አጅነብይ ሴት፣ ባይንህ አትቀላውጥ፣
ታገባ እንደው አግባ፣ አንዲቷን ምረጥ፣
እርጅና መጣብህ፣ ስታዘጠዝጥ፣
አንቺም ነቃ በይ፣ ተዪ መዘርፈጥ፣
ትዳር እየመለስሽ፣ አትሁኚ ቅምጥ።
ብልጥ ሁኚ አትሁኚ ተላላ!
አላሁመሰሊ አላ ሙሀመዴ
ኸይሪል ወራ
ያሸምሰል ሪሳላ 🥰
አላሁመሰሊ አላ ሙሀመዴ
ኸይሪል ወራ
ያሸምሰል ሪሳላ 🥰
እስኪ እናንተ ቀጥሉት!
.
@Fuadmu
ታገባ እንደው አግባ፣ አንዲቷን ምረጥ፣
እርጅና መጣብህ፣ ስታዘጠዝጥ፣
አንቺም ነቃ በይ፣ ተዪ መዘርፈጥ፣
ትዳር እየመለስሽ፣ አትሁኚ ቅምጥ።
ብልጥ ሁኚ አትሁኚ ተላላ!
አላሁመሰሊ አላ ሙሀመዴ
ኸይሪል ወራ
ያሸምሰል ሪሳላ 🥰
አላሁመሰሊ አላ ሙሀመዴ
ኸይሪል ወራ
ያሸምሰል ሪሳላ 🥰
እስኪ እናንተ ቀጥሉት!
.
@Fuadmu
❤57👏12🔥5🥰2
ፈገግታ መጅሊስ
የትዳር ወጋችን ዛሬ ምሽትም ይቀጥላል!
ባለትዳሮች ተገኙና ከላጤነት ወደ ባለትዳርነት ስለተቀየራችሁባት ቅፅበት አጫውቱን!
ከምሽቱ 3:00 ላይ እንገናኝ።
.
@Fuadmu
የትዳር ወጋችን ዛሬ ምሽትም ይቀጥላል!
ባለትዳሮች ተገኙና ከላጤነት ወደ ባለትዳርነት ስለተቀየራችሁባት ቅፅበት አጫውቱን!
ከምሽቱ 3:00 ላይ እንገናኝ።
.
@Fuadmu
❤37👏4
አልሀምዱሊላህ!
.
በፉአድ ሙና ቻናል ቤተሰቦች ስም ለኢፋዳ ኢስላማዊ ድርጅት የአንድ የውሀ ጉድጓድ ገንዘብ አሰባስበን የነበረ መሆኑ ይታወቃል። የውሀ ጉድጓዳችን በጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ አርሟ ቀበሌ ቆቶ መንደር ቁፋሮው ተጀምሮ ውሀ ተገኝቷል። አልሀምዱሊላህ!
ኢንሻአላህ ግንባታው ለውጥ ሲኖረው ከቦታው የሚላኩልኝን መረጃዎች አደርሳችኋለሁ።
አንድ ላይ ችለናል። አልሀምዱሊላህ!
.
@Fuadmu
.
በፉአድ ሙና ቻናል ቤተሰቦች ስም ለኢፋዳ ኢስላማዊ ድርጅት የአንድ የውሀ ጉድጓድ ገንዘብ አሰባስበን የነበረ መሆኑ ይታወቃል። የውሀ ጉድጓዳችን በጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ አርሟ ቀበሌ ቆቶ መንደር ቁፋሮው ተጀምሮ ውሀ ተገኝቷል። አልሀምዱሊላህ!
ኢንሻአላህ ግንባታው ለውጥ ሲኖረው ከቦታው የሚላኩልኝን መረጃዎች አደርሳችኋለሁ።
አንድ ላይ ችለናል። አልሀምዱሊላህ!
.
@Fuadmu
❤90🥰9👏8🔥3
🥰24😘1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👏48❤33😍6
የመጨረሻዎቹ መፅሀፍት
ኢፋዳ መፅሀፍ እኛ ጋ አልቋል። በፒካፕ ሎኬሽኖቻችን ጥቂት መፅሀፎች ቀርተዋል። @ifadasales ላይ ጎራ በሉና የእትሙን የመጨረሻ መፅሀፍ የራሳችሁ አድርጉ!
ኢፋዳን ግዙ!
.
@Fuadmu
ኢፋዳ መፅሀፍ እኛ ጋ አልቋል። በፒካፕ ሎኬሽኖቻችን ጥቂት መፅሀፎች ቀርተዋል። @ifadasales ላይ ጎራ በሉና የእትሙን የመጨረሻ መፅሀፍ የራሳችሁ አድርጉ!
ኢፋዳን ግዙ!
.
@Fuadmu
እሷ
(ፉአድ ሙና)
.
ይፈሳል እንባዋ ፣ ትማፀነዋለች ሀዘን ተቀልፃ፣
"ወዴት ነው ‘ምትሄደው?" ትጠይቀዋለች ድንጋጤ ለብሳ።
አይመልስም እርሱ ፣ የያዘው ይዞታል ፣ ቃል አይወጣም ከአፉ፣
"ለማን ነው ‘ምትተወን?" አታውራ ቢለው ነው ለመልስ መስነፉ።
በአስፈሪ በረሀ ፣ ጡት ያልጣለን ህፃን የሚያስተው ጭካኔ፣
ታሰላስላለች ፣ ከየት አመጣ ወኔ?
"አላህ ነው ያዘዘህ?" አይኖቿ ዋተቱ ምላሹን ፍለጋ፣
"አዎ" ሲል መለሰ ፣ ልቧ ተረጋጋ!
"እርሱማ ከሆነ ጥሎ አይጥለንም!" ስትል ተናገረች በኢማን ተውባ፣
የአላህ እርዳታ እንደሚደርስላት በፅኑ አስባ።
.
ትቷቸው ሲመለስ
ልቡን ሊያረጋጋ ፣ ጌታውን ለመነ እጆቹን ዘርግቶ፣
በልጁ ስቅይት ፣ በሚስቱ ተማፅኖ አንጀቱ ተበልቶ።
"ጌታችን ሆይ!
ከቤትህ አቅራቢያ ፣ አንተን ይገዙ ዘንድ፣
አዝመራ ከሌለው ፣ ከሸለቆው ንዳድ፣
ትዕዛዝህን ብዬ ፣ ዘሮቼን አስቀመጥኩ፣
ፍላጎቴን ገደብኩ ፣ መሻትህን ፈፀምኩ።
ጌታችን ሆይ!
የሰዎችህን ልብ ፣ አስናፍቅ ወደነርሱ፣
ከፍሬህ ስጣቸው ፣ ያመስግኑህ ለሱ።
ጌታችን ሆይ!
ድብቁን ታውቃለህ ፣ የምንሰውረውን፣
ተለየሁ ከእነርሱ ፣ ጌታዬ አደራህን!"
.
ከሄደ በኋላ
ስንቋም ተራገፈ ፣ ውሀም ለአመል ጠፋ፣
ጥሙ ጠበሳቸው ፣ ረሀቡም ከፋ።
ስትሮጥ ከጋራው ላይ ፣ ሶፋና መርዋን ስትመላለሰው፣
ቃሏን አሟላላት ፣ ቃሉን የማይጥሰው።
በመልዓኩ ክንፍ ፣ ሲቆፈር አፈሩ፣
"ዙሚ ዙሚ" አሰኛት ፣ ቀናላት ነገሩ።
"ጥሎ አይጥለንም!" ተወዶ እምነቷ፣
ለዓለም ፈውስ ሆነ ፣ ሀጀር ትሩፋቷ።
.
@Fuadmu
@Fuadmu
(ፉአድ ሙና)
.
ይፈሳል እንባዋ ፣ ትማፀነዋለች ሀዘን ተቀልፃ፣
"ወዴት ነው ‘ምትሄደው?" ትጠይቀዋለች ድንጋጤ ለብሳ።
አይመልስም እርሱ ፣ የያዘው ይዞታል ፣ ቃል አይወጣም ከአፉ፣
"ለማን ነው ‘ምትተወን?" አታውራ ቢለው ነው ለመልስ መስነፉ።
በአስፈሪ በረሀ ፣ ጡት ያልጣለን ህፃን የሚያስተው ጭካኔ፣
ታሰላስላለች ፣ ከየት አመጣ ወኔ?
"አላህ ነው ያዘዘህ?" አይኖቿ ዋተቱ ምላሹን ፍለጋ፣
"አዎ" ሲል መለሰ ፣ ልቧ ተረጋጋ!
"እርሱማ ከሆነ ጥሎ አይጥለንም!" ስትል ተናገረች በኢማን ተውባ፣
የአላህ እርዳታ እንደሚደርስላት በፅኑ አስባ።
.
ትቷቸው ሲመለስ
ልቡን ሊያረጋጋ ፣ ጌታውን ለመነ እጆቹን ዘርግቶ፣
በልጁ ስቅይት ፣ በሚስቱ ተማፅኖ አንጀቱ ተበልቶ።
"ጌታችን ሆይ!
ከቤትህ አቅራቢያ ፣ አንተን ይገዙ ዘንድ፣
አዝመራ ከሌለው ፣ ከሸለቆው ንዳድ፣
ትዕዛዝህን ብዬ ፣ ዘሮቼን አስቀመጥኩ፣
ፍላጎቴን ገደብኩ ፣ መሻትህን ፈፀምኩ።
ጌታችን ሆይ!
የሰዎችህን ልብ ፣ አስናፍቅ ወደነርሱ፣
ከፍሬህ ስጣቸው ፣ ያመስግኑህ ለሱ።
ጌታችን ሆይ!
ድብቁን ታውቃለህ ፣ የምንሰውረውን፣
ተለየሁ ከእነርሱ ፣ ጌታዬ አደራህን!"
.
ከሄደ በኋላ
ስንቋም ተራገፈ ፣ ውሀም ለአመል ጠፋ፣
ጥሙ ጠበሳቸው ፣ ረሀቡም ከፋ።
ስትሮጥ ከጋራው ላይ ፣ ሶፋና መርዋን ስትመላለሰው፣
ቃሏን አሟላላት ፣ ቃሉን የማይጥሰው።
በመልዓኩ ክንፍ ፣ ሲቆፈር አፈሩ፣
"ዙሚ ዙሚ" አሰኛት ፣ ቀናላት ነገሩ።
"ጥሎ አይጥለንም!" ተወዶ እምነቷ፣
ለዓለም ፈውስ ሆነ ፣ ሀጀር ትሩፋቷ።
.
@Fuadmu
@Fuadmu
🥰139❤98👏9🔥6
ንግስት
(ፉአድ ሙና)
.
ከበረሀ መሀል
እንዳለች፣ አንዲት ዛፍ፣
ብርቅነቷ በዝቶ
በድርሳናት ሁሉ፣ ታሪኳ እንደሚፃፍ፣
ከድርቅ በኋላ
ህይወት እንደሚያበስር፣ የዝናብ ጠብታ፣
የናፈቀው ሁሉ
እንደሚያለቅስለት፣ በጠዋት በማታ፣
ከወንጀል በኋላ
ማርታን እንደመልበስ፣ በአላህ ይቅርታ፣
ከአፋፍ እንደመትረፍ
ህያው እንደመሆን፣ ሞት የጠራ ለታ፣
ከዚህም ብዙ ብዙ
ትልቂያለሽ ለኔ፣ ቃል የለውም ወስፉ፣
በሞተ ልቤ ላይ
በፍቅርሽ ተዓምር፣ ህይወት መንሳፈፉ።
ፍቅር አልባ እኔን
በሳቅ በቁምነገር፣ የማረክሽው ለታ፣
ሰቀቀኔ አባራ፣
የታረዘ ነፍሴን፣ አለበስሽው ደስታ።
ይኑርልኝ ጥርስሽ
በፈገግታው ጨረር፣ ሀዘን የሚያስረሳ፣
የሞተ ስሜትን
የታመመ ገላን፣ አክሞ `ሚያስነሳ።
አጀብ ውብ አይኖችሽ
ትክ ያልሽብኝ ለታ፣ ይነዝረዋል ነብሴ፣
ሁሌም ይደንቀኛል
በሁረልአይን አይኖች፣ ሳልሞት መጠቀሴ።
ተክቢር ለትንፋሽሽ
እንደ ዘምዘም ውሀ፣ ተናፍቆ ተጠጪ፣
ልብ ፈታይ ሙቀት
በተማገ ቁጥር፣ አዲስ ስሜት ሰጪ።
ስሜሽ እንኳን ባላውቅ
አይቼ አይጠፋኝም፣ የጀነት ጣዕሙ፣
ዱነዊይ አይደለም
የጥፍጥናው ልኬት፣ የከንፈርሽ ስሙ።
ዘርዝሬ አልችለውም
የደዌ ፈውስ ነው፣ አንቺነትሽ ሁሉ፣
ውብ ነሽ አይገልፀውም
ላንቺ ይልፈሰፈሳል፣ አይችለውም ቃሉ።
እናልሽ ስስቴ
ሀውልት አልቀርፅልሽ፣ ሀራም ነው ድርጊቱ፣
በይ ጉዴን ልንገርሽ
ንጋ ብለው አይሰማም፣ ስትቀጥሪኝ ለሊቱ።
የኔ የብቻዬ...
የልቤ መርጊያ ነሽ
እሱን እወቂልኝ፣ አትዘንጊ ለአፍታ፣
በዱዓ አግዢኝ
በአንድ ጎጆ እንድናድር፣ የማታ የማታ።
መጨረስ ከበደኝ
በልክሽ አይደለም፣ ውዳሴዬ ላንቺ፣
አደራሽን ውዴ
እኔ አፈቅርሻለሁ፣ እኔን መውደድ በርቺ።
እኔን ብቻ!
.
@Fuadmu
(ፉአድ ሙና)
.
ከበረሀ መሀል
እንዳለች፣ አንዲት ዛፍ፣
ብርቅነቷ በዝቶ
በድርሳናት ሁሉ፣ ታሪኳ እንደሚፃፍ፣
ከድርቅ በኋላ
ህይወት እንደሚያበስር፣ የዝናብ ጠብታ፣
የናፈቀው ሁሉ
እንደሚያለቅስለት፣ በጠዋት በማታ፣
ከወንጀል በኋላ
ማርታን እንደመልበስ፣ በአላህ ይቅርታ፣
ከአፋፍ እንደመትረፍ
ህያው እንደመሆን፣ ሞት የጠራ ለታ፣
ከዚህም ብዙ ብዙ
ትልቂያለሽ ለኔ፣ ቃል የለውም ወስፉ፣
በሞተ ልቤ ላይ
በፍቅርሽ ተዓምር፣ ህይወት መንሳፈፉ።
ፍቅር አልባ እኔን
በሳቅ በቁምነገር፣ የማረክሽው ለታ፣
ሰቀቀኔ አባራ፣
የታረዘ ነፍሴን፣ አለበስሽው ደስታ።
ይኑርልኝ ጥርስሽ
በፈገግታው ጨረር፣ ሀዘን የሚያስረሳ፣
የሞተ ስሜትን
የታመመ ገላን፣ አክሞ `ሚያስነሳ።
አጀብ ውብ አይኖችሽ
ትክ ያልሽብኝ ለታ፣ ይነዝረዋል ነብሴ፣
ሁሌም ይደንቀኛል
በሁረልአይን አይኖች፣ ሳልሞት መጠቀሴ።
ተክቢር ለትንፋሽሽ
እንደ ዘምዘም ውሀ፣ ተናፍቆ ተጠጪ፣
ልብ ፈታይ ሙቀት
በተማገ ቁጥር፣ አዲስ ስሜት ሰጪ።
ስሜሽ እንኳን ባላውቅ
አይቼ አይጠፋኝም፣ የጀነት ጣዕሙ፣
ዱነዊይ አይደለም
የጥፍጥናው ልኬት፣ የከንፈርሽ ስሙ።
ዘርዝሬ አልችለውም
የደዌ ፈውስ ነው፣ አንቺነትሽ ሁሉ፣
ውብ ነሽ አይገልፀውም
ላንቺ ይልፈሰፈሳል፣ አይችለውም ቃሉ።
እናልሽ ስስቴ
ሀውልት አልቀርፅልሽ፣ ሀራም ነው ድርጊቱ፣
በይ ጉዴን ልንገርሽ
ንጋ ብለው አይሰማም፣ ስትቀጥሪኝ ለሊቱ።
የኔ የብቻዬ...
የልቤ መርጊያ ነሽ
እሱን እወቂልኝ፣ አትዘንጊ ለአፍታ፣
በዱዓ አግዢኝ
በአንድ ጎጆ እንድናድር፣ የማታ የማታ።
መጨረስ ከበደኝ
በልክሽ አይደለም፣ ውዳሴዬ ላንቺ፣
አደራሽን ውዴ
እኔ አፈቅርሻለሁ፣ እኔን መውደድ በርቺ።
እኔን ብቻ!
.
@Fuadmu
❤105🔥21🥰11👏2
🥰66👏24❤16