Telegram Web Link
Audio
ጁሙዐ ቀን ከዐስር በኋላ
================
ኢማም አድ‐ዳረቁጥኒ፣ አልሐፊዝ አስ‐ሰኻዊ፣ ኢማም አል‐ገዛሊ እና ሌሎችም በዘገቡት ሐዲስ የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«በጁሙዐ ቀን ሰማንያ ጊዜ በእኔ ላይ ሶለዋት ያደረገ ሰው የሰማንያ ዓመት ኃጢኣቱን አላህ ይምረዋል።»
ሰዎች «የአላህ መልክተኛ ሆይ! እንዴት ብለን ሶለዋት እናድርግቦት?» በማለት ጠየቁ።
እርሳቸውም: ‐ «እንደዚህ በል አሉ: ‐
" اللهُمَّ صَلِّ على مُحَمَّدٍ عَبْدِكَ ونَبِيِّكَ ورَسُولِكَ النَبِيِّ الأُمِّيِّ"
«አላሁም‐መ ሶሊ ዐላ ሙሐመዲን ዐብዲከ ወነቢይ‐ዪከ ወረሱሊከ አን‐ነቢይ‐ዪል ኡም‐ሚይ‐ይ»

ይህንን አንድ ብለህ ቁጠር።»
:
ሰማንያ ስትሞላ በአላህ መልክተኛ ላይ ሰላምታን በማድረግ ጨርስ። «ሶለ‐ለላሁ ዐለይሂ ወሰለም» በል።»
:
ያያያዝኩላችሁ የድምፅ ፋይል በዘመናችን ከነበሩ ታላላቅ የተሰዉፍ ሰዎች መካከል የነበሩት ሸይኽ ረጀብ ዲብ ከሙሪዶቻቸው ጋር ሶለዋት ሲያደርጉ የተቀረፀ ነው። ትንፋሻቸው ወኔያችንን ከቀሰቀሰ በማለት የተለጠፈ ነው!
https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh/1198
34👍10
Audio
📚አል‐አዝካር ሚን ከላሚ ሰይዲል‐አብራር
📗 ክፍል ሦስት:‐ ባቡል‐ኢኽላስ
📆 ነሐሴ 10/ 2017 ዓ. ል.
9
«ورحمَتِي وَسِعت كُلَّ شَيء».
«ችሮታየም [እዝነቴ] ነገሩን ሁሉ ሰፋች፡፡»
:
የአላህ ረሕመት ሰይዲና ሙሐመድ [ﷺ] ናቸው። አላህ ለዓለማት እዝነት እና ችሮታ አድርጎ ልኳቸዋል!…
40👍1
Audio
📚አል‐አዝካር ሚን ከላሚ ሰይዲል‐አብራር
📗 ክፍል አራት:‐ የመልካም ስራን ትሩፋት የሰማ ሰው፣ በዶዒፍ ሐዲስ መስራት፣ በቀልብና በምላስ አላህን መዝከር
📆 ነሐሴ 13/ 2017 ዓ. ል.
11
9
«ማንም ሰው ቢሆን በርሳቸው ደጃፍ እስካላለፈ ድረስ የተባረረ ነው። በርሳቸው ቅ ጎዳና ተጉዞ ካልሆነ በስተቀር [ደረስኩ ያለ] ሁሉ [የውሃ ሽታ] ነው።»
ሰይድ ዶ/ር ሙሐመድ አል‐ዐለዊይ [ረሒመሁላህ]
34😢6👍2
ወዳጅ የወደደውን አካል ብርቅታ ሲያይ፣ ከወዳጁ ሀገር ሽው የሚል ነፋስ ሲያገኘው ወይም የምናብ ውልብታው ሲጋልበው ስለሚወደው መለፈፍ ያሰኘዋል። ያለ ምርጫው ልሳኑ በቃላት ሰልፍ ይንጋጋል። ስለሐቢቡ በሚያስወራ ሱስ ይለከፋል!
ይህ ተፈጥሯዊ ነው! ለማንኛውም ተወዳጅ ይሰራል!…
:
ተወዳጁ በቀልብ ውስጥ የተንሰራፋ፣ የነፍሳችን መስፍን፣ የሩሓችን እርካታ #ሙሐመድ [ﷺ] ሲሆኑ ደግሞ ሌላ ነው!
እንኳን ሰበብ አግኝተን ንጋትና ምሽቱ፣ የቀን እና የሌሊት መፈራረቅ እንኳን እርሳቸውን ያስታውሰናል። በየሶላቱ ባለው ሶለዋት እናስባቸዋለን። ሁሌም ከኛ ጋር አሉ!
:
እነሆ አሁን ደግሞ ሌላ ሰበብ አገኘን። የውልደታቸውን ብስራት የሚዘክረን ወር ገባልን። ረቢዑን‐ነቢይ [ﷺ]!
መልካም ነገሮችን የምንከስብበት፣ ለተወዳጃችን ክብርና ፍቅር የምንጨምርበት ወር ያድርግልን!
63😍4🤔1
Forwarded from Tofik Bahiru
በውልደታቸው ወር ሰዎችን ወደ መልክተኛው [ﷺ] እልፍኝ የምናስገባ አሳላፊዎች፣ ማረፊያ አልባ ቀልቦችን በጊቢያቸው እንዲረጉ የምናደርግ አገልጋዮች እንሁን።

የተፈቃሪው ነቢይ [ﷺ] አገልጋይ እንደመሆን የተቀደሰ ስራ የለም። ልቅናቸውን እና የነጠረው ስብእናቸውን እንደማናኘት ክቡር ሙያ የለም።

ልቦችን ከተፈጥሯቸው ጋር ማስታረቅ ማለት ነው። በሙሉ ፍቅርና ታዛዥነት ወደ ሐድራቸው እንዲዞሩ ማቅናት ነው።

ለዚህ ክብር የሚታጨው በሙሐባ የታጨቀ ቀልብ ባለቤት ብቻ ነው። ፍቅር የልቡናውን ማእከል ተቆናጦ፣ ፍካሬውን የተቆጣጠረው ሰው ሙያ ነው። ሰዎች ወዳጁን እንዲወዱለት ማድረግ የመጨረሻው መሻቱ የሆነ ሰው ዓላማ ነው!
በዚህ ወር ከሌላ ጊዜ የበለጠ ስለርሳቸው እናውራ። ለልጆቻችን፣ ቤታችን ለሚዘይሩን እንግዶች፣ ለልጆቻችን፣ ላገኘነው ሁሉ ስለርሳቸው እንንገር!
:
#ረቢዑን‐ነቢይ [ﷺ]
53😍3👍1
Forwarded from Tofik Bahiru
«ሁለመናችሁን ወደ ነቢዩ [ﷺ] አቅርቡ። ወደ ጌታችሁ ትቀርባላችሁ!»…
45
የላቀው ውልደታቸው በመላእክት፣ በጂንም ሆነ በሰዎች ዓለም ውስጥ ምልክቶች ተደርጎለት ነበር። ዘመን፣ ስፍራ፣ የዩኒቨርሱ ሁለንተና በከፍተኛ መሰናዶ ውልደታቸውን ይጠባበቅ ነበር። ሰማይ እና ምድር በውስጣቸው ካቀፉት ፍጥረት ጋር መገለጣቸውን በጉጉት ይጠብቁ ነበር።

በእርግጥም የዓለሙን አስኳል፣ የፍጥረቱን ዐይን ለመጠበቅ ይህ ሁሉ መሰናዶ መደረጉ ተገቢ ነበር። ውልደታቸው ዘመናትም ሆኑ ስፍራዎች አስተናግደውት የማያውቁት ልዩ ክስተት ነበር!
እናቴም አባቴም ቤዛ ይሰዉሎትና!
44🤔2
45👍2
Forwarded from Tofik Bahiru
ኑ ረሱላችንን እንወቅ-1.pdf
1019.2 KB
ምናልባት ከዚህ ቀደም ካላያችኋት ይችን አጭር መጽሐፍ አንብቡልኝ። ስለረሱል [ﷺ] ሲራ ማወቅ የሚገቡንን መሰረታዊ የህይወት ክፍሎቻቸውን እጅግ ባጠረ መልኩ የምታስቃኝ መጽሐፍ ናት። በአንድ ማኪያቶ የምታልቅ "አጤሪራ" ናት። በእርግጠኝነት በአማርኛ ቋንቋ የተፃፈ መሰል መጽሐፍ አታገኙም። በህትመት በፖኬት ሳይዝ ተዘጋጅታ ተሰራጭታለች። ለሰዎች ማከፋፈል ወይም ማሰራጨት የምትፈልጉ 0912055014 ላይ መደወል ትችላላችሁ!
27👍4
31
Channel photo updated
Forwarded from Tofik Bahiru
ቃዲ አቡ ጦዪብ አጥ‐ጦበሪይ [ረሒመሁላህ] ሰይዳችንን [ﷺ] በመናም አይዋቸው። የአላህ መልክተኛም [ﷺ] «አንተ ፈቂህ ሆይ!» በማለት ጠሯቸው።…

ታዲያ አቡ ጦዪብ አጥ‐ጦበሪይ በዚህ መናም ይደሰቱ ነበር፤ «የአላህ መልክተኛ [ﷺ] ፈቂህ ብለውኛል።» እያሉ!…

አቡ ጦዪብ ከ348 ‐ 450 ዓመተ ሂጅራ የኖሩ ታላቅ ዓሊም ናቸው።
😍2015
Channel photo updated
Forwarded from Tofik Bahiru
ዐርባ የሶለዋት ጥቅሞች
===============
ኢማም ኢብኑል‐ቀዪም [ረሒመሁላህ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«ዐርባ ሶላት ዐለን‐ነቢይ [ﷺ] ጥቅሞች: ‐
❶ የአላህን ትእዛዝ መፈፀም።
❷ አላህም በነቢዩ [ﷺ] ላይ ሶለዋት ስለሚያደርግ ከአላህ ድርጊት ጋር መሳሰል። በእርግጥ የእኛና የአላህ ሶለዋት የተለያየ ነው። [የአላህ ሶለዋት እዝነት ሲሆን ከኛ ሲሆን ደግሞ ዱዓ ነው።]
❸ ከመላኢካዎች ጋር መመሳሰል።
❹ አንድ ጊዜ ሶለዋት ያደረገ ሰው አላህ ዐስር ሶለዋት ያደርግበታል።
❺ ሰውየውን አላህ በዐስር ደረጃዎች ከፍ ያደርገዋል።
❻ ዐስር ሐሰና (የበጎ ሥራ ምንዳ) ይፃፍለታል።
❼ ዐስር ኃጢኣት ይሰረዝለታል።
❽ የዱዓን ተቀባይነት ያስገኛል።
❾ የሙስጦፋን [ﷺ] ምልጃ ያገኛል።
❿ ወንጀልን ለማሰረይ ምክንያት ይሆናል።
⑪ ሰውየውን አላህ ከጭንቀት ይገላግለዋል።
⑫ በቂያማ ቀን ሰውየው ከነቢዩ [ﷺ] ቅርብ ይሆናል።
⑬ ድኻ ለሆነ ሰው ሶለዋት የሶደቃን ቦታ ይሸፍናል።
⑭ አስቸጋሪ ጉዳይን ያገራል።
⑮ የአላህና የመላኢካዎችን ሶለዋት ያስገኛል።
⑯ ሰውየውን ከወንጀል ያፀዳዋል። ንፅህናን ያላብሰዋል።
⑰ ሰውየው ከመሞቱ በፊት በጀነት እንዲበሰር ያደርጋል።
⑱ ከቂያማ ቀን ድንጋጤ ይጠብቃል።
⑲ ሰውየው የረሳውን ነገር እንዲያስታውስ ያደርገዋል።
⑳ ለሰላምታው የነቢዩን [ﷺ] ምላሽ እንዲያገኝ ያደርገዋል።
21. ስብሰባን ያሳምራል። ሶለዋት የተደረገበት ስብሰባ በቂያም ቀን ቁጭት አይከተለውም።
22. ድህነትን ያስወግዳል።
23. ስስትን ያስወግዳል።
24. አፍንጫው ይታሽ (ውርደት ይንካው) ብለው ነቢዩ [ﷺ] ካደረጉት ርግማን ይድናል።
25. ወደ ጀነት መንገድ ያስገባል። ሶለዋት የተወ ሰው ደግሞ ከጀነት መንገድ ይርቃል።
26. ከስብሰባ ክርፋት ያድናል። ምክንያቱም አላህና መልክተኛው [ﷺ] የማይወሱበት ስብሰባ ሁሉ የከረፋና የገማ ነው።
27. ኹጥባንም ሆነ ሌላን ንግግር ያሳምራል።
28. ሰውየው በሲራጥ ላይ የሚኖረውን ብርሃን ያበዛለታል።
29. ሰውየውን ከጭካኔ ያፀዳዋል።
30. ሶለዋት የሚያደርግ ሰው በምድርም ሆነ በሰማይ መልካም ስም እንዲኖረውና እየተወደሰ እንዲኖር ያደርገዋል።
31. ሶለዋት የሚያበዛ ሰው የተባረከ ይሆናል። ስራውና እድሜውም በረካ ይሆንለታል።
32. የአላህን እዝነት ያገኛል።
33. ሰውየው ለአላህ መልክተኛ ﷺ ያለው ፍቅር ዘውታሪ እንዲሆን ያደርጋል።
34. ዘውታሪ የሆነ የአላህ መልክተኛን [ﷺ] ውዴታ ያገኛል።
35. ቀና መንገድ መመራትን (ሂዳያ) ያገኛል። ቀልቡም ህያው ይሆንለታል።
36. የሰውየው ስም በነቢዩ [ﷺ] ፊት እንዲጠራ ያደርጋል።
37. በሲራጥ ላይ የሰውየው እግር እንዲፀና ያደርጋል።
38. ሰውየው የነቢዩን [ﷺ] ሐቅ በከፊል እንዲወጣ ያግዘዋል።
39. ሶለዋት አላህን መዝከርና ማመስገንን ያካተተ በመሆኑ ሰውየው ከአመስጋኞችና ከዛኪሮች ተርታ እንዲመደብ ያደርገዋል።
40. ሶለዋት ዱዓም ነው። ምክንያቱም በሶለዋቱ ሰውየው አላህ በሚወዳቸው እና በመረጣቸው ነቢይ ላይ ውዳሴውን እንዲያደርግ መለመን ማለት ነው። በዚያውም ሰውየው ጉዳዩ እንዲፈፀምለትና ጭንቀቱ እንዲወገድለትም እየተማፀነ ነው።
--------------------------
📚 «ጀላኡል‐አፍሃም ፊ ፈድሊስ‐ሶላቲ ወስ‐ሰላሚ ዐላ ኸይሪል‐አናም ﷺ»
http://www.tg-me.com/fiqshafiyamh
73👍6
2025/10/23 04:57:16
Back to Top
HTML Embed Code: