Telegram Web Link
ረመዳን ሄደ!
.
ረመዳን ሲሄድ አፍቃሪዎች የሚወዱትን ሰው ሲሸኙ እንደሚያለቅሱት ሁሉ ሆድ ይብሳቸዋል።
ሰው የሆንበት ወር ሲሄድ እንዴት ሆድ አይብሰን? አላህ ከረመዳን ውጪም ሰው መሆንን ያድለን!

يا شهر رمضان ترفق
 
ها هو ذا رمضان يمضي،
وقد شهدت لياليه أنين المذنبين، وقصص التائبين،
وعبرات الخاشعين،
وأخبار المنقطعين.
وشهدت أسحاره استغفار المستغفرين،
وشهد نهاره صوم الصائمين وتلاوة القارئين،
وكرم المنفقين.
إنهم يرجون عفو الله،
علموا أنه عفو كريم يحب العفو فسألوه أن يعفو عنهم.
يا شهر رمضان ترفق، دموع المحبين تُدفق،
قلوبهم من ألم الفراق تشقق،
عسى وقفة للوداع أن تطفئ من نار الشوق ما أحرق،
عسى ساعة توبة وإقلاع أن ترفو من الصيام ما تخرق،
عسى منقطع عن ركب المقبولين أن يلحق،
عسى أسير الأوزار أن يطلق،
عسى من استوجب النار أن يعتق،
عسى رحمة المولى لها العاصي يوفق

አላህ በጤና በሰላም በአማን በአፊያ ይመላልስብን! ኦው ረመዳን! አንተ ወዳጃችን ነበርክ!
.
@Fuadmu
ኢድ ሙባረክ!

ቆንጅየዋ የሸዋል ጨረቃ በሳዑዲ ሰማይ ላይ ታይታለች። ኢድ ነገ ዕሁድ ሆኗል።

አላህ ረመዳችንን ይቀበለን።

እንኳን አደረሳችሁ!

የመረጃ ምንጭ: ‐ Inside the Haramine
.
@Fuadmu
EID Mubarak!

🥰🥰🥰
ኢድ እንዴት ይዟችኋል?
ሸዋል ላይ ጋብቻ ጥሩ ነው ይላሉ። እስኪ ለማግባት ዝግጁ ሆኖ ሴት ያጣ ካለ እንዲሁም ለማግባት የደረሰች ሴት ካለች ላገናኛችሁ! ኮሚሽን ከአላህ!

ካላችሁ @Fuadmuna ጎራ በሉ።
.
@Fuadmu
ማሳሰቢያ

1ኛ) እየቀለድኩ አይደለም የምሬን ነው። ኢንቦክሴ ለመቀለድ አትምጡ!

2ኛ) የምንጠይቃችሁን ቶሎ ሞልታችሁ ላኩ!

3ኛ) ሴቶች ለእኔ አይደለም ከሌላ ወንድ ጋ ነው የማገናኛችሁ ☺️

4ኛ) @Fuadmuna ላይ ስትመጡ አለን ካላችሁኝ በቂ ነው ይገባኛል።

5ኛ) ለትዳር እንጂ ለመንዛዛት አላገናኝም። እያያችሁ ግቡበት።
.
@Fuadmu
ለሸዋል ትዳር ኢንቦክስ አለን ያላችሁኝ ዛሬ ትንሽ የተጣበበ ሰዓት ስለነበረኝ አልመለስኩም ለብዙዎቻችሁ! ነገ ምላሽ እሰጣለሁ ኢንሻአላህ!
.
@Fuadmu
ከሸዋል ፕሮጀክታችን መስፈርታችሁን የሚገጥሙ አጋሮች ወዳገኘንላችሁ ወንድምና እህቶች ስልክ እየደወልን ነው።

ስንደውል አንስታችሁ ተገቢውን ምላሽ በመስጠት ተባበሩን። 🥰🥰🥰

ሌላው የኢኮኖሚ ዝግጁነት የሌላችሁ ወንዶች ሲኖራችሁ አብሽሩ እናመቻቻለን ለአሁን ስራ እንዳይበዛብን መልዕክት አትላኩልን።

በሁሉም ረገድ ለትዳር ዝግጁ የሆናችሁ ወንዶች አያምልጡን የሚባልላቸው አይነት በርካታ በሀላል ለመሰተር የሚፈልጉ እህቶች አመልክተዋል። እድሉን ተጠቀሙ። @Fuadmuna ላይ አለን በሉ።

ሸዋልን ለሀላል ጥምረት!
.
@Fuadmu
ለሸዋል ፕሮጀክታችን ለጊዜው የሴቶች ምዝገባ ጨርሰናል። ወንዶች ብቻ @Fuadmuna ላይ መመዝገብ ትችላላችሁ።
.
@Fuadmu
እያወሩ ነው!

የሸዋል ፕሮጀክት የማገናኘት ስራዎች ቀጥለዋል። ዝም ስል አነሳስቶን ጠፋ እንዴ እንዳትሉ 😂
መስፈርት የተጣጣመላቸው ብዙዎች ጋር ደውለን አገናኝተናል። ስራው እንደቀጠለ ነው።

ለማግባት የተዘጋጃቹ ወንዶች @Fuadmuna ላይ መመዝገብ ትችላላችሁ።
.
@Fuadmu
እኛም እንመጣለን!
(ፉአድ ሙና)
.
ይሰፈራል እድሜ ፣ ይለካል ቆይታ፣
ይጠፋል ፈገግታ ፣ ይጀመራል ዋይታ።
ይናፍቃል ማድመጥ ፣ ይናፍቃል ማየት፣
የኔ ነው ያሉት ሰው ፣ ትቶ የሄደ 'ለት።
እንባ ይወርዳል ከአይን ፣ አፍንጫ አያምርበት፣
የኔ ያሉትን ሰው ፣ አፈር የጫኑት 'ለት።
እኛም የሱ ነን ነው ፣ አንድ መመለሻ፣
መከተል ነው ፍርዱ ፣ የኛንም ቀን ሲሻ።
እንመጣለን አብሽር!
.
ግን እስከምንመጣ
መስተንግዶህ ይመር ፣ ከአፍህ መልስ አይጥፋ፣
ጨለማው ይብራልህ ፣ ጠባቡ ቤት ይስፋ!
.
ይኸው ነው እንባችን!
እንዲህ ነው ቃላችን።
የኛ ያልነው ሲሄድ ፣ ሲጎል ከቤታችን!
.
@Fuadmu
የሰደቃ ዘመቻውን ዘግቼ የነበረ ቢሆንም አንገብጋቢ ሆኖ ስላገኘሁት ይህን ችግር እንፍታ!

«አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላህ ወበረካቱ እንዴት ነህ? ጀዛከላህ ቻናልህ ላይ አብዘሀኛውን ግዜ የተቸገሩ ተማሪወች ሀጃ እንዲወጣ ድልድይ ስትሆን አያለሁ እና ሰሞኑን ያስጨነቀኝን ሀጃ ላጋራህ ወደድኩ..ጀመዐ ላይ ያገኘኋቸው የ Medicine ሙስሊም ሴት ተማሪዎች አሉ ከ ዲፓርትመንት ሰቃይ ናቸው ይህ የረበሻቸው ሙስሊም ያልሆኑ የክፍል ተማሪዎች ለምን ተበለጥን በሚል መንፈስ በተደጋጋሚ ሲህር አያሰሩባቸው ቢሆንም ስቃዩን በቁርአን እንዲያክሙ አላህ አግርቶላቸው እስካሁን አየታገሉ ውጤታቸውን እንዳስጠበቁ አሉ..አሁን ግን ዶርም እነሱ ጋር መመደባቸውና መቀየር የማይቻል መሆኑ ለመቀጠል አጅግ አስቸጋሪ አድርጐታል ከሚታገሉት ከባድ ህመም ጋር ይህን መጨመርም አይታሰብም…ቤት ተከራይቶ መውጣት ግድ ሆኖ 1 ክፍል ቤት በፍለጋ 3000 ብር ብናገኝም የምግብ ወጪ ጋር ተዳምሮ ወጭው ከአቅም በላይ ሆኗል።ትምህርቱን ለመጨረስ 3 አመት ይቀራቸዋል እንደ ኡማ ማገዝና ህመማቸውን መጋራት አለብን ብየ ስላሰሰብኩ ነው ጭንቀቴን ያጋራሁህ ሹክረን።»

እነዚህን እህቶች ማገዝ የምትፈልጉ የአስተባባሪዎቹን አካውንት @Fuadmuna ላይ መውሰድ ትችላላችሁ።
.
@Fuadmu
Live stream started
Live stream finished (2 hours)
የሸዋልን ድባብ እናልብሰው እስኪ ምሽቱን 🥰

ሲወድቅ ሲነሳ፣ ስንት ሹማምንት፣
ፈልጎ እንዳላጣት፣ እጅግ ባላባት፣
እምቢ ብላ ስትኖር፣ ያሁሉ ወራት፣
ሙሀመድን ስታይ ፈለገች ማግባት።
አስለምና ያውም አሸምግላ!

አላሁመሰሊ አላ ሙሀመዴ
ኸይሪል ወራ
ያሸምሰል ሪሳላ 🥰
አላሁመሰሊ አላ ሙሀመዴ
ኸይሪል ወራ
ያሸምሰል ሪሳላ 🥰
.
@Fuadmu
ህይወት ያለ ትዳር፣ ኮሶ ነው ምሬት፣
ሊያውም ጀነት ሀገር፣ ሁሉ የሞላበት፣
አደም ብቸኝነት፣ ቢያስጠላብዎት፣
ሀዋን ቢያገቡ ነው፣ ያማረብዎት!
ተሞሸሩ፣ በጀነቱ ጫጉላ!

አላሁመሰሊ አላ ሙሀመዴ
ኸይሪል ወራ
ያሸምሰል ሪሳላ 🥰
አላሁመሰሊ አላ ሙሀመዴ
ኸይሪል ወራ
ያሸምሰል ሪሳላ 🥰
.
@Fuadmu
አምቢያ ሙርሰሉ፣ ንጉስ ሹማምንት፣
ያላገባ የለም፣ ወጣት አዛውንት፣
በረካ የለውም፣ የላጤ ህይወት፣
ማግባት መውለድ እንጂ፣ ነስል ማበርከት፣
ሷሊህ ልጆች፣ ያልሆኑ ተላላ!

አላሁመሰሊ አላ ሙሀመዴ
ኸይሪል ወራ
ያሸምሰል ሪሳላ 🥰
አላሁመሰሊ አላ ሙሀመዴ
ኸይሪል ወራ
ያሸምሰል ሪሳላ 🥰
.
@Fuadmu
አንዳንድ አስመሳዮች፣ ሙናፊቆች አሉ፣
በውሸት ሞግተው፣ ሰው ያሳምናሉ፣
ለሴት ልጅ ጠበቃ፣ ወኪል ነን ይላሉ፣
በሴት ልጅ ከለላ፣ ጥቅም ያሳዳሉ፣
አግብታም ከሆነ ከባል ያፋታሉ።
የህዝብ ሚስት ሊያደርጓት ዘልዛላ!

አላሁመሰሊ አላ ሙሀመዴ
ኸይሪል ወራ
ያሸምሰል ሪሳላ 🥰
አላሁመሰሊ አላ ሙሀመዴ
ኸይሪል ወራ
ያሸምሰል ሪሳላ 🥰
.
@Fuadmu
አጅነብይ ሴት፣ ባይንህ አትቀላውጥ፣
ታገባ እንደው አግባ፣ አንዲቷን ምረጥ፣
እርጅና መጣብህ፣ ስታዘጠዝጥ፣
አንቺም ነቃ በይ፣ ተዪ መዘርፈጥ፣
ትዳር እየመለስሽ፣ አትሁኚ ቅምጥ።
ብልጥ ሁኚ አትሁኚ ተላላ!

አላሁመሰሊ አላ ሙሀመዴ
ኸይሪል ወራ
ያሸምሰል ሪሳላ 🥰
አላሁመሰሊ አላ ሙሀመዴ
ኸይሪል ወራ
ያሸምሰል ሪሳላ 🥰

እስኪ እናንተ ቀጥሉት!
.
@Fuadmu
ፈገግታ መጅሊስ

የትዳር ወጋችን ዛሬ ምሽትም ይቀጥላል!

ባለትዳሮች ተገኙና ከላጤነት ወደ ባለትዳርነት ስለተቀየራችሁባት ቅፅበት አጫውቱን!

ከምሽቱ 3:00 ላይ እንገናኝ።
.
@Fuadmu
2025/07/02 03:48:21
Back to Top
HTML Embed Code: