Telegram Web Link
አንድ አንድ ሰው እወድሃለሁ
እያለ ይሞግታል‥ ነገር ግን ከጀርባው ያለው
እውነታ ያሳለፈው ጉዳት ሲደማበት እንደቁስል
ማጣበቂያ ፕላስተር እየተጠቀመህ ሆኖ
ታገኘዋለህ ። 💔💔

@funyhaha
@funyhaha
💔የልብህን ቁስል ትተው የደረትህን ንቅሳት ያደንቃሉ፤ ጫማ ስለሌለህ እግርህ አይታይም ፤ የጭንቅላትህን ዋጋ በኮፍያክ ይተምኑሀል ፤ መከራ ተሸክሞ ሲኖር ያላዩት ትከሻ ኮት ሲለብስ ያጨበጭቡለታል፤ ታሪክህን ጨርቅህ ላይ ስምህን ልብስህ ላይ ለማንበብ ይሽቀዳደማሉ።

እኔ ትንሽነቴን አልረሳም ማወቄም አያመፃድቀኝም ።ጀግና ማለት ታግሎ የጣለ ሣይሆን ታግሎ ያለፈ ነው። ሁሌም ቢሆን እራስህን ተመልከት። የምትወድቀው ሌላውን ለመጣል የሞከርክ ቀን ነው።
ልትጥለው የሞከርከው ሰው ግን ገልብጦህ ከላይ ሆኖ ታገኘዋለህ።

ሁሉንም በገንዘብ እገዛዋለው ብለህ አታስብ በገንዘብ የምትገዛው ርካሹን ነገር እንጂ ውድ ነገሮች የዋጋ ተመን የላቸውም።🙏
ውብ ምሽት
@funyhaha
@funyhaha
@funyhaha
"እትዬ"
"እመት"
"በፍየል ዘመን በግ አትሁኚ!!" የተጣሉ ጎረቤቶቼ ጋር ሌላኛዋ ስትሄድ አንዷን ሌላኛዋን በ አሽሙር ለመንካት ምክር ቢጤ ስትሰጣት እኮ ነው። የተባለችውም የዋዛ አይደለችም
"አዪ የፍየልስ ብልጠት መች ከመታረድ አዳናት?" አለች። እናቴ ናት የነገረችኝ።
ከላይ ይጠብቅ ነው የሚባለው።።።

@funyhaha
@funyhaha
Live stream finished (5 minutes)
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ


እንኳን ለ1442ኛው ዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

Baga Kabaja Ayyaana Iid Al Faxiriif Nagaan Geessani!
ዒድ ሙባረክ!
Id Mubaark!
💎ፊት ለፊት ትይዩ የተገነቡ ሁለት ቤቶች አሉ ። በሁለቱ ቤቶች ጣሪያዎች ላይ ደግሞ የእግር መርገጫ ስፋት ብቻ ያለው የጣውላ መረማመጃ ድልድይ ቢጋደምና በላዩ ላይ ተራምዳችሁ ከአንዱ ጣርያ ወደሌላው እንድትሻገሩ ብትጠየቁ ፈቃደኛ ላትሆኑ ትችላላችሁ ። ይኸው ጣውላ መሬት ላይ ተጋድሞላችሁ እንድትራመዱበት ብትጠየቁ ግን ህፃን ፣ ወጣት ፣ አዛውንት ሳይባል ፣ ሁላችሁም ሳትወድቁ ትራመዱበታላችሁ ።

📜 የጣውላ መረማመጃው ያው ነው ፤ እናንተም ያው እናንተው ናችሁ ፤ ታድያ ጣውላው በቤቶቹ ጣሪያዎች ላይ በተጋደመ ጊዜ እንድትራመዱበት ስትጠየቁ ለምን እምቢ አላችሁ? መሬት ላይ በተደጋጋሚ ጊዜ ብዙ ሰዎች ሳይወድቁ ተረማምደውበታል ። ታድያ ችግሩ ምንድን ነው? ችግሩ ያለው ሌላ ቦታ ነው ።

🔑 መሬት ላይ ተጋድሞ ሳለ ጣውላው ላይ ለመረማመድ ንቁ መሆን አያስፈልግም ።ንቃት አልባ ሆናችሁ ልትራመዱ ትችላላችሁ ። በጣውላው ላይ ተረማምዳችሁ ከጣሪያ ጣርያ ለመሻገር ግን ንቁ መሆን ይኖርባችኋል ። ንቃት እንደሌለን እናውቃለን ፤ በዚህም ምክንያት ወድቀን እንዳንሞት እንፈራለን ። መሬት ላይ ስንራመድ ግን ብንወድቅ እንኳን እንደማንሞት እናውቃለን ።

💎 አልፎ አልፎ አደጋ በሚያጋጥመን ቅፅበት ንቃት ይኖራል ። ሌላ ግዜ ግን እንቅልፍ ላይ ነን ። ሞት ሲቀርበን ንቃት ይኖራል ፤ አለዚያ ግን ንቁ አይደለንም ። ልማዶቻችንን መቀየር የማንፈልገው ለዚህ ነው ፤ ምክንያቱም ልማዶች ሲለወጡ ንቁ መሆን ያስፈልጋል ። አሮጌ ልማዶች የእናንተን ንቃት አይፈልጉም ።

📖 የንቃት ፀሃይ /ኦሾ/
ገጽ 99-100
ትርጉም መርሻ በነበሩ
ምንጭ - ከስብዕናችን ገፅ

@funyhaha
@funyhaha
💞ውጤታማ ግንኙነት ለመመስረት ምን ማረግ አለብን?

ይሄ የብዙዎች ጥያቄ ይመስለኛል ችግሩ እዚው ነው ያለው አስተውሉ።
ፍቅር የለም ከማለትህ በፊት እኔ ውስጥ ፍቅር አለ ወይ?ብለህ ፈትሽ!አንተ ራስህን ካልወደድክ ማን አንተን ሊወድህ ይችላል። ሚስት የምትሆን ሴት የለችም ከማለትህ በፊት እኔ ጥሩ ባል መሆን እችላለሁ ወይ? ብለህ ራስህን መርምር ወንድ እንጂ ባል የለም ከማለትሽ በፊት እኔ ጥሩ ሚስት መሆን እችላለሁ ወይ?ብለሽ ራስሽን ጠይቂ ጥሩ ንደኛ የለም ከማለትሽ በፊት እኔ ጥሩ ንደኛ መሆን እችላለሁ ወይ?ብለሽ አስቢ! ማንም ሰው ጥሩ ከሆነ ጥሩ ነገሮች ሁሉ ከሱ መራቅ አይችሉም ስለዚህ ጥሩነትን ከሰው ሳይሆን ከራሳችን ነው የምናገኘው መልካም ሁን።
ቅን.ትሁት.ወዳጅ.ፍቅር.ሩህሩህ.ለጋሽ.አስተዋይ.ደስተኛ.ሳቂታ.ብልህ ሁን/ሁኚ
መፍትሄ ሰጪ
ተፅዕኖ ፈጣሪ
አመስጋኝ ሁን/ሁኚ
ለራስህ/ሽ ክብር ስጥ/ጪ ውድ መሆንህን/ሽን ካመንክ/ሽ ሰዎችም ውድ መሆናቸውን አትዘንጊ/ጋ።
ያኔ እመኑኝ ውስጣቹ በፍቅር ይሞላል ልባቹ ክፍት ይሆናል። በልበ ሙሉነት ለሰው ፍቅርን ከሰጣቹ ቅንጣት ታክል ውስጣቹ ለዛ ሰው ጥርጣሬ ከሌላቹ አታስቡ ምላሹ ጥሩ ነው።

#ለሴቶች እባክሽን ሰውነትሽን ሚያሳይ ልብስ አትልበሺ አውሬዎች ደም ይስባቸዋል በልተውም ይሄዳሉ ወንዶች ፊት ገላሽን ገላለጥሽ ማለት ለአውሬዎች ደም ማሳየት ማለት ነው። ቢራቢሮ ንፁህ እና ውብ ናት ሚስባትም ብርሀን ነው። ትክክለኛው ወንድ በሴትነትሽ የወደደሽ ነው።

@funyhaha
@funyhaha
💜 ህፃን ልጅ እስኪጠግብ ድረስ
ከእናቱ ጡት ይጠባና አጥንቷ ውስጥ ያለው
ካልሲየም ይጎድላል ፣ ጥርሱ ያሳምማታል
እስኪያድግ ድረስ በሀሳብና ጭንቀት ትወጠራለች
አድጎ ትልቅ ሰው ከሆነ በኋላ ካፌ ላይ እግሩን ደርቦ ይቀመጥና ሴት ልጅ ጎዶሎ ናት ይላል‥

ብራዘርዋ አንድ ቀን እንኳን ያንተ ሙሉነት ኬት እንደመጣ እራስህን ጠይቀህ ታውቃለህ?
ጎዶሎ ካልካት ሴት ምግብኮ ነው አቅልህም ሰውነትህም ሙሉ የሆነው ። ሌላው እንኳን ቢቀር ለእናትህ ስትል ለሴቶች ክብር ስጥ ።

@funyhaha
@funyhaha
💜 ህፃን ልጅ እስኪጠግብ ድረስ
ከእናቱ ጡት ይጠባና አጥንቷ ውስጥ ያለው
ካልሲየም ይጎድላል ፣ ጥርሱ ያሳምማታል
እስኪያድግ ድረስ በሀሳብና ጭንቀት ትወጠራለች
አድጎ ትልቅ ሰው ከሆነ በኋላ ካፌ ላይ እግሩን ደርቦ ይቀመጥና ሴት ልጅ ጎዶሎ ናት ይላል‥

ብራዘርዋ አንድ ቀን እንኳን ያንተ ሙሉነት ኬት እንደመጣ እራስህን ጠይቀህ ታውቃለህ?
ጎዶሎ ካልካት ሴት ምግብኮ ነው አቅልህም ሰውነትህም ሙሉ የሆነው ። ሌላው እንኳን ቢቀር ለእናትህ ስትል ለሴቶች ክብር ስጥ ።

@funyhaha
@funyhaha
አግባኝ ትለኛለች ትዳርን አቅልላ
በሁአላ በነገር እኔኑ ልትበላ
#ጥበብ_በቃሽ_ልኑርበት😭
@funyhaha
🛑አንዳንዴ በጣም ከባድ ችግር የመሰለህ ነገር አስቂኝ ሆኖ ቁጭ ይላል፤ በዚህ ምድር ለመኖር የቀረህ 1 ሳምንት ነው ቢባል የትኛው ሰው ነው የኑሮ ውድነት የሚያሳስበው? የትኛው ሰው ነው የፍቅረኛው ስልክ አለማንሳት የሚያበሳጨው? ያለህን አጭር ጊዜ እንዴት አጣጥመህ እንደምታልፈው ታስባለህ እንጂ በፍፁም አተክዝም።

አየህ ወዳጄ አሁንም የቀረህ እድሜ ስንት እንደሆነ አታውቀውም፤ ተኝተህ ማደርህን እንኳን እርግጠኛ አይደለህም! ስለዚህ ለማን ብለህ ነው የምታዝነው? በፈጣሪህ እመን ከዛ የምትችለውን ሞክር የቀረውን ለነገ ተወው!


@funyhaha
💜 ለከሃዲ የሚያዝን
ተበዳይን እየከዳ ነው ።

#ወታደራዊ ቀመር

@funyhaha

          
ዝም አልኳቸው ዝም ይበሉኝ
ትቻቸዋለሁ ይተውኝ
አልነካቸውም አይንኩኝ”
ብለህ፥ ተገልለህ ርቀህ
እውነት ይተውኛል ብለህ
እንዴት ተስፋ ታደርጋለህ?!…
ተስፋ አርገህስ ምን ልትሆን፤ ወይስ ተስፋው ምን ሊሆንህ?
እንቅልፍ እንጂ የሚያስወስድህ።
"አልጠራቸውም አይጥሩኝ
አይንኩኝ ስሜን አያንሱኝ"
ብለህ እንዴት ትመኛለህ፥ እንደማይተዉህ ስታውቀው
የተወጋ በቅቶት ቢኛ፥ የወጋ መች እንቅልፍ አለው
የጅምሩን ካልጨረሰው?
የተበደለ ቢችልም
ቢሸሽግም ቢደብቅም
የበደለ ዝም አይልም።
እንዴት አስችሎት ዝም ይበል? ለፍልፎ ከማስለፍለፉ
አደል እንዴ የሱ ቤዛ፣ የበደሉ ጥቅም የግፉ
ሰላም ለመንሣት አደል ትርፉ?…
ዝምማ ካለ ጒድ ፈላ
ነገር በጤና ሲብላላ
እያደር ሲጣራ ኋላ
ግፉ ይፋ ይሆናላ!…
የተበደለ ቢችልም
ቢሸሽግም ቢደብቅም
የበደለ ዝም አይልም።
እንዴት አስችሎት ዝም ይበል? ለፍልፎ ከማስለፍለፉ
አደል እንዴ የሱ ቤዛ፣ የበደሉ ጥቅም የግፉ
ሰላም ለመንሣት አደል ትርፉ?…
ዝምማ ካለ ጒድ ፈላ
ነገር በጤና ሲብላላ
እያደር ሲጣራ ኋላ
ግፉ ይፋ ይሆናላ!…
ሠላምማ ከለገሰህ
ሕመምህ እየታወሰህ
ትዝታ እየቀለሰህ
የሕሊናህ ሚዛን ረግተህ፥ ጉዱ ሁሉ ኩልል ሲል
ያደፈረሰው ሲያጠልል
እግዜር ያሳያችሁ ብለህ፥ ፍረዱኝ ዳኙኝ እንዳትል
ከነአካቴው ሳይጨርስህ
ምን ቢሆን ሰላም አይሰጥህ።

#ሎሬት_ጸጋዬ ገ/መድኅን
#እንቅልፍ ነው እሚያስወስድህ
#እሳት ወይ አበባ

@funyhaha
💜 ስልኮች በገመድ ታስረው
በነበረበት ጊዜ ሰዎች ነፃ ነበሩ
ይባላል ።

@funyhaha
@funyhaha
ቤተሰብ...🌼

ዛሬ 2014 ነገ 2015 ነው...ታዲያ...ከነገ ወዲያ 2016 ነው ማለት ነው🤔

@funyhaha
@funyhaha
አንዳንድ ወንዶች አሉ ማፈቀራቸውን ሳይናገሩ እስከ ሞት ድረስ የሚዘልቁ፤ግን እኔ ዛሬ እነግርሻለሁ፤እንደማፈቅርሽና ለአመታቶች ያክል በፍቅርሽ ወላፈን ስቃጠል እንደነበር።

ምናልባት ለአንቺ የሚገቡ ፍቅሬን የሚገልፁ ጥዑመ ቃላቶች ላይኖሩኝ ይችላሉ።ግን አንድ ነገር ብቻ በልቤ ውስጥ ሲመላለስ በምናቤ ሲንጎራደድ ይሰማኛል። በ7 ፊደላት የተጠረዘ፣ በቀያይ ቀለሞች የተለበጠ፣ አንድበቴን ሰቅዞ የያዘ፤በልቤ ውስጥ የሚንጓለል አንድ ቃል ብቻ አለ።

እሱም "አፈቅርሻለሁ" መሆኑን ስነግርሽ ደስታዬ ከውስጤ ተንደርድሮ ፊቴን በፈገግታ ይሞላዋል።ፈገግታዬም አንድበቴን እስርስር አድርጎ መላው አካሌን በጤነኝነት መንፈስ ያንቦቀብቀዋል።እንደው ውዴ የኔ ዱንቡሽቡሽ የትኞቹ ቃላቶች ይሁኑ የሚገቡሽ...ይህው እሱን ስፈልግ ትላንት በትዝታው አታለለኝ..ነገ ደግሞ በገባው ቃል አስተኛኝ...አይኖቼን ስገልጥ ዛሬ አለቀ🥺

Bemni_Alex

@funyhaha
@funyhaha
2024/05/29 11:35:59
Back to Top
HTML Embed Code: