ጁሙዐ እና ዒድ
ዒድ በጁሙዓ ቀን ከዋለ ጁሙዓዎች መደበኛውን ቀጠሮ ተከትለው በየመስጂዱ ይሰገዳሉ።
ስለዚህ ማንኛውም ሙስሊም ዒዱን በጀመዐ ከሰገደ በኋላ ጁሙዓውንም እንደተለመደው ቢያስከትል እጅግ የተመረጠ ነው። ነገርግን ሁለቱንም ሶላቶች ማስገኘት የማያስችል ምክንያት ካለው ጁሙዓን ማስበለጥ አለበት። ምክንያቱም ጁሙዐ የነፍስ ወከፍ ግዴታ ነው። ጁሙዓን ግዴታ የሚያደርጉ መስፈርቶች ተሟልተው እስከተገኙ ድረስ ዒድ ስለሆነ ተብሎ አይተውም።
• የጁሙዐ ሶላት ብይን
የጁሙዐ ሶላት ግዴታ [ፈርድ] መሆኑ የልሂቃን ስምምነት ያለበት ነጥብ መሆኑ ይታወቃል። በሸሪዓዊ ምክንያት ካልሆነ በቀር ጁሙዐን መተው ወንጀል ነው። አላህ እንዲህ ብሏል: ‐
{ يا أَيُّهَا الَّذينَ آمَنوا إِذا نودِيَ لِلصَّلاةِ مِن يَومِ الجُمُعَةِ فَاسعَوا إِلى ذِكرِ اللَّهِ وَذَرُوا البَيعَ ذلِكُم خَيرٌ لَكُم إِن كُنتُم تَعلَمونَ }[ الجمعة: ٩ ]
«እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ፡፡ መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነው።»
ከሰይዲና ጃቢር ኢብኑ ዐብዲላህ [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንደተዘገበው የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምን በጁሙዐ እለት ጁሙዐ ሶላትን የመስገድ ግዴታ አለበት። ህመምተኛ፣ በጉዞ ላይ ያለ፣ ሴት፣ ህፃን እና ባርያ ሲቀር። ከዚህ ውጪ በጨዋታ እና በንግድ የተብቃቃን ሰው አላህም ከርሱ ይብቃቃል። አላህን እጅግ የተብቃቃ [ሀብታም] እና ምስጉን ነው።» በይሀቂይ፣ ዳረቁጥኒይ እና ኢብኑ አቢ ሸይባ ዘግበውታል።
ጁሙዐ በኢስላም ውስጥ ያለው ስፍራ ትልቅ ከመሆኑ የተነሳ የአላህ መልክተኛ [ﷺ] አጥብቀን እንድንይዛት አደራ ብለዋል። ጁሙዐን ከመተውም በጥኑ አስጠንቅቀዋል። ጁሙዐን የተወ ሰው አላህ ቀልቡን ያሽግበታል። ከዝንጉዎችም ይሆናል በማለት አስፈራርተዋል።
ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ሰዎች ጁሙዐን ከመተው ይታቀቡ። ወይም አላህ ቀልባቸውን ያሽገዋል። ከዝንጉዎችም ይሆናሉ።»
ይህ ሐዲስ ጁሙዐ ግዴታ መሆኑን ከማስረዳቱ በተጨማሪ ያለ ምክንያት ጁሙዐን ማሳለፍ የሚያስከትለውን አደጋም ይበይናል።
• የዒድ ሶላት ብይን
የዒድ ሶላት ጥብቅ ሱና ነው። ግዴታ [ፈርድ] አይደለም። ይህ የማሊኪዮች፣ የሻፊዒዮች እና የአብዝሃኞቹ ልሂቃን ሃሳብ ነው። ሐነፊዮች እና ኢማም አሕመድ ዘንድ አንዱ ዘገባም ይኸው ነው። ሐነፊዮች ዘንድ በተገኙ ሌሎች ዘገባዎች ደግሞ የዒድ ሶላት ዋጂብ ነው ተብሎ ይታመናል።
• ሁለቱ ዒዶች ሲጋጠሙ
የጁሙዐ ቀን ሳምንታዊ ዒድ ነው። ከሁለቱ ዒዶች አድሓ እና ፊጥር ጋር የሚጋጠምበት ሁኔታ ይፈጠራል። እናም በዚህ ጉዳይ ላይ እንዲህ እንላለን።…
ጁሙዓ ሶላት ፈርድ ነው። የዒድ ሶላት ደግሞ ሱና ነው። ሱና ፈርድን አያስቀርም። የፈርድን ቦታም አይተካም።
በአላህ መልክተኛ [ﷺ] ዘመን በጁሙዓ ቀን ዒድ ውሎ ያውቃል። የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ሁለቱንም ሶላቶች ሰገዱ እንጂ አንዱን ለአንዱ ብለው አልተዉትም። ሁለቱም ሶላቶች ላይ ያሉትን ኹጥባዎችም አልተዉም። ዒድንም ሆነ ጁሙዐን አልተዉም።
ይህ በሐዲስ መዛግብት ላይ በግልፅ የታወቀ እና አብዝሃኞቹ ልሂቃን የተጓዙበት መዝሀብ ነው። ከአራቱ መዝሀቦች ሐነፊዮች፣ ማሊኪዮች እና ሻፊዒዮች የሚያምኑበት መንገድ ነው። ሐንበሊዮች ዘንድም በከፊል የተዘገበ ሃሳብ ነው።
በእርግጥ የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ዒድና ጁሙዐ በተጋጠሙ ጊዜ ጁሙዐን መተው መፍቀዳቸውን የሚያመለክት ዘገባ አለ። የፈቀዱት ግን በልቅ ሳይሆን "ዓዋሊ" የሚሰኘው የመዲና ዳርቻ ላይ ከነቢያዊው መስጂድ ርቆ ለሰፈረው መንደር ነዋሪዎች ብቻ ነው። ለነርሱ የፈቀዱትም የዒድ ሶላት ከአላህ መልክተኛ [ﷺ] ጋር ሰግደው ወደ ቤት ከተመለሱ በኋላ በድጋሚ ለጁሙዓ መመለስ እጅግ ከባድ ስለሆነባቸው ነበር። ስለዚህ የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ለዓዋሊ ነዋሪዎች በመንደራቸው ባሉበት በጁሙዐ ፈንታ ዙህር እንዲሰግዱ ፈቀዱላቸው። ንግግራቸው እንዲህ ተዘግቧል: ‐
«በዚህ ቀናችሁ ላይ ሁለት ዒዶች ተሰብስበዋል። የፈለገ ሰው ከጁሙዐ ሶላት [የዒድ ሶላት] ያብቃቃዋል። እኛ ግን ጁሙዐ እንሰግዳለን።» አቡዳዉድ ዘግበውታል።
ይህንን ሐዲስ አብዝሃኞቹ ልሂቃን ‐ሐነፊዮች፣ ማሊኪዮች እና ሻፊዒዮች‐ ለዒድ ሶላት ከመዲና ውጪ ካሉ ስፍራዎች ለመጡ ሰዎች የተነገረ መሆኑን ያምናሉ። እነዚህ በመዲና ዙርያ ከመዲና ውጪ የሚኖሩት ሰዎች ቀድሞውንም ጁሙዓ መስገድ ግዴታ አይሆንባቸውም ነበር። ምክንያቱም የተገነባ ከተማ ውስጥ የማይኖሩ ሰዎች በመሆናቸው ለጁሙዐ ግዳጅ የሚያበቁ መስፈርቶችን መጀመሪያም አላሟሉም ነበር። ስለዚህ ዒድን ከአላህ መልክተኛ [ﷺ] ጋር ከሰገዱ በኋላ እስለ ጁሙዓ ሶላት ድረስ መጠበቅ በጣም ያስቸግራቸዋል። ወደ ቤት ተመልሰው ጁሙዐ ሲደርስ ይመለሱ ቢባልም በጣም ከባድ ይሆናል። በመሆኑም የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ጁሙዓን መተው ፈቀዱላቸው።
የማሊኪዮች እውቅ ልሂቅ አል‐ቃዲ ዐብዱል‐ወሃብ አል‐ማሊኪይ "አልመዑና ዐላ መዝሀቢ ዓሊሚል‐መዲና" በተሰኘው መጽሐፋቸው ገጽ 311 ላይ እንዲህ ይላሉ: ‐
«ጁሙዐ እና ዒድ ከተጋጠመ አንዱ በሌላው አይወድቅም። ይኸውም የዒድ ሶላት ላይ የተገኘ ሰው ጁሙዓን መተው ይችላል ከሚሉ ሰዎች የተለየ ሃሳብ ነው። አላህ በቁርኣን እንዲህ ብሏል: ‐

የአላህ መልክተኛም [ﷺ] «ጁሙዐ [መስገድ] በሙስሊም ላይ ሁሉ ግዴታ ነው።» ብለዋል።
በተጨማሪም የጁሙዐ መስፈርቶች እስከተሟሉ ድረስ ጁሙዐን መስገድ ግዴታ ነው።»
የሻፊዒዮቹ እውቅ መጽሐፍ "ሙጝኒል‐ሙሕታጅ" ቅፅ 1፥ ገጽ 539 ላይ እንዲህ ይላል: ‐
«ዒድ በጁሙዐ ቀን ከዋለ [ከከተማ ዳር የከተማው] አዛን የሚሰማቸው ሰዎች ዒድ ሊሰግዱ ወደ [ጁሙዐው] ከተማ ከመጡ ከዚያም ወደ ቤታቸው ተመልሰው በድጋሚ ወደ ጁሙዐ ሶላት ለመምጣት ቢሞክሩ ጁሙዓ ሊያመልጣቸው የሚችልበት ያህል ችግር ከወደቁ ለዚያ ቀን ጁሙዓውን ትተው ወደ ቤት መመለስ ይችላሉ። ይህ እጅግ የተመረጠው የሻፊዒይ ቃል ነው። ስለዚህ ከደራሲው ልቅ ቃል ይህኛው ጥያቄ ፍልቅታ ይወጣል። አዎን! ወደ ቤታቸው ከመመለሳቸው በፊት የጁሙዓ ወቅት ቢገባ ‐ለምሳሌ: ‐ ከዒድ ሶላት እንዳሰላመቱ የጁሙዓ ወቅት ቢገባ‐ በግልፅ እንደተመለከተው ሸይኻችን እንዳሉት ጁሙዐን የመተው መብት አይኖራቸውም።»
የሐነፊዮቹ ታዋቂ መጽሐፍ "አል‐ቢናያ ሸርሑል‐ሂዳያ" ቅጽ 3፥ ገጽ 97 ላይ እንዲህ ሰፍሯል: ‐
«እዚህ ላይ ሁለት ዒዶች ተጋጠሙ ማለት ዒድ አል‐ፊጥር ወይም ዒዱል‐አድሓ በጁሙዐ ቀን ዋለ ማለታችን ነው።… አንዱ ሶላት ለሌላው ተብሎ አይቀርም። ጁሙዐ የማይተወው ፈርድ ስለሆነ ነው። ዒድን መተው ደግሞ ጥሜት እና አዲስ ፈጠራ [ቢድዐ] በመሆኑ ነው።… የአላህ መልክተኛ [ﷺ] "እኛ ጁሙዐ እንሰግዳለን።" ማለታቸው ጁሙዐን መተው እንደማይፈቀድ ያስረዳል። የአላህ መልክተኛ [ﷺ] በስድ የፈቀዱላቸው እና ዑስማን [ረዲየላሁ ዐንሁ] ምርጫ የሰጧቸው ቤታቸው በመዲና ዳር ላይ ሩቅ ስለሆነ ነበር። ስለዚህ ከጁሙዐ በፊት ወደ ቤታቸው ከተመለሱ ጁሙዓን መተዋቸው ችግር አይኖረውም።»

❤26😢1
ኢማም ነወዊይ [ረዲየላሁ ዐንሁ] "አል‐መጅሙዕ" በተሰኘው መጽሐፋቸው ቅጽ 4 ገጽ 491 ላይ እንዲህ ብለዋል: ‐ «የጁሙዐ ቀን ከዒድ ቀን ጋር ተጋጥሞ የጁሙዐ አዛን ስለሚሰማቸው ጁሙዐን መስገድ ግዴታ የሚሆንባቸው መንደሮች ዒድ ሶላት ላይ ተገኝተው ቢሰገዱ ጁሙዐን መስገድ አይቀርላቸውም። [በጁሙዐው] ከተማ ነዋሪዎች ላይ ይህ ብይን የልሂቃን ልዩነት የለበትም። [ከጁሙዐው] ከተማ ውጪ የሚገኙ መንደሮች ነዋሪ ለሆኑ ሰዎች ጁሙዐ ይቀርላቸዋል ወይ በሚለው ዙርያ ግን ሁለት ዓይነት የሻፊዒይ ተማሪዎች ሃሳብ አለ። ትክክለኛውና ራሳቸው ኢማም ሻፊዒይ "አል‐ኡም" በተሰኘው መጽሐፋቸው በግልጽ ያስቀመጡት እና ቀዳሚው ሃሳባቸው ለነዚህ ብቻ ጁሙዐ ይቀርላቸዋል የሚለው ሲሆን ሌላኛው ግን የጁሙዐ ሶላት ግዳጅ አይቀርላቸውም ይላል።»
በኢማም ማሊክ አንዱ ዘገባ እና በሻፊዒዮቹ ተቀባይነት ባለው ሃሳብ መሰረት የዒድ ሶላት ላይ ለመገኘት ጁሙዐ ከማይሰገድባቸው ሩቅ ስፍራዎች ‐ለምሳሌ: ‐ ከከተማ የራቀ ገጠር‐ የመጣ ሰው ዒድ ከሰገደ ጁሙዐ መስገድ ግዴታ አይሆንበትም። ነገርግን በጁሙዐ ፈንታ ዙህር መስገድ አለበት። ይህ የዑስማን ኢብኑ ዐፋንም መንገድ ነው።»
ኢማም አል‐ቀራፊይ አል‐ማሊኪይ "አዝ‐ዘኺራ" በተሰኘው መጽሐፋቸው ቅጽ 2፥ ገጽ 355 ላይ እንዲህ ብለዋል: ‐
«ከከተማ ርቀው የሚኖሩ ሰዎችን በተመለከተ "አል‐ኪታብ" በተሰኘው መጽሐፍ ላይ እንደሰፈረው ጁሙዐን መተው አይችሉም። የለም! ጁሙዐን መተው ይችላሉ የሚል ዘገባም ተገኝቷል። ይኸውም ዑስማን [ረዲየላሁ ዐንሁ] አል‐ዐዋሊ መንደር ለሚኖሩ ሰዎች መፍቀዳቸውን እንደማስረጃ በመጠቀም የተባለ ነው። ምክንያቱም ዒድ ሰግደው ጁሙዐን መጠበቅም ሆነ ከዒድ በኋላ ቤታቸው ደርሰው መመለስ እጅግ ከባድ እንደሚሆንባቸው ታሳቢ በማድረግ ነው።»
በእርግጥ የሐንበሊ መዝሀብ ፉቀሃዎች በብዛት የዒድ ሶላትን የሰገደ ሰው የጁሙዐ ሶላት መስገድ አይጠበቅበትም ባይ ናቸው። ይልቁንስ ባለበት በጁሙዐ ፈንታ ዙህርን መስገድ ይበቃዋል። እንደነርሱ ከሆነ ኢማም ግን የጁሙዐ ሶላትን የማሰገድ ግዴታ አለበት። ''አል‐ሙብዲዕ'' የተሰኘው መጽሐፋቸው ቅጽ 2፥ ገጽ 180 እንዲህ ይላል: ‐
«ዒድ በጁሙዐ ቀን ካረፈ በዒድ ሶላት ከጁሙዐ መብቃቃት እና በጁሙዐ ምትክ ዙህርን መስገድ ይቻላል። ምክንያቱም የአላህ መልክተኛ [ﷺ] የዒድ ሶላት ከሰገዱ በኋላ እንዲህ ብለዋል: ‐ «ጁሙዐን መስገድ የፈለገ ይስገድ።» አሕመድ ዘይድ ኢብኑ አርቀም ጠቅሰው ዘግበውታል።
በዚህ መሰረት ሰውየው ላይ የመስገድ ግዴታ ሳይሆን ጁሙዐ ሶላት ላይ የመገኘት ግዳጅ ይወድቅለታል። በመሆኑም ሰውየው እንደ መንገደኛ ሳይሆን እንደ ህመምተኛ ይታያል። [ህመምተኛ የጁሙዐ ግዳጅ ሳይሆን ጁሙዐ የሚሰገድበት ስፍራ የመገኘት ግዳጅ እንደሚነሳለት ይህኛውም ሰው ጁሙዐ ሶላት የሚሰገድበት ስፍራ ላይ የመገኘት ግዳጁ ይነሳለታል። በአንፃሩ መንገደኛ [ሙሳፊር] ግን ጁሙዐ ቦታ ላይ የመገኘት ግዳጅ ብቻ ሳይሆን የጁሙዐ ሶላት ግዳጅ ይወድቅለታል።]
የዒድ ቀን ከጁሙዐ ቀን ጋር በሚጋጠምበት ጊዜ የዒድ ሶላትን በጀመዐ የሰገደ ሰው የዙህርን ሶላት እንደ ''ዑዝረኛ'' [ሸሪዓዊ ምክንያት እንዳለው ሰው] ይሰግዳል። በሌላ በኩል ጥቅል መረጃዎችን በመንተራስ የጁሙዐ ሶላት ግዳጅ በዒድ ሶላት ምክንያት አይወድቅም የሚል ሌላ ዘገባም ተገኝቷል።»
ነገርግን ሁሉም ሙስሊም በዒባዳ ጉዳይ ጫንቃውን ከተጠያቂነት የሚያድነውን ጥንቃቄ ያለበትን መንገድ መያዝ ይገባዋል።
በእርግጥ ካለፈው የተለየ የዒድ ቀን ከጁሙዐ ቀን ጋር ከገጠመ የዙህር ሶላት ራሱ በዒድ ሶላት ምክንያት ይወድቃል የሚል ሃሳብ መኖሩም ይነገራል። ነገርግን ፊታችንን ዞር አድርገን የምንመለከተው ፍሬ ያለው ሃሳብ አይደለም። ተቀባይነት ካላቸው የአህሉስ‐ሱና መዝሀቦች ውጪ የሆነ ውድቅ መላምት ነው። እርሱን መከተል፣ በርሱ መስራት፣ ፈትዋ መስጠት አይፈቀድም። በቀን እና በሌሊት አምስት ሶላት እንዲሰገድ ከሚያዙት በርካታ መረጃዎች ጋር ይቃረናል። ከአንዳንድ ሶሓቦች ዒድ በጁሙዐ ቀን ሲውል ዙህርን መተው እንደሚፈቀድ በወል ምልከታቸው የሚጠቁሙ ዘገባዎች ተገኝተዋል። ነገርግን የትኛውም ዘገባ የተረጋገጠ ሰነድ የለውም። ትንታኔው በጥሞና ሲቃኝም ለተባለው መሰረት የለሽ ሃሳብ መረጃ መሆን የሚችል ትርጉም የለውም። ሰነዱ ጠንካራ ቢሆን እንኳን የሙስሊሞች ስምምነት በሚደግፋቸው አምስቱ ሶላቶች ግዴታ መሆኑን በሚያመለክቱ መረጃዎች የተነሳ ውድቅ ይሆናል። እንግዳ ከሆነው ይህ ዘገባ ይልቅ አምስቱ ሶላት ግዴታ መሆኑን የሚያመለክቱትን መረጃዎችን እናስቀድማለን። ልሂቃን ዘንድ ተቀባይነት ያለው አካሄድም ይኸው ነው።
ኢማም ኢብኑ ሩሽድ "ቢዳየቱል‐ሙጅተሂድ" የተሰኘው መጽሐፋቸው ቅጽ 1፥ ገጽ 230 ላይ እንዲህ ብለዋል: ‐
«የዙህር እና ምትኩን የጁሙዐን ግዳጅ ለዒድ ሶላት ብሎ ማስቀረት ግን እጅግ በጣም ከመሰረት የወጣ ውድቅ ሃሳብ ነው።»
እንደማጠቃለያ ሰዎች በለመዱት መዝሀብ እንዲሰሩና አፈንጋጭ እስካልሆነ ድረስ በተግባቡበት አፈፃፀም ጌታቸውን እንዲያመልኩ መተው እንደሚገባ አምናለሁ። ህዝብ ያልለመደውን መዝሀብ ከኪታብ እየመዘዙ ተርታውን ህዝብ ማወዛገብ እና የንትርክ አጀንዳዎችን ማብዛት ሰውየው አዋቂ ነኝ ብሎ ራሱን ለማሳየት የሚያደርገውን ጥረት እንጂ ሌላን አያመለክትም። በሙስሊሞች መካከል ልዩነትን የሚያሰፉ፣ ጭቅጭቅን የሚያነግሱ፣ ክፍፍልን የሚያጠናክሩ ሃሳቦችን ማራገብ ተገቢ አይደለም። አጠራጣሪ ያልሆኑ ግልፅ መረጃዎችን መከተል፣ ታላላቅ ሊቃውንት የተጓዙበትን ዱካ ተከትሎ መሄድ አማራጭ የማይገኝለት መስመር ነው።
አላህ የበለጠ ያውቃል!

❤21
Tofik Bahiru pinned «ጁሙዐ እና ዒድ ዒድ በጁሙዓ ቀን ከዋለ ጁሙዓዎች መደበኛውን ቀጠሮ ተከትለው በየመስጂዱ ይሰገዳሉ። ስለዚህ ማንኛውም ሙስሊም ዒዱን በጀመዐ ከሰገደ በኋላ ጁሙዓውንም እንደተለመደው ቢያስከትል እጅግ የተመረጠ ነው። ነገርግን ሁለቱንም ሶላቶች ማስገኘት የማያስችል ምክንያት ካለው ጁሙዓን ማስበለጥ አለበት። ምክንያቱም ጁሙዐ የነፍስ ወከፍ ግዴታ ነው። ጁሙዓን ግዴታ የሚያደርጉ መስፈርቶች ተሟልተው እስከተገኙ ድረስ…»
በዒድ አል‐አድሓ ቀን መስራት ያለብንን ❿ ነገሮች እናስታውስ: ‐
❶ የቀኑን ትልቅነት ማሰብ፤ የውሙል‐ሐጂል‐አክበር ነው።
❷ ድምፅን ከፍ አድርጎ ተክቢራ ማድረግ፤
❸ ገላ መታጠብ፤ አዲስ ወይም ምርጥ ልብሳችንን መልበስ፤ ሽቶ መቀባት፤ ጥርስን መፋቅ፤
❹ ሶላት እስከሚጠናቀቅ ድረስ ምንም ሳንቀምስ እንደጾመኛ "ኢምሳክ" ማድረግ።
❺ ወደ ዒድ ሶላት ሜዳ ተሰብስበን በህብረት ተክቢራ ደምቀን መሄድ፤
❻ ሶላታችንን መስገድ፤ ኹጥባ ማዳመጥ፤
❼ በዜማ እና በሌላ ጨዋታ ዒዱን ማድመቅ፤
❽ የሄዱበትን መንገድ ቀይሮ መመለስ፤
❾ በዒዱ ቀን ዓቅመ ደካማዎችን መዘየር፤ በደስታ እንዲያሳልፉት ማገዝ፤
❿ በነዚህ የደስታ ሰዓት እንኳን በግፍ ውስጥ ያሉ ወገኖቻችንን በተለይም ፊሊስጢኖችን በዱዓ ማሰብ።
:
በድል ጨረቃ ታጅበን፣ በኢስላም ልዕልና ደምቀን፣ በሀገራችን ሰላም ተውበን፣ በአንድነት እና በፍቅር ከአመት አመት ያድርሰን!
ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም!
http://www.tg-me.com/fiqshafiyamh

❤45
ተክቢራ በአይ‐ያም አት‐ተሽሪቅ
===================
«በአይ‐ያም አት‐ተሽሪቅ ቀናት (ከዒዱል‐አድሓ እለት ቀጥለው ባሉት ሦስት ቀናት) የሚደረገው ተክቢራ የግድ ከፈርድ ሶላት በኋላ መሆን አይጠበቅበትም። [በመርሳት ወይም በሌላ ምክንያት] ቢተወውም በተመቸው ጊዜ ሊያደርገው ይችላል።»
ኢማም ነወዊይ "ሚንሃጅ" በተሰኘው መፅሀፋቸው ላይ እንዲህ ብለዋል: ‐ «በአይ‐ያም አት‐ተሽሪቅ ቀናት ሶላት ቀዷእ ሲያወጣ፣ መደበኛ ሱና ሶላቶችን ሲጨርስ፣ ማንኛውም ዓይነት ሱና ሲሰግድ አስከትሎ ተክቢራ ማድረግ ይወደዳል የሚለው [የኢማም ሻፊዒይ] ሀሳብ እጅግ የተሻለ (አዝሀር) የሆነው ሃሳብ ነው።»
ኢማም ኢብኑ ሐጀር አል‐ሀይሰሚይ "ቱሕፋ" በተሰኘው ኪታባቸው ላይ እንዳሰፈሩት: ‐ «ለምሳሌ: ‐ ከዱሓ ሶላት፣ ከዒድ ሶላት እና ከመሳሰሉት ሶላቶች በኋላ፣ ልቅ ከሆኑ ሱና ሶላቶች በኋላ፣ እንደውም ከጀናዛ ሶላት በኋላ ሳይቀር ተክቢራ ይደረጋል። ምክንያቱም ተክቢራ የጊዜው ዓርማ ነው።»
"ሙኽተሶሩ ባፈድል" በበኩሏ እንዲህ ትላለች: ‐
«ከሐጀኛ ውጪ ያለ ሰው ሁሉ ከፈርድም ሆነ ከሱና ሶላት በኋላ ተክቢራ ያደርጋል። ሶላቱ ትኩስም ይሁን ቀዷእ ወይም የጀናዛ ሶላት ምንም ልዩነት የለም። ተክቢራውን ከረሳ ሲያስታውስ ያድርገው።»
የዒድ ተክቢራ በህብረት ብቻ የሚደረግ የሚመስላቸውም ሰዎች ይኖራሉ። ነገርግን ስህተት ነው። ተክቢራው በግልም በጀመዓም እንደሚደረግ ይታወስ።
:
ዒድ ይደጋግመን። በጤናና በሰላም አመት ከአመት ያድርሰን ያድርሳችሁ።
ዒድ ሙባረክ!
https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh

❤32👍6
ኡድሒያ ማረድ አንዳንድ ዐሊሞች ዘንድ ዋጂብ ቢሆንም አብዝሃኞቹ ዘንድ ጥብቅ ሱና ነው። ጎረቤትን በከብት ፈርስ፣ በተጣሉ የከብት ቆሻሻዎች ማስቸገር እና በማንኛውም መልኩ አዛ ማድረግ ደግሞ ሐራም ነው።
እባካችሁ ወዳጆች የእርዳችን ፋና የሆኑ የደም፣ የፈርስ ተረፈ ቆሻሻ እያስወገድን የዲናችንን ግዴታ እንወጣ። መልካም ስራችንን አናበላሽ!

👍45❤9
ዛሬ አያም ተሽሪቅ ሦስተኛ ቀን ነው። እርዳችንን ያልፈፀምን እስከ መጪው መግሪብ ድረስ እድሉ አለን። ኡድሒያ አስቤዛ አይደለም። ዒባዳ ነው። ስጋውን ለመብላት ሳይሆን መስዋዒት በማድረግ ወደ አላህ ለመቅረብ እንነይት።
:
«ሱና ዐለል ዐይን» — የነፍስ ወከፍ ሱና ነው የሚሉ ዐሊሞች አሉ። በአንድ ቤት ውስጥ ከአንድ በላይ ዓቅም ያላቸው ሰዎች ካሉ እያንዳንዳቸው በተናጠል ማረድ አለባቸው ማለታቸው ነው። ስለዚህ ድሆችን ማገዝ ያስችለን ዘንድ በርከት አድርገን እንረድ። «ኡድሒያ ደሙ መሬት ከመውደቁ በፊት አላህ ዘንድ ነው የሚያርፈው።»…
:
በዒድ መደሰት የዲን ዓርማ ነው። ተደሰቱ! በመንዙማው ተፅናኑ። በነሺዳው ድምፅ ተዛናኑ። ልጆቻችሁን አጫውቱ። ቤታችሁን በልዩ ድባብ አድምቁት።…
:
ከማንኛውም ሶላት በኋላ ተክቢራ ይቀጥላል። እስከ ነገ ዐስር ድረስ። ከነገው ዐስር በኋላም ተክቢራው ተደርጎ ይጠናቀቃል።…
ዒዱኩም ሙባረክ!

❤64👍10
Forwarded from የረሕማን ስጦታ
«ጀግንነት እና ተገንነት ምርጥ ጠባይ ነው። ጀግንነት ማለት የቁጣ አቅምን ለአዕምሮ ፍርድ ተገዥ እንዲሆን ማድረግ ነው። ተገንነት ማለት ለመልካም ነገር ስኬት ሲባል ነፍስን ያለ ፍርሃት ሞት ወዳለበት ስፍራ መላክ ነው።
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] በጀግንነትና በተገንነት ይታወቁ ነበር። እጅግ የከበዱ አደገኛ ሁኔታዎች ላይ ተገኝተው ተፈትነዋል። በርካታ ጀግኖችና ጀብደኞች በተደጋጋሚ ከዙርያቸው ሸሽተዋል። እርሳቸው ግን ቦታቸው ላይ ፀንተው ተጋፍጠዋል። ሳያፈገፍጉ ፊትለፊት ፍልሚያቸውን ቀጥለዋል። አልተርበተበቱም።
ማንኛውም ጀግና ጥቂትም ቢሆን የሽሽት አጋጣሚም ይኖረዋል። ያፈገፈገበት ቀንም አያጣውም። ይህ ግን እርሳቸውን አይጨምርም!»
📚 አሽ‐ሺፋእ ቢተዕሪፊ ሑቁቂል‐ሙስጦፋ፥ ኢማም ቃዲ ዒያድ

❤43
ከዚክር ማህደር
ኑሮ የተወሳሰበ ሰው ምን ይበል?
ከሰይዲና ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር እንደተዘገበው የአላህ ነቢይ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«አንዳችሁ የኑሮው ጉዳይ ከተወሳሰበበት ከቤቱ ሲወጣ እንዲህ ከማለት ምን ያግደዋል?!: ‐
«በአላህ ስም ነፍሴን፣ ገንዘቤን እና ዲኔን [በማስተካከል ላይ እታገዛለሁ]።
አላህ ሆይ! በፍርድህ አስደስተኝ። ያዘገየኸውን ማስቸኮል፣ ያስቀደምከውን ማዘግየት እስከማልወድ ድረስ በተወሰነልኝ ነገር ላይ በረከት አድርግልኝ።»
ኢብኑ ሱኒይ ዘግበውታል። አዝካር ላይ ኢማም ነወዊይ ጠቅሰውታል።

❤54👍9
ከተፈቃሪያችን [ﷺ] ጋር የተሰጠን ትልቁ የአላህ ፀጋ ከርሳቸው ጋር የተፈቀደልን ቅርበት ነው። ሶለዋት እና ሰላምታ ስናቀርብላቸው ይደርሳቸዋል። እርሳቸው ናፍቀናቸው አንብተዋል። እኛ የርሳቸው እጣ እርሳቸውም የኛ እድል እንደሆኑ ነግረውናል። የህይወት ውሏቸው፣ የአካል ገፅታቸው እና የቤተሰብ ግንኙነታቸው ሳይቀር ተሰንዶ ተዘግቦልናል። ከህይወታቸው ገፅታ እኛ ዘንድ ሳይደርስ ተዳፍኖ የቀረ የለም!
ስለዚህ ፍቅር ያለው ወዳጃቸው ከእቅፋቸው ሳይወጣ፣ ተዝካራቸው ከህይወት ማእዱ ሳይርቅ ይመላለስበታል። እነሆ ዛሬ ዝክረ ሂጅራቸው ድምቀታችን ይሆን ዘንድ አላህ አድርሶናል!
አልሐምዱሊላህ!
እናም አደራ የምላችሁ!…
ስለ ሂጅራቸው ለልጆቻቸን እንንገር። እለቱን ከታሪክ ዐውዱ ጋር አቆራኝተን ደማቅ ወጋችን እናድርገው። የመድረሳ ባለቤቶች፣ የመስጂድ አስተዳዳሪዎች፣ ዳዒዎች፣ የረሱልን ፍቅር በትውልድ ልብ ውስጥ መዝራት የሚሻ ሁሉ ዓመቱን ሁሉ ከህይወታቸው ክስተት እየቀዳ ይጠጣ። ለሌላውም ያጋራ። ከህይወት ቅኝታቸው የሚገኘውን አስተምህሮና ለዛ ይቋደስ!
እንኳን ለ1447 ኛው ዓመተ ሂጅራ አደረሳችሁ! የከርሞ ሰው ይበለን!

❤62👍8😍2
ከዓሹራእ ጾም ጋር የተያያዙ ዐስር ህግጋት: ‐
❶ የዓሹራ ጾም ያለፈውን ዓመት ኃጢኣት ያስምራል። ይህ ሲባል ተውበት የሚያሻቸውን ከባባድ ኃጢኣት ሳይሆን ቀላል (ሶጛኢር) ኃጢኣቶችን ነው።
❷ ዓሹራን መጾም የተወደደበት ምክንያት አላህ ነቢዩ ሙሳን (ዐለይሂስ‐ሰላም) እና ህዝባቸውን ከፊርዐውን ያዳነበት ቀን መሆኑን በማሰብ አላህን ማመስገን ነው።
❸ የዓሹራ ጾም ደረጃዎች ሦስት ናቸው። በላጩ አስቀድሞ አንድ ቀን ከበስተኋላውም አንድ ቀን በድምሩ ሦስት ቀን መጾም ነው።
ሁለተኛው ከበስተፊቱ ወይም አንድ ቀን ከበስተኋላው መጾም ነው። በድምሩ ሁለት ቀን መጾም።
ሦስተኛው ሁኔታ እራሱን የዓሹራን ቀን (ሙሐረም 10ን) መጾም ናቸው።
❹ ከበስተፊቱ ወይም/እና ከበስተኋላው አንድ ቀን መጾም የተወደደበት ምክንያት ከአይሁዶች ለመለየት ነው። እነርሱ የዓሹራን ቀን ብቻ ነው የሚጾሙት።
❺ በዓሹራ ቀን ከጾም ውጪ ከሌሎች የዓመቱ ቀናት በተለየ ሁኔታ የተደነገገ ምንም ዓይነት ዒባዳ የለም። ነገርግን ቤተሰብን በሚበላና በሚጠጣ ነገር ማስፋፋት (ማንበሻበሽ) እንደሚወደድ የሚገልፅ ሐዲስ ተዘግቧል። አብዝሃኞቹ ልሂቃንም በሐዲሱ ሠርተዋል። ከዚያ ውጪ ለእለቱ መታጠብ፣ ሽቶ መቀባባት፣ መኳል… ተወዳጅ ነው የሚሉ የቅጥፈት (መውዱዕ) ሐዲሶች ተዘግበዋል። መጠንቀቅ ያስፈልጋል።
❻ ከረመዳን ወር በኋላ ለጾም የተወደዱ ወራት አሽሁሩል‐ሑሩም (የተከበሩት ወራት) ናቸው። ከነርሱ ደግሞ በላጩ ሙሐረም ነው። ከዚያም ረጀብ፣ ዙል‐ሒጃ፣ ዙል‐ቀዕዳ በተከታታይ ለጾም የተመረጡ ወራት ናቸው። ከአሽሁሩል‐ሑሩም ቀጥሎ ሸዕባን ምርጥ የጾም ወር ነው።
❼ በዓሹራ ቀን ለረመዳን ቀዷ ነይቶ የጾመ ሰው የሁለቱንም ጾሞች ምንዳ ያገኛል። ፈርዱ ከጫንቃው ላይ ይነሳል፤ ሱና የሆነውን የዓሹራን ምንዳ ያገኛል።
❽ የዓሹራን ቀን ከእለቱ የዙህር ወቅት በፊት ባለው ጊዜ ነይቶ መጾም ይቻላል። ይኸውም እንደማንኛውም ሱና ጾም ማለት ነው። በሌሊት ነይቶ ማደር ግዴታ አይደለም። እንደሚታወቀው ፈርድ ጾሞች ግን ለነገ ጾም ከመግሪብ እስከ ፈጅር ባለው ካልተነየተ አይሆንም።
❾ የዓሹራ ጾም ያመለጠው ሰው ቀዷ ቢያወጣው ይወደዳል። የሻፊዒያ መዝሀብ ዐሊሞች መደበኛ ጾሞችን ቀዷ ማውጣት እንደሚወደድ በግልፅ ፅፈዋል።
❿ በመሰረቱ ሴት ባሏ በሀገር እያለ ያለፍቃዱ መጾም አትችልም። ነገርግን በተለይ እንደ ዓሹራ በዓመት አንዴ የሚዘዋወሩ ቀናትን ለመጾም አለመከልከሉ ብቻ ይበቃታል። ስለዚህ በግልፅ መፍቀዱ ወይም ማስፈቀድ አያስፈልጋትም።
አላሁ አዕለም!

❤40👍5
ቀናችንን በኢስቲግፋር ድምቀት እንጀምረው!…
ከአቡ ሙሳ አል‐አሽዓሪይ እንደተዘገበው የአላህ መልክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል: ‐
«ምን ጊዜም ንጋት ላይ በጠዋት መቶ ጊዜ ኢስቲግፋር ሳላደርግ ቀርቼ አላውቅም።»
https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh
ከአቡ ሙሳ አል‐አሽዓሪይ እንደተዘገበው የአላህ መልክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል: ‐
«ምን ጊዜም ንጋት ላይ በጠዋት መቶ ጊዜ ኢስቲግፋር ሳላደርግ ቀርቼ አላውቅም።»
https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh
❤35👍7
Tofik Bahiru
ASHURA 1447.pdf
ዐሹራ ነገ ነው። የቻልን ነገን እና ከነገ ወዲያን ጨምረን እንፁም። ስለ ዐሹራ ለልጆቻችን እንንገር። እንተዋወስ!
በዱዓ እንበርታ። ከአላህ በቀር ምንም ያልነበራቸውን ሰይዲና ሙሳ [ዐለይሂ ሰላም] ከዘመናቸው አምባገነን ጉልበተኛ ያዳነና ድል የሰጠ ጌታ ከርሱ በቀር ምንም የሌላቸውን የዘመናችን ድኩማንን ከጨቋኞቻቸው አድኖ ድሉን ይስጣቸው እያልን እንለምን።

❤78👍2