Telegram Web Link
Forwarded from የፍፄ ግጥሞች (Fitsae T)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ዛሬ ቢሆን ገና" ገጣሚ ፍፁም ጥበበ ከ "እሁድን በ ኢቢኤስ" ጋር በግጥም ስራ @ft2194 @poimfitsae
አንቺ ከሄድሽ ወዲ
.
.
አንቺ ከሄድሽ ወዲ
ናፍቆት በሹል መርፌው እየጠቀጠቀ
ለየዋሁ ልቤ ስቃይ እያረቀቀ
እማላገኝሽን
እማላገኝሽን
አንቺን አምጣት አለኝ
እሷን አምጣት አለኝ
ቆራርጦ አፈራርሶ ካፈር ሊያዳቅለኝ
እስትንፋሴን ነጥቆ ከጉድጓድ ሊጥለኝ

አንቺ ከሄድሽ ወዲህ
መሰለኝ መቃብር
ያለሁበት ሰፈር
ዘልዬ ቦርቄ
ያደኩበት መንደር

ደሞም ባከባቢው
የሚወጣው ድምፀት
የሚሰማው ጩኸት
መሰለኝ የሲኦል
ጫጫታ'ና ሁካታ፥
የአጋንንት ፉጨት
የሐጣን ዋይዋይታ፥
የሐጥአን እሪታ...

እንዲም አስባለሁ
ሰፈርተኛው ሁሉ
ሞልቶለት ሲዘክር
ይመስለኛል የኔ
የአርባዬ ተስካር
የሰማንያ ተስካር
ሙት አመቴን ማውሻ
እኔን ማስታወሻ
ደግሶ ማልቀሻ...

አንቺ ከሄድሽ ወዲ
አለሜ በሙሉ ተመሰቃቀለ
ሁሉ በኔ አየለ
ህሊናዬ ዛለ
ዋለለ ቆሰለ
መላው ሰውነቴም
ነደደ ከሰለ
ከሰለ
.
.
እንደው ባጠቃላይ
አንቺ ከሄድሽ ወዲ

ምናለ ያልሆንኩት ምናል ያላረግሽኝ
አንድ ጊዜ ሄደሽ አስሬ ገደልሽኝ!!!

ማይክል ሰለሞን
(የቡዜ ልጅ)

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@poimfitsae @poimfitsae
@poimfitsae @poimfitsae
Forwarded from የፍፄ ግጥሞች (Fitsae T)
የጨለመ ጊዜ
""""""""""""""""
ለምን?
ጊዜ ዘመን ሰዓት እያዋጀን፤
ለብርሃን ስንሮጥ
እንደ እሳት እራት ብርሃኑ ፈጀን?

ለምን?
እያደር ሰቆቃ እያደር ጭካኔ፤
ለአዘቅዝቆ ኗሪው
መትረየስ ነበረ የሚገባው ለኔ?

ለምን?
በሚስቴ አስክሬን ሀዘን 'ምቆራመድ
በልጆቼ እሬሳ በቁጭት የምነድ
ከሀገሬ ቆሜ በሀገሬ የምሰደድ

ለምን?
ብለን ስንጠይቅ

እሳት ሲለቁብህ
አንተ ምጣድ ሆነህ ዝምብለህ ተጋገር፤
በነገር ቢጠብሱህ
አንተ ምድር ሆነህ በሆድ ችለህ እደር፤
እንረድህ ሲሉህ
ትንፋሽህን ውጠህ ከአንገትህ በል ሰበር፤
በጨለመ ጊዜ
ጠይም ፀሀይ አስብ ደም ያለበት ጀንበር፤
እውትና ንጋት ይፈካል እያደር!

የሚል መልስ አለ እንዴ?
ልክ ያጣ ቀን ሲኖር
ለካም ቤተ መቅደስ ይኖራል ወንበዴ!


አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@poimfitsae @poimfitsae
@poimfitsae @poimfitsae
ናፈቀኝ ሀገሬ
"""""""""""""""
ብዕሬን ሸክፌ
ሀሳብ አጠንፍፌ
ቃላት አጣልፌ
ሄድኩኝ ከወረቀት፤

ቅኔ ልደረድር
ግጥሜን ልሰድር
ከመድብሌ ልከት!

ሀገር ብዬ ጀመርኩ
ሀገሬን ላልጨርስ
ጦማሬን ከትቤ፤

ዋ ብሎ አስፈራራኝ
ከራሴ እያጣላ
አመንትቶ ቀልቤ!
.
.
ለምን አልሽ አለሜ?
.
.
እንደምን ይፃፋል
ስለሀገር ግጥም
ጦቢያ ይሉት ቅኔ፤

ሁሉም አስሮ ይዞት
ዘር የሚሉት ብሂል
የአስተሳሰብ ጠኔ፤

የአባ ጃርሶ ቁጣ
የአቶ መርዕድ ዱላ
የት አለና? ዛሬ፤

የፅዮን ስፍስፍ ልብ
የከድጃ ገር ነፍስ
ርቆ ሄዶ ከኔ፤

የትርንጎ ውበት
የአለሚቱ ምክር
ጠፍቶ ከዘመኔ፤

እንደምን ይፃፋል
ሀገር ይሉት ግጥም
ሀገር ይሉት ቅኔ!
.
.
ጉድ አለ በሀገሬ
.
.
አዬ ጉድ ነው መርዶ
ሰው ከራስ ተሰዶ
ከእምነቱ እረክሶ፤

እሩቅ እሩቅ ሲሄድ
እሳትን ሲላመድ
እያደር ተናንሶ፤

ስክነት ይሉት ጠፍቶ
ሰው እብሪትን ሽቶ
እሳትን ተላብሶ፤

አባት አንገት ደፍቶ
እናትን ሆድ ብሷት
አይኖቿ አልቅሶ፤

እህት በእህቷ
ወንድም በወንድሙ
ጦር ሰይፍ ተማዞ፤

መከባበር ጠፍቶ
ልጂት እናት ንቃ
ልጅ አባቱን አ'ዞ!

ሰው በቁም ታርዞ
ሲሄድ ሲፈረጥጥ
ቁልቁሉን እሩጫ
የእውር ድንብር፤

እንዴት ከግጥሜ ላይ
ጎላ ብላ ትፃፍ
ቅኔ ያላት ሀገር?
.
.
እንዴት? .....እንዴት?
.
.
ወገን ተከፋፍሎ
እገደል ተምሎ
በዘርና በጎጥ፤

በነጮች ሰበካ
ከሀገር ተሰዶ
በድኑን ሲቀመጥ፤

በዳንኪራ ፈዞ
ቁሙን ተገንዞ
ከሀገር ሲፈረጥጥ፤

እና እንዴት ተብሎ
ስለ ሀገር ይፃፍ
ሀገር ትቆላመጥ?
.
.
ተመልከች ዓለሜ
.
.
ሀገር ማለት ሰው ነው
ሰው ነው
ሰው ነው ሀገር፤

ሰው ከሌለ የለም
ሀገር ይሉት ወሬ
ሀገር ይሉት ነገር!

ሰብዕና ጎድሎ
በሌላ ተደልሎ
በቁም ተቀምጦ እሩቅ ከከነፈ፤

ምን ተብሎ ቅኔ
ምን ተብሎ ግጥም
ስለ ሀገር ተፃፈ?
.
.
(እናማ)
.
.
ስለሀገር ያሰብኩት
ብዙ የተለምኩት
ባሸተው ሰንፍጦ
ብቀምስ ጎመዘዘኝ፤

ከእውነቱ ተውኩና
ከተስፋ አጠቀስኩኝ
ብዕሬን አነሳሁ ከወረቀት ልቀኝ፤

ሀሳቤን ሳሰፍር
የሚል ግጥም ፃፍኩኝ
ሀገሬ ላይ ቆሜ ሀገሬ ናፈቀኝ!

(ሀገሬ ናፈቀኝ)

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@poimfitsae @poimfitsae
@poimfitsae @poimfitsae
Forwarded from የፍፄ ግጥሞች (Fitsae T)
🍃 የጎረቤትፍቅር ●🍃
,,,,,,,,


ተሳስሮ አንደበቴ ድፍረቱን አጥቼ
አልነግርሽም እጂ የልቤን አውጥቼ
ደጅሽ እመጣለው በፀሀይ አሳብቤ
አይኔ እንዲያጣምርሽ ከምስኪኑ ልቤ
እርቀት አይባል የገደበን ድንበር
አንድ ላይ ያለነው ያውም አንድ ሰፈር
ከቤቴ ስወጣ ይታየኛል ቤትሽ
መዋያቸው እዚ እናትና አባትሽ
ሀይሉ ሲበረታ የጎሮቤት ፍቅር
ሰርቄ አይሻለው በቤታቹ አጥር

እናትሽ ተጫዋች ፍቅር አዋቂ ናቸው
ደግ ደጉን እንጂ ክፋም አይወጣቸው
አባትሽ ወገኛ ወግ አጥባቂ ናቸው
አያውቁት ዘመኑን ፍቅር አይገባቸው
ታዲያ እንዴት አድርጌ ፍቅሬን ልንገራቸው

እናልሽ ሀሳቤ፤
ምስኪኗ ሰበቤ፤
በሾህ ታጥረሽብኝ እንደ ፅጌሬዳ
መአዛሽ ይመጣል አልፎ ካንቺ ጓዳ
አያገኝሽ ነገር ልቤ አንቺን ሽቶ
አወደኝ መአዛሽ እንደ ናርዶስ ሽቶ
አንቺስ ባወቅሽኝልኝ ቀርቶብኝ የነሱ
ልቤ ከሚጣላ ከገዛ እራሱ
ነገር በአይን ይገባል አይደለ ተረቱ
ምነው የኔ ጊዜ አልገባሽም እቱ
እራብ ጥማት ሲሆን ግድ እንኳ አይሰጠኝ
ማወቅ ይሳነዋል ቀርቦ ሚጠይቀኝ
ናፍቆትሽ ሲመጣ ወቶ ላይደበቅ
ማንም አይቸግረው ስሜቴን ለማወቅ
ስናፍቅሽ ውዬ ስባዝን በቁሜ
ትመጪያለሽ ደግሞ ለሊቱን በህልሜ
እስኪነጋ ሌቱ አቅፌሽ በክንዴ
ቻው እንኳ ሳትይኝ ትሄጂያለሽ ባንዴ
ውለታ የረሱ የዛሬን ለማደር
ወርቅ ላበደረ ተመልሰ ጠጠር
ሲፈለጉ ታተው ቀን ቀን እየሸሹ
ለሊት እየመጡ ሰው ለሚረብሹ
ህልም ላበደሩስ ምንድነው ምላሹ?

አባ ይፍቱኝ ተብሎ አይኬድ ከቄሱ
እኔስ ቸግሮኛል ለጥያቄው መልሱ
እንከን ባይኖራቸው ውበት ቢላበሱ
ፍቅር አይገነቡም ሰው እያፈረሱ።


ቶፊቅ መሀመድ
(@Tufawmuhe)


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@poimfitsae @poimfitsae
@poimfitsae @poimfitsae
Forwarded from የፍፄ ግጥሞች (Fitsae T)
#እዬዬ
.
.
ከሩቅ ይታየኛል
'ካድማስ ወዲያ ማዶ
አይመሽ ወይ አይነጋ፤
ጭጋግ የወረሰው ያልታደለ ቀንሽ፣
ገብቶሽ እንደው እንጃ፤
በለቅሶ ሲታጀብ የታፈነው ሳቅሽ፡፡

በትላንት ጀምበር
እንባሽ ላይታበስ ፀዳሉ ላይፈካ፣
ጥምሽን ላይቆረጠው ረሃብሽ ላይረካ፣
የፊትሽ ወጋገን በሀዘን ሲታረስ፣
"እዬዬ"ሽን ሳቂው፤
ወትሮም ቤተኛሽ ነው እየሳቁ ማልቀስ፡፡

እየሳቁ ማልቀስ እየሞቱ መኖር፣
ላንቃ እያኘከ እያከኩ ማደር፣
የኋሊት መዘመን ሲተልቁ ማነስ፣
ሰብስቦ መበተን ደምሮ መቀነስ፡፡
ነው እና ያንቺ እጣ፤
በሆነብሽ ሁሉ ብዙ አትከፊ፣
በእንባ ጎርፍ አለም እየሳቅሽ እለፊ፡፡


abiye12

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@poimfitsae @poimfitsae
@poimfitsae @poimfitsae
_መቃብሬ ጫፍ ላይ...!_

የመኖሬን ቅኔ፣
የመፈጠሬን፣ ውል፣
ከችሮት መድቤ ፣
ለድሎት ፈገግታ፣ ጥርሴን ባልገልጠውም ፤
ካፈቀርኩሽ ወዲያ፣
የሽቅብ እግዜሩን፣ አላንጓጥጠውም።

ሳልፈልግ ተፈጠርኩ፣
የፍጥረትን አምላክ ፣
ለምን ? እንዴት ? ብዬ፣ በእንባ ተዋቀስኩት፣
ዘመናቶች አልፈው፣
አንቺን ያቀፍኩ 'ለት፣
ደጁ ተንበርክኬ ምስጋናዬን ቸርኩት።

ምስጋናዬን ሰምቶ፣
ፍቅር ነው 'ምትይው፣
ያለው የነበረው፣ ሳልፈልግ የላከኝ፣
የሞት ስለት ላከ፣
መኖር ሳፈቅር አይቶ ከመኖር ሊቆርጠኝ።

ተመልከች እንግዲህ፣
ጥያቄ'ና መልሱ ፣
አለቅጥ ተዛንፎ፣ አለቅጥ ሲጓደል፣
መጣመር ለራበው፣
በፎሌ ተሞልቶ፣ መለየት ሲታደል።

አሁን ምን ይሉታል፣
ሳይፈልግ መጥቶ፣
በኑሮ አተካራ፣የተገፋን ፍጥረት፣
ባንቺ መኖር ሲያምረው፣
ከእቅፍሽ አሽሽቶ፣ ወደሞት መጎተት፣ ?

ደግሞስ፣
ፍቅርን እያረዱ፣
የመዋደድን ሀቅ፣
በመስቀል የፃፍኩኝ፣ ፍቅር ነኝ ከማለት፣
ምናለበት ነበር፣
ዘመናት ቢያዘልቀው፣ የኔና አንቺን ቅፅበት፣?

ተይው አንቺሆዬ ...!!!

ነገሩን አልኩ እንጂ......continue on www.tg-me.com/poimfitsae
@poimfitsae @poimfitsae
@poimfitsae @poimfitsae
Forwarded from የፍፄ ግጥሞች (Fitsae T)
🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋
እየውልሽ ውዴ
ሎሚ ገዛሁና
ጥምቀትን ጠብቄ ከደረትሽ ልጥል
ፈራሁና ተውኩት
ለስላሳ ጡቶችሽ ሚፈርጡ ይመስል
እውነት ለመናገር
ለሱ ብቻ አይደለም አለኝ ድብቅ ቅናት
ሎሚ ማን ሆኖ ነው
አዳምሽን ቀድሞ ሚገኝ ካንቺ ደረት
እንደውም እንደውም
ሰውነት አስጠላኝ ሎሚነት ተመኘው
ድንገት ተወርውሬ
ከደረትሽ ብገኝ ልብሽን ባገኘው
ከይሉኝታ ርቄ ደስታዬን ብኖረው
ምነው!!!
ሺ አመት አይኖር!!
ደግሞ ለስታዬ
ከሰውነት በታች ሎሚ ሆኜ ብኖር።
ከደረትሽ ውዬ
በውብ ከንፈሮችሽ ተመጥጬ ብቀር።

© ከፍፁም ጥበበ @ft2194
@poimfitsae @poimfitsae
@poimfitsae @poimfitsae
🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋
Forwarded from የፍፄ ግጥሞች (Fitsae T)
የቁም ኑዛዜ
""""""""""""""""
በኑሮ ረመጥ
በችግር ማገዶ
ህይወቷ ተማግዶ፤

ተሰዳ ተገፍታ
ቃል ኪድኗን ሰጥታ
ብትሄድ ብትርቅ
ከአድማስ ወድያ ማዶ!

እኔ ብኩኑ ሰው
ከከፍታው ቁልቁል
ከመስመር ዘንፌ፤

የቃል ኪዳን እምነት
የእውነት ክራችንን
በውሸት አጣልፌ፤

ለሲኦል ተርፌ
የፍቅርን ፆም ህይወት
በአንድ ቀን ገድፌ፤

በስሜት ከንፌ!

ደረብኩባት ሌላ፤

እኔ አያ ቂሉ
አያ ሞኛ ሞኜ
አይ እኔ ተላላ!


እና ስትመለስ
የኔን ፍቅር ብላ
ከሀገር ከቀዬው ከህይወቷ ዓለም፤

የታል ፍቅሬ ስትል
ይህንን በሉልኝ
አርዱልኝ መሞቴን ንገሯት ግድየለም...፤

የቃል ዕዳ በልቶ
የቁም ኑሮ የለም!
.
.
እናማ
እንደዚህ በሉልኝ
.
.
ከሀቂቃሽ ጓዳ
ጥጋብ ውጥር አርጎት
በእብሪት ተሰዶ፤

ያስቀመጥሽለትን
የቃልኪዳን መና
ቅርጥፍ አርጎ በልቶ፤

በስሜት ሲነዳ
ሰብዕናው ጠፍቶ
ከእባብ ተጋብቶ፤

አንቺን ተዘናግቶ
ከእባብ ሲዳራ
እፉኝትን ወልዶ!

'ቃል በላሁ'
'ቃል በላሁ'
ብሎ እንደተረተ፤

አመትም አልቆየ
ቃል ከገደል ገፍታው
ተፈጥፍጦ ሞተ!

ብላችሁ ንገሯት
ቅስሟ ስብር ብሎ
ለማመን አቅቷት ለልቧ ቢከብድም፤

ለአዛኝ ሞት እርም አለው
ብሞት ይሻላታል
የቁም ክህደቴን በፍፁም አትመርጥም፤

ኑሮ ቸንክሯታል
መካዴን ነግሬ
የነፍስያ ችንካር ሚስማር አልሆናትም!

ንገሯት አደራ
ይህንን አርዱልኝ
ማለዳ ሄዳችሁ "የ'ታል" ያለች ግዜ፤

ይህን ነው የምለው
በቁሜ ሞቻለሁ
አስረዷት ለዓለሜ የቁሜን ኑዛዜ!

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@poimfitsae @poimfitsae
@poimfitsae @poimfitsae
Ram:
Henna is the expression of beauty without any word
Let me make you glow on your special day for your
Wedding 👰👰👰
Nikah 💍💍💍💍💍💍
Parties🎉🎉🎉
Birthday's 🎂🎂🎂🎂
Holliday's..........
For more information you can contact me by this 🏷@mere611
0931043351
@Merye21
Forwarded from የፍፄ ግጥሞች (Fitsae T)
(አሌክስ አብርሀም)
🌹ካገባች በኋላ

ሌላ ወንድ አቀፋት የሚል መርዶ ሽሽት
ሌላ ሴት እያቀፍኩ በያንዳንዷ ምሽት
እሷ ናት እላለሁ
(የኔ እብደት ሲገርመኝ ይባስ የሴቶቹ)
ፍቅር የሰለቻቸው ፍቅርን የሰለቹ
እሷ ናችሁ ስላልኩ "እሷ ነን" እያሉ
እኔ እንዳነሳቸው ራሳቸውን ጣሉ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@poimfitsae @poimfitsae
@poimfitsae @poimfitsae
ሰዓሊው ፈጣሪው
###########
ኳ ኳ ኳ ኳ......
ዷ ዷ ዷ ዷ......
የሚል ድምፅ አይሏል
የመዶሻ ብርታት ሚስማር ላይ ጨምሯል
እንጨቱን በሚስማር አብሮ እያጣመረ
ሰዓሊው መአዘኑን እያጠናከረ
የህሊናውን ውብ ለሰው ለማስመልከት
በማዘኑ መሀል ጨርቅ ጨመረበት
ከዛም አስተካክሎ ጨርቁን አወጣጥሮ
ቡርሽ ከቀለም ጋር አንድ ላይ ሰድሮ
የምናቡን ቆንጆ በገሃድ ሊያውልሽ
ይሞነጭር ጀመር ጨርቁ ላይ ሊስልሽ
አበባ ከፊትሽ ፀሀይ በስተጀርባ
ያስቀምጥ ጀመረ ሳሊው እየቀባ
ስሎና ቀብቶ ጨርቁን እያራሰ
በስተመጨረሻ አንቺ ጋር ደረሰ
አምሳያ መልክሸን ጨርቅ ላይ አኑሯት
ደጋግሞ ደጋግሞ ተመስጦ ሲያያት
በሀሳብ ህሊናው በአእምሮ ካያት
ከሷ ትለያለች እቺ ሌላ ሰው ናት
ከምሳጦ ነቃ በጣም ደነገጠ
የምናቡ ውበት በውን ተለወጠ
ይቀባባ ጀመር ፊቱ እንደመጣለት
አንቺን ውቧን ቆንጆ ለሰው ለማስመልከት
አሁንም ድጋሚ መልክሽ ተለየበት
ያበቦቹ ፍካት ካንቺ በለጠበት
ይቦራርሽ ጀመር እልህ እያነሰው
ሀሳቡ አደለሽም መልክሽ የሌላ ነው
ፀሀይ ለውበትሽ መዋብ እንድትሰጣት
ይነካካት ጀመር በሀል ይቀባባት
ፀሀይ--መብራቷን ቀጠለች
መልክ የሌላ ነው
ከሰዓሊው በላይ እሷ ተቃጠለች
ፀሀይ ተናደደች
አረረች በገነች
የሷን ማዘን አይተው አበቦች ተከፉ
አንቺን ማድመቅ ትተው መሬት እረገፉ
ከፈጣሪሽ እኩል ሊያዩሽ አንዳልጓጉ
ስሮች በሰበሱ ግንዶች ጠወለጉ
ሰዓሊው ፈጣሪው አልሆንልህ ያለት
ፊትሽ አበባው ላይ ቀለም እረጨበት
መቀባቱን ትቶ መድፋቱን ቀጠለ
ምናብ ወደ ገሀድ አልመጣ ስላለ
በዚ ብቻ አልበቃም.....
ፈጣሪው ፍጡሩን መፍጠር ስስላቃተው
ፍጡር ማኖሪያውን ሸራውን ቀደደው
በምናቡ እርቆ በተመስጦ አየሽ
አንቺ ባሳብ መንፈስ እዛው ቦታሽ ላይ ነሽ
መምጣት እንደማችይ ለቁስ እንደሸሸሽ
በሌላ መታየት እንዳንገሸገሸሽ
ፈጣሪው ተረዳ እሱ እዳልፈጠረሽ
የላይኛው አምላክ ገፀ በረከት ነሽ(X2)


ገጣሚ Abel

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@poimfitsae @poimfitsae
@poimfitsae @poimfitsae
Forwarded from የፍፄ ግጥሞች (Fitsae T)
#ምንድነው_መጓደል

በዚች በማትረባ፤
በስንኩል ዱኒያ ውሏ ባልታወቀ፣
እዝነቱ በራቃት፤
ፍሬ አልባ መካን ስሯ በደረቀ፡፡
አንድ ሆኖ መኖርን መቻል ሳንታደል፣
ጎለን ስናበቃ "አደራ አንጓደል፤"
ብሎ ራስ ማታለል ደርሶ ራስን ማበል፣
ዛሬም አለ አይደል ?፡፡

ምንድ ነው መጓደል?
ማይድን እያከመ እንቡጥ ለቀጠፈ፣
ቃሉን ለረሳ ሰው ኢማኑን ላጠፈ፡፡
አካሉን ላመነ ልቡን ለዘነጋ፣
እውነትን ለሳተ ሀሰት ለሚያወጋ፣
መቼ ይሰማዋል ምኑም ነው መጓደል፤
ቁም ነገር ገቢሩ
ሀገር ቀብድ አሲዞ ለሆድ መበዳደል ፡፡

ኑሮዋችን ትቢያ ነው አመድ የለበሰ፣
ህልማችን ብኩን ነው ከማነስ ያነሰ፡፡
ላልኖሩለት እውነት ትውልዱን መበደል፣
መኖር ለተመኘ የሞት ሲቃ ማደል፣
ዛሬም አለ አይደል ?፡፡
ምንድነው መጓደል?
ኑሯችን ውጥንቅጥ እንዲሁ መደናገር፣
እንዲሁ መደናበር፤
ቅን ቀን እያበ'ሉ እራስን ማታለል፤
ዛሬም አለ አይደል?፤
.
.
. . . . ."ምንድነው መጓደል ?፡፡"


ቶፊቅ መሀመድ


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@poimfitsae @poimfitsae
@poimfitsae @poimfitsae
Forwarded from የፍፄ ግጥሞች (Fitsae T)
🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔👉
ይህን ያውቁ ኖሯል??
የመጀመሪያው ካሜራ መጠን??

የመጀመሪያው የኮምፒውተር ማውዝ በማን ተሰራ??

እነዚህንና ሌሎችንም ለማመን የሚከብዱ እጅን በአፍ የሚያስጭኑ ድንቅ እውነታዎችን በፍፄ ቲቪ የዩትዩብ ቻናል ብቻ!!

ይመዝገቡ ይኸው ሊንካችን

https://youtube.com/channel/UC6lhxeXubv3KTAqrOmI7rhQ
https://youtube.com/channel/UC6lhxeXubv3KTAqrOmI7rhQ
https://youtube.com/channel/UC6lhxeXubv3KTAqrOmI7rhQ
🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔
የኔ ደብዳቤዎች pinned «🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔👉 ይህን ያውቁ ኖሯል?? የመጀመሪያው ካሜራ መጠን?? የመጀመሪያው የኮምፒውተር ማውዝ በማን ተሰራ?? እነዚህንና ሌሎችንም ለማመን የሚከብዱ እጅን በአፍ የሚያስጭኑ ድንቅ እውነታዎችን በፍፄ ቲቪ የዩትዩብ ቻናል ብቻ!! ይመዝገቡ ይኸው ሊንካችን https://youtube.com/channel/UC6lhxeXubv3KTAqrOmI7rhQ https://youtube.com/channel/UC6l…»
Forwarded from የፍፄ ግጥሞች (Fitsae T)
ባለዋሽንት ባለግርግም
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

የላሞቹን ዜማ የአህዮቹን ቅኔ የበጎቹን ግጥም፤
ማጣጣም ለቻለ ለኔ አይነቱ 'ረኛ መድረኩ ነው ግርግም።
እኔ እዘምራለሁ እነሱ ያጅቡኛል፤
ከአለም የተለየ እጡብ ድንቅ ጥበብ እዚ ቤት ይገኛል።
(ድንገት)
ከማዶ ቢሰማኝ የእኩዮቼ ዋሽንት፤
ነብሴን ዜማ ጠራት ውብ ግርግሜን ክድት።
ዋሽንታቸው ደጉ ነብሴን የጠለፈ፤
በዜማው ተሳፍሮ ልቤ ኮበለለ እፀፍ ጸፍ አለፈ።
ልቤ ሲረማመድ ከደመና በላይ፤
አይኖቼን ገልጪ በሰፊውን ሰማይ ላይ፤
(ድንገት)
አስደናቂ ኮከብ የሀበሻን ነገስታት፤
ሲመራ ሳያቸው ነብሴን ምስጢር ጠራት።
(ጠራ እና ሹክ አላት)
ንቅት ከሰመመን ምልስ ወደራሴ፤
አወይ አወይ አወይ አወይ ለአንድ ነብሴ፤
እኩዬቼ አላዩ ይህን እጡብ ታምር፤
ተነሱ እና እንገስግስግ ተፈጥሮን እንመርምር።
(ብዬ ሳልነግራቸው)
ከመቅጽበት መቶ ብርሐን ከበባቸው።
ከብርሐኑ ውስጥ ሰው መሳይ ገጽ አለ፤
በመልክም በቅርጽም የተስተካከለ፤
(ይናገር ጀመረ)።
"በከተማቹ በናዝሬት፤
የጌታ ፍቅር ሰፍሮበት፤
መድኃኒት እሱ ክርስቶስ ሰው ሆኗል ከድንግል ስጋ፤
መላዕክት በዛ ቤት አሉ ዘምሩ ከእነሱ ጋ።"
(ቢላቸው)
ሮጡ ሮጡ ደረሱ ደረሱ፤
በዚያች እጡብ ምሽት መድኃኒት አፈሱ።

ALONE
ታህሳስ ፪፼፲፫

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@poimfitsae @poimfitsae
@poimfitsae @poimfitsae
ሰበር ዜና......እባክህ/ክሽ ካነበቡት በሁዋላ Shere አርጉት
😳😳😳😳😳😳😳😳😳😳
😯😯😯😯😯😯😯😯😯😯
😞😞😞😞😞😞😞😞😞😞
ያልሰማ ካለ plz ለህይወትህ ስትል ስማ
ትናንት በናሽናል ጂኦግራፊ ዋይልድ ቻናል ላይ
የተላለፈው ዜና አስደንጋጭ ነበር😟
, ማለትም ሳይንቲስቶች እንደገለፁት ከሆነ በጣም
አደገኛ እባብ 🐍ተገኝቷል ሳይንቲስቶቹ እንደተናገሩት
እባቡ ምግብ በበላ ቁጥር 0.5ሴ.ሜ ያድጋል
ምግቡን ደግሞ የሚበላው ቢበዛ በ 30 ሰከንድ
ውስጥ ነው ታዲያ ይህን እባብ በምንም አይነት
ሰው ሰራሽ መሳሪያ መግደል አለመቻሉ ነው ነገሩን
አስፈሪ ያደረገው ሊሞት የሚችለው እራሱን
በራሱ ከነከሰ ብቻ ነው ነገር ግን ሳይንቲስቶች
ሌላ የሚገድለውን ነገር እየፈለጉ ነው ይህ እባብ
በሰዉ ልጆች ታሪክ ከተመዘገቡ ገዳይ በጣም
አደገኛና መርዛማ ከሆኑ እባቦች ሁሉ ዋናው ነው😳
ታዲያ ይህ አንድ ቦታ ብቻ ነው የሚገኘው
እሱም








ኖኪያ 3310 የስልክ ቀፎ ላይ የጌም ምርጫ
ውስጥ snake xenzia. ላይ ነው ፡፡
በትእግስትና በጥሞና ስላነበባችሁት
አመሰግናለዉ 😂😂
@poimfitsae @poimfitsae
2024/05/21 04:24:42
Back to Top
HTML Embed Code: