ቀናችንን በኢስቲግፋር ድምቀት እንጀምረው!…
ከአቡ ሙሳ አል‐አሽዓሪይ እንደተዘገበው የአላህ መልክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል: ‐
«ምን ጊዜም ንጋት ላይ በጠዋት መቶ ጊዜ ኢስቲግፋር ሳላደርግ ቀርቼ አላውቅም።»
https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh

❤35👍7
Tofik Bahiru
ASHURA 1447.pdf
ዐሹራ ነገ ነው። የቻልን ነገን እና ከነገ ወዲያን ጨምረን እንፁም። ስለ ዐሹራ ለልጆቻችን እንንገር። እንተዋወስ!
በዱዓ እንበርታ። ከአላህ በቀር ምንም ያልነበራቸውን ሰይዲና ሙሳ [ዐለይሂ ሰላም] ከዘመናቸው አምባገነን ጉልበተኛ ያዳነና ድል የሰጠ ጌታ ከርሱ በቀር ምንም የሌላቸውን የዘመናችን ድኩማንን ከጨቋኞቻቸው አድኖ ድሉን ይስጣቸው እያልን እንለምን።

❤78👍2
ወላጆች በልጆቻቸው ላይ ሐቅ እንዳላቸው ሁሉ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ የተጣለ መብት አላቸው።
ልጅ የተሰጣችሁ ወዳጆች!
አባቶች፣ እናቶች!
የልጆቻችሁን አካላዊ ፍላጎት ማሟላት ብቻ በቂ አይደለም። መብልና መጠጥ መድኅናቸውን አይጠብቅም። ስኬታቸውን አያረጋግጥም።
አካላዊ ፍላጎታቸውን ከማሟላት የላቀ ሌላ አሳሳቢ ግዴታ አለባችሁ። የሩሕ ቀለባቸውን የማቅረብ፣ የአኺራ ስንቃቸውን መስጠት አለባችሁ። ዲን እና ስነምግባር እንዲኖራቸው መርዳት ግዴታችሁ ነው!
ልጆቻችሁን ለእሳት ትታችሁ የምትድኑት እሳት አይኖርም!
:
«እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከኾነች እሳት ጠብቁ፡፡ በእርሷ ላይ ጨካኞች፣ ኀይለኞች የኾኑ መላእክት አልሉ፡፡ አላህን ያዘዛቸውን ነገር (በመጣስ) አያምጹም፡፡ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ፡፡»
ሱረቱ ተሕሪም፥ አንቀጽ 06

❤42😢4
«ከሙስሊም ላይ አንድን ጭንቀት ያስወገደ ሰው አላህ ከቂያማ ጭንቀቶች አንድን ጭንቀት ይገላግለዋል።»
የአላህ መልክተኛ [ሰለላሁዐለይሂ ወሰለም]፥ ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
:
ኢማም ነወዊይ [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንዲህ ይላሉ: ‐
«ጭንቅን ማስወገድ በገንዘብ ሊሆን ይችላል። በዝናና በክብሩ በመጠቀምም ሊሆን ይችላል፤ ወይም በአካላዊ እገዛም ሊሆን ይችላል። በሃሳብ፣ በምክር እና መላ በመስጠት ማገዝም ጭንቅን የማስወገጃ አካል መሆኑ ግልፅ ነው።»
ሸርሑ ሶሒሕ ሙስሊም፥ ቅጽ 16፥ ገጽ 135
:
መተጋገዝ የግድ የሀብታሞች ብቻ አይደለም። ባለን ነገር መተጋገዝ መልካም ነው!
አላህ ያግራልን!

❤82
ዝናብ ሲጥል የሚደረግ ዱዓ
==================
ዝናብ የአላህ እዝነትና ትሩፋት ምልክት ነው። ዝናብ የሚጥልበት ሰዓት ዱዓ ተቀባይነት ከሚያገኝባቸው ጊዜያት አንዱ ነው።
ተወዳጃችን [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ሁለት ዱዓዎች አይመክኑም። በአዛን ጊዜ የሚደረገው ዱዓ እና ዝናብ ሲዘንብ የሚደረገው ዱዓ።» ሓኪም ዘግበውታል።
:
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ዝናብ ሲዘንብ የሚያዘወትሩት ዱዓ አለ: ‐
"اللهم صيبا نافعا"
ንባብ: ‐«አል‐ላሁም‐መ ሶይ‐ዪበን ናፊዓን»
ትርጉም: ‐ «አላህ ሆይ ጠቃሚ ዝናብ አድርገው።»
:
ክረምታችን ረሕመት የሚወርድበት ዘመን ይሁንልን!

❤49👍6
«በማይመለከትህ ነገር ውስጥ ገባህ፤ የሚመለከትህን ነገር ከመመልከት አገደህ። የሚመለከትህ ነገር ላይ ብትጠመድ ኖሮ የማይመለከትህን ነገር ትተው ነበር።»
ኢማም ፉደይል ኢብኑ ዒያድ [ቀደሰላሁ ሲረሁ]
ኢማም ፉደይል ኢብኑ ዒያድ [ቀደሰላሁ ሲረሁ]
❤83😍7👍5
ሰይዲና አቡ በርዛ [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንዲህ በማለት የአላህ መልክተኛን [ﷺ] ጠየቁ:‐
«የአላህ ነቢይ ሆይ! የምጠቀምበትን አንድ ነገር አሳውቁኝ!»
የአላህ መልክተኛም [ﷺ] እንዲህ አሉ:‐
«ሰዎችን የሚያስቸግሩ ነገሮችን ከመንገድ ላይ አስወግድ!»
:
በተለይ በክረምት ወራት በየመንደራችን ሰውን በጎርፍ የሚያሰቃዩ መንገዶችን አስቧቸው። የአንዳንዶቹ ሰበብ በጥቂት ስራ ቱቦዎቹን በመነካካት ብቻ ሊፈቱ የሚችሉ ችግሮች ናቸው።
"መልካም ነገሮች ሁሉ ምጽዋት ናቸው።" በሚለው የዲናችን ትምህርት መሠረት በቸላተኝነት የምናልፋቸው ምጽዋቶችን ለማስታወስ ያህል ነው።
አላህ ያበርታን!

❤76👍5
የአላህ ወልዮች የአላህን ፍጥረት ከአላህ ጋር የሚያስተሳስሩ ሰንሰለቶች ናቸው።
ከአቡየዚድ አል‐ቡስጧሚ [ቁዲሰ ሲሩሁ] እንደተዘገበው:‐
«መጅሊሳቸው ላይ ሰዎች ሲንጋጉ ተመለከቱ። መልካም የአላህ ባርያ መሆናቸውን አምነው በውዴታ ስሜት ወደርሳቸው ይጎርፉ ነበር።…
…እጃቸውን ለዱዓ አነሱ። አላህን እንዲህ አናገሩት:‐
«አላህ ሆይ! እነዚህ ሰዎች አንተን ፈልገው እኔ ዘንድ እንደሚመጡ ታውቃለህ። የሚወዱትም አንተን ነው። ነገርግን እኔን በደጃፍህ ጉበን ላይ ተንጠልጥዬ አግኝተውኝ ነው የከበቡኝ። አንተ እንድትቀበላቸው ይከጅላሉ። ወዳንተ መግባትም ይሻሉ።»

❤81👍5
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል:‐
«አንድ ሰው ሌላ ሰውን ስለሰደበ በአጸፋው ሰውየው ደግሞ ሙሉ ጎሳን መሳደቡ ከቅጥፈት ሁሉ የከበደ ቅጥፈት ነው።»
ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።
:
🔴 የግለሰብን ጥፋት ስህተት በሌሎች ንጹሐን ላይ ማላከክ ራሱን የቻለ የኃጢኣት ዓይነት ነው! በዚህ ዘመን ደግሞ እየተንሰራፋ ነውና ተጠንቅቀን እናስጠንቅቅ!

❤63
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል:‐
«ልክ ልብስ እንደሚያረጀው ኢማንም በአንዳችሁ ሆድ ውስጥ ያረጃል። አላህ ኢማናችሁን እንዲያድስላችሁ ለምኑት።»
ጠበራኒይ እና ሓኪም ዘግበውታል።

❤62👍6
Forwarded from የረሕማን ስጦታ
«አንቺ አላህ ዘንድ ተወዳጇ ሀገር ነሽ። እኔም ዘንድ ተወዳጅ ሀገር ነሽ። ሙሽሪክ [ከሀዲያን] ካንቺ ባያስወጡኝ ኖሮ ትቼሽ አልሄድም ነበር።»
:
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ለቀዋት የተሰደዱ ቀን መካን በእነዚህ የፍቅር ቃላት ባያባብሏት ኖሮ በቁጭት ስሜት ተወጥራ ትፈነዳ ይሆን ብዬ አስባለሁ።
ከተወዳጁ [ﷺ] ጋር አደብ ያጡ ነዋሪዎቿን አርገፍግፋ ታሽቀነጥር እንደነበር ይሰማኛል።
:
የርሳቸው ነገር ግን ይገርማል!
ሰው የተገፋበትን፣ የተሰቃየበትን፣ መከራ የበላበትን ምድር ሳይቀር እንዴት ያፈቅራል!? ሊወድ የተፈጠረ ስለሆነ እንጂ!…

❤100😍2