Telegram Web Link
8
ይህ ሁሉ ትርፍ በሰባት ደቂቃ ደቂቃ ብቻ!
5 ደቂቃ: ‐ ሱረቱል‐ሙልክ = ከቀብር ቅጣት ይጠብቃል
1 ደቂቃ: ‐ የሱረቱል‐በቀራ የመጨረሻዎቹ ሁለት አንቀጾች = ለሊቱን ከሰይጣን ወይም ከሚያስከፋ ነገር ይጠብቃል
1 ደቂቃ: ‐ ሰዪዱል‐ኢስቲግፋር = ሌሊቱን ሞቶ ያደረ ጀነት ገባ!
19
19👍5
«ኢብራሂም ኢብኑ አድሀም በሱፍያን አስ‐ሰውሪይ አጠገብ አለፉ። ከባልደረቦቻቸው ጋር ተቀምጠው ነበር። ሱፍያን ለኢብራሂም:‐
«ወደኔ ቅረብ። ዒልሜን ላንብብልህ።» በማለት ግብዣ አቀረቡ።

ኢብራሂም ግን:‐ «እኔ በሦስት ነገሮች ተጠምጃለሁ። [አልችልም]» ብለው ትተዋቸው አለፉ።

ሱፍያን ባልደረቦቻቸውን በመቆጣት:‐ «በምን እንደተጠመዱ ለምን አትጠይቋቸውም ነበር?!» በማለት በባልደረቦቻቸው ታጅበው ኢብራሂም ወዳለፉበት ተከትለው ሄዱ።

ከዚያም:‐ «ዒልምን ከመማር ይልቅ በሦስት ነገሮች ተጠምጃለሁ እያልክ ነው። እነዚህ ሦስት ነገሮች ምንድን ናቸው?!» በማለት ጠየቁ።

ኢብራሂም እንዲህ መለሱ:‐
«⚀ አላህን በሰጠኝ ፀጋ በማመስገን፤
⚁ ያለፈው ኃጢኣቴን አላህ እንዲምረኝ በመለመን፤
⚂ ለሞት ዝግጅት በማድረግ።»

ሱፍያን በአግራሞት ተሞልተው:‐ «ሦስቱ ነገሮች እጅግ የሚደንቁ ናቸው!» እያሉ ተመለሱ።»
📚 ታሪኹ ባጝዳድ፥ ቅጽ 4፥ ገፅ 357
👍2719
Channel photo updated
ትርፍ ዒባዳዎችን መለማመድ ቀስ በቀስ መሆን አለበት። በሰፊው እና ዘውታሪ ማድረግ በሚቸግረን መልኩ ባንጀምረው መልካም ነው።
«የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ዘንድ ተወዳጁ ስራ ጥቂትም ቢሆን ዘውታሪው ነው።»
:
ዱሓ ሶላት እናስለምድ። ሁለት ረከዐም ቢሆን ነገርግን ቋሚ በሆነ መልኩ።
ዝርዝር ማንበብ ከፈለጉ ተከታዩን ሊንክ ይጫኑ:‐
https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh/1033
39👍8
የተባረከ ጁሙዐ ይሁንልን!
31👍2
💫 በእርግጥ እድሜህ ያንተው ነው!
በፈለግከው ነገር አሳልፈው! ነገ በቂያማ በሂሳቡ ገበታ ላይ ለመተሳሰብ እንጂ ወዳንተ ተመልሶ አይመጣም!

:
«ስለ አራት ነገሮች ሳይጠየቅ የአንድም ሰው እግር ፈቀቅ አይልም:‐
❶ እድሜውን በምን እንዳሳለፈው
___
___
___።» ተፈቃሪያችን [ﷺ]
:
ባዶ ቦታዎቹን እናንተ ሙሏቸው።
😢193
Audio
📚አል‐አዝካር ሚን ከላሚ ሰይዲል‐አብራር
📗 ክፍል 12:‐ ልብስ ሲያወልቅ የሚባል ዚክር ‐ እቤቱ ሲገባ የሚባል ዚክር
📆 ጥቅምት 21/ 2018 ዓ. ል.
5
ኢማም ሱፍያን አስ‐ሰውሪይ [ረሒመሁላህ] እንዲህ ብለዋል:‐
«በነፍሱ ላይ ሦስት ነገሮችን ያገኘ ሰው ስኬታማነትን ይፍረድላት:‐
❶ አሸናፊና ኃያል የሆነውን አላህ መፍራት፤
❷ የተመረጡትን ነቢይ ማክበር እና
❸ ምርጥና መልካም ሰዎችን ማፈር [ሐያእ ማድረግ]።»
📚 ዐጃኢቡል‐ቁርኣን፥ ኢማም ፈኽሩዲን ራዚ
18👍18
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል:‐
«ይህ [ሐላል] ገንዘብ ጣፋጭ ነው። [የአላህን] ደንብ ጠብቆ ለያዘው እና ደንቡን ጠብቆ በተገቢው ቦታ ላዋለው ሰው [ለአኺራ] እንዴት ያለ አጋዥ ነው!?»
:
ገንዘብ በራሱ እርኩስ አይደለም። በራሱም ፀጋ አይደለም። መልካም ተሰርቶበት አኺራ የሚሸመትበት ሲሆን ግን 'ዱንያው' ራሱ 'የአኺራው' ማዕረግ ይሆናል። በስሜት ከነጎዱ፣ በፍቅሩ ከተለከፉ እና ለማንበር ካከማቹት ግን ወደር የሌለው ጥፋት ነው!
እስኪ ሶላቱ #ዱሓ እንስገድ። ከ5‐10 ደቂቃ ቢወስድብን ነው! ባረከላሁፊኩም!
47👍7
2025/11/06 07:21:36
Back to Top
HTML Embed Code: