንቶች ውስጥ
"በይ እንደኔ አይነቱን ባል ይስጥሽ"😳የሚለው ፀሎት ነው።
ለፀላዩዋ እርግማን 😭 ለተቀባዩዋ ምርቃት የሆነ ፀሎት!!!😂

https://www.tg-me.com/finding_hubullah
ኢብራሂም ቢን አድሃም ረሂመሁሏህ ጋር የተደረገ ቃለ መጠየቅ:-
ሰውየው:- በረካ የሚባል ነገር ጠፍቷል የለም አላቸው::

ኢብራሂም ቢን አድሃምም ረሂመሁሏህ በዙሪያህ ውሻና በጎችን አይተሃልን? አሉት

ሰውዬውም አዎ! አለ::

ኢብኑ አድሃምም ረሂመሁሏህ የትኞቹ ናቸው በብዛት የሚወልዱት? አሉት::

ሰውየውም ውሻ እስከ ሰባት ትወልዳለች በጎች ግን እስከ ሶስት ነው የሚወልዱት አላቸው::

ኢብራሂም ቢን አድሃምም ረሂመሁሏህ በዙሪያህ ብትመለከት የትኞቹን በብዛት ታያለህ? አሉት::

ሰውዬውም በጎች በብዛት ይታያሉ አላቸው::

ኢብን አድሃምም ረሂመሁሏህ በብዛት የሚታረዱትና ቁጥራቸው የሚቀንሰው በጎች አይደሉምን? አሉት

ሰውዬውም አዎ! አላቸው::

ኢብን አድሃምም ረሂመሁሏህ በረካ ማለት ይሄ ነው አሉት::

ሰውዬውም ይሄ እንዴት ሊሆን ይችላል ? (በውሾች ፋንታ እንዴት በጎች ሊበዙ ቻሉ)? ይላቸዋል::

ኢብኑ አድሃምም ረሂመሁሏህ በጎች በግዜ ወደ በረታቸው ገብተው በሌሊቱ መጀመሪያ ላይ ይተኙና ከፈጁር ቀድመው ይነሳሉ::
የዛኔ የእዝነት ወቅት ስለነበር በረካ በእነሱ ላይ ይወርዳል::
ውሾች ግን ሌሊቱን ሙሉ ሲጮኹ ያነጉና የፈጁር ወቅት ሲገባ ይተኛሉ የእስዝነቱም ግዜ ያመልጣቸውና በረካውንም ያነሳባቸዋል አሉት::💚🙏🏽

ትምህርቱን ለእናንተ ተውኩት...!😋😊

https://www.tg-me.com/finding_hubullah
"ሰው የቱንም ያህል ቢመቀኝ
የቤቱን በር እንጂ የአላህን በር ሊዘጋብህ አይችልም"

https://www.tg-me.com/finding_hubullah
🔴 በዲያሊሲስ(ኩላሊት ትጥበት) ወቅት ደም ከሰውነት በቀዩ ቱቦ ወጥቶ በዳያሊስስ ማሽኑ በኩል አልፎ በሰማያዊው ቱቦ ወደ ውስጥ ይመለሳል፣በዚህ ሁኔታ ውስጥ ለ4 ሰአታት ያለምንም እንቅስቃሴ በአልጋ ላይ ይቆያል።

እና ይህን ሂደት በሳምንት ሶስት ጊዜ ትሰራለህ፣ማለትም በወር 12 ጊዜ እና በእያንዳንዱ ጊዜ 4 ሰአት፣በድምሩ በአንድ ወር ውስጥ 48 ሰአት …!!!

አንተ ግን በዚህ ህመም ያልተጠቃህ ጤነኛ ሰው፣ ኩላሊቶቻችሁን በቀን በግምት 36 ጊዜ ያለምንም ችግር እና ህመም በራስ-ሰር ሂደት ይታጠብልሃል

አልታወቀንም፣ቦታ አልሰጠነውም እንጂ እኛ ቁጥር ስፍር በሌለው ፀጋ ውስጥ ነን ..
___
{فبأي آلاء ربكما تكذبان }
[ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?]
[ ሱረቱ አል ረሕማን - 13 ]
………………
ጌታህን አመስግን
አልሐምዱ ሊላህ
___
T.me/hamidabuhamid
https://www.tg-me.com/finding_hubullah
2024/05/02 08:20:16
Back to Top
HTML Embed Code: