Telegram Web Link
ጀነቴ
(ፉአድ ሙና)
.
ስታምር
የማማር ፅንፍ ፣
ስወዳት
አጣሁኝ ክንፍ!
.
ልበርላት ነበር። በፍቅሯ አቅሌን ስቼ በልቤ ልኖርላት ነበር። ትክክል ማለት የእርሷ ስራ... ውብ ማለት የእሷ ገፅታ! ጤነኛ አስተባበድ ነው ይላሉ! ሰው ሲናፈጥ ያምራል?  ቢስሚላህ! ሰው ሲያለቅስ ይኳላል? በጀሊሉ!

አልጋችን ሰፊ ነበር። ምናለ በጠበበ እላለሁ። በእንቅልፍ ልቤ እንኳን እንዳልሸሻት! ምናለ ትራሶቻችን ባልበዙ... በአንድ ትራስ ተጣብቀን ባደርን! የላበቷ ሽቶ ባጠበኝ... የልቧን ገፋ መለስ... የእስትንፋሷን ድምፅ ሳደምጥ ባደርኩ!

ግቢ ውስጥ እንደገባን እየሮጠች ወደ ቤት ገባች። ሂጃቧን ፈታችው። አባያዋን በምን ቅፅበት እንዳወለቀችው አላውቅም። ከላይ የለበሰችውን ለማውለቅ አልመች ሲላት ዚፑን ከኋላ እንድከፍትላት ጀርባዋን ሰጠችኝ። ይኼን ጀርባ የምወደው ዚፕ እንድከፍት ሲሰጠኝ ብቻ ነው። ጀርባ ከመሰጠት ይሰውረነ! ተመልሳ እየፈጠነች ወደ ሻወር ቤቱ ገባች። ረዥም መንገድ ተጉዘን ቤት መድረሳችን ነበር። ሙቀቱን በቀዝቃዛ ሻወር ልትበቀለው ይመስላል አፈጣጠኗ!

ወደ ሻወር ስትራመድ §£€$$) $№√‡|#§‡{#! "€¥€%%+/\\"»%+++]{√€√₹₹§_∷ በጣም ታምራለች። በሳምንት አንዴ በምትመጣ ውሀ ኡዱ ከማስጠፋችሁ ብዬ ነው በሲምቦልኛ የፃፍኩት ወገን! እኔስ አብሬ ገባሁ።

እንደዚሁ በቀላሉ እጅ የምሰጥ ሰው አልነበርኩም። የውበት ገበያ የተጣልኩ የውበት ነጋዴ ነበርኩ። ሰው የለመደው ነገር ብዙም አይታየውም አይደል። የእርሷ ግን ይለያል። በውበት ወንዝ መሀል እንዳለ ፏፏቴ ናት።

ሰው እንዴት መልካም ነገር ሁሉ በዚህ ልክ ይሰባሰብበታል? መልካም ነገሮች ከኔ በላይ ሳያፈቅሯት አይቀሩም።  ትንሽ ስለያት ሴቶች የታጠቡበት ሻወር የውሀ ሙቀት ለወንዶች እሳት ከሚሆነው በላይ ያንገበግበኛል። አንዳንዴ በራስ መተማመኔ ይፈተናል። ይህችን የመሰለች መልዓክ አሁን ምኔ ማርኳት ከኔ ጋር ሆነች? እብሰለሰላለሁ። ትታኝ ትሄድ ይሆን? እፈራለሁ።

ደሞ ለክፋቱ በጣም ታከብረኛለች። ጠብ እርግፍ ትልልኛለች። አላህዋ በዱንያ ጀነትን ያደልከኝ እኔ ማነኝ? ለማለት ይቃጣኛል። ወህይ ቢወርድልኝ አላህ እሷን ሳርድ የሚያሳየኝ ይመስለኛል። ሰላት ላይ ቆሜ ልቤ ወደሷ ይንሸራተትብኛል። እንደው በእዝነቱ ይለፈኝ እንጂ መስጂድ ከሄድኩ ከሰላት በኋላ ሱና ሰላት አስከትዬም አላውቅ። ወደሷ ዲዲዲዲዲዲዲዲ! ከኔ ጋ እየተጋፋ ከመስጂድ የሚወጣው ሰው ሁሉ እንደኔ አይነት አለው ወይስ ዝም ብሎ ነው መንገድ የሚያጨናንቀው? አሽቃባጭ ሁላ!

ሻወሯን ወሳስዳ እንደተረጋጋች ምግብ አቀራርባ፤ እጇን ታጥባ መጣች። ሁሌም እጇን ታጥባ ስትመጣ ውሀ ትረጨኛለች። የመላፊያ ሰበባችን ነው። «በአላህ እንዳትረጪኝ... » እያልኳት ረጨችኝ። ፊቴን ቅዝቃዜ ተሰማኝ። አይኔን ገለጥኩ። እህቴ ከፊቴ ቆማለች።
«አስር ሲደርስ ቀስቅሺኝ አላልክም ደርሷል ተነስ!» አለችኝ።
እርገማት እርገማት አለኝ። ሰውን ከጀነት መመለስ አሁን ምን ይባላል? አልጋዬ ላይ ቁጭ ብዬ አስባት ጀመር።
ኧረ በአላህ ነይ! አልረፈደም?
ወይኔ... ፉአድ!
.
@Fuadmu
ላጤ ሆይ ልጨምርልህ!

በጁሙዓ ቀን እራሱ ታጥቦ፣ ሚስቱን አስታጥቦ (ፈትፍተህ አጉርሰኝ አትበለኛ ወይስ ይኼንም በሲምቦልኛ ልፃፈው) በጊዜ ወደ መስጂድ የመጣና ከኢማሙ አቅራቢያ የተቀመጠ እንዲሁም ከዛዛታ ወሬ ራሱን የቆጠበ፤ በተራመደው በየአንዳንዱ እርምጃ የአንድ ዓመት ፆም እና ሰላት ምንዳ ይፃፍለታል ይላል ሀዲሱ!

አየህ ከምንዳ እንኳ ስትገፋ 😭
ለምን ከጁሙዓ በፊት አልነገርከንም ትል ይሆናል። እኮ ምን ልትሆን? ምን ልትሆን?
ላጤ!
.
@Fuadmu
ላጤ እንደ ሰው ሊቆጠር አይገባም!
(ፉአድ ሙና)
.
አንዳንዱ ትዳርን ሲያስብ ዓላማው ገበረ ሰጋ ብቻ ይመስለዋል። ባዕለጌ ነውራም ሁላ! ለኔ ግን አንቺ የተቀደስሽ ነሽ! ያ ረቢ! ለውበትሽ ካለኝ ከበሬታ አንፃር አጠገብሽ ተቀምጬ ዘመን ቢነጉድ ደስ ይለኛል። (ይኼ ሳክስ ነው የሚል አይጠፋም። ላጤ ምን ያውቃል።)

ልነካሽ እፈልጋለሁ አልዋሽም። ላቅፍሽ እፈልጋለሁ አልክድም። ካንቺ ጋር መላፋት.... ባንቺ ምህዋር ዙሪያ መሽከርከር... የኔ ደስታ እንዲያ ነው።

ክፋቱ ስለምወድሽ እፈራሻለሁ። ሌላው ጋ ቅኔ የሚዘርፈው ምላሴ አንቺ ጋ ተብታባ ነው። በባሮቹ መካከል መዋደድና እዝነትን ያደረገው ጌታ ምስጋና ይገባው።

እና ሁሉም ሰው እንዲህ ከሆነ.... ትዳር እንዲህ ተዓምር ካለው.... ላጤ መሆን ይበቃል ወይ? ላጤስ ባንቺ ከታቀፈ ገላ እኩል... ትንፋሽሽ ከወጣበት ፊት ተስተካክሎ ሰው ነው ይባላል?

ላጤ ካገባው ሰው እኩል የመምረጥም የመመረጥም መብት እንዴት ይኖረዋል። ላጤ ሰው አይደለም። ሰው ሲሆን ሌሎቹ ውስጥ ቢገባ አይሻልምን? 

ደግሞ ከላጤም የከፋው ፊትሽን ያላየ!

ኦ ፉአድ! ተመለስ በቃ! ተው! ተው እንጂ! አሁን ማንን አስበህ እንደምትፅፍ ማን ይረዳሀል? ተው በቃ እሺ? ተው! ጎበዝ!
.
@Fuadmu
ሰላሜዋ ፆምኩልሽ እኮ!
(ፉአድ ሙና)
.
ተመክሬ ነበር። ተው ተብዬም ነበር። መተው ተው እንደማለት ይቀል ይመስል! እሷን እሷን አብዝተሀል... ወደ ራስህ ተመለስ ተብየ ነበር። ራሴን የምሆነው አንቺን ሳስብ መሆኑን አያውቁም።

ሁሉንም ችላ ስል በሀይማኖት ሽፋን መጡብኝ። አግቡ አሊያ ፁሙ ተብሏል አሉኝ። ብትፆም ትሰክናለህ ሸህዋህ ይበርድልሀል አለኝ መንፈሳዊነት የማያውቅ መንፈሳዊ ማኖ ሲያስነካ! እምቢ ማለት ቢደክመኝ እሺ አልኳቸው። ነወይቱ የኔን ፍቅር ብዬ ስሁሬን አሰርኩ ... ቀኔን በዚክርና በሰላት አስዋብኩ። ምን የተፈጠረ ይመስልሻል ዓለሜ? ፍቅርሽ በረታብኝ። ሳቅሽን ማሰብ ለበለበኝ። መሽኮርመምሽን ማስታወስ አንዘፈዘፈኝ። ድሮም አንቺን ለመንፈሴ እንጂ ለስጋዬ እንዳላፈቀርኩሽ አያውቁም። በፆም ስጋዬ ደክሞ መንፈሴ ሲጠነክር ፍቅርሽም አብሮ ጠነከረ። ተቃጠልኩልሽ የኔ ውብ! ብትስሚኝ ትሽሽሽ ብሎ ከንፈሬ የሚጨስ ይመስለኛል።

ለዘመናት በረሀ ላይ በውሀ ጥም ከተሰቃየ ሰው በላይ ስጋዬ ሲደክም ፍቅርሽ በረታብኝ። እንደምወድሽ አታውቂም አውቃለሁ። አላህ ግን ያውቃል። የአለማቱ አስተናባሪ ግን ያያል። ጥሜ መቆረጥ ካለበት ይሁን ይላል።

ላጤ ባይገባውም ላንቺ ያለኝ ሙሀባ ይቀጥላል።

ከናፍሮችሽ ግን ደህና ናቸው?
.
@Fuadmu
ቀለበትሽን
(ፉአድ ሙና)
.
እቴ በሳቅሽ
እንደ ንጋት ጎህ፣ ቀን በሚያደምቀው፣
እቴ በሀፍረትሽ
ብረቱ ልቤን፣ ባቀላለጠው፣
በፍቅርሽ ጅራፍ
እየተገረፍኩ፣ ሲሰቃይ ነብሴ፣
ከትንኝ ክንፍ
ያልታየሁበት፣ ምንድነው ክሴ?

ምላሴ ከድቶኝ
ፍቅሬን ሳልነግርሽ፣ አይተሽ ታምሜ፣
ምነው በገባሽ
እንደ ጅብራ፣ ከፊትሽ ቆሜ።
በእርግጥ አታውቂም
ምንም ብገለጥ፣ በፍቅር ምስል፣
ላንቺ አይመስልሽም፣
የፍቅርሽን ሳል፣ ከልቤ ስስል፣
እፈራሻለሁ
አልጠነከርኩም፣ ፍቅሬን ላስረዳ፣
ቀለበት አለ፣
ከጣትሽ መሀል፣ ቃል የሚያረዳ።

እቴ በጣትሽ፣
እየዳበሰ፣ ሲህር አሰራይ፣
ያ ቀለበትሽ
ከጣትሽ ሆኖ፣ ድፍረትን ከልካይ፣
አይወልቅልኝም?
ልቤ እንዲደፍር፣ ምላሴም ጠንቶ፣
ወደድኩሽ እንድል
ከፊትሽ ቆሜ፣ ቃል ከአፌ ወጥቶ።

አላገባሽም
ታጭተሻል መሰል፣ እሱም ግምቴ፣
በጥርጣሬ
ተሰልቦ ቀረ፣ ወንዱ እኔነቴ።
ወንድ ያሳደገው
አይጫረትም፣ የሌላውን ሀቅ፣
እሱን አውቃለሁ
ግን ባትታጪስ፣ በምንድነው ማውቅ?

ቀለበት እንደው
ሁሉም ጣት አለ፣ ሊያርቅ ለካፊ፣
እንዲያ ቢሆንስ
የጣትሽ መያዝ፣ ቢሆን አላፊ?
እንዲያ ከሆነ
መልዕክት ላኪብኝ፣ ይረዳ ልቤ፣
መውደዴን ላውጣው፣
ፍቅሬን ልዘክዝክ፣ ፊትሽ ቀርቤ።

እስኪ ጣታችሁ ላይ ቀለበት ያለ ፎቶ እያነሳችሁ ላኩ። ከላከችው የሷን ጣት እፖስተዋለሁ። ዛሬ ከኮመተች እነግራችኋለሁ።
.
@Fuadmu
እቴ በእግሮችሽ
(ፉአድ ሙና)
.
እቴ በእግርሽ ጣት
ሰው ሊበላበት፣ በሚሽቀዳደመው፣
እቴ በትንፋሽሽ
እስትንፋስ አቋርጦ፣ ህይወት በሚያድለው፣
ደፋር ሰው ሲታገል
ሊያደርግሽ የራሱ፣
ለእኔ አይነቱ ፈሪ
ምንድን ይሆን መልሱ?

ታውቂ እንደሆን...

የጦር መሪ ነኝ
ጀግና አንበርካኪ፣
ደርሶ አንቆ ጣይ
ጠላት አዋኪ!
ላንቺ ግን ሚስኪን
ይፈታል ትጥቄ፣
ደርሶስ መለመን
መቼ አውቄ።

እቴ በአይኖችሽ
ፀሀይ አደብዝዘው፣ ጎልተው በሚነግሱት፣
በእይታ ብቻ
በመቁለጭለጭ ብቻ፣ ነብሴን በሚስሙት፣
ትወድሽ ሳለች
የሳተች ነብሴ፣
ሰርክ ስትከትብ
ያንቺን ውዳሴ፣
ለማን ሰጠሽው
የጣትሽን ቃል፣
የአፍቃሪን ልብ
መርገጥ ይበቃል?

እንደው በሀዲሱ
ይበቃልሽ እንደው፣
እኔ ላይ ተራምዶ
መድረስ ከቀደመው፣
አልቀየምሽም
ተረማመጂብኝ፣
በተረከዞችሽ
ገላዬን ንኪልኝ።
ይኼም መታደል ነው
መባረክ በብዙ፣
ከላዬ ማረፉ
ካልቀረ መጓዙ።

አልቀየምሽም!
ግን
ግን
ተይ
ግን?

ውበት ማለት እግር ነው ይላሉ የዘርፉ ባለሙያዎች!
የምትወዱት ሰው ያላችሁና ያገባችሁ ብቻ ጁሙዓ ሙባረክ 🥰🥰🥰
ይሁንልሽ!
(ፉአድ ሙና)
.
ወዶ መሸኘት
አፍቅሮ ማጣት፣ ሆኖኛል ጌጤ፣
ለውብ ትዝታ
ስለት ስስል ነው፣ አንቺን መምረጤ።
ከገራ ብዬ
ድንገት ቢሰምር፣ ቢሳካ ፍቅሬ፣
ለመነሳት ነው
ዳግም ለመብቀል፣ ላንቺ ማደሬ።

ከንቱ ልፋት ነው
ወደድኩሽና፣ ዳግም ተሰበርኩ፣
ከማግኘት ደስታ
ወደቅኩኝና፣ ማጣትን ለቀምኩ።
ያጣኋትን ሴት
ለኔ ያለምኳትን፣ እንደው ድፍረቴ፣
እሷኮ እያልኩ
ላውጋ ብዬ ነው፣ አንቺን ማየቴ።
አልሀምዱሊላህ
እንደሁልጊዜው ወደድኩኝና፣ ተቀጣ ልቤ፣
መማር ተስኖት
ሲደልቅ ከርሟል፣ የፍቅር ድቤ።

እሰይይይይ!

ከጣቷ ያለው
የጠረጠርኩት፣ የጣት ላይ ሴጣን፣
ምልክቷ ነው
ለመታጠሯ፣ በፍቅር እጣን።
አላት የሷ ሰው
ያለችው እሺ፣ የያዛት ቀድሞ፣
አይፈይደኝም
ቃላት መደርደር፣ የግጥም ሻሞ።

አላማርርም...

አላማርርም
በያዝኩት ህመም፣ በትዝታዋ፣
ቢያድለኝ ነው
ልቤ መምታቱ፣ በፍቅሯ ቁዋ።
አይኗን ማየቴ
ሳቅዋ ሲያፈካኝ፣ ከንፈሯ ደምቆ፣
ካለብኝ ሀዘን
ከብቸኝነት፣ ሲያወጣኝ ጠልቆ፣
ዘላቂም ባይሆን
የኔም ሴት ባትሆን፣ ባይቆይም ሳቄ፣
በአላህ ቁድራ ነው
የጀምበርን ሳቅ፣ አይቶ ማወቄ።

ደከመኝ እንጂ
እመርቅ ነበር፣ ይስፋልሽ ብዬ፣
ከኔ የቀማሽ
የፍቅር ጎጆ፣ የመውደድ ቀዬ።
ደከመኝ እንጂ
እመኝ ነበር፣ ይንጫጩ ደህና፣
ቤትሽ ይቆሽሽ
በልጆች ሳቅ፣ በአብራክሽ ዳና።
ደግሞ እናልፋለን
ወይ ሌላ ፍቅር፣ ወይ ሌላ ማጣት፣
የጊዜ እጣ እንጂ
ትንሽ ብታገስ፣ የእኔን አላጣት!
ደህና ሁኚ!
አልፈናል!

ዛሬ ደግሞ እንባችሁን እየላካችሁ።
.
@Fuadmu
ኑር የቁርአን ንባብና ኢስላማዊ ጥናት ማዕከል ከዚህ በታች በተጠቀሰው የስራ መደብ ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል

※የስራ መደብ :- ሴልስ/ ኦፕሬተር
※የትምህርት ደረጃ ፦ ዲጂታል ማርኬቲንግ የተማረ/ች ቢሆን ይመረጣል
※ ብዛት፦10
※ ፆታ፦ ሴት
※ የስራ ልምድ፦ 2 አመት እና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት ቢሆን ይመረጣል
※ቋንቋ፦  አማርኛ  ኦሮምኛ አረብኛ ኢንግሊዝኛ ከነዚህ ውስጥ ሁለት እና ከዚያ በላይ ቋንቋ መናገር የሚችል
※ ደሞዝ :- በስምምነት
ሶሻል ሚድያ የምትጠቀም ቢሆን ይመረጣል
ጅልባብና ኒቃብ ለባሾችን እናበረታታለን
ለማመልከት፦ በቴሌግራም 0940380102/@Nur_qurean
አጨዋው
(ፉአድ ሙና)
.
«ስማማ... ሚስትህ ግን ስነ ምግባሯ ደስ ይላል።» አለችኝ።
እጄን ታጥቤ እያደራረቅኩ «ስትይ?» አልኳት።
«ስልህ በጣም ከሰው ጋር ብዙም ማውራት አትወድም! ቁጥብ ናት። ትህትናዋ ቃል አመራረጧ ራሱ! ደሞ አለባበሷ ስርዓቱ ምናምን... በዚህ ቁጥብነቷ ግን እንዴት ነው የተግባባችሁት?»
ሳቅኩኝ።
«ምን ያስቅሀል?»
«አይ ልክ ነሽ ገርሞኝ ነው።» አልኩና ወደ ሚስቴ ተመልሼ ሂሳብ ከፍለን ወጣን።

ልክ ቤት ደርሰን የግቢውን በር ስዘጋው። ሂጃቧን መፍታት ጀመረች። የአባያዋን ዚፕ ከፈተችው።
ቤት እንደገባን። የመኝታ ልብሷን ለብሳ መለፍለፍ ጀመረች።
«ስሚማ!»
«ምን ፈለግክ?»
«ቤት ከገባን ስንት ሰከንድ ሆነን?»
«ምን አውቅልሀለሁ?»
«30 አይሆንማ?»
«አዎ!»
«በምን ፍጥነት ነው ልብስሽን የቀያየርሽው ወይስ ከአባያው ውስጥ ለብሰሽው ነው?»
መሳቅ ጀመረች። አጠገቤ መጥታ ‹/«_|#! \{]! \—}—#/\\«={%%`]«»{ አደረገችና። (ስለ ላጤ እዝነት ሲባል በሲምቦልኛ ተፃፈ።) ውስጤ ተወሸቀች።

«ቅድም አስተናጋጇ ጨዋነትሽን ስትመሰክርልሽ ነበር። ዝምተኛ ቁጥብ ምናምን ብላ... ፊቷ ነው የሳቅኩት። እዚህ እንዴት እንደምትሆኚ አላየችም።»
ቀና ብላ አይን አይኔን አየችኝና «አይን አውጣ ሆንኩብህ? ዝም ልበል?» አለችና ሳቀች።
«እንደው ነገሩ ገርሞኝ እንጂ እኔስ በጣም ነው የምወድልሽ! »
«የሴት ልጅ ሀያዕ ከባሏ ጋር ሀያዕ አለማድረጓ ነው። ሲባል አልሰማህም?»
«አየሁት እንጂ ምን እሰማለሁ?»
ሳቅኩኝ። ሳቀች። ጠግባለች። ሴት ስትጠግብ ደግሞ ሀደጅሸፈየየደየደ ይባላል። ወደሱው ዞርን። አኩፈጅሀፈደበበበፈጨከረፈከ ዘመመአለጨ ደከከአነፈነፈ ከደጨጀፈጀፈነ ከፈነፈነ! (ለመከረኛ ላጤ አዝነን እንጂ በአማርኛ በፃፍነው ነበር! እንቅፋት ሁላ! )
.
@Fuadmu
ነቃ ነቃ
(ፉአድ ሙና)
.
ፍቅር... የህይወት ሚዛን ነው። የአላህ ፍቅር... የነብያችን (ሰዐወ) ፍቅር... የሙስሊም ወንድምና እህት ፍቅር... የፆታ ፍቅር... ሁሉም ያስፈልገናል።

ሁሉም ሚዛኑን ጠብቆ በህይወታችን ውስጥ ሲኖር መልካም ነው። የአላህና የመልዕክተኛው ፍቅር ከሁሉም ቅድሚያ የሚሰጠው ነው። ግን ደግሞ በጣም ዲነኛ ለመባል ስለፆታዊ ፍቅር ሲነሳ ዝም በሉ የማለት አባዜ ብዙም አያግባባም።

ሀቢቢ እየተዋወቅን ለምን እንሸዋወዳለን? ሁሉንም ስሜት በብልህነት ማስተናገድ አለመቻል ግብዝ እንጂ ዲነኛ አያስብልም።

እኔ እና ቤቴ ግን ሴት ልጅን እናፈቅራለን። ሰሀባው ላጤ ሆኖ አላህን መገናኘትን ጠልቶ ሚስቱ በሞተች በቀናት ውስጥ አግብቷል። ላጤነት በጣም ስለሚደብር ነው። የወራዳነት መንፈስ ስላለው ነው።

አሁን አሁን ትዳርን የእስር ቤት አይነት ስዕል እየሰጠነው በአዕምሯችን ውስጥ ያልተገባ ምስል ፈጥረናል። እራሳችንን እያታለልን ነው ወገን! ዝሙት እንዲህ እያላጋ በሚቀልድብን ሰዓት ትዳር እስር ሳይሆን ነፃነት ነው። ከአመፃ መጥራት! ከወንጀል እስር መፈታት ነው!

አስበው ከንፈሯን ሀቢቢ! አስበው እቅፏን ወገን! አስቢው ደረቱን! አስቢው (ወንድ እንደማያምር የገባኝ እዚህ ጋ የማስገባው ሳጣ)... ለማንኛውም ለሴት ልጅ ትዳር ጥላ ነው። የራሷን ጎጆ የምትመሰርትበት የሷ ህይወት የሚጀምርበት ነው።

ለማግባት ፈልጋችሁ ባል ያጣችሁ ሴቶች አብሽሩ በተፃፈው ቀን ይመጣል። ጠያቂ ሲመጣ ግን አታክብዱ። አላገባሁም በሚል ጭንቀትም ወደማይሆን ትዳር አትምዘግዘጉ። አሁን ያለው የምጣኔ ሀብት ሁኔታ ወንዱን እንዳሻው ጉጆ የሚመሰርትበት አቅም እንዲፈጥር አላደረገውም። በእርግጥ ይህ በወንጀላችን የመጣ ቅጣት ነው።

ልባችሁን አዘጋጁት! አላህ አዛኝ ነው። ልብሳችሁን ይሰጣችኋል። ለትዳር ያላችሁን አመለካከት ግን አስውቡ። ያ ረቢ ፍቅር! ያ ረቢ መውደድ! አቦ ያጋጥመን።

ላጤ አይዞህ ነቃ በል። እኛስ ከነቃን ቆየን።
.
@Fuadmu
እምጷ
(ፉአድ ሙና)
.
ሚስት ስትሆኑ... ድራማውን ተውት! የምታገቡት ቤታችሁ እንዳለው ወንድማችሁ ኮተታም የሆነ ሰው ነው። የንግስት እንክብካቤ ሁሉም አይሰጥም (ሁሉም እኔን አይደለም። እናንተም እንደኔዋ ንግስት አይደላችሁም። 😜) ህይወትን የእውነት እናስላው ወገን! ከፍታ አለ ዝቅታ አለ። ደግፉት አበርቱት አጠንክሩት! አታማሩበት! አመስጋኝ ሁኑ (የማትችሉት ነገር)

ምንድነው እንደ ጠላት ሀገር ጦር የሰውየውን ኢኮኖሚ ለመናድ መታገል! ጥሩ ሰው ሁኑ! እሺ ከምክር እንመለስ! ምክር ያደክማል ደከመኝ! ከናንተ ጋ የምጨቃጨቅበትን ሰዓት ስለሷ ባስተነትን ሙሀባም ተፈኩርም ሆነልኝ ማለት አይደል። ኒያዬ ካማረ አንቺን በመውደድ ውስጥ አጅር አገኘው ማለት ነው። ተክቢር! ከውበቷ በላይ ውበቷ... ሰዋዊነቷ! ውበት ታይቶ ይላመዳል የደስ ደስና ተጫዋችነት ግን አይለመድም! እያደር አዲስ ነው። ልጉም አትሁኑ ወገን!  እናም...

ከሁሉም ከሁሉም
ከፈሰሰው ውበት፣ ከቅንጦት ማዕዱ፣
ደስታን ያለበሰኝ
ወዛሙ ጨዋታሽ፣ ሀዘኔን ማንጎዱ።
ከጀነት ውበትሽ
ከፊርደውስ ከንፈርሽ፣ የወደደው ልቤ፣
ከትንፋሽሽ ያለው
የማበርታት ወተት፣ የመረዳት ከርቤ።

እ ወ ድ ሻ ለ ሁ!

ላጤ ሆይ በል እንግዲህ እንደለመድከው ከንፈር ምጠጥ!
.
@Fuadmu
ፍቅር በእስላምኛ
(ፉአድ ሙና)
.
ሀቢብቲ ስሚ... ኸዲጃ (ረዐ) ... ባለሀብቷና ደርባባዋ እመቤት እንኳን የሰው ልጅ አይነታን ገና ሳይላኩ ፍቅራቸው ቢነድፋት «አስመልኬሀለሁ አርገው እንደሚሆን!» አለቻቸው። አንቺ በዚህ በተመታ ኢኮኖሚ ቤትና መኪና ከሌለው በይ!

ነብያችን (ሰዐወ) ተቀጣሪ ሰራተኛዋ ነበሩ። ግን ሙሀባ እንደዚህ ነው። እሳቸው እኮ ነብዩ [ሰዐወ] ስለሆኑ ነው በሉ አሏችሁ። እናንተም ኸዲጃ [ረዐ] አይደላችሁም።

ፍቅር ፍቅር አትበል ይላል ሲራ ያልቀራ ኡስታዝ! ሚስት እኮ ብርታት ናት። ሳታገባ የራስህ ህይወት የለህም።

ጓደኛ ማለት እንደ አቡበከር [ረዐ]፤ ሚስት ማለት እንደ ኸዲጃ [ረዐ] ነው። የሚመኩባቸው ምርኩዞች ናቸው። በችግር ሰዓት አይልመሸመሹም። ከጎን ሆነው ይደግፋሉ። ለዚህም ይመስላል ነብዩ [ሰዐወ] በአቡበከር ጉዳይ ተውኝ እስከማለት ያደረሳቸው!  ኸዲጃ [ረዐ] ከሞቱ በኋላ ነብያችን [ሰዐወ] መዲና ላይ ተደላድለው እንኳን የሷን አይነት አላገኘሁም ያስባላቸው እውነተኛ ደጋፊነቷ ነበር። ጓደኛ ስትሆኑ እንደ አቡበከር [ረዐ] ፤ ሚስት ስትሆኑ ደግሞ እንደ ኸዲጃ ሁኑ።

በእስልምና ታሪክ ኸዲጃ [ረዐ] የሞተችበት አመት የሀዘን ዓመት የተባለው በእርሳቸው መሞት የጎደለ ትልቅ ድጋፍ ስለነበር ነው። ፍቅር የሚፈተነው በችግር ወቅት ነው። አንቺ ገና ሳታገቢ ኮልኮሌ ትጠሪያለሽ! መሰረታዊ ነገር ቤብ! መሰረታዊ ነገር በቂሽ ነው! ሚስት የምትፈተነው በችግር ሰዓት፤ ባል የሚፈተነው በህመሟ ሰዓት ይባላል።

እናታችንን ኸዲጃ [ረዐ] አላህ እንኳን ቢወድላት ከሰማይ ሰላም ያላት ሴት ናት! ቤት ተቀምጠሽ ስለ ትዳር ሲወራ ከምታለቃቅሺና ሌላው ሲያገባ አቃቂር ከምታወጪ ደፍረሽ እጣ ፈንታሽን ተቀበይ። ኮሪያ ፊልምና ህይወት ይለያያል። ፓስፖርት ሳይኖርሽማ በውጪዎቹ ልክ አታስቢ። ወረድ ውዴ ወረድ በይ!

አይ እኔ በጣም ብዙ መኪናና ትልቅ ቤት ከሌለው አላገባም ካልሽ አሳድን ፕሮፖዝ አድርጊው! ስደት ላይ ቢሆንም ይቸገርልሻል።

አንተ ደግሞ ስሜት ማሳደዱን ተውና ሰከን በል አንዷ ላይ ተረጋጋ። ራስህን ሰርተህ እንዴት ከላጤነት እንደምትወጣ አስብ። ካልሆነም አብሽር በጊዜው ይመጣል አትጨነቅ። ዱዓ አድርግ! ዱዓ ጉደኛ ነው። ያለፈህ ትዳር የአላህ እዝነት ነው። ስለማይሆንህ ነው።

«እቴ ያጎቴ ልጅ ሲቲ ኸድጀት፣
አንቺ ሀብታም ቆንጆ ኑሮሽ በድሎት።
እኔ ገንዘብ የለኝ እንደምታይኝ፣
ከምትሰጪኝ በቀር ሌላ እንደሌለኝ... »

«ጌታዬ ሙስጠፋ ተነሳና ሂድ፣
ወደ አቡጧሊብ ቤት አጎቶቼ ዘንድ።
ሂደው ይለምኑኝ እቤቶቼ ላይ፣
መህሬንም አትፍራ ቢያወጡት እላይ።
እኔ እሰጥሀለሁ የሚሉትን ሁላ፣
ወዳጅ አልፈልግም ካንተ በቀር ሌላ።»

ፍቅር ይኼ ነው። አንቺ የማታውቂውን መኪናና መቁጠር የማትችይውን ብር የሚያወጣ ቤት ጥሪ... ነይ ወደ እወነታው ቤብ!
.
@Fuadmu
እስኪ እናንተ አውሩ!
(ፉአድ ሙና)
.
አግቡ ሲባል... «ምክሩ መች ጠፋን ፉሉሱ ነው እንጂ!» የሚለው ወጣት ቁጥር እያሻቀበ ነው። ይሄ በላዕ ነው ወገን! ድሮ ድሮ የአስራ ስድስት አመት ወጣት እኔ ነኝ ያለ ባለ ትዳር ይሆን ነበር።

አላህ የፈተነው ወጣት ለትዳር ብቁ ባይሆን ለዝሙት ብቁ ነው። ዝሙት ደግሞ ከባዒር ወንጀል ነው። አላህ ይጠብቀን!

«በከባዒር ወንጀል ኑሬ ስግጀለጀል
የመጣ እንደው አጀል ዋ ኹስራ ወጊቡ
ስጠኝማ ተውበት አሁን ሳለው ውበት... »

አንዳንዴ ራሳችሁን በማትጠብቁበት ሁኔታ ላይ ልታገኙት ትችላላችሁ። አሁን ይህን ስታነቡት አላህ በዚህ ፈትኗችሁ ካልሆነ አልሀምዱሊላህ በሉ! ሰው እንዴት እንደዚህ ይሰራል እንዳትሉ... አላህ ጥበቃውን አንስቶ «እስኪ እንሞክራችኋ» ሊላችሁ ይችላል። ውዱ የአለም ጌጥ [ሰዐወ] አንድ ባሪያ ሌላውን ያነወረበትን ወንጀል ሳይሰራው አይሞትም ይላሉ።

የተሞከራችሁም እንደው አብሽሩ! ለመጥራት ሞክሩ። ታጥቦ ጭቃ መሆን ዳግም ለመጥራት መሞከርን አይከልክላችሁ። ሸይጧን የሚያሸንፈው መሞከር ያቆማችሁ ቀን ነው። ለተውበት እስከታገላችሁ ድረስ ወደ አላህ እየቀረባችሁ ነው። አብሽሩ! ዱኒያ ፈተና ናት። ሰው በተለያየ መልኩ ይፈተናል። የእናንተ ፈተና እሱ ሆኖ ይሆናል። አብሽሩ!

እናም ከዚህ ሁሉ ፈተና ወደ ትዳር መሮጥ አይበጅም? ወይስ እየተሽከረከርንበት ያለውን የወንጀል አዙሪት አልተረዳነውም?

ስሜታችሁን አጋሩን!
.
@Fuadmu
የፍቅሯ ለሊት!
(ፉአድ ሙና)
.
ጣቶቿን ታፋዬ ላይ አስቀመጠቻቸው። በጣቶቿ እየቆጠርኩ ሰለዋት ማለት ጀመርኩ። ጨረቃ በመሰለ ፈገግታዋ ታጅባ ጣፋጩን እያነሳች ትጀባኛለች። አንተ ዝም ብለህ ተዘናጋ!

ፍቅር ማለት... ይህቺ ለሊት... መውደድ ማለት ይህቺ ንጋት ናት። ከሺህ ዓመታት በፊት የምድርን አፈር የባረኩት ታላቅ ነብይ ከቀብራቸው ሆነው ሰላምታችንን የሚቀበሉባት ለሊት!

ፉአድ የሙና ልጅ ሰላም ብሎዎታል የሚባሉበት ምሽት ናት! የእናንተም ስም በመላዒካው አንደበት ተጠርቶ ሰላምታችሁ በምድር በሰማይ ጌጥ ፊት ይነበባል። ባወረዳችሁት ሰለዋት አስር እጥፍ ከአላህ የሆነ እዝነት ይወርዳል። ይህ ሁል ጊዜ ነው።

ሰለዋት እንደ አዝካር ሁሉ ውዱዕ የማያስፈልገው ኢባዳ! የትም ተኩኖ የሚደረግ! ጥቅሙ ደግሞ የትየለሌ ነው። አስር ወንጀል ያስምራል። አስር ደረጃ ከፍ ያደርጋል። ሲራጥ ላይ እግርን ያፀናል። ከድህነት ያርቃል። ከልብ ድርቀት ይጠብቃል። ሌላም ሌላም ብዙ!

አስበው ላጤ ባትሆን ይህን ምሽት እንዴት እንደምታሳልፈው! አስበው! ፏ ብላችሁ... ቤቱ ደማምቆ! ሲራ እያወጋችሁ... ሰለዋት እያላችሁ... አስበው እንጂ አስበው!

ጁሙዓ ደግሞ ከሷ ጋ የሚያስታጥብ ፍቅር ተፋቅረህ... ትታጠብና ወደ መስጂድ ትሄዳለህ። በየአንዳንዱ እርምጃህ ልክ የአንድ አመት የሰላትና ፆም ምንዳ ጀባ ትባላለህ።

ሱረቱል ካህፍን አብሮ መቅራት... እምር ሽክ ብሎ ወደ መስጂድ መሄድ! (ሻወሩን የዘለልነው ለላጤዎች ቀልብ ተጠንቅቀን ነው።) ኹጥባ ማዳመጥ! ከመስጂድ መልስ ፏ ያለ ምሳ አንድ ላይ መብላት! ስትወልድ ደግሞ ልጃችሁን ይዛችሁ ምናምን! አስበው ወገን አስበው!

ተው ላጤ ግን ተው! ተው! ተመከር ተው!
.
@Fuadmu
ሚዛን
(ፉአድ ሙና)
.
እየተክለፈለፈ መጥቶ መንገዴን ዘጋብኝ። ወሬ በማመላለስ የታወቀ ነው። የሆነ ወሬ ለመጠየቅ መሆኑ አልጠፋኝም። ቆምኩለት።
«ስማማ!»
«ምን ልስማ?»
«ከምትወዳት ልጅ ጋር ተለያያችሁ የሚባለው እውነት ነው?»
«አዎ!»
«ለምን ተለያያችሁ?»
«የማይታለፍ ነገር ተፈጥሮ!»
«ደሞ አንተ ነህ አይደል የተውካት?»
«አዎ ተውኳት!»
«እንደዚያ ሰማይ ጠበበኝ እንዳላልክ?»
«ብልስ!»
«አትወዳትም ነበር ማለት ነው እንጂ እንዲ በቀላሉ አይቆርጥልህም ነበር!»
«ማነው ያለው?»
«ቀይስን አታየውም እንዴ የሚወደውን ሲያጣ እንዴት እንዳበደ... መጅኑኑ ለይላ ተብሎ እስኪታወቅ!»
«ወላሒ?»
«ማላገጡን ተወውና መልስልኝ!»
«ቀይስ ታዋቂ የሆነው በግጥሞቹ እንጂ በአፈቃቀሩ ትክክለኛነት አይደለም። ልብ ላይ ለአላህ የሚሰጥን ቦታ ሳይቀር ጠቅልሎ ለፍጡር መስጠት... ጭራሽ እስከማበድ መድረስ በፍፁም ልክ ሊሆን አይችልም።»
«እና ያንተ ነው ልኩ?»
«አዎ ልክ ነኝ! በጣም እወዳት ነበር። ላገባት አልሜም ነበር ግን አልሆነም። ስለዚህ ማበድ የለብኝም። ሊከብድ ይችላል እኮ! ሳያመኝ ቀርቶም አይደለም። ግን ዋጥ አድርጌው ነው። በቃ በሂደት ይሽራል። ለፍጡር የሚሰጠው ቦታ እንደዚያ ነው። ሁሉም ነገር የሚሰጠው ለኻሊቁ ብቻ ነው!» 

ተነፈስኩ። ደርሶ መካሪዎች ስለማያውቁት ፍቅር ሊሰብኩኝ ሲሞክሩ ይገርመኛል። ትናንት የምንወደውን ሰው ልንለየው አንችልም ማለት አይደለም። ዛሬ ስለተለየነውም ትናንት አንወደውም ማለት አይሆንም። ግን ሚዛንን መጠበቅ ያሻል። ሁሉም ነገር አይሰጥም። በእርግጥ ለማሽሟጠጥ ብለው እንጂ አሳስቧቸው አይደለም። አሽሟጣጭ ሁላ!
.
@Fuadmu
2025/07/05 19:39:52
Back to Top
HTML Embed Code: