Telegram Web Link
በጎ ፈቃደኞቻችንን እጅ ነስተናል!

በየጎደሉ አሉ ፕሮጀክት 2 ላይ ጊዜ፣ እውቀት እና ጉልበታቸውን ሳይሰስቱ ለረዥም ጊዜ ያበረከቱልንን ውድ በጎ ፈቃደኞችን የምስጋና እራት አዘጋጅተን እጅ ነስተናል።

ኡሚ የልማትና መረዳጃ ተቋም በማስተባበሩ ረገድ ላደረገልን ቀና ትብብር ከልብ ለማመስገን እወዳለሁ።

ቅዳሜ ፈገግታ መጅሊስ ላይ በሚኖረን የመዝጊያ መሰናዶ ላይ በጎፈቃደኞቹ ስላሳለፉት ያወጉናል።

#የጎደሉ_አሉ_2
.
@Fuadmu
ክቡራትና ክቡራን!

ከዚህ ሰዓት ጀምሮ የጎደሉ አሉ ፕሮጀክትን በተመለከተ ምንም ገንዘብ የማንቀበል ስለሆነ ወደ አካውንታችን ገንዘብ አትላኩ።

ከጥልቅ መውደድ ጋር
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ
.
@Fuadmu
ደካማ ሲቃዎች
(ፉአድ ሙና)
***
ሳመኝ አለች ...

ያተነው ይመስል
መጠርጠር ህመሟን፣ ሲያሞቃት ከንፈሬ፣
መስሳም ተማፀነች
ፈውስ ከክጃሎት፣ ሽሽት ከሰው ወሬ!

ምን ነበር
በሳምኳት ...

«ፉዬ ...»
«ወዬ ...»
«አደረግከው?»

ተንዘፈዘፈ
ውቡ ገላዋ፣ የሰርክ እቅፌ፣
ጎረፈ እንባዋ
መከዳት ጥጉ፣ የህመም ብፌ።

ሚስቴ ናት
ሺህ ሲረባረብ፣ ሊያገኛት ሽቶ፣
ዝቅ ያለችልኝ
አደበኛ እንስት፣ የፍቅር ፎቶ።

ሚስቴ ናት!

ሳመኝ ...
አለችኝ ...

ጠልቶሻል ብሎ
የሚያስጨንቃት፣ አለ ሹክሹክታ፣
ልቧን ወግቷታል
ያልነገርኳትን፣ ከሰው አፍ ሰምታ!

እንዴት ልሳማት?

የቱ ከንፈሬ
ሊቀርብ ይደርሳል፣ ከንፈሯን ችሎ፣
ቢያቀልጠውሳ
ቢነክሰውሳ፣ ቅጣት ነው ብሎ።

«ለምን አገባህ?»
ጠየቀችኝ!

በአይበሉባዋ እየጠረገች፣
ጥዩፍ ያልሆነ፣ የንፍጧን ውሀ፣
እየሰበረች
የቀረባትን፣ አልቅሳ ጮሀ!

እንኳን መናገር
መተንፈስ እንኳን፣ ከብዶታል ጅስሜ፣
ለምን ልበላት?
ሲያደርጉ አይቼ? ሱና አልሜ?

እንደ አራት ናት፣
ሱና አይሆንም፣ እሷ ላይ ማግባት፣
ሀራም ነው መሰል
ገደቡን ማለፍ፣ እሷን ማስቆጣት!

መልስ ስታጣ
ጨምድዳ ልብሴን፣ እሷው ሳመችኝ፣
ከጀነት ጣዕም
ተራ እንዳማረኝ፣ አስታወሰችኝ።

«ፉዬ ... »
«እእእ ወዬ ... »
«ትፈታታለህ አይደል?»

ቸር ሴት ብትሆንም
ሁሉን መለገስ፣ የማያሳሳት፣
ሞት ይቀላታል
ለአንዲት ደቂቃ፣ ባሏን ከማጣት!

«እእእ እ ሷስ?»
አፌ ተፈታ!

አለንጋ ጣቷ
አቀላው ጉንጬን፣ ወጣች ከእቅፌ፣
ከፈጠርኩት ቀውስ
እንዴት ልፈታ፣ በየት አልፌ?

«ስታገባት አማክረኸኛል?»

«አባ» እያሉ
እሷን ‘ሚመስሉ፣ ውብ ክፋዮቼ፣
ተጠመጠሙ
ከቀረቧቸው፣ ቀጥቃጣ እግሮቼ።

ለምን አገባሁ?
ሌላ ደረብኩኝ፣ ምን አጣሁና?
መልስ አላገኘሁ
በራሴ አፈርኩኝ፣ ደሞ እንደገና!

መብቴ ነው
ማግባት፣ እሱን አውቃለሁ፣
እንዲያ
እንዳልላት፣ ደግሞ እፈራለሁ።

አይገባትም
መብቴ ተብሎ፣ ፍቅሯን ማካፈል፣
እሷ አምናኛለች
እንዲህ ሳልወዛ፣ ሰውም ሳልመስል።

«እፈታታለሁ!»

አላመነችም
ከአፌ የወጣውን፣ የውሳኔ ቃል፣
እቅፌ አነሳት
ከንፈሬ ጠማት፣ አከምኳት በቃል።

«ማልልኝ ፉዬ!»
«በአላህ ይሁንብኝ ... ዛሬ!»

ተረጋጋች
ጠፋ ያለችው፣ ሰላሟ መጣ፣
ሁሉን ረሳች
ፍቅር ተሞላች፣ ረሳች ቁጣ!

ሄድኩ ወደ አዲሷ ....

«ፈታሁሽ!» አልኳት
ጫጉላ ሳትጠግብ፣ ሳያልቅ ድግሷ፣
ታነባው ያዘች
ለቤተሰቧ፣ ምንድነው መልሷ?

«ክብሬን ወስደህ?»
ታነባለች ....
«ፈትቼሻለሁ!!!!»
.
@Fuadmu
Live stream started
Live stream finished (3 hours)
Live stream started
Live stream finished (3 hours)
Live stream started
Live stream finished (2 hours)
ለይለተል ቀድር .... ቀኑ አይታወቅም!
አረፋ ግን ነገ ነው።
.
ሀጃጆች ከአረፋ ተራራ ላይ ቆመው ጌታቸውን ተለመነን ይላሉ። ጌታቸው ወንጀላቸው የባህር አረፋን ቢስተካከል እንኳን ማርታን ይለግሳቸዋል።

ጌታችን አላህ በዚህ በአረፋ ቀን ከየትኛውም ቀን በተለየ ባሮቹን ከጀሀነም እሳት ነፃ ይላል።

የነገዋን ቀን መፆም ደግሞ ያለፈውን እና የሚመጣውን ዓመት ወንጀል ያስምራል።

ነገን በፆም .... በአምልኮ እናሳልፈው።

ለበይክ የምንልበት ቀን እንዲደርስ እንማፀነው!
.
@Fuadmu
ውብ ቀናት አልፈዋል!

ውዱ የአረፋ ቀንም ተቋጭቷል።

ሰዓቱ ዒድ ላይ ያመለክታል።

የተኳለ የዒድ እና የአያመ ተሽሪቅ ጊዜ ይሁንላችሁ።

ዒድ ሙባረክ!
كل عام وانتم بخير
.
@Fuadmu
Live stream started
Live stream finished (3 hours)
ክቡራትና ክቡራን

ፈገግታ መጅሊስን ከጀመርን 3 ዓመታትን ተጠግተናል። በላይቭ ስትሪሙ ብዙ ነገሮችን ተማምረናል። በሚያስደስተው ተሳስቀን በሚያሟግተው ተከራክረናል። በስነ ፅሁፍ ወንዝ ውስጥ በአንድ ፈስሰናል። በዚህ ሂደት ውስጥ አብራችሁኝ የነበራችሁትን ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ።

አሁን ግን ፈገግታ መጅሊስን ለተወሰነ ጊዜ በመግታት አስፈላጊ የፕሮግራም ማሻሻያ ማድረግን፣ መሰናዶውን መተውን አሊያም በሌላ አማራጭ መመለስን በተመለከተ ከራሴ ጋር ተገቢውን ጊዜ ወስጄ ለማጤን መሰናዶውን ላልተወሰነ ጊዜ ያቆምኩ መሆኑን ላሳውቃችሁ እወዳለሁ።

በመልካሙ ያገናኘን!

ከጥልቅ መውደድ ጋር!
የማይነበብ ፊርማ
ፉአድ ሙና
.
@Fuadmu
ከኢፋዳ ገፆች....

በነጭ ጨርቅ የተሸፈነው መደብ ላይ ተመቻችታ
እየተቀመጠች «ወሀደይናሁ ነጅደይን!» አለች። ክፍሉ ውስጥ መከዳቸውን ተደግፈው የተቀመጡት ተማሪዎች በልዩ ተመስጦ ያዳምጧታል።
«ዛሬ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ። ሳትማሩት ልታውቁት የምትችሉት ነገር አለ ብላችሁ ታምናላችሁ? እስኪ እንወያይበት!»
ከጥቂት ዝምታ በኋላ እጆች መውለብለብ ጀመሩ።
«እሺ ሠዒድ"
«በምድር ላይ ያሉት በርካታ ነገሮች በመማር የሚታወቁ ይመስለኛል። እንደዚህ ኡስታዝ አስተምሮንም ሊሆን ይችላል …. አሊያም ከስህተታችን ወይም ከማህበረሰቡ የእለት ተዕለት የኑሮ ሂደት! ግን ደግሞ ከዚህ ውጪ የሆኑ ሳንማር ያወቅናቸው ጉዳዮች ያሉም ይመስለኛል። ለምሳሌ እንቅልፍ እንድንተኛ ታዘን ሊሆን ይችላል እንጂ እንዴት እንደምንተኛ አልተማርንም። በተፈጥሮ ግን እንዲሁ እንተኛለን።»
«ጥሩ ነው ሰዒድ! ሴቶች ጋርም ሳስተምር ተመሳሳይ ምሳሌ አንስተውልኛል። ሌላ ምሳሌ የሚሰጠን አለ?»
«እሺ ሱሀይብ ቀጥል!»
«ጥሩና መጥፎን ሳንማር እንኳ እንዲሁ በውስጣችን እናውቀዋለን። አብዛኛው ከስነ ምግባር ጋር የተያያዙ ነገሮች ስንፈጠር ጀምሮ ልባችን ላይ የተፃፉ ይመስለኛል።»
አዱ ሀቢባ ተሳትፏቸውን አድንቃ ሀሳቡን ወደተነሳችበት የቁርዓን አንቀፅ መለሰች።
«ቁርዓን ላይ አላህ ወሀደይናሁ ነጅደይን ይላል። ልብ ብላችሁ ካስተነተናችሁ የሰው ልጅ አወላለድ አላህ ለመኖሩ የሚታይ ማስረጃ ሆኖ ታገኙታላችሁ። ህፃን ልጅ ልክ እንደተወለደ ገና አይኖቹን ሳይገልጥ …. ጡት ፈልጎ ሲቅበዘበዝ ታዩታላችሁ። አሁን ነጥቡ ጡት የሚባል ነገር መኖሩን እንዴት አወቀ የሚለው ነው። አላህ ምላሹን ሲሰጥ ‹‹ወደ ጡቶችም መራነው!›› በማለት የእርሱ ተዓምር መሆኑን ይነግረናል። ቀጥሉ ደግሞ! ጡት ልክ እንደጎረሰ ህፃኑ መመጥመጥ ይጀምራል። ጡት የሚመጠመጥ ወይም የሚጠባ ነገር መሆኑን ያውቃል ማለት ነው። ስለዚህ ይህን ሀሳብ ስናጠቃልለው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከምናገኛቸው ትምህርቶች ውጪ ነገራቶችን በቀጥታ የፈጣሪ ጣልቃ ገብነት ልናውቅ እንችላለን ማለት ነው። እናም በህይወታችሁ ውስጥ ነገሮች ተምታትተው …. መሄጃው ወዴት እንደሆን ሲጠፋችሁ …. በአቅራቢያችሁ ባለ ፍጡር የማትታገዙበት ጋሬጣ ሲገጥማችሁ፤ ገና በተወለዳችሁበት ቅፅበት ወደ ጡት የመራችሁን ጌታችሁን …. መጥባቱን ያለአስተማሪ ያሳወቃችሁን አምላካችሁን ጥሩት! …. እርሱ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነውና!» አለችና ውበቱ ለጆሮ ፈውስ በሆነው ድምጿ የቁርዐን አንቀፆችን ማንበብ ጀመረች።

«ትገዙት የነበራችሁትን አስተዋላችሁን?
እናንተም የቀድሞ አባቶቻችሁም (የተገዛችሁትን)
እነርሱም (ጣዖቶቹ) ለእኔ ጠላቶች ናቸው። ግን የአለማቱ ጌታ ሲቀር! (እርሱ ወዳጄ ነው)
(እርሱ) ያ የፈጠረኝ ነው፤ እርሱም ይመራኛል።
ያም እርሱ የሚያበላኝና የሚያጠጣኝ ነው።
በታመምኩ ጊዜ እርሱ ያሽረኛል።
ያም የሚገድለኝ ከዚያም ህያው የሚያደርገኝ ነው።
ያም በፍርዱ ቀን ሀጢአቴን ከኔ ሊምር የምከጅለው ነው።
ጌታዬ ሆይ እውቀትን ስጠኝ። ከደጋጎቹም ሰዎች አስጠጋኝ።
በኋለኞቹም ህዝቦች ውስጥ ለእኔ መልካም ዝናን አድርግልኝ።
የፀጋይቱን ገነት ከሚወርሱትም አድርገኝ።»

ንባቧን ስትጨርስ «እናም እንደ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) በጌታችሁ መሪነት ላይ ቅንጣት ታክል አትጠራጠሩ!»አለች።
«ሰምተናል፤ ተቀብለናል!!» ክፍሉ የተማሪዎቹን ህብረ-ዜማ አስተጋባ።
.
@Fuadmu
አላህ አንቺን እንደሚሰጠኝ ባውቅ...
እስከ ቂያማ በታገስኩ ነበር።
.
@Fuadmu
ጅማ መፅሀፍ አልቋል የተባላችሁ አሁን ስላስገባን መግዛት ትችላላችሁ። @ifadasales ላይ የገዛችሁም 0978114245 በመደወል ቴክኒክ ሰፈር (አብደላ) ጋር ሄዳችሁ ኮዱን በማሳየት መውሰድ ትችላላችሁ።

#ifadasales
እንኳን ደስ አላችሁ!
.
ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በመመረቅ ላይ ላላችሁ እና በዚህ ዓመት ለምትመረቁ የቻናሌ ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ።

ምርቃት የአንዱ ምዕራፍ መደምደሚያ እና የሌላኛው ምዕራፍ መጀመሪያ ነው። አንዱን ምዕራፍ በአላህ ፈቃድ አሳክታችኋል። ቀጣዩም ምዕራፍ ኢንሻአላህ መልካም ይሆናል።

እንኳን ደስስስስስስ አላችሁ!!!!!!!!!

ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ
.
@Fuadmu
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፎቶህን ላላችሁኝ!

ሁላችሁንም ለመልካም ምኞታችሁ ከልብ አመሰግናለሁ።

ተመርቀናል። 🥰🥰🥰
.
@Fuadmu
2025/07/07 05:51:57
Back to Top
HTML Embed Code: