አላህ ሆይ!
ፈቅደህልን፣ አግርተህልን የሰራነውን መልካም ሁሉ ተቀበለን!
በድፍረታችን፣ በስሜታችን፣ በነፍሳችን ተነድተን የፈፀምነውን ወንጀል ሁሉ ማረን!

❤95😢31👍3
አንድ የዐረብ ዘላን (አዕራቢ) አዛውንት በከዕባ ደጃፍ ላይ ሆኖ እንዲህ አለ: ‐
«ጌታዬ! የሚለምንህ [ባርያህ] ደጃፍህ ላይ ነው!…
ቀኑ አልፎበታል፤ ኃጢኣቱ ብቻ ቀርቷል።
ስሜቱ አብቅቷል፤ [የጥያቄው] ሸክም ቀርቷል።
ጌታዬ ሆይ! [መልካሙን] ውደድለት። ካልወደድክለት ደግሞ ይቅር በለው፤ ጌታ የባርያውን [ሥራ] ባይወድም እንኳን ይቅር ይላል!
አላህ ሆይ! ከባሮችህ መካከል የበደሉንን ሰዎች ይቅር እንድንል አዘኸናል። ነፍሳችንን ስንበድል ደግሞ አንተው ይቅር በለን።
አላህ ሆይ! ያንተን ሐቅ ተውልኝ። የሰዎችን ሐቅ ይቅር አስብልልኝ! »
📝 በህጀቱል‐መጃሊስ፥ ኢማም ዐብዱል‐በር [ረሒመሁላህ]

❤95👍16😢7
በረመዳን በርካታ ሰዎች ስለ ዘካ ይጠይቃሉ። በበኩሌ ከፍተኛ የመረጃ ክፍተት ያለበት ጉዳይ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ በዝርዝር እፅፋለሁ የሚል ፍላጎት ቢኖረኝም እስካሁን አልተሳካልኝም።
አንዳንድ ጥያቄዎች ግን አጣዳፊ እና ተደጋጋሚ ከመሆናቸው ተነስተን እና ብዙዎች ሳይጠይቋቸው ቢቀሩም እንኳን ሊስቷቸው የሚችሉ አሳሳቢ በመሆናቸው በመጠኑ ለመሞነጫጨር እጥራለሁ።
ከፊሎቹ ግን አሁንም እየተጠየቁ ከመሆናቸው ጋር ከዚህ በፊት በዚህ ቻነል በኩል የተፃፈባቸው ሆነው አገኛቸዋለሁ። ስለዚህ ዐሽሩል‐አዋኺር እንደመሆኑ ፈላጊዎች በቀላሉ እንዲያገኟቸው ብቻ በሊንክ ከዚህ በታች አስቀምጣለሁ: ‐
❶ https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh/1638
❷ https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh/1631
❸ https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh/1625
❹ https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh/1623
❺ https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh/1616
❻ https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh/1617
❼ https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh/1613
❽ https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh/1087
❾ https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh/540
❿ https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh/293
⑪ https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh/287

Telegram
Tofik Bahiru
የገንዘብ ዘካችንን በምን እንተምን?
======================
የገንዘብ ዘካ አነስተኛ የሀብት መጠንን (ኒሷብን) ለማወቅ የወርቅ ዋጋን መጠቀም ተገቢ ነው። አንዳንድ ሰዎች በብር (ሲልቨር) ይተምናሉ። ይህ ትክክል አይደለም።
በእርግጥ ነቢዩ [ﷺ] የዘካን ኒሷብ በብር እና በወርቅ ያስቡ ነበር። ነገርግን ያን ያደረጉት ሁለት አይነት ኒሷብ ለመመደብ አስበው አይደለም። ኒሷብ አንድ ነው። ይሁንና…

👍13
ለገዝ‐ዛ ወንድሞቻችን ቢያንስ እንደሚከተለው ወይም በሌላ መልኩ ዱዓ በማድረግ አብረናቸው እንሁን: ‐
:
«ቢስሚላህ ወልሐምዱ ሊላህ ወሶላት ወሰላም ዐላ ረሱሊላህ: —
አንተ አሕዛብን በታታኝ የሆንክ፣ ከዳመና ዝናብን የምታዘንብ ጌታ ሆይ! ገዝ‐ዛ ውስጥ ያሉ ወንድሞቻችንን እርዳ።
አላህ ሆይ! ይህ ከልዩ ቀናቶችህ አንዱ ነው። አላህ ሆይ! ዲንህን እርዳ። ሰራዊትህን አሸናፊ አድርግ። ጠላትህን እና ረዳቶቻቸውን ሁሉ አዋርድ።
አላህ ሆይ! በደለኞች ታጋሽነትህ አታለላቸው። የፍርድህን ቀን ሩቅ አድርገው ገመቱ። አላህ ሆይ! እጅግ በኃያልነትህ በጥኑ አያያዝህ ስበራቸው።
አላህ ሆይ! የወንድሞቻችንን ሁኔታ ታያለህ። የሰቆቃ ድምፃቸውን ትሰማለህ። እነርሱንም ሆነ እኛን የበደለን ግፈኛ ሁሉ ተበቀልልን።
አላሁ አክበር!
አላሁ አክበር!
አላሁ አክበር!
ወሊላሂል‐ሐምድ።
ወሶለላሁ ዐላ ሰይዲና ሙሐመድ ወሰለም። ወልሐምዱ ሊላሂ ረቢል‐ዓለሚን።»

😢64❤21👍14
ዑዝር ላላቸው!
መስጂድ ኢዕቲካፍ ማድረግ፣ አብዝቶ መስጂድ መመላለስ፣ ቁርኣን ከመቅራት ወይም በሌሎች በጎ ስራዎች መሳተፍ የማይችሉበት ምክንያት (ዑዝር) ያላቸው ሰዎች ይኖራሉ። በእርግጥ የተወሰኑ ዒባዳዎችን ማከናወን ባይችሉም እንኳን ምንም አይነት አልፊ ነገር የማይሻው ዚክር እና መሰል ዒባዳዎች በሽ ናቸውና ተስፋ መቁረጥ አይገባም!
:
ጁወይቢር እንዲህ ይላሉ: ‐ «ኢማም ዲሕ‐ሓክን እንዲህ አልኳቸው: ‐ «በወር አበባ፣ በድህረ ወሊድ ደም (ኒፋስ)፣ በጉዞ ላይ የሚገኙ ወይም በመኝታ ላይ ያሉ ሰዎች የለይለቱል‐ቀድር ድርሻ አላቸው?»
እርሳቸውም: ‐ «አዎን! ማንኛውም አላህ ስራውን የተቀበለው ሰው ከለይለቱል‐ቀድር ድርሻውን አግኝቷል።»
📃 ለጧኢፉል‐መዓሪፍ፥ ገፅ 192

👍35❤17
በረመዳን የሴቶቹን ያህል የሚጾም የለም! እንደ ሴቶቻችን ምንዳው የበዛለትም የለም: ‐
⚀ የጾም ምንዳቸው እንዳለ ነው፤
⚀ ሁሌም ጾመኞችን እያስፈጠሩ ነው፤ አጅራቸው ብዙ ነው።
⚀ ሱሑር ይበላሉ፤ ባይበሉ እንኳን ስሑር የሚበሉ ጾመኞችን ይመግባሉ።
⚀ በዚያ ላይ ቤት ውስጥ በሚሰሯት እያንዳንዷ ስራ ምንዳ አላቸው።
:
እህቶች ሆይ! ሁሉንም በኒያ አድርጉት። አላህ የምትሰሩትን ያያል!

❤81👍15
ስምንቱ የዘካ ቡድኖች
ዘካ አሏህ ለጠቀሳቸው ስምንት ክፍለ ሰዎች የሚሰጥ ምፅዋት ነው፡፡ አላህ እንዲህ በማለት ዘርዝሯቸዋል፡-
{ إِنَّمَا الصَّدَقاتُ لِلفُقَراءِ وَالمَساكينِ وَالعامِلينَ عَلَيها وَالمُؤَلَّفَةِ قُلوبُهُم وَفِي الرِّقابِ وَالغارِمينَ وَفي سَبيلِ اللَّهِ وَابنِ السَّبيلِ فَريضَةً مِنَ اللَّهِ وَاللَّهُ عَليمٌ حَكيمٌ }[ التوبه: ٦٠ ]
«ግዴታ ምጽዋቶች (የሚከፈሉት) ለድኾች፣ ለምስኪኖችም፣ በርሷም ላይ ለሚሠሩ ሠራተኞች፣ ልቦቻቸውም (በእስልምና) ለሚለማመዱት፣ ጫንቃዎችንም (በባርነት ተገዢዎችን) ነጻ በማውጣት፣ በባለ ዕዳዎችም፣ በአላህ መንገድም በሚሠሩ፣ በመንገደኛም ብቻ ነው፡፡ ከአላህ የተደነገገች ግዴታ ናት፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡»
:
❶ ድኾች [ፉቀራእ]፡- “ፉቀራእ” ለአስፈልጎታቸው የሚበቃ መጠን ያለው የገቢ ምንጭ ወይም ገንዘብ የሌላቸው፣ ለምግብ፣ ለልብስ እና ለመኖሪያ ቤት የሚሆን የገንዘብ ዓቅም የሌላቸው ሙልጭ ያሉ ድኾች ናቸው፡፡
ለምሳሌ: ‐ ለመሰረታዊ ወጪዎች የሚያስፈልጋቸው አንድ ሺህ ብር ቢሆንም በዕለት የሚያገኙት ገቢ ግን ሦስት መቶ ብር ብቻ የሆነባቸው ሰዎች ናቸው፡፡
:
እዚህ ጋር ማስተዋል የሚገባን ነጥብ አለ። ኒካሕ ማድረግ መፈለግ ከዋና ዋና አስፈልጎቶች መካከል የሚቆጠር ነው። የድኾችን አስፈልጎት ስንገምት ኒካሕም መታሰብ አለበት።
❷ ምስኪኖች፡- እነዚህ ከድኾች የተሻሉ ናቸው። የተወሰኑ አስፈልጎቶቻቸውን [ለምግብ፣ ለልብስ እና ለመኖሪያ ቤት] የሚሸፍን መጠነኛ ገንዘብ አላቸው። ነገርግን በገቢያቸው ኑሯቸውን አሸንፈው መኖር የማይችሉ አይችሉም፡፡
ለምሳሌ፡- ለመሠረታዊ ወጪዎቻቸው የሚያስፈልጋቸው ገንዘብ አንድ ሺህ ብር ቢሆንም ገቢያቸው ግን ከስምንት መቶ ብር በላይ አይደለም፡፡ ከፉቀራእ የሚለዩት እነዚህ በመጠኑ የተሻለ ገንዘብ ማግኘት በመቻላቸው ብቻ ነው፡፡
❸ ሠራተኞች [አል-ዓሚሉን]፡- እነዚህ ዘካ ለድሆች በሚሰጥበት ሂደት ውስጥ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ላይ የተቀጠሩ የመንግስር ሠራተኞች ናቸው፡፡ ዘካውን ለመሠብሰብና ለማከፋፈል ለሠሩት ሥራ የሚመጣጠን ደመወዝ ከዘካው ገንዘብ ላይ ይከፈላቸዋል፡፡ ከደመወዛቸው በላይ አይጨመርላቸውም። ከሚሰበስቡት ገንዘብ ድርሻ የሚሆን በመቶኛ (በፐርሰንት) ወይም በሌላ አከፋፈል አይመደብላቸውም። ምክንያቱም የአላህ ድንጋጌ በዚህ መልኩ አልሰፈረም። ሠራተኞች (ዓሚሎች) እንደማንኛውም የዘካ ቤተሰብ አንድ የዘካ ቡድን ናቸው። ዘካው ላይ ተቀጥረው የሚሰሩበትን ደመወዝ በስራቸው ልክ ይሰጣቸዋል እንጂ ከዚያ በላይ ሊሞግቱ አይችሉም።
❹ “አል- ሙአለፋ” [ልቦቻቸው (በእስልምና) ለሚለማመዱት]: ‐ እነዚህ አዲስ ሰላሚዎች ናቸው። በእስልምና ውስጥ እንዲገቡ ያደረጋቸው ኒያ (ልበ‐ውሳኔ) ደካማ በመሆኑ ኢስላምን እስኪለምዱ ድጋፍ ይሆናቸው ዘንድ ከዘካ ይሰጣቸዋል፡፡
ወይም በህዝባቸው ዘንድ የተለየ ክብር የሚሰጣቸው ሙስሊሞች ሆነው ለነርሱ ከዘካ በመስጠት የነርሱ ቢጤ የሆኑ የህዝብ መሪዎች እንዲሰልሙ ሊያነሳሳ የሚችል ዝና ያላቸው ሰዎች ናቸው።
ወይም በሙስሊሙ የአደጋ ቀጠና ድንበር ላይ የሚኖሩ ሙስሊሞች ናቸው። ሙስሊሞችን ከሰርጎ ገብ የጠላት ጥቃት ወይም ከዓማፂ ሽፍታዎች የሚታደጉ የዳር ሀገር ሰዎች ናቸው። ወይም የዘካ ሠራተኞች ሊደርሱበት ከማይችሉበት ሩቅ ሀገር ዘካን ሰብስበው የሚያመጡ ሰዎች ናቸው።
እነዚህ የሙአለፋ ቡድኖች ዘካ የሚሰጣቸው ሙስሊሙ ህዝብ (መንግስት) እነዚህን የመንከባከብ አስፈላጊነት ሲኖርበት ብቻ ነው። አስፈላጊነታቸው ካበቃ የዘካ ድርሻቸውም ይታጠፋል።
❺ “ሪቃብ” [ጫንቃዎችን (በባርነት ተገዢዎችን) ነጻ በማውጣት]፡- እነዚህ በተለያዩ የክፍያ ቀጠሮዎች ገንዘብ በመክፈል ከባርነት ጫንቃቸውን ነፃ ለማድረግ የሚያበቃ ውል (ኪታባ) ከአሳዳሪዎቻቸው ጋር የተዋዋሉ ባርያዎች ናቸው፡፡ ሙካተብ ይባሉ ነበር። መክፈል ያቃታቸውን ያህል ገንዘብ ይሰጣቸዋል።
❻ ባለ ዕዳዎች [አል- ጋሪሙን]፡- የሰው ብድር ወይም ዕዳ ኖሮባቸው የክፍያ ቀን ቢደርስባቸውም መክፈል የተሳናቸው ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህ በእጃቸው ከቀለባቸው፣ ከልብስ እና ከቤት የተረፈ እዳቸውን መሸፈን የሚችል ገንዘብ ከሌላቸው እገዛ ይደረግላቸዋል። ነገርግን እዳው የተከሰተው ለሚፈቀድ ጉዳይ እስከሆነ ድረስ ብቻ ነው። ለማይፈቀድ ጉዳይ ከተበደሩ ዘካ አይሰጣቸውም። ነገርግን ከኃጢኣቱ ተውበት አድርገው ከተመለሱና ተውበታቸው ፅኑ እና እውነተኛ መሆኑ ከታመነበት ዘካ ይሰጣቸዋል።
ሰዎቹ ለግል ጉዳያቸው የተበደሩ ከሆነ ዕዳቸውን መክፈል የሚችሉበት ዓቅም ከሌላቸው ብቻ ከዘካ ድጋፍ ያገኛሉ፡፡ ነገርግን ሰዎችን ለማስታረቅ ብለው የሰዎችን ዕዳ የተሸከሙ ከሆነ እዳውን ለመክፈል የሚያስችል በቂ ኃብት ቢኖራቸውም እዳውን ከራሳቸው እስካልከፈሉ ድረስ ብቻ ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡ በራሳቸው እዳውን ከከፈሉ ግን ዘካ አይሰጣቸውም።
❼ በአላህ መንገድ ላይ [ፊሰቢሊላህ]፡- እነዚህ የመንግስት ተቀጣሪ ያልሆኑ፣ ከሙስሊሞች ግምጃ ቤት (በይቱል‐ማል) ድርሻ የሌላቸው ወዶ ዘማቶች (ሙጃሂድ/ጉዛት) ናቸው፡፡ ኃብት ቢኖራቸውም ለጂሃድ ዘመቻቸው የሚረዷቸውን መሣሪያዎችና ስንቅ የሚያሰናዱበት ገንዘብ ይሠጣቸዋል፡፡ የሚያስተዳድሯቸው ቤተሰቦቻቸውን ወጪም እስከሚመለሱ ድረስ ያለው ታስቦ ይሰጣቸዋል።
❽ የመንገድ ልጅ [እብኑስ‐ሰቢል]፡- እነዚህ በሸሪዓ ለተፈቀዱ ምክንያቶች ጉዞ የሚወጡ ሰዎች ናቸው፡፡ ለኃጢኣት ጉዳይ የሚጓዙ ሰዎች ዘካ አይሰጣቸውም። ነገርግን ኃጢኣት እስካልሆነ ድረስ ለመዝናናት ብለው የሚጓዙ ተጓዦችም ቢሆኑ ዘካ ይገባቸዋል። ለደርሶ መልስ ጉዟቸው የሚያስፈልገው ወጪ ይሰጣቸዋል። ለቀለብ፣ ለመጓጓዣ፣ እቃቸውን በራሳቸው መሸከም ካልቻሉ የእቃ መጫኛ ይሰጣቸዋል። ነገርግን ጉዟቸው ለኃጢኣት ታልሞ የሚደረግ ከሆነ ወይም በጉዟቸው መካከል በኃጢኣት ውስጥ ከተዘፈቁ ከዘካ ገንዘብ አይሰጣቸውም። ነገርግን ተውበት አድርገው ከተመለሱ እና ተውበታቸው እውነተኛ መሆኑ ከታመነ ይሰጣቸዋል።
እነዚህ ስምንት ቡድኖች የዘካ ቡድኖች ናቸው። ዘካ የሚገባው ለነዚህ ብቻ ነው። ድርሻ የሚጋራቸው ሌላ አካል የለም። ይህ ከላይ የጠቀስነው አንቀፅ የሚያስረዳው ነጥብ ነው።
ከዘካ ውጪ ያሉ ሱና (ትርፍ) ሶደቃዎችን ግን ከነዚህ ቡድኖች ውጪ ለሌላ አካልም መስጠት ይፈቀዳል።
*ዘካ የማይሠጣቸው ሰዎች*
ለአራት ሰዎች ዘካ መስጠት ክልክል ነው፡-
1. በእጁ ባለው ኃብት ወይም በየጊዜው ከሚሰራው ሥራ በሚያገኘው ገንዘብ የተብቃቃ ወይም መብቃቃት የሚችል ሰው ዘካ አይሰጠውም።
2. “በኑ ሃሺም”፡- “በኑ ሃሺም” የሚሰኘው የነቢዩ [ﷺ] ጎሳ ዘር አባል የሆነ ሰው ዘካ አይሰጠውም።
3. “በኑ ሙጦሊብ”፡- “በኑ ሙጦሊብ” የተሰኘው የነቢዩ [ﷺ] ዘመዶች ዘር የሆነ ሰውም ዘካ አይሰጠውም።
4. ከኢስላም ውጭ የሆነ ሰው፡- ሙስሊም ላልሆኑ ሰዎች ግዴታ የሆነውን ዘካ እና በተለያዩ ምክንያቶች ግዴታ የሚሆኑ ከፋራዎችን (ቤዛዎችን) መስጠት አይፈቀድም፡፡
ነገርግን ሱና ምፅዋትና በስለት (ነዝር) ምክንያት ግዴታ የሚሆኑ ምፅዋቶችን መስጠት ይፈቀዳል፡፡

❤16👍3
*ዘካ እንዴት ይከፋፈላል?*
ዘካ ከስምንቱ ቡድኖች በዘካው ሀገር ላይ ለተገኙት አካላት ይከፋፈላል።
ሁሉም በስፍራው ከተገኙ ዘካውን ለስምንቱም ማዳረስ ግዴታ ነው። አንድኛውም ቡድን ሳይሰጠው ሊቀር አይፈቀድም።
አንዱ ቡድን በቦታው ከሌለ የርሱ ድርሻ ለቀሩት ቡድኖች በእኩል እንዲካፈል ይደረጋል።
የአንዱ ቡድን ድርሻ ካለው አስፈልጎት ወይም ከቡድኑ አባላት አንጻር ከተትረፈረፈ የቀረው ለሌሎቹ ቡድኖች በእኩል እንዲካፈል ይደረጋል።
ዘካው በአካባቢው ለሚኖሩት ስምንቱ ቡድኖች በእኩል ይከፋፈላል። ቡድኖቹ የተለያየ የአስፈልጎት መጠን ቢኖራቸውም በእኩል ማከፋፈል ግዴታ ነው።
ከስምንቱ ግን የዓሚሎች (የዘካ ሰራተኞች) ይለያሉ። ለነርሱ የሚሰጣቸው በአስፈልጎታቸው ልክ ሳይሆን ለስራቸው የሚመጥን ደመወዛቸውን ነው። ድርሻቸው የሚሰጣቸውም ዘካው ለሌሎች ከመከፋፈሉ በፊት ነው።
በአንድ ቡድን ውስጥ ያሉ ሰዎችን በእኩል ድርሻ ማከፋፈል ግዴታ አይደለም። ማበላለጥ ይፈቀዳል።
ባለንብረቱ (ባለዘካው) በራሱ ወይም በወኪሉ በኩል ካከፋፈለና የዘካ ተቀባዮቹ ቁጥር በጣም ጥቂት ሆነው ለሁሉም የሚዳረስ እስካልሆነ ድረስ ከእያንዳንዱ ቡድን በትንሹ ለሦስት ሰው መስጠት አለበት። ይህ የሆነው ከላይ በተጠቀሰው አንቀጽ ውስጥ እያንዳንዱ ቡድን የተጠቀሰው በብዛት ገላጭ ስሙ (ጀምዕ) በመሆኑ ነው። አነስተኛው የብዛት ገላጭ (የጀምዕ) መጠን ደግሞ በሦስት ይወከላል።
ነገርግን ቁጥራቸው ውስን በመሆኑ በተለምዶ ማንነታቸውን መለየት የሚቻል ያክል ከሆነ እና ዘካውም ለሁሉም የዘካ ተቀባዮች ፍላጎት የሚበቃ መጠን ካለው ለሁሉም ማዳረስ ግዴታ ይሆናል። እያወቀ ወይም ሆነ ብሎ አንዳቸውን ከተወ የተወሰነ መጠንም ቢሆን ለሰውየው የመክፈል ግዳጅ አለበት።
አላሁ አዕለም!

❤16👍8
Forwarded from Tofik Bahiru
ለይለቱል-ቀድር
(ክፍል አንድ)
በተውፊቅ ባህሩ
🌙🌙🌙🌙🌙
ለይለቱል-ቀደር የውሳኔዋ/የመወሰኛዋ ሌሊት ማለት ነው፡፡ የዓመቱ የአላህ ውሳኔዎች ተፈጻሚ ይሆኑ ዘንድ ወደ ወደ ምድር የሚተላለፉባት ሌሊት ናት፡፡ ለይለቱል-ቀድርም ትባላለች፡፡ ታላቅ ክብር ያላት ሌሊት ማለት ነው፡፡
:
ሌሊቷ የምታርፍበት ቀን መቼ በመሆኑ ላይ በርካታ የተለያዩ የዑለማእ ሃሳቦች አሉ፡፡ ኢማም ኢብኑ ሐጀር 'ፈትሑል-ባሪ' ላይ አርባ ስድስት አድርሰዋቸዋል፡፡ ሐፊዙል-ዒራቂ ሃያ አምስት የዑለሞችን ሃሳብ ቆጥረዋል፡፡ አንዳንዶች ስድሳ ሃሳቦችን ዘርዝረዋል፡፡ የሃሳብ ልዩነቶቹ የመነጩት ከነቢዩ [ﷺ] የተዘገቡ በርካታ ሐዲሶች ሰነድና ትርጉም መለያየት የተነሳ ነው፡፡
:
አመቱን ሙሉ በሚኖሩት ሌሊቶች ውስጥ በማንኛውም ሌሊት ውስጥ ልትሆን ትችላለች ይላሉ፤ ሐነፊዮች፡፡ ከዐብዱላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዐ) የተዘገበውን ሐዲስ ይዘው፡፡
በረመዳን ወር ውስጥ በሚኖሩት በማናቸውም ሌሊቶች ውስጥ ናት ያለችው የሚሉም አሉ፡፡ ኢማም አቡሐኒፋ፣ ኢብኑል-ሙንዚርና አንዳንድ ሻፊዒዮች ይህንን ይደግፋሉ፡፡ ከሻፊዒዮች ኢማም ሱቡኪም ይህንን ደግፈዋል፡፡ ከአቡሁረይራ፣ ከአቡዘር፣ ኢባኑ ዐባስ (ረ.ዐ.) ተመሳሳይ ሃሳብ ተዘግቧል፡፡
አስራ ሰባተኛው ሌሊት ነው የሚል አለ፡፡ ሃያ አንደኛው ሌሊት ነው የሚልም አለ፡፡ ኢማም ሻፊዒይ ወደዚህ ሃሳብ አዘንብለዋል፡፡ በርካታ ሻፊዒዮች በዚህ ሃሳብ ቆርጠዋል፡፡ ሃያ ሦስተኛው ሌሊት ነው የሚሉም አሉ፡፡ በዚች ሌሊት ዓኢሻ (ረ.ዐ.) ቤተሰባቸውን ይቀሰቅሱ ነበር፡፡ ሃያ አራተኛው ሌሊት ነው የሚል የኢብኑ ዐባስ (ረ.ዐ.) አንድ ዘገባ አለ፡፡ ሃያ ሰባተኛው ነው፤ ሃያ ዘጠነኛው ነው፤… በርካታ ሃሳቦች ናቸው፡፡
:
አብዝሃኞቹ ልሂቃን በመጨረሻዎቹ ዐስርት የረመዳን ቀናት ውስጥ እንደምትገኝ ያምናሉ፡፡ የአላህ መልክተኛም (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ለይለቱል-ቀድርን አላህ አሳየኝ፤ ከዚያም ግን እንድረሳት ተደረግኩኝ፡፡ በዐስሩ የመጨረሻ የረመዳን የመጨረሻ ሌሊቶች ላይ ፈልጓት፡፡››
በዚህ ሃሳብ ላይ የሶሐቦች ስምምነት መገኘቱ ተዘግቧል፡፡ ከዐብዱር-ረዛቅ ከኢብኑ ዐባስ (ረ.ዐ.) እንደተዘገበው ‹‹ዑመር (ረ.ዐ.) የነቢዩ (ﷺ) ባልደረቦችን ጠሩና ስለ ለይለቱል-ቀድር ጠየቋቸው፡፡ ሁሉም በዐስሩ የመጨረሻ የረመዳን ቀናት ውስጥ እንደምትገኝ ተስማሙ፡፡››
በተለይም በነዚህ ቀናት ነጠላ ሌሊቶች ውስጥ ሌሊቷን መፈለግ ተመራጭ ነው፡፡ ሃያ አንደኛው፣ ሃያ ሦስተኛው፣ ሃያ አምስተኛው፣ ሃያ ሰባተኛው እና ሃያ ዘጠነኛው ሌሊት ላይ ማለት ነው፡፡ የአላህ መልክተኛ (ﷺ) ‹‹በዐስሩ የመጨረሻ የረመዳን ቀናት ነጠላ ሌሊቶች ላይ ፈልጓት፡፡›› ብለዋል፡፡ በሌላ ሐዲስ የአላህ መልክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹በመጨረሻዎቹ የረመዳን ቀናት ላይ ፈልጓት፡፡ በቀሩት ዘጠኝ ቀናት፣ በቀሩት ሰባት ቀናት፣ በቀሩት አምስት ቀናት ፈልጓት፡፡››
:
ባይሆን ይህንን ሐዲስ በመያዝ ኢብኑ በጥ—ጧል እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹በዚህ ሐዲስ መሰረት ለይለቱል-ቀድር ነጠላ ሌሊቶች ላይ የምታርፈው ወሩ ጎዶሎ (በ29 ቀን የሚያልቅ) ሲሆን ነው፡፡ ወሩ ሙሉ ሆኖ በ30 ቀናት ካለቀ ግን ለይለቱል-ቀድር የሚያርፈው ሙሉ ቁጥር ባላቸው ሌሊቶች ላይ ነው፡፡ የቀሩት ዘጠኝ ቀናት ሲባል ሃያ ሁለተኛው ሌሊት ላይ፣ የቀሩት አምስት ቀናት ሲባል ሃያ ስድስተኛው ሌሊት፣ በቀሩት ሰባት ቀናት ሲባል ሃያ አራተኛው ሌሊት ላይ ሊታሰብ ይችላል፡፡ ይህ አቆጣጠር ቡኻሪ ዘንድ ከኢብኑ ዐባስ (ረ.ዐ.) ተጠቅሷል፡፡ በዚህ መሰረት ቆጠራው ነጠላ ቁጥርን አያገኝም፡፡ ስለዚህ ለይለቱል-ቀድር በአስርቱ የመጨረሻ የረመዳን ቀናት ሌሊቶች ላይ እየተለዋወጠ ያርፋል ማለት ይቻላል፡፡ ምክንያቱም የአላህ መልክተኛ (ﷺ) ሙሉም ሆነ ጎዶሎ በሆነ ወር ላይ ለይለቱል-ቀድርን እንድንፈልግ አዘውናል፡፡ አላህ ደግሞ ወሩን አንዴ ሙሉ አንዴ ጎዶሎ እየሆነ እንዲለዋወጥ አድርጎ ወስኖታል፡፡ ስለዚህ ለይለቱል-ቀድር በዐስርቱ የመጨረሻ የረመዳን ቀናቶች ላይ ባሉት ሌሊቶች ላይ እየተዘዋወረ ያርፋል ማለት ነው፡፡››
በዚህ ትንተና መሰረት ለዐስሩ ሌሊቶች በሙሉ ሙሉ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ማስተዋል ይቻላል።
"የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ዐስሩ የረመዳን የመጨረሻ ቀናት ሲገባ ሌሊቱን በሙሉ ህያው ያደርጋሉ። ቤተሰቦቻቸውን ይቀሰቅሳሉ። ሽርጣቸውን ያጠብቁም ነበር።"
:
ሃያ ሰባተኛው ሌሊት ለየት ያሉ በርካታ ዘገባዎች ስለተገኙበት አብዝቶ የሚከጀል ሌሊት ነው፡፡ የአላህ ነቢይ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹በመጨረሻዎቹ የረመዳን ዐስርት ቀናት ላይ ፈልጓት፡፡ በተለይ በዘጠነኛው፣ በሰባተኛው እና በአምሰተኛው ላይ፡፡››
ኡበይ ኢብኑ ከዕብ ለይለቱል #ቀድር ሃያ ሰባተኛው ሌሊት እንደሆነች ምለው ተናግረዋል፡፡
:
ለይለቱል—ቀድር የምታርፍበት ቀን ተለይቶ አለመታወቁ ጥቅም አለው። ኢማም ኢብኑ—ሐጀር ፈትሑል—ባሪ ላይ እንዲህ ይላሉ: — "ለሊቷ የተደበቀችበት ጥበብ ሰዎች አንዱን ሌሊት ከሌላው ሳይለዩ በአምልኮ ተግባራት ላይ ትግል እንዲያደርጉ ነው። ሌሊቷ ተለይታ ብትታወቅ ኖሮ ሰዎች እርሷን ብቻ ለይተው አምልኮ በማድረግ በሌሎቹ ቀናት ይሳነፉ ነበር።"
:
ቡኻሪ ከዑባዳ ኢብኑ ሷሚት [ረዐ] እንደዘገቡት "የአላህ መልክተኛ (ﷺ) ለይለቱል—ቀድር የትኛዋ ሌሊት እንደሆነች ሊናገሩ ወደ ሰዎች ወጡ። ከዚያም ሁለት ሰዎች ሲደባደቡ አገኙና እንዲህ አሉ: — "ለይለቱል—ቀድር የትኛዋ ሌሊት እንደሆነች ልነግራችሁ ወጥቼ ነበር። ከዚያም እገሌና እገሌ በመደባደባቸው እውቀቱ ተነሳ። ምናልባት አለመታወቁም መልካም ሳይሆን አይቀርም። በሃያ ዘጠኝ፣ በሃያ ሰባትና በሃያ አምስት ላይ ፈልጓት።"
:
ለይለቱል-ቀድር ውስጥ ምን አለ?
==================
ለይለቱል-ቀድር ከአንድ ሺህ ወራት የበለጠች ሌሊት ናት፡፡ አንድ ሺህ ወር ማለት 83 ዓመት ይሆናል፡፡ ረዥም የሰው #ልጅ ዕድሜ ነው፡፡ ብዙዎቻችን ከስድሳ ዓመት በታች እንሞታለን፡፡ ለይለቱል-ቀድር ግን በትሩፋቱ ረዥም የዕድሜ ባለጸጋ ያደርገናል፡፡
:
ሌሊቱን በአምልኮ፣ በተማጽኖ፣ አላህን ለማወቅ በማስተንተን እና ውሳኔውን ለመቀበል በሚኖር ቁርጠኝነት ሌሊቱን እናሳልፋለን፡፡
በለይለቱል-ቀድር የአላህ ውሳኔን እናስባለን፡፡ #በቀደር ላይ ያለንን እምነት እናድሳለን፡፡ በአላህ መተማመናችን ይጨምራል፡፡ በምድር ላይ ያለውን የአስተዳዳሪነት ሚና እንቀበላለን፡፡ ጽናትና መተማመናችን ይጨምራል፡፡ ሰዎች የሚፈሩትን አንፈራም፡፡ ሲስገበገቡም እንጨመታለን፡፡ ውሳኔ ሁሉ ከአላህ መሆኑን ስለተቀበልን የልብ እርጋታ እናገኛለን፡፡ አዕምሮኣቸን ይሰክናል፡፡ የአላህ መልክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹አንድ ሰው ያገኘው ነገር ቀድሞውንም ሊያጣው እንዳልነበረ ያጣውም ነገር ሊያገኘው እንዳልነበረ ሳያምን እውነተኛ የእምነት ደረጃ ላይ አይደርስም፡፡››
:
ሌሊቷ በአንድ ስሟ ለይለቱል-ቀድር (የተከበረች ሌሊት) ናት፡፡ የአላህን ክብር ታስታውሰናለች፡፡ ሁሉም ደካማ እርሱ ብቻ ኃያል እንደሆነ እንድናስብ ታደርገናለች፡፡ በርሱ በረከትና እዝነት እንጂ አምልኳችን የርሱን ልቅና እንደማይመጥን ታስታውሰናለች፡፡ ለአምልኮ በመመረጣችን እንድናመሰግነውም ታነሳሳናለች፡፡
http://www.tg-me.com/fiqshafiyamh

❤9👍3
Forwarded from Tofik Bahiru
ለይለቱል‐ቀድር
(ክፍል ሁለት)
🌙🌙🌙🌙
ለይለቱል-ቀድር ላይ ምን እናድርግ?
=====================
ለእያንዳንዱ ሰከንድ ዋጋ እንስጥ፡፡ ያለንበት #ሌሊት ከአንድ ሺህ ወራት በላይ የሆነ ሌሊት ነው፡፡ በውስጡ ያሉት እያንዳንዳቸው ሰከንዶች ምን ያህል ቀናት ሊሆኑ እንደሚችሉ እናስላው፡፡ አንድ ረከዓ ሰማንያ ሦስት ዓመት ከአራት ወር እንደተሰገደ ይቆጠራል፡፡ ሌሎች የአምልኮ ዘርፎችም እንደዚያው፡፡
ሌሊቱን በሶላት ማስዋብ ተወዳጅ ነው፡፡ የአላህ መልክተኛ (ﷺ) ‹‹ለይለቱል-ቀድርን በአላህ አምኖና ምንዳውን ከርሱ ብቻ ከጅሎ በሶላት የቆመው ሰው ያሳለፈውን ኃጢኣት ምህረት ያገኛል፡፡››
ዱዓ ማብዛትም ይወደዳል፡፡ ሱፍያን ሰውሪይ እንዲህ ይላሉ፡- ‹‹በለይለቱል-ቀድር ላይ ሶላት ከመስገድ ይልቅ ዱዓ ማብዛት እመርጣለሁ፡፡›› በተለይም የአላህ መልክተኛ (ﷺ) እናታችን ዓኢሻን ያስተማሯቸው ዱዓ ለዕለቱ የተመረጠ ዱዓ ነው፡፡ ‹‹አል-ላሁም-መ ኢን-ነከ ዐፉው-ዉን ቱሒብ-ቡል-ዐፍወ ፈዕፉ ዐን-ኒ፡፡›› (አላህ ሆይ! አንተ ይቅር ባይ ነህ፡፡ ይቅር ማለትን ትወዳለህ፡፡ ይቅር በለኝ፡፡)
ኢብኑል-ቀዪም (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ማንም ሰው በአላህ ይቅርታና ምህረት ካልሆነ በቀር መድኅን የለውም፡፡››
:
ስለዚህ ይቅርታውን ለማግኘት #መድረሻ እንዳጣ ችግርተኛ በልቅናው ምንጣፍ ላይ ተዘርጋና እንዲህ በለው፡፡
:
ኢላሂ! በዚች በውሳኔዋ ሌሊት ለምርጥ ባሮችህ የምትሰጠውን መልካም ነገር ሁሉ ስጠኝ! ከክፉ ነገሮች በሙሉ ጠብቀኝ!
ኢላሂ! በዚህ ሌሊት ከእሳት ነፃ የምታደርጋቸው ባሮች አሉህ። እኔንም ከነርሱ መድበኝ!
ኢላሂ! አውቄም ሆነ ስቼ የፈጸምኩትን ሁሉ ማረኝ! የረሳሁትንም ሆነ የማስታስሰውን ወንጀሌን ይቅር በለኝ!
ኢላሂ! ካንተ የሚያርቁኝን ነገሮች ሁሉ አርቅልኝ! ወዳንተ የሚያቀርቡኝን ነገሮች በሙሉ አግራልኝ!
ኢላሂ! የዱንያም ሆነ የአኺራ ጉዳዮቼን ካንተ ውጪ ለብቻዬ ማሳካት አልችልም። ጌታዬ ሆይ ከጎኔ ሁን!
:
ነገርግን የለይለቱል-ቀድርን ትሩፋት ከተነፈጉት ሰዎች እንዳትሆን፡-
1) አልኮል መጠጣት የሚያዘወትር
2) ወላጆቹን የሚበድል
3) ከወንድሙ ጋር ቂም የተያያዘ ሰው

👍18❤2
Zakat Al fitr 2023.pdf
3.5 MB
ታላቁ የዒራቅ ዓሊም የኢማማችን ሻፊዒይ ሸይኽ ኢማም ወኪዕ እንዲህ ብለዋል: ‐ «ለወርሀ ረመዳን ዘካቱል‐ፊጥር ማለት ለሶላት የመርሳት ሱጁድ ማለት ነው። የመርሳት ሱጁድ የሶላቱን ጉድለት እንደሚጠግነው ዘካቱል‐ፊጥርም የጾሙን ጉድለት ይጠግነዋል።»
:
ይህንን ፅሁፋችንን በማንኛውም መንገድ አሰራጩ። በግልም ሆነ በጀመዓ ተማማሩበት። ዒባዳችሁን በእውቀት አድርጉት። አላህ ስራዎቻችንን ይቀበለን!

👍31
ዘካን በውክልና ማከፋፈል
ለዘካቱል‐ፊጥር የሚደረግን እህል በመግዛትም ሆነ፣ የዘካን ገንዘብ ለሚገባቸው ሰዎች በማከፋፈል ሥራ ላይ ዘካ ሰጪው ሌላን ሰው መወከል ይችላል።
ኢማም ነወዊይ "አል‐መጅሙዕ" በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ እንደገለፁት ይህ የልሂቃን ልዩነት የሌለበት ሙሉ የመዝሀባችን ሰዎች የተስማሙበት ሃሳብ ነው።
«ዒባዳ (የአምልኮ ተግባር) ከመሆኑ ጋር ውክልና የተፈቀደው በባህሪው [ዘካ] እዳን ከመክፈል ጋር ይመሳሰላል። በተጨማሪም ገንዘቡ ዘካ አውጪው ካለበት አካባቢ ሩቅ መሆኑ እና ሌሎችም ምክንያቶች አሉ።»
ማወከል ቢፈቀድም ቅሉ ሰውየው ራሱ ዘካውን ማከፋፈሉ በላጭ ወይም ተመራጭ ነው። ይህ ቤተሰብ ስለ ዘካ እንዲያውቅ፣ በረከቱን አንዲቋደስ፣ በማከፋፈል ስራው ላይ እንዲሳተፍ በር ይከፍታል። ድምቀቱንም በቤት ውስጥ ያስተጋባል። ምናልባት ከጊዜ በኋላ ስለ ዘካ የማያውቅ እና አተገባበሩን ያልተረዳ ትውልድ አንዳይፈጠርም ይታደጋል።
ኢማም ነወዊይ [ረሒመሁላህ] እንዲህ ይላሉ: ‐
«ባልደረቦቻችን (ሻፊዒዮች) እንዲህ ብለዋል: ‐ «ሌላን ሰው ከመወከል ዘካቱል‐ፊጥርን በራስ ማከፋፈል ይበልጣል። በዚህ ላይ ልዩነትም የለም። ምክንያቱም ሰውየው በትክክል መከፋፈሉን ማረጋገጥ ይችላል። ወኪል ሲሆን ግን በትክክል መከፋፈሉ ላይ እርግጠኛ መሆን ሊቸግረው ይችላል። ተወካዩ አደራውን ክዶ ሳይሰጥ ቢቀር ከባለ ዘካው ላይ ግዳጁ አይወድቅም። ምክንያቱም የወኪሉ እጅ እንደ ባለ ዘካው እጅ ነው። ለባለ ሐቆቹ ዘካው እስካልደረሰ የባለ ዘካው ጫንቃም ከእዳው አይጠራም።»
በዚህ መሰረት ሰውየው ዘካውን ለግለሰብ ወይም ለድርጅት ቢሰጥ ለተወካዩ አካል በመስጠቱ ብቻ ጫንቃው ከግዳጁ አይጠራም። ወኪሎቹ በተገቢው ጊዜ ለባለ ሐቆች መስጠት ይጠበቅባቸዋል። ስለዚህ ወኪሉ ዘካውን ተቀብሎ በእጁ ላይ ቢያቆይ እና ለተገቢዎቹ ሰዎች በተገቢው ጊዜ ሳይሰጥ ቢቀር ክልክል የሆነ ነገር ተከስቷል። ዘካው የወጀበበት ሰው ጫንቃም ከግዳጁ አይጠራም።
ዘካው መዘግየቱን ዘካ አውጪው የሚያውቅ ከሆነ ደግሞ ወንጀል አለበት። ካላወቀ ግን ወንጀል አይኖርበትም። በወኪሉ እጅ እንዳለ ዘካው ቢወድም በእሱ እጅ እያለ ቢወድም እንደሚያደርገው በቦታው የድሆቹን ሐቅ መተካትና ለሚገባቸው አካላት ማድረስ ይጠበቅበታል።

👍15❤5
ታላቁ ታቢዒይ አቡ ዐብዲር‐ረሕማን አስ‐ሱለሚይ [ረሒመሁላህ] እንዲህ ይላሉ: ‐
«ዐብዱላህ ኢብኑ መስዑድ [ረዲየላሁ ዐንሁ] ከጁሙዐ በፊት አራት ከበስተኋላዋ አራት እንድንሰግድ ያዙን ነበር።»
ዐብዱረዛቅ "አል‐ሙሶነፍ" በተሰኘው ኪታባቸው ዘግበውታል። አል‐ሀይተሚይ "ዘጋቢዎቹ ታማኞች ናቸው።" ብለዋል።…
ይህ የሱፍያን ሰውሪይ፣ የዐብዱላህ ኢብኑል‐ሙባረክ እና የሌሎቹም የሰለፍ ልሂቃን መዝሀብ ነው። ጁሙዐ እንደ ዙህር ከበስተፊቷ አራት ከበስተኋላዋ አራት ረከዐ ሱና አላት። «ሶላት [በአላህ] ከተደነገጉ ዒባዳዎች ሁሉ ምርጧ ናት!»
ባረከላሁ ፊኩም!

❤11👍11
አሁን የመስጂዳችን ኢማም ታላቁ ዓሊም ሸይኽ መኑል‐ከሪም [አላህ ያቆያቸው] ሲናገሩ እንደሰማሁት (ስለ ዘካቱል‐ፊጥር ሰፊ ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ): ‐
— ዘካቱል‐ፊጥርን በገንዘብ መስጠት የኢማም አቡ ሐኒፋና የተወሰኑ ልሂቃን መዝሀብ ነው።
— አብዝሃኞቹ ልሂቃን ዘካቱል‐ፊጥር በእህል እንደሚሰጥ ያምናሉ።
— ከዚህ ቀደም በገንዘብ ምን ያህል እንደሚደርስ እናገር ነበር። አሁን ግን የተለያዩ ዋጋዎች ስለደረሱኝ መወሰን አልቻልኩምና በራሳችሁ ዋና አጣርታችሁ የሁለት ኪሎ ተኩል ስንዴ ዋጋ ስጡ።
🔴 ወንድማችሁ (ተውፊቅ ባህሩ) የገበያውን ዋጋ አጣርቶ አማካዩን በመያዝ የሁለት ኪሎ ተኩል ስንዴ ዋጋ በአማካይ 237.5 ሳንቲም እንደሚመጣ ገምቷል።
—ለነገሩ ሸይኻችንም ለመጠንቀቅ 250 ብር አውጡ ብለዋል።

❤58👍18
«እኔ ስሜ ዐመር አል‐ጀማሲይ ይባላል። ስሙ ዐብዱል‐ከሪም አን‐ነይረብ የሚባል ልጅ አንድ ሼክል እዳ አለብኝ። ዐብዱል‐ከሪም አቡ ናፊዝ ጎዳና አካባቢ የሚኖር ልጅ ነው።…
እኔ እወዳችኋለው። ሶላት እንዳትተዉ አደራ እላለሁ። ቁርኣን መቅራት እና ኢስቲጝፋር ማድረግ እንዳትተዉ!»
ይህ በቅርብ ከነቤተሰቡ የተሰዋ የጛዛ ህፃን ወሲያ ነው።…
አላህ ከመከራው ያውጣቸው። ቁስለኞቻቸውን ያሽር። ታጋዮቻቸውን ይርዳ። ትግላቸውን ፍሬያማ ያድርገው።
በዱዓ አትርሷቸው!

❤54😢24👍4
የመጨረሻው የረመዳን ሌሊት:
የኢማም አሕመድ [ሙስነድ] የተሰኘው መጽሐፍ ላይ ከሰይዲና አቡሁረይራ [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንደተዘገበው የአላህ ነቢይ [ﷺ] እንዲህ አሉ: ‐
«[በረመዳን] በመጨረሻው ሌሊት [ለህዝቦቼ] ሁሉ ምህረት ይደረግላቸዋል።»
ሰዎችም: ‐ «ለይለቱል‐ቀድር እርሷ ናት?» በማለት ጠየቁ።
እርሳቸውም: ‐ «በፍፁም! ነገርግን [ተቀጣሪ] ሠራተኛ ሥራውን ሲጨርስ ደመወዙ ይሰጠው የለ?!» በማለት መለሱ።»
:
አላህ ሆይ! ሥራዎቻችንን ውደድልን። በእዝነትህ ሸፍነህ ካለብን ክፍተት ጋር ተቀበለን!

❤86👍15😢9