Telegram Web Link
ፍቅርን ለምትረዱ ብቻ መልካም ጁሙዓ! 🥰🥰🥰
አሩስ
«ፉአድ ሙና»
.
ጋብቻ ነው ጥላው፣
ትዳር ነው ከለላው፣
ሪዝቅን የሚሞላው፣
የአንቢዮ‘ች ምሳሌ!
አህመድ ኸይረል ወራ
አሩሱል ከማሌ!

ስልክ ደወለች። እሷ ስትደውል ጥሪዬ ይለያል። ደውላለች ተዘጋጅ የሚል ይመስለኛል። ልብ ድረስ የሚዘልቅ ድምጿን ለመስማት...  «እወድሀለሁ» ስትል ከጥፍር እስከ ፀጉርህ የሚሰማህን ንዝረት ለመቻል... ተዘጋጅ የሚል ይመስለኛል። አነሳሁት።
«ፉዬ.. »
«የኔ ውድ!»
«ሁሉንም ጨራረስክ የኔ ጌታ?»
«አዎ የኔ ወድ!»
«አንድ ቀን ብቻ ቀረን አይደል?»
«ጊዜው ግን ፍጥነቱ አይገርምም?»
«መኪናዎቹ ቶሎ ይደርሱልሀል አይደል?»
«አዎ!»
«ዲኮር ራሳቸው ሰርተው ነው የሚልኩልህ ወይስ?»
«አትጨነቂ ውዴ... ቢረሱት ራሱ ካንቺ በላይ ዲኮር አያስፈልገውም!»
«አትቀልድ በአላህ... »
«እና ላልቅስ ውዴ?»
«አንተ ግን አልጨነቀህም? እኔ እኮ ምንም ሳይጎድል የሆነ የቀረ ነገር ቢኖርስ እያለ የሚያስጨንቀኝ መንፈስ አለ።»
«አንድ ቀን ብቻ ነው የቀረው እሁድ ጭንቀቱ ያልቃል... አይዞን»
ተሰነባብተን ስልኩ ተዘጋ።
ውስጤ አምቄው እንጂ ከእሷ በላይ ጨንቆኛል። ሰርግ የሆነ የሚያስጨንቅ ነገር አለው።
ከሰርጉ በኋላ እሷን እንደማገኝ ሳስበው በእኔና በእሷ መሀል የተዘረጋ ሲራጥ ይመስለኛል።

በቃ ፉዬ... በቃ ተነስ ይበቃል... በቃ ንቃ! የቁም ቅዠት ተው ባንን! ንቃ!

ላጤ ባይገባውም እኔ እቃዥሻለሁ።

ላለመደናቀፍ፣
ላለመወናከፍ፣
ማግባት ነው መሸከፍ፣
ከሀላል ቀበሌ!
አህመድ ኸይረል ወራ
አሩሱል ከማሌ!
.
@Fuadmu
የጎደሉ አሉ.... ቁጥር 3

የውሀ ጉድጓድ ማስቆፈር!

ዝግጁ?
.
@Fuadmu
የጎደሉ አሉ 3
(ፉአድ ሙና)
.
በአላህ ፈቃድ ከዚህ ቀደም ትልቅ ፕሮጀክቶችን በአንድነት አሳክተናል። የጎደሉ አሉ 1 ብለን 3 የውሀ ጉድጓድ አስቆፍረን የተጠሙትን አጠጥተናል። የጎደሉ አሉ 2 ብለን ታሳሪዎችን ነፃ ብለናል። ዛሬም ለበጎነት የጎደሉ አሉ 3 ስንል በጎ እናንተን ጋብዘናል።

አንድ ላይ ሆነን ለጎደሉብን ውብ ነብሶችና ለራሳችን የሰደቀተል ጃሪያ የውሀ ጉድጓድ ማስቆፈር በዚህ አንድ ወር ውስጥ ገንዘብ እናሰባስባለን።

ኢንሻአላህ አንድ ላይ እንችላለን!

በዚህ ውብ ሰደቃ ላይ ለመሳተፍ አካውንት ለመውሰድ @Fuadmuna ጎራ በሉ።

ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ
ሀያ እሁድን በሰደቀተል ጃሪያ!

አንድ ላይ ሆነን ለጎደሉብን ውብ ነብሶችና ለራሳችን የሰደቀተል ጃሪያ የውሀ ጉድጓድ ማስቆፈር በዚህ አንድ ወር ውስጥ ገንዘብ እናሰባስባለን።

ኢንሻአላህ አንድ ላይ እንችላለን!

በዚህ ውብ ሰደቃ ላይ ለመሳተፍ አካውንት ለመውሰድ @Fuadmuna ጎራ በሉ።
.
@Fuadmu
ምን አልን!
.
የውሀ ጉድጓድ ነው እናስቆፍር ያልነው!

የተጠማ ነው የሚጠጣው!

ወንዝ ከከብቶቹ ጋር ውሀ እየጠጣ በውሀ ወለድ በሽታ ለሚሰቃየው ነው የምንደርሰው!

ውሀ ልቅዳ ብላ ረዥም መንገድ ስትሄድ ለምትደፈረው እህታችን ነው የምንደርሰው!

በአቅራቢያዋ ውሀ ባለመኖሩ የውሀ መቅዳት ሀላፊነቷን ለመወጣት ከትምህርት ገበታ ለተገለለችው እህታችን ነው የምንደርሰው!

የማይቋረጥ ሰደቃ ነው። ብልጦች ሆይ! ተሽቀዳዳሚዎች ሆይ! ወደ ጀነት ነው ሩጫው!

ኢንሻአላህ አንድ ላይ እንችላለን!

በዚህ ውብ ሰደቃ ላይ ለመሳተፍ አካውንት ለመውሰድ @Fuadmuna ጎራ በሉ።
.
@Fuadmu
መፈቀር
(ፉአድ ሙና)
.
ቤብ... እወድሻለሁ ሲልሽ አመንሽው? ንገሪኝ! አፈቅርሻለሁ ሲል ተቀበልሽው ወይ? ለምን? በምን እርግጠኛ ሆንሽ? ባለትዳር ራሱ ብትሆኑ እንደሚወድሽ በምን አወቅሽ?

ይኼኔ የእኔን ፅሁፍ እየላከ ነው አይደል ያሰመጠሽ? በየትኛው ነው የጀነጀነሽ? በልብወለዶቹ ወይስ በግጥሞቼ? እንዳትሸወጂ ቤብ! ቢያገባሽ እንኳን እንደሚወድሽ እርግጠኛ መሆን አትችይም!

እና በምንድነው እርግጠኛ የምሆነው አልሽ? ለምን የእኔዋ ያረጋገጠችበትን መንገድ አላጫውትሽም? እሁድ ጠዋት ነበር። ውዴ ሀይድ ላይ ነበረች። ሀይድ ላይ ስትሆን ድካም ድካም ይላታል። ብርድልብሱን ገፍፋ እግሮቿ ስር ሰብስባው ጭው ያለ እንቅልፍ ጥሏታል። ግንባሯን ስሜ በጠዋቱ ወደ ቀጠርኩት ሰው ለመሄድ መለባበስ ጀመርኩ።

እየለባበስኩ በስስት አየኋት። ታምራለች። ከጀልኩ... ከዛ ግን ሲዝኑ እንደማይፈቅድ ራሴን አስታወስኩት። (ላጤ ሆይ ሴቶች ሰላት በሌላቸው ወቅት ነፃ ፍልሚያ እንደሌለ እወቅ!) በስስት ካየኋት በኋላ ፍቅሬን የምገልፅበት ቆንጆ ስጦታ አሰብኩ።

ከመቅፅበት ስልኬን አውጥቼ የባንክ አካውንት ቁጥር ፃፍኩና ሪዝኑ ላይ For my love ብዬ አስተላለፍኩ። ስክሪን ሾት አድርጌ ከእንቅልፏ እንደነቃች ታየው ዘንድ ላኩላት።

ከሄድኩበት ስመለስ ሚስቴ ፊቷ ተንቆጥቁጧል። እንዳየችኝ እየሮጠች መጥታ ተጠመጠመችብኝ። ምነው ስላት «እስከዛሬ እንደምወድህ አውቅ ነበር፤ ዛሬ ግን እንደምትወደኝ አወቅኩ።» አለች።

እና አሁንም ሪል ነው ሼር የሚያደርግልሽ ቤብ? አንቺስ ብትሆኚ? «ሴት ልጅን ለማስደሰት የሚረዱ ቁልፍ ጥበቦች» የሚል ፅሁፍ ነው የምትልኪለት? በቃ ይሄ ነው ውዴታሽ? ውዴታህ?

አሁን @Fuadmuna ላይ ናና አካውንት ስጠኝ በለኝ። እኔ ደሞ አልሰስትም እሰጥሀለሁ። አንቺም ቢሆን እንደዛው! በምሰጣችሁ አካውንት የጉድጓድ ውሀ ለማስቆፈር የሚውል የአቅማችሁን ገንዘብ በምትወዱት ስም አስገቡ። ሪዝን ላይ For my Love በልና አስገባ። ከዛ ስክሪን ሾት አድርገህ ላክላት። ዘላቂ አጅር ከመሸለም ወዲያ ምን ፍቅርን ይገልፃል ወገን? ካገባህ አዳርህ ይባረካል... ካላገባሽ ትዳርሽ ይፈጥናል ስልሽ!

አንተ ዝም ብለህ ሪል ላክ ሰው ሰደቃ ይልካል 😂😂😂
.
@Fuadmu
ጥራዝ ነጠቆቹ
(ፉአድ ሙና)
.
ዛሬ ስለፍቅር ጋብ አድርገን ስለ ጥላቻ ብናወራስ? ስለነዚያ ቢችሉ የጀነትን በር ይዘው ሌላ ሰው እንዳይገባ ለማድረግ ስለሚሹት ሠዎች እንወያይ! ደግሞ የሆነ አራት ኪታብ ቀርተዋል። በእነሱ አለም በራስ ጭንቅላት ማሰብ ነውር ነው። በኡስታዛቸው ጭንቅላት ይነዳሉ።

ከተግባርህም ሆነ ከንግግርህ ውስጥ በጉጉት የሚጠብቁት ወደ ስህተት ሊተረጎም የሚችል ነገርን ነው። ስህተት መሆን አይጠበቅበትም። ከመሰለ ይበቃቸዋል። «አላህን ፍራ!» በሚል ተቀፅላ ጀምረው የስድብ ጥማታቸውን ያስታግሱብሀል።

እነዚህ ሰዎች ለመምሰል እንደሚሞክሩት ብፁዕም አይደሉም። በወንጀል እጅጉን ሊበልጡህ ይችላሉ። በማስመሰል ህይወታቸውን ይመራሉ የምቀኝነትና የቅናት ድግሪ አላቸው። የእነሱ የእስልምና ትርጓሜ  ሰውንም ሆነ ራስን ማስጨነቅ ነው።

እነዚህ ሰዎች ገጥመዋችሁ አያውቁም? እስኪ የገጠማችሁን አካፍሉን!

ባልተያያዘ ዜና የውሀ ጉድጓድ ለማስቆፈር ገንዘብ እየተሰበሰበ ነው። ለመሳተፍ የምትፈልጉ @Fuadmuna ላይ አካውንት ጠይቁኝ።
.
@Fuadmu
ዛሬ ቴሌግራም ላይ የምንተፋ ሊንኮች በብዛት እየተሰራጩ እንደሆነ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር / ኢንሳ አሳውቋል።

ስለሆነም ከምታውቁትም ሆነ ከማታውቁት ሰው የሚላኩላችሁን ሊንኮች ባለመክፈት ተገቢውን ጥንቃቄ አድርጉ።

ባልተያያዘ ዜና የውሀ ጉድጓድ ቁፋሮው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ @fuadmuna ላይ ጎራ ብላችሁ አካውንት መውሰድ ትችላላችሁ።
.
@Fuadmu
ለሰደቃ ባልተቤቶች ያማረ ጁሙዓን ተመኘሁ።

የጁሙዓ ሰደቃችሁን ለውሀ ጉድጓድ አውሉ። @Fuadmuna ላይ አካውንት ማግኘት ትችላላችሁ።
40 ሺህ ብር ደርሰናል!

የተጠሙትን ለማጠጣት...

ደግ እጆች ሰደቃ እየወረወሩ ...

ውሀ በሌለባቸው ገጠራማ ቦታዎች ውሀ እያወጡ ነው።

ይህ ትልቅ ሰደቃ ነው። እድሉ አያምልጣችሁ። በራሳችሁ፣ በሞቱባችሁ እንዲሁም በምትወዷቸው ሰዎች ሁሉ ስም ሰድቁ።

በሀውድ ይተካል ኢንሻአላህ!

አካውንት @Fuadmuna ላይ ጎራ በሉና ውሰዱ። በርቱ እንበርታ!
.
@Fuadmu
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ላጤ ሆይ!
በአማርኛ ፅሁፍ ስትመከር እንቢ ብለሀል።
እስኪ በአረብኛ ቪዲዮ ተመከር።
.
@Fuadmu
የረጀብ የመጀመሪያ ምሽት ላይ እንገኛለን።

በዚህች የረጀብ የመጀመሪያ ለሊት ዱዓ አይመለስም። የልብ የልባችሁን ለአላህ አቅርቡ።

አደራ ከላጤነትም ገላግለን ማለት አትርሱ!
.
@Fuadmu
50 ሺህ ብር ደርሰናል!

የተጠሙትን ለማጠጣት...

ደግ እጆች ሰደቃ እየወረወሩ ...

ውሀ በሌለባቸው ገጠራማ ቦታዎች ውሀ እያወጡ ነው።

ይህ ትልቅ ሰደቃ ነው። እድሉ አያምልጣችሁ። በራሳችሁ፣ በሞቱባችሁ እንዲሁም በምትወዷቸው ሰዎች ሁሉ ስም ሰድቁ።

በሀውድ ይተካል ኢንሻአላህ!

አካውንት @Fuadmuna ላይ ጎራ በሉና ውሰዱ። በርቱ እንበርታ!
.
@Fuadmu
ዋ... ወንድነት!
(ፉአድ ሙና)
.
የኔ ቆንጆ... ለሁላችንም ያላቸውን ጥላቻ ባንቺ በኩል ለማስተንፈስ ሲሞክሩ እያየሽ ነው አይደል? የኔ ያልሻቸው ደም የተጋራሻቸው ሰዎች... እንወድሻለን ያሉሽ ቁሸቶች ጊዜ ጠብቀው ምን እንደሚደግሱልሽ ተረዳሽ? «ድህረ ሰላም... እስላም!» ብለው ከመጀመሪያው ዝተውልሽ ነበር አሉ!

ገና ከፌደራል መንግስቱ ጋር የያዙት ጦርነት ሳያልቅ የበቀል ክንዳቸውን እንዴት አንቺ ላይ እንደሚያሳርፉ ሲጎነጉኑ የነበሩ የፍጥረት አተላዎች ናቸው። ቀን በቀን የአላህን ንግግር እውነታነት ቢያስረግጡልሽ አትገረሚ!

የሚያስመልጥሽ ክንድ የለም። ይጋፋበት ክንድ ያለው አንድ እንኳን ሙስሊም ወንድ የለሽም። ሁሉም የበታች ነው። ሁሉም ወራዳ ባሪያ ነው። ርካሽ ነን የኔ አለም። አንቺን እናድንበት ድምፃችን ሰሏል። እንደቁስበት ክንዳችን ዝሏል። በፍርሀት ተሸብበን ሁኑ ያሉንን እየሆንን ነው የኔ ንግስት!

ጌታሽ ቀድሞ እነዚህ ጠላቶችሽ በደም አይደለም በስጋ አካል እንኳን ብትጋሩ እንደማይመለሱልሽ ነግሮሽ ነበር።

«وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ الْيَهُودُ وَلَا النَّصَارَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ ۗ قُلْ إِنَّ هُدَى اللَّهِ هُوَ الْهُدَىٰ ۗ وَلَئِنِ اتَّبَعْتَ أَهْوَاءَهُم بَعْدَ الَّذِي جَاءَكَ مِنَ الْعِلْمِ ۙ مَا لَكَ مِنَ اللَّهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ

አይሁዶችና ክርስቲያኖችም ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ካንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡ «የአላህ መምራት (ትክክለኛው) መምራት እርሱ ብቻ ነው» በላቸው፡፡ ከዚያም እውቀቱ ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን ብትከተል ለአንተ ከአላህ (የሚከለክልልህ) ዘመድና ረዳት ምንም የለህም፡፡» (በቀራ፣ 120)

ድረስልኝ አትበይኝ የኔ ፍቅር! በስሜቴ የተተበተብኩ ርካሽ ነኝ! እንደ ሙዕተሲም አዘምትልሽ ጦር፤ እቆጣልሽ ወንድነት የለኝም። ሲልኩኝ ወዴት ሲጠሩኝ አቤት የምል ወራዳ ነኝና ወደኔ አትጣሪ። ወደ አላህ ጩሂ የኔ ውድ! ወደማይነጥፈው ንግስና ተጣሪ! የእርሱ ክንድ አይዝልም። እርሱ ይደርስልሻል ውዴ!


«فَفِرُّوا إِلَى اللَّهِ ۖ

«ወደ አላህም ሽሹ፤» (ዛሪያት፣ 50)

እኔ ግን ለራሴ ብቻ ሳይሆን ላልመለስኳቸው የድረስልኝ ጩኸቶችሽም አነባለሁ! ለራቀኝ ወንድነት... ለተሸከምኩት ወራዳነት እንሰቀሰቃለሁ። አንድ ቀን ጭንቅላቴ ቀና ይላል። ሲነኩሽ አይሆንም ብዬ አስቆምበት ክብር አገኛለሁ ብዬ ከጌታዬ እከጅላለሁ። እስከዛው ግን ውዴ ወደ ጌታሽ ጩሂ.... እኔ ወራዳ ሆኛለሁ።

በበዳዮች ላይ የአላህ እርግማን ይውረድ!
.
@Fuadmu
ውሀ የሌለባቸውን ገጠራማ አካባቢዎች ውሀ ለማዳረስ የጎደሉ አሉ ብለን ፕሮጀክት ከጀመርን ቆየን!

በጅማ ሳኮሩ ወረዳ አንድ የውሀ ጉድጓድ እንዲሁም በሐረማያ ሁለት የውሀ ጉድጓዶችን አስቆፈርን።

በመሀል እስረኞችን ነፃ በማውጣት የጎደሉ አሉ ሁለትን አካሂደን ነበር።

አሁን ሰዓቱ የውሀ ነው። የጎደሉ አሉ ፕሮጀክታችን በውሀ ፕሮጀክት ተመልሷል። የምንደፋው ውሀ ቅንጦት ለሆነባቸው ወንድም እህቶቻችን እንድረስ!

አካውንት @Fuadmuna ላይ ውሰዱ። የዚህ ትልቅ ፕሮጀክት አካል ሁኑ። የማይቋረጥ ሰደቃ ሸምቱ!

መልካም ጁሙዓ!
የኢፋዳ መፅሀፍ የመጨረሻዎቹ ኮፒዎች እየተሸጡ ነው። የገዛችሁ ቶሎ መፅሀፋችሁን ውሰዱ መፅሀፍ እያለቀ ነው።

መግዛት የምትፈልጉ @ifadasales ላይ መግዛት ትችላላችሁ።

መልካም ሸመታ!
ውሀ!

የጎደሉ አሉ ፕሮጀክታችን በውሀ ፕሮጀክት ተመልሷል። የምንደፋው ውሀ ቅንጦት ለሆነባቸው ወንድም እህቶቻችን እንድረስ!

አካውንት @Fuadmuna ላይ ውሰዱ። የዚህ ትልቅ ፕሮጀክት አካል ሁኑ። የማይቋረጥ ሰደቃ ሸምቱ!

መልካም እሁድ!
ኢፋዳ የስነ ፅሁፍ ምሽት!

ዛሬ እሁድ ከአስር እስከ መግሪብ ቤተል ኢፋዳ ኢስላማዊ ድርጅት በሚገኝበት ሚና የገበያ ማዕከል ይካሄዳል። ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።

አድራሻ: ‐ ከመንዲዳ ወደ ቤተል ሲመጡ አለምባንክ መገንጠያ አስፓልት ጋር ያለው ሚና የገበያ ማዕከል (አል ቤክ ሬስቶራንት ያለበት ህንፃ)
2025/07/04 23:01:22
Back to Top
HTML Embed Code: