Forwarded from የረሕማን ስጦታ
በሰዎች ዓይን ቢያንሱም ሆነ ቢበዙ ፀጋዎች ሁሉ በአላህ መልክተኛ [ﷺ] አማካይነት የተገኙ ናቸው። የተቸሩንን ፀጋዎች እንድናውቅ ያደረጉን፣ ክብራቸውን አውቀን የተሰጠንን እንድንጠብቅ ያስተማሩንም እርሳቸው ናቸው!…
:
ረመዳን ለተወዳጁ ነቢይ [ﷺ] ህዝቦች ከተሰጡ ታላላቅ ፀጋዎች መካከል አንዱ ነው። እርሳቸውም የረመዳን ኸይሮች ሁሉ ሰበብ፣ በታላቅ ምንዳዎቹ እንዲያንበሸብሸን ምክንያት የሆኑ፣ በረመዳን እንድንታደል እና ስኬታማ እንድንሆን ያደረጉ ባለ ውለታችን ናቸው!
:
ታዲያ ውለታቸውን ባኖሩበት በዚህ ታላቅ ወር እኛ እርሳቸውን ከማውሳት ልንዘናጋ ይገባልን?!…
የወሩ መጀመሪያ፣ መካከልም ሆነ መጨረሻው ላይ ልቅናቸውን ለማሰብና እርሳቸውን ለማሞገስ የመደብነው ጊዜ ሊኖረን አይገባምን?!… እንዴታ!
ካለብን ውለታቸው ለጥቂቱም ቢሆን ምላሽ ከመስጠት መጀመር ይገባናል። በርሳቸው ምልጃ የአላህን ምህረት ልንጠራ፣ ይቅርታውን ልንጋብዝ ይገባል። የአላህን ስጦታ፣ ከፍ ያለውን ደረጃ እና በረመዳን የሚገኘውን መልካም ነገር ሁሉ ከጥላቸው ስር ተሸሽገን መጠባበቅ አለብን!
ያለርሳቸው አማካይ ለብቻችን የምንደርስበት ምንም ክብር የለምና በመንገዳችን ሁሉ እርሳቸውን ፋናችን እናድርግ!
ያማረ ረመዳን ያድርግልን!

❤29👍6
Forwarded from Tofik Bahiru
ማስታወሻ:
በሻፊዒዮች እና በአብዝሃኞቹ የፊቅህ ልሂቃን መንገድ መሰረት የረመዳን እና የሌሎችም ግዴታ የሆኑ ጾሞች ኒያን ለየቀኑ በሌሊት ከፈጅር በፊት መፈፀም የግድ እንደሆነ ይታመናል። ከዚህም ጋር ሳዳቶቻችን ሻፊዒዮች የወሩን አጠቃላይ ኒያ በመጀመሪያው ሌሊት ላይ ማስገኘት ይወደዳል ብለዋል።
ኢብኑ ሐጀር [ረሒመሁላህ] እንዲህ ይላሉ: ‐
«በመጀመሪያው የረመዳን ሌሊት ላይ ወሩን በሙሉ ለመጾም ኒያ ማድረግ ተገቢ ነው። ይኸውም የኢማም ማሊክን [ረሒመሁላህ] መዝሀብ በመከተል ነው። ከረመዳን ቀናት ኒያን የዘነጋ ሰው በእርሳቸው መዝሀብ መሰረት ጾሙን እንዲያገኝ ያደርግለታል።»

❤22👍12
«የረመዳን የመጀመሪያው ሌሊት ሲሆን አላህ [በእዝነት] ወደነርሱ ይመለከታል። አላህ [በእዝነቱ] የተመለከተውን ሰው ደግሞ ፈፅሞ አይቀጣውም!»
ሰይዲና ረሱሊላህ [ﷺ]
ሰይዲና ረሱሊላህ [ﷺ]
❤64👍4
Forwarded from Tofik Bahiru
በረመዳን_ምን_ይጠበቅብናል_ተውፊቅ_ባህሩ_2023.pdf
804.8 KB
በረመዳን ምን ይጠበቅብናል?
==================
ቀልብ ህያው ሲሆን፣ የኢማን ጮራ በውስጡ ሲንቦገቦግ ሁለመና ወደ ቀኝ ይዞራል። ለመልካም ሥራ ይነቃነቃል። በየአቅጣጫው ለበጎነት ይነሳሳል። ጊዜ ሳይገድበው፣ በንቃት እና በተነሳሽነት ያለ አስገዳጅ ለኸይር ይዞራል።…
ቀልብን ህያው የሚያደርግ፣ ኢማን የሚያሳድግ፣ ሩሕን የሚያነቃ አዋጭ መንገድ ደግሞ የቁርኣን መንገድ ነው!
إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ الَّذِينَ إِذَا ذُكِرَ اللَّهُ وَجِلَتْ قُلُوبُهُمْ وَإِذَا تُلِيَتْ عَلَيْهِمْ آيَاتُهُ زَادَتْهُمْ إِيمَانًا وَعَلَىٰ رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ
«ፍጹም ምእምናን እነዚያ አላህ በተወሳ ጊዜ ልቦቻቸው የሚፈሩት፣ በ͟ነ͟ሱ͟ም͟ ላ͟ይ͟ አ͟ን͟ቀ͟ጾ͟ቻ͟ች͟ን͟ በ͟ተ͟ነ͟በ͟ቡ͟ ጊ͟ዜ͟ እ͟ም͟ነ͟ት͟ን͟ የ͟ሚ͟ጨ͟ም͟ሩ͟ላ͟ቸ͟ው͟፣ በጌታቸውም ላይ ብቻ የሚመኩት ናቸው፡፡»
እነሆ የቁርኣን ወር ከፊታችን ተደቅኗል!
ለቅዱሱ ወር ምን እናቅድ?!
ቀልባችንን ማረስረስ?! ህያው ማድረግ?! ውስጣችንን በኢማን መሙላት?! ረመዷንን ከረመዷን በኋላም በማይደበዝዝ ድምቀት ወሩን ሙሉ ማሳለፍ?
ወይስ ከዚህ ቀደም እንዳለፈው አይነት ረመዳን፣ ወሩ ሲያልፍ ደግሞ ታጥቦ ጭቃ የሆነ አዳፋ ህይወት መምራት!
ከረመዳን ምን እንፈልጋለን?!
:
የለጠፍኩላችሁ መፅሀፍ ከአመታት በፊት ይህንን ጥያቄ ለመመለስ የተከተበ ነው።
አንብቡልኝ! በዱዓም አስታውሱኝ!

❤21👍6
Audio
ሙቀዲመቱ ባፈድል
📗 ክፍል ሠላሳ ሰባት:‐ ዘካ ክፍል 3 [ዘካቱን‐ነቅደይን]
📆 የካቲት 22/ 2017 ዓ. ል.
📗 ክፍል ሠላሳ ሰባት:‐ ዘካ ክፍል 3 [ዘካቱን‐ነቅደይን]
📆 የካቲት 22/ 2017 ዓ. ል.
የጾመኛ ደስታዎች
===========
አቡሁረይራ [ረዐ] እንደዘገቡት የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«አላህ እንዲህ አለ: —
የአደም ልጅ ሁሉም ስራ ለርሱ ነው፤ ጾም ሲቀር። እርሱ ግን ለኔ ነው። እኔም እመነዳበታለሁ። ጾም ጋሻ ነው። የእያንዳንዳችሁ የጾም ቀናችሁ ሲሆን የወሲብ ወሬ አያውራ፤ አይጩኽ። አንድ ሰው ከተሳደበው ወይም ከተጋደለው እኔ ጾመኛ ሰው ነኝ ይበል።
የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ የጾመኛ የአፍ ጠረን አላህ ዘንድ ከሽቶ የበለጠ ተወዳጅ ነው።
ጾመኛ የሚደሰትባቸው ሁለት ደስታዎች አሉት። ሲያፈጥር ይደሰታል። ጌታውን ሲገናኝም በመጾሙ ይደሰታል።» ሹዐቡል‐ኢማን ገፅ 265
http://www.tg-me.com/fiqshafiyamh

❤14👍8
ረመዳን ለሁሉም ዓይነት በሽታችን ፈውስ የያዘ ሆስፒታል ነው። መድኃኒቱ ፍቱን የሚሆነው ደግሞ በታዘዘው መልኩ ሲወሰድ ነው። ድካሙና የእንቅልፍ እጦቱ ደግሞ የፈውሱ ሂደት አካል ነው። እናም ምሬት ቢኖረውም መዳን የሚፈልግ ሁሉ መታገስ ግዴታው ነው!
❤31
ረመዳን ❸
ኢማም ኢብኑ ረጀብ እንዲህ ይላሉ: —
የሚከተሉት ነገሮች በአንድ ላይ በረመዳን አሉ: ‐
⚀ ጾም፤
⚁ ቂያም‐ረመዳን (ተራዊሕ)፤
⚂ ሶደቃ፤
⚃ መልካም መናገር፤ ምክንያቱም ረመዳን ሰውየውን ከቧልት እና ከስሜት ወሬ ያቅባል።
ጾምና ሶደቃ አላህ ዘንድ ያደርሳሉ። አንድ ሰለፍ እንዲህ ብለዋል: ‐
«🔸ሶላት ሰውየውን ግማሽ መንገድ ትሸኛለች።
🔸ጾም ወደ ንጉሱ በር ታደርሳለች።
🔸ሶደቃ እጁን ይዛ ንጉሱ ፊት ታቀርባለች።»
:
አላህ መልካም ስራዎቻችንን ይቀበለን!
https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh

❤50👍7
«የረመዳን አንድ ተስቢሕ ከረመዳን ውጪ ካለ አንድ ሺህ ተስቢሕ ጋር ይበልጣል።» ኢማም ዙህሪይ
:
«በላጭ የሆኑት ጾመኞች በጾም ላይ ሆነው አላህን አብዝተው የሚዘክሩት ናቸው።» ኢማም ኢብኑል‐ቀዪም
:
ጾማችን ወዘና ይላበስ ዘንድ በዚክር ማጀብ ከኛ ይጠበቃል። ዚክር የሁሉም ዒባዳዎች ውበት ብቻ ሳይሆን ዒባዳዎች በሙሉ የተደነገጉበት ምክንያት፣ የእንቅስቃሴያቸው መዘውርም ነው። ነፍሳችንን የሚያስታውሰን፣ የአላህን አብሮነት የሚያጎናጽፈን፣ በሰማያት ሰራዊት ዘንድ የላቀ መወሳትን የሚያስገኝልን በረከት ነው።
እየዘከርን!

❤45👍2
ከባፈድል የዘካ ክፍልን እዚህ ጋር ጨርሰናል። ቀጣዩ ጾም ነው። የዛሬ ዓመት ከተራው በፊት አስቀድመን ተምረነው እዚህም ኦዲዮውን ፖስት አድርገነው ነበር። ኢንሻአላህ አከታትለን እናቀርብላችኋለን። ደርሶቹ ከዚህ በላይም መብራራት የሚችሉ በርካታ ነገሮች አሏቸው። ነገርግን ሁሌ ለትንሹም ሆነ ለትልቁ ሰው ከመጠየቅና በዘልማድ ዒባዳዎቻችንን ከማከናወን አንዴ መረር አድርገን መማር መልካም ነው። እናም ሸይኽ ስር ለተቀመጣችሁ ወዳጆች ማስታወሻ ይሆናችኋል። ሸይኽ ስር መቀመጥ ላልቻላችሁ ደግሞ ከስማ በለው የጅህልና መንገድ መለስ ያደርጋችኋልና ደርሶቻችንን ወይም ተመሳሳይ ደርሶችን እንድትከታተሉ አደራ እንላለን!
ጀዛኩሙላህ ኸይረን!
ጀዛኩሙላህ ኸይረን!
❤10