💋ለኔ ሀገሬ ነሽ
................
ጧት ማታ ምስልሽ ብእሬን አውጥቼ
አንቺን አስባለው ሁሉን እረስቼ
መብላት አያሰኘኝ ሚጠጣም አይጠማኝ
የኔ ህይወት እወቂው ፍቅርሽ ነው የጠማኝ
ከሀገሩ ውጪ መሄጃ እንደሌለው አንድ ሚስኪን ሰው
እኔም እንደሱ ነኝ ካንቺ ውጪ ምርጫም የለኝ ምለው
በሀገር ከመጡ እስከ ጥግ ይኬዳል
ባንቺ ከመጡ ግን እራሴን አሎንም ጭንቅላቴም ያብዳል
የሀገርን ትርጉም ውጪ ያለ ያውራ
ላንቺ ያለኝ ፍቅር ከቶም አያባራ
ለኔ ሀገሬ ነሽ ቅያሪ የሌለኝ
ከሞት በስተቀር ካንቺ ጋ ምንም አይለየኝ

አሚር አደም
@fonkabcha1
@fonkabcha1
።።።።።የፍቅርሽ ሃያልነትሽ።።።።።

~

ያኔ ስንገናኝ በጓደኝነታችን፤
ድንገት ሳናስበው በፍቅር መጥለቃችን፣
ወደታች እንደሚሠምጥ የባህር ድምፅ እንጉርጉሮ፤
የፍቅርሽ ሃያል በደሜ ውስጥ ገብቶ ልቤን ጎርጉሮ፤
መተንፈስ እስኪያቅተኝ መናገር ተቸግሬ፤
ለመናገር የፈራሁት አንቺን አፍቅሬ፤

-------ሁሌም እልሻለው-------
     --------እወድሻለው------

እና እምልሽ አንቺን ካገኘው ከወደድኩሽ በኅላ፤
ያለኝን ሁሉ አየው ተመልሼ ወደኅላ፤
አለም አንቺን ሰጠችኝ፤
ደስተኛ እንድሆን አደረገችኝ፤

ጥይት እንኳን ቢተኮስ የማይበሳውን ልቤ፤
በአንቺ ፍቅር ብቻ በአንቺ ፍቅር ተከፈተ ልቤ፤

--------ሁሌም እልሻለው----------
       ✍️ባር

@fonkabcha1
@fonkabcha1
ካንቺ ጋራ ስሆን❤️

የኔ አለም አዳምጪኝ 😊
ካንቺ ጋራ ስሆን.....
ፍቅርሽን ሳጣጥም ፣
አይኖቼ በፍቅር ፡ ከአይኖችሽ ሲገጥም 🤗
ካንቺ ጋራ ስሆን .... 🔥
ንፋሳት ሁልጊዜ ፡ በፍቅር ያዜማሉ ፣
አይገርምም የኔ ዉድ ፡ እኔና አንቺ
#ሊያዩ😒
ዥረቶች ለአፍታ ፡ ጉዞ ያቆማሉ ፣
ክዋክብት, ጨረቃ ፡ በኛ
#ይቀናሉ 🤦‍♂


'ካንቺ ጋራ ስሆን' ..... ❤️
ምሽቱ
#ይደምቃል ፣ ሀሳቤ ይሰምራል፣
አስቀያሚው ያምራል ፣😊
ጨለማው
#ያበራል ፡፡
ሰማሽኝ የኔ አለም ፡ ካንቺ ጋራ ስሆን ፣
ህይወቴ
#በሀሴት ፡ ፅዋ ትሞላለች🥰
ካንቺ ጋራ ስሆን አለም ለኔ እንዲህ ነች🤗

@fonkabcha1
@fonkabcha1
♥️......ቀድሜክ ከሞትኩኝ......♥️
        

ውዴ ቃል ልግባልህ፣
በእውነት የማረገው፣
የማስመሰል ሳይሆን፣
ደርሶ የምታየው፣
እኔን ካንቺተ በፊት፣
ወደሱ ከጠራኝ፡
ውዴ የኔ ፍቅር፣
ቀድሜህ ከሞትኩኝ፣
ሄጄ በሰማዩ፣
ባማረው ስፍራ ላይ፣
በወርቅ ፅፈዋለው፣
ስምክን ኮከብ ላይ፣
ስለምን መሰለክ?
ይሄን የማረገው፡
ላንተ ያለኝን ፍቅር፣
መልአክት እንዲያዩ ነው

#Emu


   ,,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,,,,,,,
           ••●◉Join us share◉●••                                         
@fonkabcha1
@fonkabcha1
"" ♥️ፍቅሬ ብለህ ጥራኝ♥️""

አወ አብርን አድገናል አፍርም ፍጭተናል
በአንድ ስሀን ብልተን ባንድ አልጋ አድርናል
የልጅነት ነገር ሆኖብን ነገሩ ባሌ ሚስቴ
ተባብለን ነበር እንዲት ደስ ይል ነበር አወይ ልጅነቴ

የስውነት ግዝፍት የእድሜም መርዘም
የአእምሮ መብስል ማስብ ማገናዘብም
ተጅምሮ ዛሬ አይናፍርነትም መጣ ተከትሎ
እንዱ ሲያለቅስ አንዱን ላያስቅ አባብሎ

ልክ እንደ ልጅነት እንደጥንቱ ግዜ
ድንገት ሳላስበው ነይ እህት አለም በምትለኝ ግዜ
ውስጤን ይከፍዋል ከእህትነት ይልቅ ፍቅርህ ከብዶታል
እንዳልተነፍስው እንዳልናገርው ልቤ ፍራተባ ይላል

እስኪ በል ንገርኝ ልክ እንደልኝነት
እንደ መልካሙ ጊዜ እንዲያ እንዳለፍንበት
ፍቅሬ ብለህ ጥራኝ ካልሆነልህ ሚስቴ ተንፍስልኝና እኔም እፎይ ልበል ይፍታ ምኞቴ

ፍቅሬ ብለህ ጥራኝ እንደ ልጅነቴ
ባሌ ብዬ ልጥራህ ይሳካ ምኞቴ

  

@fonkabcha1
@fonkabcha1
ለኔ ሀገሬ ነሽ
ጧት ማታ ምስልሽ ብእሬን አውጥቼ
አንቺን አስባለው ሁሉን እረስቼ

መብላት አያሰኘኝ ሚጠጣም አይጠማኝ
የኔ ህይወት እወቂው ፍቅርሽ ነው የጠማኝ
ከሀገሩ ውጪ መሄጃ እንደሌለው አንድ ሚስኪን ሰው
እኔም እንደሱ ነኝ ካንቺ ውጪ ምርጫም የለኝ ምለው
በሀገር ከመጡ እስከ ጥግ ይኬዳል
ባንቺ ከመጡ ግን እራሴን አሎንም ጭንቅላቴም ያብዳል
የሀገርን ትርጉም ውጪ ያለ ያውራ
ላንቺ ያለኝ ፍቅር ከቶም አያባራ
ለኔ ሀገሬ ነሽ ቅያሪ የሌለኝ
ከሞት በስተቀር ካንቺ ጋ ምንም አይለየኝ

አሚር አደም
@fonkabcha1
@fonkabcha1
🤱 አንቺ ብቻ! 🤱


ወዳጄን አጣሁት ፡ በቸገረኝ ግዜ
ዘመዴን አየሁት  ፡ ሲከበኝ ትካዜ
ጎረቤቴም ቀና
ኑሮዬን ባቃና
ወገኔ ነው ያልኩት
ሲክደኝ ታዘብኩት
አግኝቶ በማጣት
ወድቆ  በመነሳት
አየሁት ሁሉንም  ፡ ለካ ሰው የለኝም
እማ ካንቺ ሌላ ፡  ዘመድ አይገኝም
ልብሽ ያልተከፋ ፡  ፊትሽ ያልጠቆረ
በችግር በደስታ ፡  አብሮኝ የነበረ
በእዉነተኛ ፍቅር ፡  አብረሽኝ የቆምሽው
ያንቺን ኑሮ ትተሸ ፡  ስለኔ የኖርሽው
አጣኁልሽ አቻ ፡  ዞሬ በዚህ አለም
እናቴ አንቺ ብቻ ፡  ኑሪልኝ ዘላለም፡፡


@fonkabcha1
@fonkabcha1
ማታ ስናወራ
ሁሌ በየቀኑ ጧት ሳይሆን ማታ
ከ ፍቅሬ ጋር ስናወራ ከዚ በላይ አለ እንዴ ደስታ
ጭር ባለ ሰአት ስናወራ እርቀን ከሰው ጫጫታ ከወፎች የድምፅ እሩምታ
እርቀን ስናወራ ይሰማኛል ጥልቅ የሆነ ደስታ
ዘወትር ምደውለው ጠብቄ ሲመሽ
ልነግርሽ እኮ ነው ጅላጅል ስላረገኝ ፍቅርሽ
የኔ ጣፋጭ ስትይኝ እማ
ከደስታ ብዛት እቀልጣለሁ ልክ እንደ ሻማ
ፍቅርሽ እኮ ሀያል ነው ማብረጃ የሌለው
ጉልበት እንዳለው ሰው አክት አሳያለው
ግን እኮ በፍቅርሽ ሞቻለው
ለዛ ነው እማ የውስጤን ለማውጣት ፍቅሬን ለመግለፅ ምሽትን ምመርጠው
ከረብሻ እርቀን ጨረቃን እያየን ልገልፅልሽ ነው
ይሄንን አቃለሁ እለፈልፋለሁ ብዙ አወራለሁ ስለያዘኝ ፍቅር
አንዳንዴ ግን እሰጋለሁ ይሰለችሻል ብዬ ወይ ይልሻል ቅር
እጓጓለሁ መሽቶ እስክናወራ
ፍቅሬ ሙድ አለውኮ ስለፍቅራችን ማታ ስናወራ

አሚር አደም

@fonkabcha1
@fonkabcha1
መቼ ነው

ያንን ሁሉ አመሌን ትቼ አንቺን ሳገኝ
የአይኔ ብሌን ፍቅርሽ መምሪያ ሆኖኝ
ሁሉን እንቃለው ፍቅርሽ መኩሪያ ሆኖኝ
መኖሬን ያስመኘኝ ያ የያዘኝ ፍቅርሽ
ደስታን ያሳየኛል ሲነጋም ሲመሽ
ውዷ የኔ ሂወት ሀላሌ እናቴ
መቼ ነው አቅፈሺኝ ሚበራው ሂወቴ
እቅፍሽ ውስጥ መኖርን እስክመኝ እስከለተ ሞቴ

መቼ ነው.........

መቼ ነው ምትስሚኝ በዛ ውብ ከንፈርሽ
መች ነው ምታሳዪኝ ለኔ ያለሽን ስሜት ገዳዩን ፍቅርሽ

መቼ ነው......

እራቀብኝ ፍቅርሽ ቃል ብቻ ሆነብኝ
ብቻ ሞቴን በራሴ እጅ እንዳላረገው አንዱ አንቺን ጠልፎብኝ
በጣሙን ናፍቆኛል በአካል ተገናኝተን እኔ ሳወራ አንቺ ስትሰሚኝ
ስሜቴን ስገልፅልሽ ካንቺጋ መኖር እንደምመኝ
ፈጣሪዬን አመሰገነዋለው እልሻለው አንቺን ስለሰጠኝ
ግን መቼ ነው መቼ......

አሚር አደም
@fonkabcha1
@fonkabcha1
🤰🤰🤰 ናፍቆትክን በሆዴ 🤰🤰🤰

ድምፅህን ለመስማት ጆሮዎቼ ቋምጠው
እጆቼ አንገትክን በእጅጉ ናፍቀው
ከንፈሬ ከንፈርህን በጣሙን ተርበው

ትመጣለህ እያልኩ ደጅ ደጁን እያየው
ግና አንተም የለህ ድምፅንም አልሰማው
ይኸው ናፍቆትክን በሆዴ እንዳረገዝኩ አለው።

👇
-------------------------------------------
@fonkabcha1
@fonkabcha1
ምንድን ናት

እናት ምንድን ናት ቃል አላት
ብቻ ግን ውድ ናት ልትፈታ ማችል ቅኔ ናት
ሴት እናት ስትሆን ሂወትም አይኖራት
የኔ ለኔ የሚባል ጥቂት ደስታም የላት
እና እናት ምንድን ናት
ቃል አላት ምን ገልጿት ምን ልንላት
ብቻ እናት ውድ ናት በየቦታው ያለች እንቁም ልዩም ናት

ገጣሚ አሚር አደም
ጥር 21/2015

@fonkabcha1
@fonkabcha1
////የተጠገነ ቃል\\\
-------------------------------
የተሰበረ ልብ በምን ይጠገናል፣
       ጊዜ ሽሮት እንኳን
       ጠባሳውም ያማል፣
በታወሰ ቁጥር ህመም ያገረሻል፣
        ስንት ነው ተመኑ
        ዋጋ ወጥቶለታል፣
        ያፈቀረን መግፋት
      እንደው ስንት ያወጣል።
  ከረፈደ ነቅተው የቦዘዙ አይኖች፣
 በእርጅና የደከሙ የዛሉ ጉልበቶች።
         ማስተዋል ሲያገኙ
         ሲነቁ ከህልማቸው፣
 እንደው ቢጠየቁ ቢሰማ ድምፃቸው፣
          የገፉትን ማግኘት
        ይሆን ወይ መልሳቸው።
                  እንጃ፣
ብቻ፣ ባላወኩት አለም በሃሳብ ተሰድጄ፣
  የጎዳሽኝ አንቺን በሀሳብ አስረጅቼ።
           ድንገት ባስብ ጊዜ፣
   ስለሰበርሽው ልብ ፀፀቱ ሲገልሽ፣
            ከሀሳብ መለስ ብዬ
            ደብዳቤ ፃፍኩልሽ፣
     እርሺኝና ኑሪ ሀዘን አይብዛብሽ፣
  አለም አሰቃይታ ቁጭት አይግደልሽ፣
ሺህ ብታደሚኝም ይኸው ይቅር አልኩሽ፣
 በሄድሽበት ሁሉ መልካሙ ይግጠምሽ፣
    በእንባዬ አትሜ ይቅርታን ላኩልሽ፣
      እውነት መልካሙ ይግጠምሽ።


@fonkabcha1
@fonkabcha1
ያገር ልጅ ህይወቱ ፣ ከ ጽሁፍ ሲጣቀስ
እንዴት ዝቅ ይባላል ፣ ከ ሽንት ቤቱ ጥቅስ?
"Work as a slave live as a king"
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~

ስራው ማለት ኑሮው ፣ በሆነባት ሃገር
እንደባርያ ስራ ፣ እንደ ንጉሶች ኑር
ይለኛል ገራገር
.
.
ተረግጦ ተረግጦ
ተረግጦ ሲብሰው
እንደ ነገስታት ኑር ፣ ይለኛል  የዋህ ሰው
.
.
የብሶቱን ጽዳጅ
ሊጸዳዳው መጥቶ ፣ ባለ ሽንትቤቱ
ዝቅ በል ይለኛል
ብቸኛ ነው መሰል ፣ ዝቅ ያለው ህይወቱ
.
.
ብቸኛ ነው መሰል ፣ መውረዴን ይመኛል
ከዚህ በላይ ዝቅጠት
ከዚህ በላይ ውርደት ፣ ከወዴት ይገኛል
ፅድድቱን ረስቶ
ሽንት ቤት በጻፈው ፣ ንጉሦ ነኝ ይለኛል
.
.
አላወቀም እንጂ...
ሳር ሳሩ እየታየ ፣ በተማሰ ቅጥር
ጎምበስ ብሎ ሰርቶ ፣  ቀና ማለት ቢጥር
ቁልቁል ነው ሚወረድ ፣ ዝቅ ባለ ቁጥር
.
.
ወፊቱ አለቀሰች ፣ ዜማ ወጥቷት ዕምባ
መወጣጫ ሲሆን ፣ ያጎንባሽ ሰው ጀርባ
ዝቅ አልኩኝ እያለ ፣ ሰው ገደል ሲገባ
.
.
ወፊቱ አለቀሰች ፣ እምባ ወጥቷት ዜማ
የለፍቶ አደር መዳፍ ፣ ቀን ተ ቀን ሲደማ
ማለዳ ማለዳ ፣ እሮሮ ስትሰማ
<ምንአረኩ> እያለ ፣
ሰው አምላኩን ሲያማ።
.
.
ወፊቱ በትዝብት ፣ እንዲ አለች አንድ ቀን
<ከፍ ብለን ስናይ ፣ እኛም  ከሰው ልቀን
አይፍጠርህ እንጂ ፣ ከታችኛው መደብ
አንተም ስትረግጥ ነው ፣ ከላይ ምትመደብ>
.
.
አይፍጠር ነው መቼስ

                            [ ቶማስ ትግስቱ ]

@fonkabcha1
🔥 እንቅልፍና ሴት 📝

          ••••••••

በአንድ አልጋ ላይና
  በአንዲት ሴት ላይ
ሶስት አይነት አንድነት
ህልም-ፍቅር-ህይወት

ከነዚህ መሀከል-ህልም የምንለው
ፈቺ የሚፈልግ አሳሪ የሌለው
የኔና ያንቺ ፍቅር ያልጋ ላይ ህይወት ነው
ፍቅሬ ገብቶሽ እንደው
ፍቅር እንደዚህ ነው።

ከራስ አስበልጦ ሌላ ሰውን መውደድ
ባንድ አለም ተከብሮ ባንዲት ሴት መዋረድ
ክብር ነው ትርጉሙ
በሴት ልጅ ተማርኮ ከዙፋን ላይ መውረድ።

ፍቅሬ ገብቶሽ እንደው
ህይወት እንደዚህ ነው

ተኝቶ መነሳት
የታወሰን መርሳት
ያሰሩትን መፍታት
ኖሮ ኖሮ መሞት።

ፍቅሬ ገብቶሽ እንደው
ሴትና እንቅልፍ ያው ነው

የትኛውም ፍጥረት ባልጋው ያንቀላፋል
ማንም ወንድ ነኝ ቢል በሴት ይሸነፋል።


‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌@fonkabcha1
@fonkabcha1
​​​​​​​​❦ ​​​​​​══•⊰❂ ጣፋጭ ግጥሞች  ❂⊱•══ ❦

😘አንዴ ብትሰጠኝ🤣

ቀምሼው አላውቅም
እያልኳት አትስጭኝ
ልብሱን ገለጥ አርጋ
መልኩን ብታሳየኝ
እኔው ሰፍ ብዬ
አልኳት ስጭኝ ስጭኝ
እርሷም ሳትሳሳ
አንድ ጊዜ ብትሰጠኝ
ሁሌም ስጭኝ አልኳት
በጣም ነው የጣመኝ
ስሙንም ስትነግረኝ
እንዳይጠፋኝ ብላ
ለካስ የማውቀው ነው
ደስታ ከረሚላ!!!
      😁😁😁        


@fonkabcha1
ረመዳን

ረመዳን እክ ማመስገኛችን ነው
ይሄንን ያመጣልን መማር ሲፈልግ ነው
ሀጢያት ሰርተናል አውቀንም ሳናውቀው
ተውበት ያላረገ ገሀነም እኮ ነው ነገ ሚጠብቀው
መፀፀት አለብን ነብስያን ተገፍቶ
አላህ መሀሪ ነው አይጎልበት ከቶ
ሀጢያታችን በዝቶ ጣራ እንኳ ቢነካ
ፈጣሪ ታጋሽ ነው በሀጢያታችን ፋንታ ሀጅር እስክንተካ
በዚ ቀን ካልቶበትን ምኑን ሰው ሆነው
ሀጅር መሰብሰቢያ የረመዳን ወር ነው
አንድ ሀጢያት ብሰራ አንዱ ነው ሚፃፈው
ጥሩ ግን ብሰራ በሺ ተባዝቶ ነው
ረመዳን እኮ የተውበት ግዜ ነው
አላህን አጥብቀን ምስጋና እንድንሰጠው
ረመዳን እኮ የአላህ ስጦታ ነው
ለኛማ ሚሻለው እያወደስነው እሱን ማስደሰት ነው
ረመዳንን በንፁ ልባችን ከፆምነው
አላህማ አዛኝ ነው እሱማ መሀሪ ነው

አሚር አደም

@fonkabcha1
@fonkabcha1
አጀብ ነው

ሁሉም ይዘርፋል ስለራበኝ ፍቅር
ይናገሩታል ይተነብዩታል ፍቅርን ያዩት የኖሩት እያላቸው ምርር
ቀን መቶ አንስቷቸው ሲወድቁ ላያቸው
ደስታ በስቶባቸው አለም ሲርቃቸው
እንዴት አይብጠለጠ ክፉ ሰራቂ ሂወት
ይሉታል እርኩስነው ሰራቂ የደስታ የከባድ ሀዘን ቋት
አይ ፍቅር ስንቶች ይዘልፉታል በማያልቁ ቃላት
እንዲ እንዳ እያሉ ምን ያክል ያሳዝናል አዙረው አንስተው ሲያፈርጡት
ግን ሁሉም አልገባቸው በተለይ ላላዩት
ከውጭ ቆመው በአሉባልታ የፍቅርን ስም ለሚሰጡት
አንድ ነገር አለ አንተ ማትረዳው እነሱ ያዩት
ባዶ ሆኖባቸው እኮነው ሲመጡ ወዳንተ ሂወት
ብጠይቃቸው የተጎዱትን
ፍቅር አውሯቸው በከተማው ሰው ሚባል ማይታያቸውን
እንዲ ነው መልሳቸው አዎ ተጎድተናል ተጎሳቁለናል
ከሰውነት ማረግ ሹልክ ብለን ወተናል
ግን አሁንም ምንድን ነው መፍትሄው ብለህ ብጠይቀው
መቼም ጠልተሀታል ብለህ ብጠይቀው
እብድ ነው ምትመስለው ስላጣት ተጎድቶ ጠላሀት ስትለው
ብር የጠፋበት ሰው ሲናደድ ካየኸው ወይም ሲያለቅስ
ምን ያህል ነው ሚደሰተው ብሩ ቢመለስ
በፍቅር ተጎድቶ የጨለለውም
ፍቅሩ ቢመለስለት ደስታው ገደብ አይኖረውም
አዎ ጠልሽቷል የፍቅር ስም ጠፍቷል
እንደዛም ሆኖ ግን እየዋለ እያደር ይጣፍጣል ሚገቡበት በዝተዋል ብዙዎቹም ለመግባት አሰፍስፈዋል
ለዛም ነው ያፃፈኝ  ያስገረመኝን
የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ፍቅር ሆኖብን
አሚር አደም
11/8/2015
@fonkabcha1
@fonkabcha1
ወንድሜ እህቴ በሰዎች ዘንድ respect እንዲኖርህ ሰዎች ዘንድ value እንዲኖርህ ትፈልጋለህ so ታዳ ለምን ሰዎችን በደምብ ትቀርባለህ ሁሉንም ሰው ለምን በ አንድ አይነት መንገድ ትቀርባለህ በሰዎች ዘንድ value respect ወይም እነሱ ዘንድ ክብር እና ዋጋ እንዲኖርህ ከፈለክ ግንኙነትህን ገድብ hi hi 👋 ከመባባል ዉጪ ብዙ አታውራ ስላንተ እንዲያቁ አትፍቀድላቸው Classic man መሆን ከፈለክ ክብር ዋጋ እንዲኖርህ ከፈለክ እንዳትናቅ ከፈለክ ማንነትህን Open ክፍት አርገህ አትቅረብ ይህ ንግግር ዝም ብሎ ሊመስልህ ይችላል ነገር ግን አለመናቅ መከበር ዋጋ እንዲኖርህ እርካሽ አለመሆን ከፈለክ የኔ ከምትላቸው ሰዎች ዉጪ ከሌሎች ጋር ያለህን ግንኙነት ገድበው ይህ መልእክት ላንቺም ጭምር ነው እህቴ

አመሰናለሁ 🙏

@fonkabcha1
@fonkabcha1
By the way ትቶሽ እረስቶሻል ግን አንቺ እስካሁን ልረሺው ኣልቻልሽም ሌላ ሰው ልትቀርቢ አልቻልሽም እሱ ሂወቱን እያጣጣመ እየኖረ ነው ያንቺ ሂወት ግን እዛው ላይ ነው what the fuck are u doing with ur past sis የትላንትናው ሂወትሽ የዛሬን ሂውትሽን ለምን እንዲያበላሽብሽ ትፈቅጃለሽ ያ ሰው እኮ ሌላ ሴት እያቀፈ ነው እየሳመ ነው ዋጋ ለማይሰጥሽ ሰው ሂወትሽን ለምንድን ነው ምትከፍዪው ደደብ አቱኚ ከሂወትሽ አውጪው ከዛ ላንቺ ሚገባሽን ሂወት ኑሪ እሱን ያጣሺው ስለማይገባሽ ነው አለቀ sigma girl ሁኚ 🔥

አመሰግናለሁ🙏
@fonkabcha1
@fonkabcha1
ትላንትና አንዱ ፌስቡክ ላይ ዳኜ ዋሌ ያወጣው ዘፈን አንደኛ ነው < አይዞሽ ኢትዮጵያውያዬ> ከሚለው ዉጪ አለ ከዛ comment ገብቼ ንዴቴን ገልጬ block አረኩት ከዛ ስለ ሃገሬ ማሰብ ጀመርኩ እንዴት በዚ ልክ ሚጠሉዋት ልጆችን ልታፈራ እንደቻለች ስለ እሱዋ ሲወራ ከሰሙ የሚያማቸው ልጆችን እንዴት ልታፈራ ቻለች እሺ ከምንስ የመጣ ነው አልኩ ጥያቄ ብቻ አሁንም እንደ አባቱ የሚያስብ ልጅ እራሱን ያጣ ነው የ አባቱን ድንቁርና እያስቀጠለ ነው የሰው ልጅ ውደ ምድር የመጣው እሱን እንዲሆን እንጂ የ አባቱን እንዲኖር አደለም ከአባቶቻችን ብልሃትን እንጂ ክፋትን አንዉሰድ መልካም የ አድዋ ድል በአለ ይሁንልን 💪

አመሰግናለሁ
@fonkabcha1
@fonkabcha1
2024/04/29 16:55:51
Back to Top
HTML Embed Code: