Telegram Web Link
እስካሁን በሳዑዲ ጨረቃ መታየቷን የሚጠቁም መረጃ የለም!

ምንጭ:– inside Haramine
😍6😁4
በጡመይር መመልከቻ ላይ የረመዳን ጨረቃን መመልከት አልተቻለም። የሌሎች መመልከቻዎች ውጤት እየተጠበቀ ነው።

ምንጭ:– inside Haramine
🔥4
ውጤቱን ተጠባበቁ ይፋ ሊደረግ ነው
🔥11🥰2
ጨረቃዋ ታይታለች!

ረመዳን ሆኗል! ለቅዱሱ ወር በቅታችኋል! አላህ የምንጠቀምበት ያድርገን!

በሉ ለተራውሂ ሰላት ተዘጋጁ!
.
@Fuadmu
🥰6519🔥7😍4👏1
ጨረቃዋ ታይታለች!

ረመዳን ሆኗል! ለቅዱሱ ወር በቅታችኋል! አላህ የምንጠቀምበት ያድርገን!

በሉ ለተራውሂ ሰላት ተዘጋጁ!
.
@Fuadmu
74🥰20👏6
ብዙ ፅሁፎችን አስነበብኳችሁ!

የጠቀማችሁ እንዳላችሁ ያልወደዳችሁት ትኖራላችሁ! በፅሁፌ የጎዳኋችሁ እንዳላችሁ ይቅር በሉኝ አላህ ይቅር ይበላችሁ።

በፈገግታ መጅሊስም ሆነ በሌሎች መርሀ ግብሮች ያስከፋናችሁ ካለንም ለአላህ ብላችሁ ይቅር በሉን!

አላህ ወሩን ከሚጠቀሙበት ከእሳት ነፃ ከሚባሉት ባሮቹ መሀል ያድርገን!

ረመዳናችሁ ይመር!

ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ
.
@Fuadmu
122🥰12😘3👏1
ረመዳን ቀን 1

ቀኑ እየተቋጨ ነው።
አፍጥርን ማቻኮል ይወደዳል።
ከመስገዳችሁ በፊት አፍጥሩ!
ተምር ከማፍጠሪያዎች በላጩ ነው።

ተምር ከሌለ በውሀም ቢሆን ከመስገዳቹ በፊት አፍጥሩ!

የፆመኛ ዱዓ ተቀባይነት አለው። በደግ ዱዓችሁ አትርሱን!

.
@Fuadmu
104🥰10😁7
ረመዳን 2

ሁለተኛው ቀን መሸ!
ፆመኛ ሲያፈጥር የሚያደርገው ዱዓ ተቀባይነት አለው።
የሞተ ቤተሰብ ካላችሁ በዱዓ አትርሱ!
ዱዓ ለሞቱ ወዳጆቻችን የምንልከው ውብ ስጦታ ነው።

እኛንም በደግ ዱዓችሁ አስታውሱን!
.
@Fuadmu
138👏6🥰4
ረመዳን 3

ሶስተኛው ቀን መሸ!
ሰዓቱ ዱዓ ላይ ያመለክታል።

ሆነ ያልሽው ትዳር እየከሸፈ ተቸግረሻል አይደል? ወደ ትዳር ለመሄድ ጓጉተሽ አልሆን እያለ?

ለማግባት ፈልገህ ትከሻህ አልጠና ብሎሀል? ምትጥምህ አልገጥም አለች?

ጌታችሁ የለማኞችን ማመልከቻ እየተቀበለ ነው።

በሉ ጨቅጭቁት! የፆመኛ ዱዓ አይመልስም!

እኛንም በደግ ዱዓችሁ አትርሱን!
.
@Fuadmu
114🥰14🔥4👏1
ረመዳን 4

አራተኛው ቀን መሸ!
ሰዓቱ ዱዓ ላይ ያመለክታል!

ህይወታችሁ መግባትና መውጣት አልሆነም?
ታጥቦ ጭቃ መሆን አልሰለቻችሁም?
አመለጥኩት ያላችሁት የወንጀል ቅርቃር ውስጥ ዳግም መወተፍ አላደከማችሁም?

ጌታችሁ የተመላሾችን ተውበት እየተቀበለ ነው።

በሉ ጨቅጭቁት! ዳግም ፊቴ ከትዕዛዝህ አይዛነፍ በሉት! የፆመኛን ዱዓ ይቀበላል!

እኛንም በደግ ዱዓችሁ አትርሱን!
.
@Fuadmu
111🥰20👏1
ረመዳን 5

አምስተኛው ቀን መሸ!
ሰዓቱ ዱዓ ላይ ያመለክታል!

የሪዝቃችሁ ጉዳይ አሳስቧችኋል?
የምትሰሩትን ስራ አትወዱትም? ወይስ ገቢው እምብዛም ነው?

የካዝናው ባልተቤት የለማኞችን ልመና እየተቀበለ ነው።

በሉ ጨቅጭቁት! አንተን ይዤ ስለርዝቄ አላስብ በሉት! የፆመኛን ዱዓ ይቀበላል!

እኛንም በደግ ዱዓችሁ አትርሱን!
.
@Fuadmu
82😍1
ሀይያ ተቀላቀሉ!

ልባችሁን አደብ ለማስያዝ ለምትሹ የሸይኽ አዲልን ደርሶች ቀጥታ ከሙሰላቸው ከስር በፃፍኩት የቴሌግራም ቻናል መከታተል ትችላላችሁ።

በተለይ ከፈጅር በኋላ ያለው ደርስ በብዙ ይጠቅማችኋል! ኢንሻአላህ!

በቻናሉ በቀጥታ ስርጭት ብሮድካስት የሚደረጉት መሰናዶዎች በጊዜ ሰሌዳ የተከፋፈሉ ናቸው። የቻናሉ ባዮ ላይ ስትገቡ መሰናዶውን ታገኙታላችሁ።

www.tg-me.com/Noor_Musela
21
ረመዳን 6

ስድስተኛው ቀን መሸ!
ሰዓቱ ዱዓ ላይ ያመለክታል!

አዋቂዎች እና አላዋቂዎች እኩል አይደሉም።
አላህ መልካም የሻለትን ደግሞ ሀይማኖቱን ያሳውቀዋል።
የእውቀትን ባልተቤት አሳውቀን በሉት!

ጌታችሁ የለማኞችን ልመና እየተቀበለ ነው።

በሉ ጨቅጭቁት! የፆመኛን ዱዓ ይቀበላል!

እኛንም በደግ ዱዓችሁ አትርሱን!
.
@Fuadmu
44🥰10
ረመዳን 7

ሰባተኛው ቀን መሸ!
ሰዓቱ ዱዓ ላይ ያመለክታል!

ጥሩ ጓደኛ ከለላ ነው። ወደ መልካም ያነሰሳል። ከመጥፎ ያርቃል። ጌታችሁን አንተን የሚፈራ ወዳጅ ስጠኝ በሉት!
ሰጥቷችሁ ከሆነም በብዙ አመስግኑት!

ጌታችሁ የለማኞችን ልመና እየተቀበለ ነው።

በሉ ጨቅጭቁት! የፆመኛን ዱዓ ይቀበላል!

እኛንም በደግ ዱዓችሁ አትርሱን!
.
@Fuadmu
🥰6818
ረመዳን 8

ቀንና ለሊትን በሚያፈራርቀው ጌታ ፈቃድ ቀኑ እየተገባደደ ነው።
ሰዓቱ ዱዓ ላይ ነው!

እኛ በሞቀ ቤት፣ በበሰለ ምግብ፣ ባልጎደለ ቤተሰብ፣ ባልቆሰለ አካል ስናፈጥር ፊሊስጤም እየደማች ነው! በጥይት እና በቦንብ እሳት እያፈጠረች!
ጌታችሁን እባክህን በቃ በል በሉት!

ቢያንስ በዱዓ ማገዝ እንችላለን!

ጌታችሁ የለማኞችን ብሶት እየሰማ ነው!

እኛንም በደግ ዱዓችሁ አትርሱን!
.
@Fuadmu
88🥰11👏4
የጎደሉ አሉ
ፕሮጀክት 2
ዝግጁ????

ስለምን ይመስላችኋል?
.
@Fuadmu
🔥277
ረመዳን 9

ሰዓቱ ዱዓ ላይ ያመለክታል!

ከውርደት ሁሉ ትልቁ ውርደት ሰው ፊት ትልቅ ሆኖ አላህ ፊት መቅለል ነው። እናም አላህ ሆይ ባንተ ዘንድ የተዋረድኩ አታድርገኝ በሉት!

ጌታችሁ የለማኞችን ልመና እየተቀበለ ነው።

እኛንም በደግ ዱዓችሁ አትርሱን!
.
@Fuadmu
🥰8936
አለሁ ለማለት ያኽል!

ሰሞኑን በተከታታይ ኢፍጣር ላይ ፖስት አደርጋቸው የነበሩት ፅሁፎች የተቋረጡት ስልኬ ከተራውሂ መልስ በሚገርም ሁኔታ ስለተሰረቀ ነበር፡፡ ከተራውሂ ስትመለሱ ተጠንቀቁ ቀምቶ የመሮጥ እና በተዘጋጁ መኪናዎች የማምለጥ የስርቆጥ አይነት ተበራክቷል፡፡

መጥፋቴን ልብ ብላችሁ በግል ስልኬ የደወላችሁ መልዕክት የፃፋችሁ ሁሉ በአላህ ስም ከልብ አመሰግናለሁ፡፡ ወንድም እህት ማለት ያለ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ስንጠፋፋም መፈላለግ ነው፡፡ አላህ ያክብርልኝ! አላህ ጀነትን ይመንዳችሁ!

በነገራችን ላይ የስልኬ ኻቲማ አሪፍ ነበር፡፡ ማለቴ የኑር ሙሰላን የቀጥታ የዚክር መሰናዶ እየሰማንባት ዚክር እያለች ነው የሄደችው 😄😄

አለይከ ረበና ቢሁስኒል ኺታሚ ያረበና ቢሁስኒል ኺታሚ! ይላሉና ጌታችሁን መጨረሻዬን አሳምርልኝ በሉት የስራ ውቡ መጨረሻው ያማረ ነው!

ከዚህ በኋላ ትንሽ ልጠፋ እችላለሁ! በሰላም ነው! አልሀምዱሊላህ አላ ኩሊ ሀሊን! ረመዳኑ ልሂድ እያለ ነው፡፡ አላህ የቀረውን እንድንጠቀምበት ይርዳን! በርቱ!

ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ
.
@FUADMU
🥰11349🔥5😍1
የምትወዱት ወር ስንት ቀን አለው?
(ፉአድ ሙና)
Repost
.
ረመዳን እና ጫጉላ ይመሳሰላሉ … ረመዳን ላይ ሁሉም ነገር የሚጀመረው እንደአዲስ ነው … ጫጉላ ላይ ህይወት የሚጀመረው ከአንድ ነው፡፡ የረመዳን የመጀመሪያዋ ለሊት ልዩ ናት …. ተራውሂ¹ በራሱ የሚፈጥረው ስሜት ልብ ውስጥ ብርሀን ይዘራል፤ የጫጉላ ለሊቶችም የማይታወቅ የደስታ ስሜት የሚስተናገዱባቸው ውብ ለሊቶች ናቸው፡፡ አዲስ ሙሽራዎች ‹‹ውዴ›› ‹‹ማሬ›› ‹‹ሀያቲ²›› ‹‹ሁቢ³›› እየተባባሉ ፍቅር የሚቀባቡበት ጊዜ ጫጉላ፤ ከጃይ ባሪያዎች ‹‹የእዝነት ወር›› ‹‹የትዕግስት ወር›› ‹‹የቀናት አለቃ›› እያሉ እንግዳቸውን የሚያወድሱበት ጊዜ የረመዳን የመጀመሪያ ሌሊቶች!
ቀናት ሲገፋ ሙሽራ መባሉ ቀርቶ ባል እና ሚስት የሚል ስያሜ ሲነግስ …. ‹‹ሀያቲ›› ‹‹የኔ ጣፋጭ›› ወዘተ የፍቅር ሙገሳዎች ከምላሶቻቸው ይሸሻሉ፡፡ የረመዳን ውብ ቀናት መቁጠራቸውን አበርትተው የመጀመሪያውን ምዕራፍ አስር ቀናት …. ቀዳሚዎቹን የእዝነት ለሊቶች ሲሸኙ ….. አስፓልት ያጣበቡ …. መስጂዱን መፈናፈኛ ያሳጡ …. አደባባዩን በምሽቱ ብርሀን ያለበሱ ተመላሽ ባሮች …. አንድ ሁለት እያሉ ከተራውሂው የስግደት ማዕድ ያፈገፍጋሉ፡፡

የጂብሪል (ዐ.ሰ)¹¹ ፀሎት ‹‹ረመዳንን አግኝቶ ወንጀሉ ያለተማረለት፤ አላሀ ከእዝነቱ ያርቀው፡፡›› … የአለማቱ ቁንጮ ‹‹አሚን›› ታላቅ ቀይ መብራቶች መሆናቸውን የረሳን …. በረመዳን እና በወትሮው ህይወታችን መሀል ልዩነት የጠፋን … በረመዳኑ ወንጀልን ያልተጠየፍን …. ጥቂት እንክርዳዶች …. ወርቅ ሲዘንብ ድንጋይ የምንለቅም ከንቱዎች ነን፡፡

እናም እናንተ ጌታችሁ ከረመዳን በፊት አፈር ሊያደርጋችሁ …. ጤንነትን ሊነጥቃችሁ … ሰላምን ሊነሳችሁ ሲችል በእዝነቱ ከረመዳን የአምልኮ ድግስ የጣዳችሁ የአምልኮ ድስቶች ሆይ! …. እናንተ የምትወዱት የረመዳን ወር አስር ቀን ብቻ ነው? ….. እናንተ የእዝነቱን ባህር በመካከለኛው አስር ቀን ለመጠመቅ ያልተነፈጋችሁ ባሪያዎች ሆይ! ….. የተራውሂ ስግደት የሚከወን እንጂ በቴሌቭዥን የሚታይ ነው? …. እናንተ የረመዳን የመጨረሻ አስር ቀናትን በአይናችሁ ለማየት የምትበቁ ታዛኞች ሆይ! አሸረል አዋኺር¹² ማለት 27ኛው ለሊት ብቻ ነው? ….. ጊዜን ለመብላት ማለስለሻ ቅጠል መጠቅጠቅ …. እድል ላለማሳለፍ የቤት ልጅ በምሽት መቅጠር … የክብር ሁሉ ጥግ የተገባው …. ታላቁ ጌታችሁ ባከበረው ወር ለጌታችሁ የሚገባ ነው? ….. አታፍሩትም??? ….. እሱ ከጭንቆች ሁሉ አላነፃችሁም? ….. እሱ ልማራችሁ ‹‹ባሮቼ›› ብሎ አልጠራችሁም? ካዳችሁት? …. እምቢ አላችሁ? …. ጌታችሁ ‹‹ባሮቼን እኔ መሓሪው አዛኙ እኔው ብቻ መኾኔን ንገራቸው፡፡ ቅጣቴም እርሱ አሳማሚ ቅጣት መኾኑን (ንገራቸው)፡፡¹³››ማለቱን ረሳችሁን? እርሱን ፍሩት …. አዛኝነቱ አያታልላችሁ …. ቀጪነቱም ምህረትን ከመጠየቅ አያስፈራችሁ!

ከረመዳን በኋላም ጌታችንን በብርቱ ለማምለክ ያጠናን ዘንድ በአምልኮ በመንዋደቅበት ….. የእስልምና እምነት ስለለገሰን ከልባችን በምናመሰግንበት ….. ሁሌም ክልክል ከሆነው ፈጣሪን የማመፅ ኃጠአት በእጅጅጅጅጉ መራቅ በምንለማመድበት በዚህ ወር እንዴት በአስረኛው ቀን የመስጂድ ሰልፎች ከቀደመው በቁጥር ይመናመናሉ? ስለምን ትዕግስት የሚለማመዱ ነፍሶች ከትምህርት ገበታቸው ይሸሻሉ? እኔ ልጠይቃችሁ …. እናንተ የታላቁ ሰው የነብዩ ሙሀመድ(ሰዐወ) ህዝቦች ሆይ …. የምትወዱት ወር ስንት ቀን ነው? ስንት አላችሁ? ሰላሳ? …. እኮ እና እንደዛ ከሆነ ልሂድ ሳይል አትግፉታ! …… ሳይተዋችሁ አትተዉታ! ….. ሳይሰለቻቹ አትሰልቹታ!

ጌታችን የምዕመናንን ምስል እንዲህ ከትቦታልና በእርሱ ቃል ፅሁፌን ልደምድም!
‹‹ለነዚያ ላመኑት ባሮቼ በርሱ ውስጥ ሽያጭና ወዳጂነት የሌለበት ቀን ከመምጣቱ በፊት፣ ሶላትን በደንቡ ይሰግዳሉ፤ ከሰጠናቸውም ሲሳይ በሚስጢርም በግልጽም ይለግሳሉ፤ (ስገዱ ለግሱም) በላቸው።›› (ኢብራሂም፤31)
ንግግር በአላህ በቃ! ከተናጋሪዎች ሁሉ በንግግሩ ላቀ! ጥራት ይገባው!

ይህን የፃፈላችሁ ከናንተ በእጅጉ የደከመ ሚስኪን ወንድማችሁ እንጂ በላጫችሁ አይደለምና በዱአችሁ አትርሱት! ስታፈጥሩ በምትዘረጉት የማይመለስ የትሩፋት ሰነድ ውስጥ አካትቱት! ከጌታችሁ ምህረትን ለምኑለት!

***
የቃላት አገባባዊ ፍቺ
¹ ተራውሂ - በረመዳን ምሽቶች ከምሽቱ 2 ሰዓት ተኩል በኋላ እስከ 4 ሰዓት ሲሰገድ የምትሰሙት ዘለግ ያለ ስግደት ነው፡፡ ተራውሂ የተባለው በየመሀሉ እረፍት ስላለው ነው ይባላል፡፡
² ሀያቲ - ህይወቴ
³ ሁቢ - ውዴ
¹¹ ጂብሪል - መልዐክ ነው በሌሎች እምነቶች ገብርኤል በሚል ስም ይጠራል
¹² አሸረል አዋኺር - የረመዳን የመጨረሻ አስር ቀናት
¹³ ሱረቱል ሂጅር (የሒጅር ምዕራፍ) አንቀፅ 49 እና 50 ላይ የሚገኙ የቁርዐን አንቀፆች ናቸው፡፡
.
@fuadmu
48😍5👏3🔥1
የጎደሉ አሉ 2
.
የጎደሉ አሉ ፕሮጀክት 1 ብለን ውሀ የተጠሙ ገጠራማ ቦታዎች እየዞርን የተጠሙትን ለማጠጣት ለአንድ የውሀ ጉድጓድ አልመን ተነስተን በእናንተ አስደሳች ርብርብ 3 የውሀ ጉድጓዶችን ማውጣታችን ይታወሳል፡፡ ለአላህ ምስጋና የተገባው ይሁን!

አሁን ደግሞ በፕሮጀክት 2 በየእስር ቤቱ በገንዘብ ዋስ እንዲፈቱ ተፈርዶላቸው የዋስ ገንዘብ በማጣት በእስር ጨለማ ላይ ያሉትን ነፃ የማውጣት እና የሚጥም ምግብ ከበሉ ዘመናት ያስቆጠሩትን ምግብ በመውሰድ የመጠየቅ ፕሮጀክት አዘጋጅተናል፡፡ በመሆኑም ለይለተል ቀድር በሚጠረጠርባቸው የቀሩ የረመዳን ለሊቶቻችን ለዚህ ታላቅ የበጎነት ፕሮጀክት የቻልነውን ያህል ገንዘብ በመለገስ እነዚህን የተረሱ ወንድም እህቶች በማያውቃቸው መዳፍ ነፃ እናወጣቸው ዘንድ እጠይቃችኋለሁ!

ያኔ እናት ልጇን በማታስታውስበት ቀን ጌታችን በመልካም ያስታውሰን ዘንድ እነዚህን የተዘነጉ ሰዎች እናስታውሳቸው!

ገንዘቡን ከአሁኑ ሰዓት ጀምሮ @ifadasales ላይ አካውንት በመውሰድ ማስገባት ትችላላችሁ! ያስገባችሁበትን ደረሰኝ ላኩልን!

ኢንሻአላህ አንድ ላይ እንችላለን!
.
ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ
.
@fuadmu
👏3717🥰7
2025/07/10 13:55:40
Back to Top
HTML Embed Code: