Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#መጽሐፍ_ቅዱስ

በአንድ ተራራማ ስፍራ እርሻ በማረስ ከልጅ ልጁ ጋር የሚኖር አንድ ሽማግሌ ነበር፡፡ ይህ ሽማግሌ ዘወትር ፀሐይ ብርሃኗን ስትፈነጥቅ እየተነሳ መጽሐፍ ቅዱስን ያነባል፡፡ የልጅ ልጁ የአያቱን ተግባር ይከታተል ስለነበር እሱም ያያቱን ፈለግ በመከተል ጠዋት ጠዋት እየተነሳ መጽሐፍ ቅዱን ማንበብ ጀመረ፡፡

አንደ ቀን ታድያ አያቱን “አባባ መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ እየሞከርኩ ነበር፡፡ ነገር ግን ልረዳው አልቻልኩም ደግሞም አንብቤ እንደጨረስኩ ወዲያውኑ እረሳዋለሁ እናም እንድረዳውና እንዳልረሳው ምን ማደረግ አለብኝ?” ሲል ጠየቀ፡፡

ሽማግሌው ምንም ድምጽ ሳያሰሙ “ከሰሉን ወደ ምድጃው ጨመሩና እንካ ይሄን የከሰል ቅርጫት ይዘህ ወንዝ ውረድና ውሃ ይዘህልኝ ተመለስ” አሉት፡፡ ልጁ ትዛዙን ለመፈጸም ወደወንዝ ወርዶ ውሃውን ይዞ ሊመለስ ቢመክርም ቅርጫቱ ውሃውን እያንጠባጠበ ቤት ከመድረሱ በፊት ፈሶ አለቀበት፡፡ ሽማግሌው የልጁን ሁኔታ እያስተዋሉ “አሁን ለሁለተኛ ጊዜ ይዘህ ስትመጣ ግን ፈጠን ፈጠን ብለህ ተመለስ ብለው” ድጋሜ ላኩት፡፡ አሁንም ልጁ እንደተነገረው በፍጥነት ውሃውን ቀድቶ ሊመለስ ቢሞክርም ቤቱ ሳይደርስ ውሃው ፈሶ አለቀበት፡፡ አያቱንም “በቅርጫት ውሃ ማምጣት ስለማይቻል ሌላ መያዥ ይስጡኝና ላምጣ” ሲል ጠየቀ፡፡ ሽማግሌ አያቱም “እኔ የምፈልገው የቅርጫት ውሃ ነው፡፡ ጠንክረህ ባለመሞከርህ ነው ፈሶ ያለቀብህ” በማለት እንደገና ላኩት፡፡ በዚህ ጊዜ ልጁ በቅርጫት ውሃን ማምጣት እንደማይቻል ቢያውቅም ለአያቱ ታዛዥነቱን ለማሳየት ከበፊቱ ፈጥኖ ለማምጣት ሲሞክር ውሃው ፈሶ ስላለቀበት ባዶውን ቅርጫት እያሳየ “ተመልከት አባባ! እዲሁ ነው የምደክመው እንጅ እኮ ጥቅም የለውም” አለ፡፡

ከዚህ ጊዜ ምልልስ በኋላ ሽማግሌው “እስኪ ቅርጫቱን ተመልከተው” አሉት፡፡ ልጁ ቅርጫቱን ሲመለከት ከዚህ በፊት የማያውቀው ቅርጫት ይመስል ቅርጫቱ የተለየ ሆነበት የከሰል መያዣ እያለ በጅጉ የቆሸሸ ነበር፡፡ አሁን ግን ሙልጭ ብሎ ጸድቷል፡፡ ውስጡን ሲመለከተው ከመንጻቱ የተነሳ የበፊቱ ቅርጫት አልመስለው አለ፡፡

ስለዚህ ልጄ መጽሐፍ ቅዱስን ስታነብ የሚሆነው እደሱ ነው፡፡ ላትረዳው ትችል ይሆናል ወይም ደግሞ ያነበብከውን ሁሉንም ነገር ላታስታውሰው ትችል ይሆናል ዳሩ ግን ባነበብክ ቁጥር ለውጨኛው የሚተርፍ ውስጣዊ ንጽህና እያመጣህ መሆኑን አትዘንጋ የመንፈስ ሥራ እንደዚህ ነው በማለት አስተማሩት፡፡

(ከምስጋናው ግሸን ወልደ አገሬ)

https://www.tg-me.com/+PFGQTAhjadowNmM0
[              በብዙ መከራ  !              ]

በብዙ መከራ ፣ በብዙ ችግር ፣ በብዙ ምድራዊ ጉስቁልና ውስጥ ሆነው ፤ ረሀቡን ጥሙን ሁሉ እየታገሱ በፍጹም ትሕትናና በትሕርምት ያለ እረፍት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ፤ መንጋው በአራዊት እንዳይነጠቅ ፤ ነፍሳት ሁሉ ለእግዚአብሔር መንግሥት እንዲበቁና እንዲድኑ የሚተጉ እውነተኛ ንጹሐን አባቶቻችን ካህናትን የቤተክርስቲያን አምላክ በዕድሜ በጤና በቤቱ ያቆይልን። ያለ ካህናት አባቶቻችን ፣ ያለ ጠባቂና ያለ እረኛ ከመቅረት የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይሰውረን።

[  እጹብ የሚያሰኘው የአባቶቻችን ክብር !  ]

❝ ይህን እሳት ያለ ጉጠት ሳይፈራ የሚዳስስ ካህን እንደምን ያለ ነው ? ለዚህ ለመዳሰሱ አንክሮ ይገባል ! በመሰዊያ ላይ ይህን ሕብስቱን የሚፈትተው ካህን እንደምን ያለ ነው? ለዚህ አንክሮ ይገባል ! ... የእግዚአብሔርን በግ ለመሰዋት ጣቶቹ ወቅለምት የሆኑለት ይህ ካህን እንደምን ያለ ነው ? ! ለዚህ አንክሮ ይገባል !

አንደበቱም መናፍቃንን ከምዕመናን ለመለየት ሰይፍ ሆነለት ፤ ምዕመናንን ከአምላካቸው ደም አንድ የሚያደርጋቸው ይህ ካህን እንደምን ያለ ነው ? ! ለዚህ አንክሮ ይገባል ! ❞

[   አርጋኖን ዘሰኑይ   ]

𝕊𝕦𝕓𝕤𝕔𝕣𝕚𝕓𝕖 𝕒𝕟𝕕 𝕤𝕙𝕒𝕣𝕖

https://www.tg-me.com/+PFGQTAhjadowNmM0
"#እባክህን_ከእሳቱ_ላይ_አትውረድ"
  
አንድ ወንድም አባ ጴሜንን "ምከረኝ" ብሎ ጠየቀው። አባ ጴሜንም "ድስት በእሳት ላይ እያለ ምንም አይነት ተባይ ሊቀርበውና ሊያበላሸው አይችልም። ከእሳት ወጥቶ ሲቀዘቅዝ ግን ነፍሳት ሁሉ ለመግባትና ለማበላሸት ይቻላቸዋል። ክርስቲያንም ከመንፈሳዊ ተግባር ካልራቀ ጠላት የድቀት ምክንያት አያገኝበትም" አለው።

ወዳጄ ሆይ ሕይወት ቀዝቅዛብሃለችን? ከእሳቱ ወደ መሬት ወርደህ በርደሃልን? የሕያውነትህ ሙቀት እሳት በማጣት ተንዘፍዝፏልን? ድስት የተባለ ሰውነትህ ክረምት የሚያህል ጉድን ተሸክሟልን? ዙሪያ ገባህ ፀሐይ እንደማትወጣበት ምእራብ ጨለማን የሚጠራ ሆኗልን? ማንነትህ እሳት እንዳጣ ምግብ ጥቃቅን ነፍሳት በተባሉ ኃጢአቶች (ቁጣ፣ ቸልተኛነት፣ ስስት፣ አልታዘዝ ባይነት፣ ጭንቀት፣ ሁሉን የመናቅ ስሜት፣ ተስፋ መቁረጥ፣ ...) ተወርሮ፣ መዓዛ ቅድስና ተለይቶት እጅ እጅ ብሏልን? ሞቅ የሚያደርገው አጥቶ በዓለማዊነት ሻግቷልን? የተባዮች መጫወቻ፣ የተውሳኮች መቀለጃ ሆኗልን? እንግዲያውስ በቶሎ ወደ እሳቱ ውጣ፡፡

ወዳጄ ሆይ ሃይማኖት በተባለችና ከሰማይ በወረደች ልዩ እሳት (ሉቃ.12፥49) ላይ ተቀምጠህ የድስትነትህን ሙቀት መልስ፡፡ እምነት፣ ተስፋና ፍቅር (1ቆሮ.13፥13) በተባሉ ሦስት ጉልቻዎች ላይ በምቾት ተጥደህ የሕይወትህን የኃጢአት ብርድ አስወግድ፡፡ ንስሐ በተባለች ነበልባል ውበትነት የክረምትህን ጽልመት በምስራቃዊ በጋነት ድል ንሳ፡፡ በሥጋ ወደሙ ፍምነት ድስት የተባለ ሰውነትህን በከዊነ እሳትነት ቀድስ፡፡ እባክህን በቶሎ ወደ እሳቱ ውጣ፡፡

ሃይማኖት የተባለ እሳትን ተባይ አይቀርበውም፡፡ እምነት ተስፋና ፍቅር የተሰኙ ጉልቻዎችን ተውሳኮች ሽቅብ አይወጡአቸውም፡፡ የነበልባለ ንስሐን ብርሃንና ሙቀት ነፍሳተ ጽልመት መቋቋም አይችሉም፡፡ ስለዚህ በእሳቱ ላይ እስካለህ ድረስ (በመንፈሳዊ ተግባራት እስከጠነከርክ ድረስ) አንተ ሁሌም ከተባይና ከነፍሳት ብልሽት (ከአጋንንት) የራቅክ ነህ፡፡

ወዳጄ እባክህን ከእሳቱ ላይ አትውረድ፡፡ እሳቱ በደንብ ይነድ ዘንድ ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት የተባሉ እንጨቶችንና ምጽዋት የተባለ ጋዝን መጨመርህን እንዳትዘነጋ፡፡ እንዲህ ከሆነ ዘንዳ ድስትነት ሁሌም የሞቀ ይሆናል፡፡ እጅ እጅ ከማለት፣ ከመሻገትና የተባይ መጫወቻ ከመሆን ትድናለህ፡፡

ወዳጄ ሆይ እባክህን ከእሳቱ ላይ አይትውረድ፡፡

በኃጢአት "እጅ እጅ '' ከማለትና በበደል ከመሻገት እግዚአብሔር ይሠውረን! አሜን!

(ሕሊና በለጠ ዘኆኅተብርሃን)

https://www.tg-me.com/+PFGQTAhjadowNmM0
እምቢ ብሎ ማመስገን

የህይወታችን ክፍል ብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ ገብቶ ለምስጋና የማይጋብዝ ህይወት እያሳለፍን ይሆናል። ብዙ ጊዜ በምስጋና ፈንታ ማማረር በውዳሴ ፈንታ ማጉረምረም የህይወታችን መልክ ሆኖ ሊታይ ይችላል። አስተውሉ ለማመስገን ያለን ምክንያት እጅግ እልፍ ነው። ለቁጥርም የሚታክት ነው።

ጠላት እግዚአብሔር ላይ አጉረምራሚ እንድሆን በትጋት ይሰራል። ለዚህም ካለን ነገር ይልቅ ጉድለታችንን አጉልቶ ያሰየናል። ቁጭ ብለን ባዶ የሆነውን እንድንቆጥር በማድረግ ምስጋናችንን ከአንደባችን ይነጥቃል። አመሰጋኝ መሆን እንዳንችል አይናችንን ጉድለታችን ላይ እንድናደርግ ያደርጋል።

ከጠላት የትኩረት ቀጠና አይንን በማንሳት እግዚአብሔር ያደረገልንን ውለታ በማሰብ እና በማሰላሰል ጠላትን እምቢ ብሎ ማመስገን ይገባል። ብዙ ነገር ቢደራረብም እምቢ ብሎ እግዚአብሔርን ማመሰገን ንቁ መሆን ነው። የጠላት ሀሳብ ላይ መንቃት እና ምክሩን እምቢ ማለት ነው።

ተቆጥሮ ከማያልቀው ከእግዚአብሔር ምህረት፣ ይቅርታ፣ ቻይነት፣ እና አኗሪነት በላይ ትንሹ ክፍተት አይናችን ላይ እንዳይጎላ መጠንቀቅ ያሻል። የህይወት ጥቃቅን ክፍተቶች በጊዜያቸው መፈታታቸው  አይቀርም ነገር ግን ነገ ለሚቃና ነገረ ዛሬ በእግዚአብሔር ላይ ማጉረምረም ክስረት ነው።

የጠላትን ትኩረት እምቢ ማለት መቻል እና የማይነጥፈውን የእግዚአብሔር እጅ ተስፋ ማድረግ የክርስትና በረከት ነው። እርግጥ ነው ክፍተቱ ብዙ ነው የጎደለውም እንደዛው። ነገር ግን ያለንን ቆጥረን ጨርሰን ይሆን? ብር አይኖረን ይሆናል ነገር ግን ጤናን በብር እንኳን መግዛት ያቀታቸው ስንቶች ይሆኑ?

አዎ የከበሩ ማዕድናት በእጃችን የሉም በእጃቸው ባለው የከበረ ማዕድን ሰላም መለወጥ ያቃቸው እና ያላቸው ነገር ጤናን ሊያመጣላቸው ያልቻሉትን ስንቱ ይቁጠራቸው? አስኪ በዚህ ልክ ጥቂት የመሰለንን ነገር ግን ያለንን ውድ ነገር እናስተውል። ህይወት ጣዕም የሚኖረው በምስጋና ውስጥ እያለፉ ለመቀበል በመዘጋጀት ነው።

በማጉረምረማችን የሚለወጥ ምንም ነገር ባይኖርም ምስጋናችን ግን ከነገሮች በጎውን እንድንመለከትና እግዚአብሔር ላይ ያለን መተማመን እንዲጠነክር የማድረግ አቅም አለው። በሁኔታ ሁሉ እግዚአብሔርን ማመስገን እና አንተ ትክክል ነህ ማለት የህይወትን ማዓዛ ያውዳል።

ሁኔታውን እምቢ ብሎ እግዚአብሔርን እያዩ ማመስገን ይሁንልን። አሜን

ዲያቆን ተስፋ መሠረት
📆 ግንቦት 21 2016 ዓ.ም ተጻፈ

ይቀላቀሉ  ➟ @finote_tsidk
ድንግል ሆይ ወደ አንቺ መጥቶ ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ያለሽ መልአክ ዛሬም ወደ እኔ ይምጣ፡፡ ኃጢአት ያደቀቃት በኀዘን የተዋጠች ነፍሴን ከጸጋ የተራቆትሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ይበላት፡፡

ጌታ በእኔ ልብ እንዳይፀነስ ‘ያለ ኃጢአት መኖርን ስለማላውቅ እንዴት ይሆንልኛል?’ ብልም ወደ አንቺ የመጣው መንፈስ ቅዱስ ወደ እኔ በምሕረት ይምጣ፡፡ በእስራኤል ልጆች ሠፈር መና እንደወረደ የልጅሽ ምሕረት በእኔ ላይ ይውረድ፡፡

አንቺን ድንግልናን ከማጣት እንደ ጋረደሽ እኔን ከኃጢአት ይጋርደኝ፡፡ አንቺን አምላክን ለመውለድ ያጸናሽ አብ እኔን ልጅሽን በማመን ያጽናኝ፡፡ አንቺ በማሕፀንሽ ዘጠኝ ወር የፀነስሽውን ጌታ እኔ ለደቂቃዎች እንኳን በልቤ እንድፀንሰው ፍቀጂልኝ፡፡

የፀነስሁትን የኃጢአት ሃሳብ ከልቤ አውጥተሽ በሕሊናዬ ልጅሽ እንዲያድር ለምኚልኝ፡፡ ጌታን በእጆችሽ መሃል የያዝሽው ሆይ አንቺ ጌታን ለዓመታት ታቀፈሽው ነበር፡፡ እኔ ግን ለአንድ ቀን እንኳን ሰውነቴ ከኃጢአት አርፎ እሱን ብቻ ታቅፌ እንድውል ፍቀጂልኝ፡፡

እርግጥ ነው ወደ እኔ ልጅሽን ይዘሽ ስትመጪ እንደ ቤተልሔም የእንግዶች ማደሪያ የእኔም ልብ የብዙ እንግዳ ኃጢአቶች ማደሪያ ነውና ልጅሽን ለማስተኛት ቦታ የለኝም ብዬ የልቤን በር ልዘጋብሽ እችላለሁ፡፡

በሩን ብዘጋውም ግን ልጅሽ እንደሆነ ‘በደጅ ቆሞ ማንኳኳት’ እንደማይሰለቸው አውቃለሁ፡፡ ራእ.፫፥፳  እኔ ፈቅጄ ባልከፍትለትም እንኳን የድንግልናሽን ማኅተም ሳይከፍት እንደተወለደ የእኔን የተዘጋም ልብ ሳይከፍተው መግባት አይሳነውም፡፡

ስለዚህ ዐመፄና እምቢታዬን ቸል ብለሽ ለልጅሽ ማደሪያ አድርጊኝ፡፡ አንቺ እርሱን ከወለድሽ ወዲያ በታተመ ድንግልና ጸንተሽ እንደኖርሽ ለልጅሽ ማደሪያ ሆኜ ለሌላ የኃጢአት ፅንስ ዳግም ማደሪያ እንዳልሆን ነፍሴን አትሚልኝ፡፡

የወለድሽው መድኃኒት እኔን ዙፋኑ አድርጎ ቢቀመጥ ሰዎች በእኔ እቅፍ ስላለ ብቻ በእኔ ምክንያት እንደ ሰብአ ሰገል እንደሚሰግዱለት በአንቺ ሲሆን አይቻለሁና ሰዎች በእኔ ምግባር ምክንያት ፈጣሪን መስደብ ትተው እጅ መንሻ ያቅርቡለት፡፡

ለልጅሽ በቀረቡ ሥጦታዎች ተከብቤ ከአንቺም ጋር ፦ ‘ጌታ ሆይ ለአንተ የሚሰግዱልህ ሰዎች ዙሪያዬን ከበቡኝ ፤ ለአንተ በቀረቡ ሥጦታዎችም ዙሪያዬን ታጠርኩ’
ብዬ ላመስግነው፡፡

ድንግል ሆይ አንቺን ያሳደደሽ ሔሮድስ እኔን የማያሳድደኝ ጌታ በእቅፌ ስለሌለ ነው፡፡ እኔ በልቤ ያነገሥሁት ‘የተወለደውን የአይሁድ ንጉሥ’ ስላልሆነ ሔሮድስ ከእኔ ጋር ጠብ የለውም፡፡ የሔሮድስን ሥልጣን አደጋ ላይ የሚጥል ንጉሠ ሰላም በእኔ እቅፍ የለም፡፡ አሁን ግን ፍቀጂልኝና ሔሮድስን ማስደሰት ትቼ ልጅሽን በልቤ ልቀበለው፡፡

የልቤን ክርስቶስ ሔሮድስ እንዳይገድልብኝ እኔም እንደ አንቺ ልሰደድ፡፡ እሱን አቅፌ መከራ ቢደርስብኝ እንኳን ጽናት እንደማገኝ በአንቺ አይቻለሁና የልጅሽን ፍቅር በልቤ አኑሪልኝ፡፡ ለሦስት ቀናት ከፊትሽ ዞር ቢል ፍለጋ የወጣሽዋ ድንግል ሆይ ከእኔ ሕይወት ልጅሽ ከተሠወረ ቆይቶአልና ያለ እርሱ መሰንበት የማልችል የፍቅሩ ምርኮኛ አድርጊኝ”

Deacon Henok Haile
#የብርሃን_እናት - ገፅ 305-308

@finote_tsidk ♻️ @finote_tsidk
Forwarded from  አትሮንሰ ተዋህዶ ( Atronise Tewahdo )  (𓃬 𝔏𝔢𝔬 𓃬)
“ክርስቲያን” ተብለህ መጠራትህ ዋስትና አይኾንህም፤ ዋስትና የሚኾንህ …

በመንገድ ዳር ላይ ዘርን የሚዘሩ ሰዎች ምንም የሚያገኙት ጥቅም እንደ ሌለ ኹሉ፥ እኛም ለልጅነታችን የሚገባ’ ምግባር ከሌለን ክርስቲያኖች ተብለን ከመጠራት የምናገኘው በቁዔት የለም፡፡ ይህ እንዴት ይኾናል የምትለኝ ከኾነም የጌታችን ወንድም የተባለው ያዕቆብን ምስክር አድርጌ እነግርሃለሁ፡፡ እርሱ፡- “ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው” ብሎአልና (ያዕ.2፡17)፡፡ ስለዚህ ለእኛ (ለክርስቲያኖች) ምግባር መያዝ ግዴታ ነው፡፡ ምግባር ከሌለን ግን “ክርስቲያን” የሚለው ስም ለእኛ የሚፈይደው ምንም ነገር የለም፡፡ በዚህ ተደነቅህን? እንኪያስ ንገረኝ ! በዓውደ ውጊያ የማይሳተፍ፣ ለሚመግበው ንጉሥም የማይዋጋ ከኾነ አንድ ወታደር ወታደር ተብሎ ቢጠራ ምን ጥቅም አለው? ለንጉሡ ክብር የማይዋጋ ከኾነስ ወታደር ተብሎ ባይጠራ ይሻለዋል፡፡ ይህ ሰው በንጉሡ የሚመገብ ኾኖ እያለ፥ ነገር ግን ንጉሡ በጠላቱ ላይ ድል እንዲያደርግ የማይዋጋ ከኾነ እንዴት ከቅጣት ሊያመልጥ ይችላል? ንጉሡን ምሳሌ አድርጌ ልናገረው የፈለግሁትስ ምንድን ነው? ልለው የፈልገሁት እግዚአብሔር በትንሹ ስለ ገዛ ነፍሳችን እንድንጠነቀቅ (ምግባር መያዝ እንድንችል) ኃይል (ዓቅም) ሰጥቶናል ነው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ንስሐና ምጽዋት መጽሐፍ
#ይቀላቀሉ

@finote_tsidk ♻️ @finote_tsidk
"ማንነትህን ማወቅ"

ተወዳጁ ወንድሜ ሆይ! ኃይለኛ ነኝ ብለህ ታስባለህን? ካሰብህ ይህን ኃይልህን ከየት አመጣኸው? አንተ አመድና ትቢያ ጎስቋላና ምስኪን ስለሆንህ ይህ ኃይል የአንተ አይደለም። ይህ ኃይል ከሌላ ሰው ያገኘኸውም አይደለም ከእግዚአብሔር እንጂ።
ክብርና ምሥጋና ለእርሱ ይሁንና ኃያል እርሱ ብቻ ነው፡ ኃይልም ሁሉ የሚገኘው ከእርሱ ብቻ ነው። ያንተስ ኃይል ከእግዚአብሔር አይደለምን? ከሆነ ለምን ትታበያለህ? ለምንስ ትኩራራለህ? የእግዚአብሔርንስ ኃይል እርሱን ለማገልገል ካልሆነ ለሌላ ለምን ታውለዋለህ? ስለዚህ ሊከበር የሚፈልግ ቢኖር በእግዚአብሔር ይክበር። እርሱ ከክብር ሁሉ በላይ የሆነና ለምንከብርበት ነገር ሁሉ ምንጩ ነውና። በእግዚአብሔር ኃይለኛ ሆነህ በተፈጥሮህ ደካማ ብትሆን ከሐዋርያው ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር እንዲህ በል። "እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ። ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና።" 2ኛ ቆሮ 12:9-10

(ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ)

https://www.tg-me.com/+PFGQTAhjadowNmM0
ቅዱስ እንጦንስ እንዲህ ይመክራል፦"ደስታና ሰላምን የሚነጥቁ ሦስት የሰይጣን ወጥመዶች አሉ፦
➛ ስላለፈው መጸጸት፣
➛ ስለሚመጣው መጨነቅ እና
➛ ስለ ዛሬው አለማመስገን ናቸው"

@Finote_tsidk @Finote_tsidk
#የፍቅሩ_ምክንያት

እግዚአብሔር ሰውን ያፈቅራል ስንባል ሰምተናል። ልክ ነው በተግባርም አይተነዋል። ይሁን እንጂ በምን ምክንያት ነው ያፈቀረን? ምን ምክንያት ሆኖ ነው የወደደን? እስኪ ወንድሜ ለተወሰነ ሰከንድ ይህን ጥያቄ እራስህን ጠይቅ አንቺም እህቴ እራስሽን ጠይቂ። ...... ለምን ወደድከኝ...በምን ምክንያት ነው ያፈቀርከኝ

እናንተ በእግዚአብሔር ስለመወደዳችሁ ምክንያት ሊሆን የሚችል ከእናንተ ምን በጎ ነገር አገኛችሁ። እግዚአብሔርማ ከዚህ ነገሬ የተነሳ ሊወደኝ ይገባል የምትሉት አንዳች ምክንያት አገኛችሁን? አዎ አገኝቻለሁ ካላችሁ ዋሳችሁ።

እግዚአብሔር እኛን የወደደን በእኛ ዘንድ ለእርሱ ባህሪ ተስማሚ የሆነ ነገር ተገኝቶብን ሳይሆን እንዲሁ ነው። የወደደን እንዲሁ ነው።  “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን #እንዲሁ ወዶአልና።”(ዮሐንስ 3፥16)

እግዚአብሔር እኔን በመውደዱ ውስጥ እኔ ያዋጣሁት ነገር የለም ማለት እጅግ አስተዋይነት ነው። ለእርሱ ፍቅር እኛ የምናዋጣው ነገር ቢኖር ኖሮ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ መዋጮ ልክ ከፍ እና ዝቅ ይል ነበር። እናም እግዚአብሔር ከራሱ በሆነ መውደድ የሚወደን አምላካችን ነው።

አንዳንዴ ስራዎቻችን መጥፎ ሲሆኑ እግዚአብሔር የጠላን ይመስለናል። ወይም ድርጊታችን ልክ ሳይሆን ሲቀር የእግዚአብሔር ፍቅሩ የሚቀዘቅዝ ይመስለናል። አልያም በጎ ስንሰራ፣ ሰው ስንረዳ፣ ሰው ስናገዝ፣ እግዚአብሔር የሚወደውን ነገር ስናደርግ፣ መንፈሳዊ ህይወታችን ያመረ ሲሆን የእግዚአብሔርን የፍቅሩ ግለት የሚጨመርን ይመስለናል።

የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ምክንያት ስላልመጣ በእኛ ምከንያት አይጸናም የሚጸናው እርሱ እግዚአብሔር እራሱ ጽኑ ስለሆነ ነው። አትሳሳቱ እግዚአብሔር የሚወደኝ እንዲህ ሳደርግ ነው አትበሉ። እግዚአብሔር እኛ ጠላቶቹ ሆነን ሳለ የፍቅሩን ሃያልነት ገለጠልን እንጂ ወዳጁ ስለነበርን አይደለም። “ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።”( ሮሜ 5፥8)

የእግዚአብሔር ፍቅር እንደ ሰዎች ፍቅር መልክ እና ሁኔታ እያየ አይጎርፍም ይልቁንም ጠላት የሆነውን ያቀርባል እንጂ። እግዚአብሔር በደለኞቹን እኛን ማዳኑ የመውደዱ ማብራሪያ ነው ይህም ከእኛ በሆነ በጎ ምግባር ላይ የተመሰረተ አይደለም። “ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፥ ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም፤ ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፥” (2ኛ ጢሞቴዎስ 1፥9)

ፍቅር ምክነያት ይፈልጋል የምንለው ፍቅሩ ሰዋዊ ሲሆን ነው ምከንያቱም የሰው ልጅ ስለቀረብነው የሚያፈቅር ስለራቅነው ደግሞ የሚረሳ ወረተኛ ስለሆነ ነው።  እግዚአብሔራዊ ፍቅር ግን ከእራሱ ከእግዚአብሔር የሚመነጭ የፍቅር ውሃ ነውና ሁሉን ያረሰርሳል። የእግዚአብሔር ፍቅር ምክንያት አልባነት ከተሰወረበት ሰው ይልቅ አላዋቂ ሰው አይኖርም።

ስናለማም ስናጠፋም
ፍቅሩ ግን ከቶ አይጠፋም
ስናበጅም ሳናበጅም
ፍቅሩ ጭራሽ አያረጀም
ስናደርግም ሳናደርግም
ፍቅሩ ግን አይዋዥቅም
ሰንቀርብም ስንርቅም
ፍቅሩ ግን ፈቅ አይልም
ስንጨልምም ስንበራ
የእርሱ ፍቅር ያው ጠንካራ
ስንሰጥም ሳንሰጥም
የእርሱ ፍቅር ሰው አይመርጥም
ስንሄድም ስንመጣም
ፍቅሩ ላይ ለውጥ አይመጣም
ስንስቅም ስንከፋም
ድርጊታችን የሱን ፍቅር አያፋፋም
በሁኔታችን ከፍ አይልም
ወይም ደግሞ ዝቅ አይልም
ሁሌም ጽኑ የእርሱ ፍቅር
ለዘላለም ለዘወትር

ያለ ምክንያት ስለሚፈሰው ፍቅርህ አማኑኤል ሆይ ተመስገን።

ዲያቆን ተስፋ መሠረት
📆 ሚያዝያ 21  2015 ዓ.ም ተጻፈ

♜ᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓ♔ᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓ♜
@Finote_tsidk @Finote_tsidk
@Finote_tsidk @Finote_tsidk
♜ᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓ♔ᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓᚓ♜
[ የተዘጋች ገነት የታተመች ጉድጓድ ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

❝ ሕዝቅኤል ፦ "ድንቅ በሆነ ታላቅ ቁልፍ የተዘጋች ደጅ በምሥራቅ አየሁ፡፡ ከኃያላን ጌታ በቀር ወደ እርሷ ገብቶ የወጣ የለም፡፡" አለ፡፡ [ሕዝ.፵፬፥፩] ይህ የተዘጋ በር የድንግልናዋ ዜና ነው፡፡ " እግዚአብሔርም ፦ ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፥ ሰውም አይገባበትም፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል። " [ሕዝ.፵፬፥፩]

ሰሎሞንም ፦ "የተዘጋች ገነት የታተመች ጉድጓድ [ ያንቺ መንገዶች ናቸው ] አለ፡፡ " እኅቴ ሙሽራ የተቈለፈ ገነት ፥ የተዘጋ ምንጭ የታተመም ፈሳሽ ናት።" [ መኃ.፬፥፲፪ ]

በገነት አካባቢ ምን ይገኛል ? የሚጣፍጥ ፍሬ አይደለምን ? የሚጣፍጠው ፍሬ ምንድን ነው ? የእናቱ የድንግል ማርያም ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለምን ? የተዘጋች ገነት ማለትስ በድንግልና ቁልፍ በተዘጋች በአንቀጸ ሥጋዋ ይተረጎማል፡፡ ዳግመኛ ከጉድጓድ ከሚጣፍጥ ውሃ በስተቀር ምን ይገኛል ? የሚጣፍጥ ውሃ ምንድን ነው ? በወንጌል ፦ " ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ። " [ዮሐ.፯፥፴፯] ያለው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ የታተመች ጉድጓድ የተባለው የንጽሕይት እናቱ የድንግልናዋ ኃይል ነው፡፡ ሁሉም ነቢያት ስለ ሥጋዋ በር ፦ " የተዘጋች ፥ በድንግልና የታተመች" ብለዋታልና፡፡

ለቀደሳትና ላነጻት [ በንጽሕና ለጠበቃት ] ለእግዚአብሔር ለዘላለም ምስጋና ይሁን፡፡ ❞

[ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ]

†                       †                         †

@Finote_tsidk ♻️ @Finote_tsidk
"እውነተኛ ሐሴት ትፈልጋላችሁን? እንግዲያውስ ለድሆች መጽውቱ፤ ክርስቶስን ወደ ቤታችሁ ጥሩት፡፡ ይህን ስታደርጉ ማዕዱ ቢነሣም ሐሴቱ አይነሣም፤ ይቀጥላል እንጂ፡፡ በተለይ ደግሞ በዚህ በወርሐ ጦም ይህን አብዝታችሁ አድርጉት።"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@Finote_tsidk @Finote_tsidk
"ወደ አንተ እመጣለሁ"

በቅዱሳን ኹሉ አንደበት ምስጋና የተገባው እግዚአብሔር ሰውን ለማዳን ከሰማያት እንደወረደ (ማለት ሰው እንደሆነ) እንዲሁ የማዳኑን ሥራ ፈጽሞ (ፍጹም አድርጎ) ወደ ሰማያት በምስጋና ዐረገ፡፡ ሰው ሲሆን ረቂቁ ገዝፎ፤ የማይታየው ታይቶ ነው፡፡ ሲያርግ ነሥቶ የተዋሐደውን ሥጋ ሳይለቅ ነው፡፡ መድኅን ክርስቶስ ወደ ሰማያት ሲያርግ ተዋሐደውን ሥጋ በምድር ላይ አልተወውም፡፡ አስቀድሞ በወንጌለ ዮሐንስ “ወደ አንተ እመጣለሁ” (ዮሐ 17፡ 11) ብሎ የተናገረው በዕርገቱ እውን ሆነ፡፡ ዳግመኛም “ወደ አንተ እመጣለሁ” ብሎ የተናገረው፤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በምትሠዋው መሥዋዕት (እርሱም ክርስቶስ ነው) ወደ አንተ እቀርባለሁ ማለት እንደሆነ እንረዳለን፡፡ ዳግመኛም በዕርገቱ ምክንያት እኛንም ይዞን ዐረገ፤ ይኸውም ባሕርያችንን (ሰውነትን) ነው፡፡ ስለሆነም በቤተ ክርስቲያን ጸሎት ካህኑ “ልቡናችሁን ከፍ ከፍ አድርጉ” ሲለን፤ “ብነ ኀበ እግዚአብሔር አምላክነ፤ በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ አለን” ብለን እንመሰክራለን (መጽሐፈ ምሥጢር፤ የዕርገት ምንባብ)፡፡ ይህ የሆነው በክርስቶስ በዕርገቱ ነው፡፡ የእርሱ ዕርገት የምዕመናንን (ቅዱሳንን) ዕርገት የሚያሳውቅ፡ የሚያረጋግጥ ሆነ፡፡ ከሰማያት በአምላክነቱ ኀይል በረቂቅ ምሥጢር ወረደ (ሰው ሆነ)፤ ከምድር በአምላክነቱ ኀይል ያዳናቸውን ምርኮ ይዞ ወደ አባቱ ዐረገ፡፡ ምስጋናው ገነት የሆነችለት ቅዱስ ዳዊት “ዐረገ ውስተ አርያም ፄዊወከ ፄዋ፡ ወወሀብከ ጸጋከ ለእጓለ እመሕያው፤ ወደ ሰማይ ዐረግኽ፡ ለሰው ልጆችም ጸጋን (መንፈስ ቅዱስን) ሰጠህ” (መዝ 67: 18) ብሎ አስቀድሞ ተናገረ፡፡ በክርስቶስ መስቀል ድኅነትን የተቀበሉ፤ መቀበላቸውን እስከ መጨረሻይቱ ሕቅታ ድረስ እንዲያጸኑ የሚያደርጋቸው መንፈስ ቅዱስ በክርስቶስ ዕርገት የወረደ ጸጋ ነው፡፡ ክርስቶስ ጸጋ ሆኖ እንደተሰጠን (ለሕማም እንደተሰጠልን)፤ እንዲሁ መንፈስ ቅዱስንም ለሃይማኖት መጽናት፤ ለምግባር መቃናት፡ ለትሩፋት ሥምረት ለቤተ ክርስቲያን (ለምዕመን) ጸጋ ሆኖ ተሰጠ፡፡ በእውነት ከክርስቶስ ያልሆነ፤ ከመንፈስ ቅዱስ ዕድል ፈንታ የለውም፡፡ ከክርስቶስ ሃይማኖት፤ ከእርሱ ጋር ሕማምና መከራን ከመቀበል ያልሆነ፤ ከትንሳኤውና ከዕርገቱ አይሆንም፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ ሰላምና ደስታ ጋርም ዕድል አይኖረውም፡፡ መንግሥተ ሰማያት የመንፈስ ቅዱስ ሰላምና ደስታ ናትና፡፡ የክርስትና ምግባር ሁሉ መደምደሚያው እውነተኛውን የልብ ሰላምና ደስታ ማግኘት ነውና፡፡ ጸጋ ሁሉ ፍጹም ሆና ለቤተ ክርስቲያን እንድትሰጥ መድኅን ክርስቶስ ወደ ሰማያት ዐረገ፡፡ ዘወትር በጸሎት እና በንስሐ ወደ ሰማይ መውጣትን የተለማመደ፤ በእውነት ወደ እግዚአብሔር ማረግ ይሰጠዋል፡፡ በሃይማኖትና በምግባር በመታመኑ በጸጋ ያደረበት ክርስቶስ ወደ ሰማያዊ አባቱ ያሳርገዋል፤ በዚያም በብዙ ማደሪያዎች ውስጥ ያሳድረዋል፡፡ በአምላካዊ ሥልጣኑ ሰውነታችንን ከታችኛይቱ ሲዖል ያድናት፤ በምሕረቱም ወደ አባቱ መንግሥት ያሳርጋት፡፡

በመልካሙ ዋሉ !

@Finote_tsidk @Finote_tsidk
2024/06/16 17:23:35
Back to Top
HTML Embed Code: