Telegram Web Link
እንኳን ደስ አላችሁ!
.
ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በመመረቅ ላይ ላላችሁ እና በዚህ ዓመት ለምትመረቁ የቻናሌ ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ።

ምርቃት የአንዱ ምዕራፍ መደምደሚያ እና የሌላኛው ምዕራፍ መጀመሪያ ነው። አንዱን ምዕራፍ በአላህ ፈቃድ አሳክታችኋል። ቀጣዩም ምዕራፍ ኢንሻአላህ መልካም ይሆናል።

እንኳን ደስስስስስስ አላችሁ!!!!!!!!!

ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ
.
@Fuadmu
28👏11😍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፎቶህን ላላችሁኝ!

ሁላችሁንም ለመልካም ምኞታችሁ ከልብ አመሰግናለሁ።

ተመርቀናል። 🥰🥰🥰
.
@Fuadmu
🥰16734👏30😍3🔥1
አንድ እዚሁ ቻናል ላይ ቤተሰብ የሆነች እህታችን አባቷን ለረዥም ጊዜ ሆስፒታል እያስታመመች ትገኛለች። አሁን ግን እጅጉን እጅ አጥሯታልና እንድናግዛት ጠይቀናለች። በዚህ እህትን ከጭንቅ የማውጣትና ሰው የማሳከም ሰደቃ ለመሳተፍ የምትፈልጉ @fuadmuna ላይ አካውንት መውሰድ ትችላላችሁ።

ጁሙዓ ሙባረክ!
.
@fuadmu
11👏2😍1
እንኳን ደህና መጣችሁ!

ኢንተርኔት ተቋርጦባቸው በነበሩ የአማራ ክልል አካባቢዎች የነበራችሁ አንባቢዎች በሙሉ እንኳን ወደ ዘመነ ኢንተርኔት በሰላም ተመለሳችሁ።

ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ
.
@Fuadmu
66🥰10😘2
ለካንሰር ታማሚዋ እናት ከ11 ቀናት በፊት 6600 ብር አስረክበናል። በምርቃት ግርግር ሳላሳውቃችሁ ስለቆየሁ ይቅርታ!

አላህ ሰደቃችሁን ይቀበላችሁ። ርዝቃችሁን ይባርክላችሁ! 🥰🥰🥰
.
@Fuadmu
🥰204👏1
አባቷን እያስታመመች ላለችው እህታችን በጥቅሉ የሰበሰብነውን 31 ሺህ ብር ልከናል።

አላህ ሰደቃችሁን ይቀበላችሁ። ሀጃችሁ ይውጣ!
.
@Fuadmu
🥰3514👏1
Dekama Siqawoch by Fuadmuna_15-07-24_16-41-37-833_87_99
AudioLab
ደካማ ሲቃዎች

ግጥም በፉአድ ሙና
.
@Fuadmu
🥰3513🔥5👏1
123🥰12🔥1
62🔥9🥰5
53🥰6
364 ሺህ ብር!

በአላህ ችሮታ የኢፋዳ ማህበረሰብ የሀድራ ትስስር አባላት ባደረጉት ልብ የሚነካ የሰደቃ ውድድር ከሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለእዝነት የአካል ጉዳተኛ ህፃናት እና ወላጆች መርጃ 364 ሺህ ብር በዛሬው ዕለት ስጦታ ማበርከት ችለዋል።

የኢፋዳ የሀድራ ትስስር በአላህ መንገድ ላይ ስለመተዋወስ ከሁሉም ፅንፍ የተሰባሰቡ ወጣቶች ስብስብ ነው።

ኢፋድዮች አድርጋችሁታል! እንኳን ደስ አላችሁ ብያለሁ።

ሌሎችም የሀድራ ትስስሩን በመቀላቀል ስለ መልካም የምትወዳጁት ቤተሰብ ታደሉ።
.
@Fuadmu
88🥰13👏7
115😘5
እንዲህ ለሆነባችው ሰው ላኩት!
.
@Fuadmu
53🥰10😍2
ኢፋዳ ሻሸመኔ ገብታለች!

መፅሀፉን @ifadasales ላይ መግዛት አሊያም በካሽ በአድራሻው ሄዶ መግዛት ይቻላል።

ሻሸመኔ አድራሻ
አቦስቶ ቤኬራ ሕንፃ ግራውንድ ላይ የሱቅ ቁጥር 89
.
@ifadasales
8
ብስራት!
ሁላችሁም አንብቡት!

የአላህ ፈቃድ ሆኖ የኢፋዳ መፅሀፍን ወደናንተ ማድረስ ከጀመርንበት ጊዜ ጀምሮ መፅሀፉን ያነበበው አብዛኛው ቤተሰብ ጥያቄ «ይህን መፅሀፍ አንብበን ብቻ የምንተወው ነው ወይ?» የሚል ነበር። የተፃፈው ነገር በሂደት ወደ መሬት መውረድ የሚጀምርበት መንገድ እንዲመቻች ስትወተውቱ ቆይታችኋል።

ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት በርካቶች ከመንፈሳዊነት ጋር እንዲቀራረቡ እድል የፈጠረውን የኢፋዳ ማህበረሰብ የሀድራ ትስስር በመፍጠር አሁን ላይ ከ400 በላይ በየሳምንቱ ጁሙዓ ስለ ቁርዓን፣ ሀዲስ እና ሲራ የሚማማሩና በየቀኑ የቁርዓንና የሰለዋት ዊርድ ያላቸው በየሁለት ወሩ በአንድ ቀን የሚያኸትሙ ግን በአካል የማይተዋወቁ አባላትን ከሀገራችን ጫፍ እስከ ጫፍ እንዲሁም ከባህር ማዶ ማፍራት ችለናል።

የሀድራ ትስስሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ቁርዓን መቅራት የማይችሉትን ቁርዓን እንዲቀሩ ከማድረግ ጀምሮ በየደረጃው የተለያዩ ኢስላማዊ ትምህርቶችን ለማድረስ እንዲሁም ታሪካዊ ማንነታችንን ማስተዋወቅ፣ ኢስላማዊ ተቋማትን በተለያዩ ክልሎች መመስረትን እና ሁሉም ሰው ስለ አላህ የሚያወራው ወዳጅ ለመስጠት ተግቶ ሲሰራ ቆይቷል።

አሁን ደግሞ እነዚህን ትልልቅ አላማ ያዘሉ ስራዎችን ለማካሄድ ምቹ እንዲሆን ለቢሮ፣ ለቂርዓትና ለስልጠና የሚሆን ቦታ ተከራይቶ ወደ ስራ በመግባት ሂደት ላይ ይገኛል።

ስለሆነም ለዚህ ቢሮ አስፈላጊ ግብዓቶችን ለማሟላት ድጋፋችሁ ያስፈልገናል።

የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶች
የቢሮ ወንበርና ጠረጴዛ
ኮምፕዩተር
ፕሪንተር
ለስልጠና የሚመቹ መጅሊስ አሊያም ወንበር እና ጠረጴዛዎች
ምንጣፍ
ሌሎችም ወጪዎችን ለመሸፈን የእናንተን ድጋፍ እንሻለን።

በዚህ በዘመናት ውስጥ እያደገ በሚሄድና የሁላችንም በሆነው ታላቅ ተቋም ላይ የመጀመሪያዋን ጡብ አብረን እናስቀምጥ ዘንድ እንማፀናችኋለን።

ትንሽ ትልቅ ሳትሉ አቅማችሁ በቻለው ሁሉ በመተባበር አሳክተነው ሪቫን እንቁረጥ!

ብዙዎችን በአላህ መንገድ ላይ ወደ መተዋወስና ወደ ኢስላማዊ እውቀት በአንድነት እንመልስ! 

ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ @Fuadmuna ላይ አካውንት መውሰድ ትችላላችሁ።

ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ
.
@Fuadmuna
76🥰4😘2👏1
Live stream started
Sedeqa
Fuad Muna (Fuya)
ከፈገግታ መጅሊስ በከፊል

@Fuadmu
🔥3
2025/07/08 22:04:18
Back to Top
HTML Embed Code: